cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አዲስ ሪፖርተር - NEWS

🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው ! => በቻናሉ 📌 ፈጣን ፥ 📌 ትኩስ ፥ 📌 ወቅታዊ እና 📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል ! 🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል ! For promotion @Addis_reporter_bot #ADDIS ABABA, ETHIOPIA

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
39 421
مشترکین
-1524 ساعت
-837 روز
-45730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በሕገ ወጥ ድርጊት የሚጠረጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደጀመረ አስታወቀ በትግራይ ክልል የተባባሰውን ሕገ ወጥ ድርጊቶች ለማስቆም እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ገለጸ። አዲስ ማለዳ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በተመለከተችው አጭር መግለጫ፤ በክልሉ የተለያዩ ሕገ ወጥ ተግባራት ከጊዜ ወደጊዜ እየተበራከቱ በመምጣታቸው ምክንያት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መንግስት፤ መንግስትን የሚፈታተኑ እና የህዝቡን ደህንነት አደጋ ውስጥ የሚከቱ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር በተለያዩ ኮሚቴዎች አማካይነት ሲያጣራ እንደቆየ ተገልጿል። አብዛኛው ምርመራ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሕገ ወጥ ድርጊቶችን ለማስቆም እና ተጠርጣሪዎችን በሕግ ቁጥጥር ስር ለማዋል ቅድመ ዝግጅት ማድረጉ በመግለጫው ተጠቁሟል። በዚህም መሰረት በሕገ ወጥ የብረታ ብረት ዝርፊያና በመሳሰሉት ከባድ ወንጀሎች ላይ ከትላንት ሐምሌ 4 ቀን 2016 አንስቶ ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል ጀምሯል ተብሏል። ሰኔ 22 ቀን 2016 የመቀሌ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት በ2016 ዓመት 11 ወራት ውስጥ 4 ሺህ 340 ወንጀሎች ተመዝግበው በዚህም 12 ሴቶች ሲገደሉ፣ 80 የአስገድዶ መደፈር፣ 1 ሺህ 953 የስርቆት፣ 583 የድብደባ፣ 178 የግድያ ሙከራ እንዲሁም 10 የጠለፋ ወንጀሎች መፈጸማቸውን እንዳስታወቀ አዲስ ማለዳ መዘገቧ አይዘነጋም። ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በመቀሌ ከተማ ከ170 በላይ የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ ሃይሎችን የማጠናከር ስራ ተሰርቷል ተብሏል።  የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ትላንት በሰጠው መግለጫም ተጠርጣሪዎችን በሕግ ቁጥጥር ስር ለማዋል በሚደረገው እንቅስቃሴ የመንግስት መዋቅሮች፣ የፀጥታ መዋቅርን ጨምሮ መላው ህዝቡ ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል። በቅርቡ በክልሉ ዋና ከተማ እና ሌሎችም አካባቢዎች በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ግድያ እና አፈና ለማውገዝ ሰላማዊ ሰልፎች እንደተካሄዱ መዘገባችን አይዘነጋም። @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በቀጣዩ አመት ቤት ለቤት የፓስፖርት እደላ እጀምራለሁ አለ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በዛሬው እለት የ 2016 አመት የስራ አፈጻጸሙን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። አገልግሎቱ በቀጣዩ የ 2017 አመት በባለሃብቶች እና ታዋቂ ሰዎች ጥያቄ መሰረት የቤት ለቤት የፓስፖርት እድላ እንደሚጀምር ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። አገልግሎቱ በ ቪአይፒ (VIP) እና ሌሎች አገልግሎቶች የሚኖሩት ሲሆን ለቤት ለቤት አገልግሎቱም የተለየ ክፍያ እንደሚተመንለት ለማወቅ ችለናል። ለአዲሱ አገልግሎት በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ አሰራርን ለመተግበር አቅጃለሁም ብሏል። @Addis_Reporter
نمایش همه...
🤔 8🥰 7👍 1 1
የኬንያው ፕሬዚዳንት የህዝብን ተቃውሞ ለማርገብ ሲሉ ካቢኔዎቻቸውን አሰናበቱ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻጓ እና ከጠቅላይ ካቢኔ ፀሀፊ ሙሳሊያ ሙዳቫዲ በስተቀር ካቢኔያቸውን በትነዋል። ይህ ውሳኔ የተወሰደው የ 2024 ፋይናንስ ረቂቅ እንዲነሳ ካስገደዱ የቅርብ ጊዜ ክስተቶች በኋላ ነው ተብሏል። ፕሬዝደንት ዊልያም ሮቶ በዛሬው ዕለት የወሰዱት እርምጃ በመላው ሀገሪቱ ለተነሳው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ እንደምላሽ ነው የተወሰደው። ፕሬዝደንቱ እርምጃውን የወሰዱት የሕዝባቸውን ድምፅ በመስማት መሆኑን ተናግረዋል። @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 5
"ተማሪዎቹ ተለቋል!" የኦሮሚያ ክልል "ልጆቻችን አልተለቀቁም!" ወላጆች የታገቱት ተማሪዎች፤ የመንግሥት መግለጫና ቤተሰቦች ባለፈው ሳምንት ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ አካባቢ በታጣቂዎች ከታገቱት 167 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች 160ዎቹ መለቀቃቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ቢናገሩም ቤተሰቦች ግን እስካሁን ልጆቹ እንዳልተለቀቁ አስታወቁ። ዶቼ ቬለ ካነጋገራቸው መካከል እህታቸውን እስከትናንት ድረስ በስልክ አግኝተው ማነጋገራቸውና አሁን እዚያው በአጋቾቹ ቁጥጥር ስር መሆኗን የገለጹልን ቤተሰብ የተለየ ነገር አለመኖሩን አረጋግጠዋል። ዛሬ ጠዋትም እህታቸውን እንዲያነጋግሩ ከሚያገናኟቸው አጋቾች አንዱን በስልክ አግኝተው እንደነበር የገለጹት እኒሁ እማኝ እህታቸውን ወዲያው ማነጋገር ያልቻሉት ግለሰቡ ታጋቾቹ ከሚገኙበት አካባቢ ባለመሆኑ ከ30 ደቂቃ በኋላ እንዲደውሉ እንደነገራቸውም አክለው ገልጸዋል። ትናንት ማምሻውን የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ «በተደረገ ጥብቅ ኦፕሬሽን ከ167 ታጋች ተማሪዎች መካከል 160ዎቹ ተለቀዋል» ማለታቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ዜናውን መስማታቸውን ለዶቼ ቬለ የገለጹት እህታቸው የታገተችባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ «በጣም ይገርማል በእውነት፤ እኔ እኮ በእራሳቸው ስልክ (በአጋቾቹ ማለታቸው ነው) ትናንት ጠዋትም ከሰአት በኋላም እራሴ አግኝቻታለሁ በድምፅ፣ ሰዎቹንም አግኝቻቸዋለሁ። ልጆቹ አሁንም እዚያው ነው ያሉት፤ ተፈተዋል ምናም የሚባለው ነገር ውሸት ነው። ማታ ዜና ስንሰማ ነበር። እንዴት እንዲዚህ ያለ ነገር ይሰራል እስኪ?» በማለት ጠይቀዋል። በተመሳሳይ ከሀዋሳ ያነጋገርናቸው የታጋች ተማሪ ቤተሰብ ምንም የተለየ ነገር እንደሌለ ነው የተናገሩት። እሳቸውም እንዲሁ የታገተችው እህታቸው መሆኗን በመግለጽ እስካሁን ያለችበትን እንዳላወቁ ሆኖም ግን 700,000 ብር ቤዛ መጠየቃቸውን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን «ተለቀዋል» የሚለው ዜና መስማታቸውን የገለጹት የሀዋሳው ነዋሪ ካለፉት ሦስት ቀናት ወዲህ ግን ከአጋቾቹ ወገን ስልክ እንዳልተደወለላቸው አመልክተዋል። ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ጠዋት ከአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባሕር ዳር መኪና ተራ የተነሱት ሦስት አውቶብሶች እንደነበሩ፤ ቀድመው በወጡት ሁለት አውቶብሶች ውስጥ የተሳፈሩት አብዛኞቹ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደነበሩ ነው ከእገታው ካመለጡ ተማሪዎች ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው። በሦስተኛው አውቶብስ ውስጥም እንዲሁ የተሳፈሩት አብዛኞቹ ተማሪዎች ነበሩ ነው የተባለው። በጉዞ ላይ ሳሉም ብዛታቸው ከ25 እስከ 30 የሚገመት ክላሽና አንዳንዶቹም ስናይፐር የታጠቁ አጋቾች ከፊት ያሉት አውቶብሶች እንዲቆሙ አስገድደው የተወሰኑት ለማምለጥ መሞከራቸውን፤ በዚህ ጊዜም ወደ ሰማይ ጥይት መተኮሳቸውንም ዘርዝረዋል። አጋቾች ለታጋቾቹ ቤተሰቦች ስልክ በማስደወል ገንዘብ የጠየቁ ሲሆን ቤተሰቦች የተጣለባቸውን የቤዛ ገንዘብ ለመክፈል መጨነቃቸውን እየተናገሩ ነው። የታጋቾቹ ጉዳይ የሀገር ውስጥ እና የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ቀልብ የሳበ ሲሆን በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ በተለይም በኦሮሚያ እና አማራ ክልል እገታ መደጋገሙ እንዳሳሰበው የሚያመለክት መግለጫ አውጥቷል። በዚህ መሃል ከመንግሥት ባለሥልጣናት የአብዛኞቹ ታጋቾችን መለቀቅ የሚያመለክት መግለጫ ቢሰጡም ቤተሰቦቻቸው እንደሚሉት ግን እስካሁን የተለየ ነገር የለም። በ2012 ዓ,ም ጥር ወር በተመሳሳይ የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሆኑ ከ17 በላይ ሴት ተማሪዎች ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸው ይታወሳል። በወቅቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕረስ ሴክረታሪ የነበሩት አቶ ንጉሡ ጥላሁን «በመንግሥት ብርቱ ጥረት» ተማሪዎቹ መለቀቃቸውን የገለጹ ሲሆን የተባለውን ቤተሰቦቻቸውም ሆነ ልጆቹ ወጥተው አላረጋገጡም። እስከዛሬ ድረስም የታገቱት ሴት ተማሪዎችን ዕጣ ፈንታ የሚያመለክት ነገር አልተሰማም። ዘገባው የዶቼ ቬለ ነው። @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 12 1
አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ ከተማ አካባቢ በተፈጸመው የበርካታ ሰዎች እገታ "የመንግሥት የደኅንነት አካላት" እና "የበታች የፓርቲ ካድሬዎች" እጅ አለበት ብሎ እንደሚያምን አስታውቋል። ቡድኑ በክልሉ እየተበራከተ ለመጣው እገታ በክልሉ መንግሥት ሥር ተመስርቷል ያለውን ኢመደበኛ የጸጥታ ኮሚቴ ተጠያቂ አድርጓል። ገዥው መንግሥት የሰላማዊ ሰዎችን እገታ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን ለማሸማቀቅ በፖለቲካ መሳሪያነት ይጠቀምበታል በማለትም ቡድኑ ከሷል። ቡድኑ፣ ከመንግሥታዊ አካላትና ከበታች ካድሬዎች ሌላ፣ በመንግሥት ተስፋ የቆረጡ ሥራ አጥ ወጣቶችም የመንግሥት የጸጥታ መዋቅር መዳከሙን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም የታጋች ማስለቀቂያ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ሰላማዊ ሰዎችን ያግታሉ ብሏል። @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 1🤔 1
በሞቃዲሾ የአሜሪካ አምባሳደር አምባሳደር ሪቻርድ ሪሌይ፣ ትናንት ወደ ሐርጌሳ አቅንተው ከሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ፣ ከፖለቲከኞችና ከሲቪል ማኅበራትና ከንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ተነጋግረዋል። የአሜሪካ ኢምባሲ፣ ለዲፕሎማሲያዊ እና የጸጥታ ችግሮች መፍትሄው ቀጠናዊ ትብብርና ንግግር መኾኑን አምባሳደሩ በውይይቶቹ ወቅት እንዳሠመሩበት ገልጧል። አምባሳደሩ፣ የምርጫ ማካሄጃ መርሃ ግብሮችን ማክበር እንደሚያስፈልግ ለባለሥልጣናቱ እንዳሳሰቡና፣ አሜሪካ በቀጠናው ብልጽግና እንዲሰፍንና ዲሞክራሲያዊ ተቋማት እንዲጠናከሩ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸዋል ተብሏል። @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 3
09 52400019 09 52400019 ሰላም እዴት ናችሁ ወድሞች እህቶች አንድ ሰው ላስተዋውቃትሁ መሪጌታ ይባላሉ እደኔ ከበሽታችሁ ከችግራችሁ መላቀቅ ለምትፈልጉ አዴ ብቻ አናግሯቸው የሳቸው መድሀኒት የደረሳችሁ ሼር አትርሱ እባካችሁ አዴ ብቻ አናግሯቸው    መርጌታ የባህል መድህኒት ቀማሚና ሰሪ ለማነኛውም በሽታ መዳን እዳለ አትርሱ ከምንሰራቸው በትንሹ    📳09 52400019 ✅የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል 1 ለመፍትሔ ስራይ 2 ለህማም 3 ጋኔን ለያዘው ሰው 4 ቡዳ ለበላው 5 ለቁራኛ 6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው 7 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር) 8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ) 9 ለዓቃቤ ርዕስ 10 ለመክስት 11 ለቀለም(ለትምህርት) 12 ሰላቢ የማያስጠጋ 13 ለመፍትሔ ሀብት 14 ለመስተፋቅር 15 ለሁሉ ሠናይ 16 ለገብያ 17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ) 18 ለመድፍነ ፀር 19 ሌባ የማያስነካ 20 ለበረከት 21 ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ) 22 አፍዝዝ አደንግዝ 23 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ) 24 ለግርማ ሞገስ 25 መርበቡተ ሰለሞን 26 ለዓይነ ጥላ 27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ 28 ለሁሉ መስተፋቅር 29 ጸሎተ ዕለታት 30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ 31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) 32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ 33 ለድምፅ 34 ለብልት ♦️በአለም ላይ የብዙ ትዳሮች መፍረስ  #የወሲብ_ግኑኝነት ጥሩ አለመሆን ነው። ስለዚህ የገጥመዎትን ችግር ቀጥታ በመጠዬቅ መፍትሔ በማግኘት ደስተኛ ህይወት ይኑራችሁ ♦️ስንፈተ ወሲብን እንዴት ማከም ይቻላል? የሀበሻ መድሃኒት ህክምና፡ መድሃኒቶች የደም ፍሰትን ይጨምራሉ እንዲሁም የፆታዊ ፍላጎት በሚኖርበት ጊዜ ብልት በምላሹ እንዲቆም የሚያደርጉ ናቸው። የብልት መጠንን መጨመር የሚችሉ መድሀኒቶችን አቅርበንላችኋል 1.የብልት አለመቆም ችግር 2.ቶሎ የመርጨት ችግር 3.የብልትን ቁመትና ውፍረት ማነስ ችግር ካለብሆት በፍጥነት ☎️ 09 18 43 46 89 ይደውሉ እና ያማክሩን 🏇በፍጥነት ያሉበት ቦታ እናደርሳለን 🔑🔑ማሳሰቢያ  ከምንም የጎንዮሽ ጉዳት ነፃ መሆኑ የተረጋገጠ አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸውጨ የተጋቡ ካሉ አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት አለ ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል                    09 52400019
نمایش همه...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ተቆፍረው ክፍት በተደረጉ ጉድጓዶች ምክንያት 72 ሰዎች ለህልፈት ተደርገዋል፡፡ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ለኮንስትራክሽን እና ለተለያዩ አገልግሎቶች ተብለው በተቆፈሩ ጉድጓች ገብተው ለህልፈት የሚዳረጉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡ ይህ ቁጥር በ2016 አመት የተከሰተ እንደሆነ ነው የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያስታወቀው፡፡ በበጀት አመቱ በጠቅላላ 78 ሰዎች በተለያዩ ድንገተኛ አደጋዎች መሞታቸውንም ገልጻል፡፡ የአዲስ አበባ እሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ድንጋይ እና ማእድናት ለማውጣት በሚል የሚቆፋፈሩ ጉርጓዶች ክፍት በመተዋቸው ምክንያት ውሃ እንዲያቁሩ እና ዋና ለመዋኘት የሚገቡ ሰዎች ህይወታቸውን የሚያጡበት ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ በግለሰብም ሆነ በመንግስት ለግንባታ ስራዎች ተብለው ተቆፍረው የሚተዉ ጉድጓዶች እንዳሉም ገልፀው ፤ በዚህም አንዳንዶቹ ስራው ሲካሄድ በቂ ከለላ እና ጉድጓድ ስለመኖሩ ምልክት እንደማይቀመጥና አደጋዎችም እየተበራከቱ መምጣታቸውን ገልፀዋል፡፡ ድንጋይ ለማውጣትም ሆነ ሌሎች ማዕድናትን ለማውጣት ፍቃድ የሚሰጠው አካል አስፈላጊው ክትትል ማድረግ ፣የተቆፈሩ ጉድጓዶች አካባቢ መከለል፣አደጋን ተከላክለው ከሚሰሩ ተቋማት ልምድ መውሰድ ፣ የተቆፈሩ ጉድጓዶችን ተከታትሎ መክደን / መድፈን/ መዝጋት እንደሚገባ መክረዋል፡፡ ህብረተሰቡም የራሱን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ነው የተናገሩት፡፡ @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 7👏 5 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከል ባለሃብቶችንና የውጭ ኢንቨስትመንቶችን ይጎዳል በማለት እንደተቃወመ ሪፖርተር ዘግቧል። ኮሚሽኑ ለትራንስፖርት ሚንስቴር በጻፈው ደብዳቤ፣ የሕግ ድንጋጌ ሳይኖርና ግልጽ ሕግ ሳይወጣለት ከበላይ አካል በተሰጠ ትዕዛዝ ብቻ ነዳጅ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ ማገድ አግባብነት የለውም በማለት ቅሬታውን እንደገለጠ ዘገባው ጠቅሷል። ውሳኔው፣ በግብርና፣ በግብርና ምርት ማቀነባበር፣ በአበባ እርሻ ልማት፣ በቱሪዝም፣ በማኑፋክቸሪንግና ግንባታ በተሠማሩ ባለሃብቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጥሯል ተብሏል። ኮሚሽኑ፣ ላንዳንድ ኢንቨስትመንቶች ከባሕሪያቸው አንጻር በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዲያስገቡ እንዲፈቀድላቸው መጠየቁን ጋዜጣው አመልክቷል። @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 5
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት፣ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች በአገሪቱ ውስጥ ተቀጥረው መስራት እንዲችሉ የሚያስችል መመሪያ አዘጋጅቷል። ተቋሙ መመሪያውን ያዘጋጀው፣ በ2012 ዓ፣ም የወጣው መመሪያ በስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች አዋጅ የተካተቱ ከሥራ ቅጥር ጋር የተያያዙ መብቶችን ባለመያዙ እንደኾነ ገልጧል። መመሪያው የተዘጋጀው፣ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር፣ ከሥራና ክህሎት እና ከገቢዎች ሚንስቴሮች ጋር በመተባበር እንደኾነ ተገልጧል። አዲሱ መመሪያ፣ ስለ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች የሥራ ቅጥር፣ ሥራ ፍቃድ፣ በንግድ ሥራ ስለመሠማራትና ስለግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ዝርዝር ድንጋጌዎችን ይዟል ተብሏል። @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 7 1
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.