cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

AASTU Muslims union

ይህ የቴሌግራም ቻናል ሁሉንም የ አአሳቴዩ ሙስሊም ተማሪዎች የሚመለከት ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ኢስላማዊ ትምህርቶች፣ የተለያዩ ዳእዋና ሙሃደራዎች እንዲሁም ጀመዓውን የሚመለከቱ መልእክቶች ይለቀቁበታል። ከዚህ ውጪ ሌላ ቻናል የሌለን መሆኑን እና የትኛውም ከዚህ ቻናል ውጪ የሚለቀቅ ነገር እኛን እንደማይወክል እናሳስባለን። ለማንኛውም አስተያየት @ab097ab097 @abduw99

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 381
مشترکین
+124 ساعت
+77 روز
+2530 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ሙሐረም እና ዓሹራ- ~በቁርኣን ዉስጥ እንደተጠቀሰው የዓመቱ ወራት 12 ናቸው፡፡ ከነርሱ ዉስጥም አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ሦስቱ ተከታታይ ወራት ናቸው፡፡ ዙልቂዕዳ፣ ዙልሒጃ፣ ሙሐረም፡፡ ረጀብ ተነጥሎ ነው የሚገኘው፡፡ አሁን የተከበረው ሙሐረም ዉስጥ ነው ያለነው፡፡ ከተከበሩ እና ልቅና ከተሠጣቸው የዓመቱ ወራት ዉስጥ አንዱ ነው፡፡ በኢስላማዊው ጨረቃ አቆጣጠር የመጀመሪያው ወርም ነው፡፡ 1446 ዓመተ ሂጅራ ከገባ ዛሬ ሰኞ 2ኛ ቀናችን ይዘናል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) «ከረመዷን ቀጥሎ ምርጡ ፆም የአላህ ወር ሙሐረም ወር ፆም ነው፡፡ ከግዴታ ሶላት ቀጥሎ ምርጡ ሶላት የሌሊት ሶላት ነው፡፡» ብለዋል፡፡ ሙሐረም የአላህ ወር ነው መባሉ በራሱ ልቅናውን ከፍ ያደርገዋል፡፡ ሙሐረምን ጨምሮ በአራቱ የተከበሩ ወራት ዉስጥ ራሣችሁን አትበድሉ ተብለናል፡፡ በደል ሲባል ብዙን ጊዜ ለኃጢኣት ነው፡፡ አላህ ልቅና በሠጠው ወር ዉስጥ ወንጀል መፈፀም በትልቁ ራስን መበደል ነው፡፡ በርግጥ ወንጀል ሁሌም ክልክል ቢሆንም፤ በነኚህ ወራት ዉስጥ ክልክነቱ ጠብቋል፡፡ አላህ ይጠብቀን፡፡ የሙሐረም ወር አሥረኛው ቀን ዓሹራ ይባላል፡፡ በዚህ ቀን ዉስጥ ትልቅ ክስተት ተከስቷል፡፡ ትልቅ ድልም ተበስሯል፡፡ እውነት በዉሸት ነግሷል፡፡ ነቢያችን (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ከመካ ተሰደው መዲና ሲደርሱ የመዲና አይሁዶች የዓሹራን ቀን ሲፆሙ አገኟቸው፡፡ «ምንድነው ይህ የምትፆሙት ቀን?» በማለትም ጠየቋቸው፡፡ «ይህ ቀን አላህ ሙሳን እና ህዝቦቹን ነጃ ያወጣበት ፈርዖንና ሠራዊቱን በዉሃ ያሠጠመበት ቀን ነው፡፡ ሙሳ አላህን ለማመስገን ብለው ፆሙት፡፡ እኛም ለዚያ ብለን ነው የምንፆመው፡፡» አሉ፡፡ የአላህ መልዕክተኛም «ከናንተ ይልቅ እኛ ነን ለሙሳ የምንቀርበው፡፡» አሉና ፆሙት፤ ተከታዮቻቸዉም እንዲፆሙት አዘዙ፡፡» አሉ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሙስሊሞች ይፆሙታል፤ ልጆቻቸዉንም ያስፆማሉ፡፡ በዚህ ወር ዉስጥ መልካም ሥራ የተባለን ሁሉ ማብዛት ይወደዳል፣ ፆም ከሥራዎች ሁሉ ምርጡ ሥራ ነው፡፡ ሰደቃ፣ ዱዓእ፣ ሶላት፣ አላህን ማውሳት ማብዛት እና ሌሎችም ብዙዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በአሥረኛው ቀን መፆም የተወደደ ነው፡፡ ሳያስበው አፍጥሮ ያነጋ ሰው እንኳን የተቀረዉን ቀኑን በፆም ቢያሳልፍ ይመረጣል፡፡ ነቢያችን ቀኑን ፆመውታል፤ ግና በሚመጣው ዓመት አላህ ካኖረኝ ዘጠነኘዉንም ቀን ጨምሬበት እፆማለሁ ብለው ነበር፡፡ በሌላም ሐዲሥ ዓሹራን አንድ ቀን ከፊቱ አሊያም ከኋላው ፁሙ ብለው ነበር፡፡ •አላህ ሆይ ወሩንና ዓመቱን ሁሉ መልካም አድርግልን፡፡ በረከትህንና ችሮታህንም ለግሰን፡፡ አላህ ሆይ ሙስሊም አድርገህ አኑረን፣ በእስልምና ላይም ግደለን፡፡ منقول
نمایش همه...
👍 9
Photo unavailableShow in Telegram
💐🌹🥀🌻💐🌹🥀🌻💐🥀💐🌹🥀🌼💐🌹🥀🌻💐🥀💐🌹🥀🌻💐🌹🥀🌻💐🥀💐🌹🥀🌼💐🌹🥀🌻💐🥀💐🌹🥀🌻💐🌹🥀🌻💐🥀💐🌹🥀🌼💐🌹🥀🌻💐🥀 Congratulations to all of AASTU Muslim graduates❗️                 ﻣﺒﺮﻭﻙ ﻟﺠﻤﻴﻊ ﺧﺮﻳﺠﻲالمسلمين في جامعة AASTU ❗️ We're proud to see so many of brothers and sisters  move on to the next chapter of their life! AASTU Muslim students union wish you every success. ﻧﺤﻦ ﻓﺨﻮﺭﻭﻥ ﺑﺮﺅﻳﺔ ﺍﻟﻜﺜﻴﺮ ﻣﻦ ﺍلإخوة والأخوات ﻳﻨﺘﻘﻠﻮﻥ ﺇﻟﻰﺍﻟﻔﺼﻞ ﺍﻟﺘﺎﻟﻲ ﻣﻦ ﺣﻴﺎﺗﻬﻢ! التحادطلاب المسلمين فيAASTU ﺗﺘﻤﻨﻰ ﻟﻜﻢ ﻛﻞﺍﻟﺘﻮﻓﻴﻖ ! 💐🌹🥀🌻💐🌹🥀🌻💐🥀💐🌹🥀🌼💐🌹🥀🌻💐🥀💐🌹🥀🌻💐🌹🥀🌻💐🥀💐🌹🥀🌼💐🌹🥀🌻💐🥀💐🌹🥀🌻💐🌹🥀🌻💐🥀💐🌹🥀🌼💐🌹🥀🌻💐🥀
نمایش همه...
👍 24
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ‼️ውድ የ ኣ.አ.ሳ.ቴ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰሞኑን ለዕረፍት ወደ የቤታችሁ እንሄዳችሁ (except fresh and Gc) ይታወቃል። 🔹አደራ ጊዜያችሁን ዱንያዊም ይሁን አኼራዊ  በሚጠቅም ነገር ላይ እንድታሳልፉት ይሁን። ከተቻለ ክረምቱን መርከዝ በመግባት፣ኮርሶችን በመከታተል እንዲሁም ሰፈር ላይ በሚሰጡ ደርሶች በመሳተፍ ተጠቃሚ ሁኑ። 🔶አደራ ቤተሰቦቻችሁንም በመርዳት(በመኻደም) እና ዲናቸውንም በማስተማር ላይ በርቱ። መልካም የዕረፍት ጊዜ! مع السلامة‌‌ ____ قال الله تعالى، يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ،     سورة الحشر، ١٨ እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡   قالَ رسولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : {اتَّقِ اللهَ حَيْثُمَا كُنْتَ، وَأَتْبِعِ السَّيِّئَةَ الْحَسَنَةَ تَمْحُهَا، وَخَالِقِ النَّاسَ بِخُلُقٍ حَسَنٍ} رواه التِّرمذيّ، وقالَ حديثٌ حَسَنٌ. وفي بعضِ النُّسَخِ حسنٌ صحيحٌ. ረሱል ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦"የትኛውም ቦታ ብትሆን አላህን ፍራው፤ለመጥፎ ስራክ ጥሩ ሰራ አስከትልበት፤ያብሰዋል፡፡ በመልካም ስነምግባር ሰዎችን ተኗኗራቸው።" ___
نمایش همه...
👍 22
Add a comment
Photo unavailableShow in Telegram
👍 4💯 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 2
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ رضي الله عنه : "ቁርአንን ቅሩ ልባቹንም አንቀሳቅሱበት   በምትቀሩ ጊዜም የአንዳቹ ጭንቀት   (ትኩረት) የሱራው መጨረሻ መድረስ    አይሁን ይላሉ። " .
نمایش همه...
👍 12
☁️ 🌟 🌟 🌟 ☁    صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ የአላህ መልእክተኛ👉 🌱አያመ አልተሽሪቅ መብያና መጠጫ       እንዲሁም አላህን ማውሻ ቀን ነው       ብለዋል።🌱 👆👆👆👆👆👆👆 እዚህ ሀዲስ ላይ ምርጥና ድንቅ የሆነ ትልቅ ሚስጥር ይዟል። እሱም የሰው ልጅ በሁሉም ጊዜያትና ሁኔታዎች ላይ ከጌታው ባርነትነና ታዛዥነት ጋር የተቆራኝ እንደሆነ ያመላክታል 👉አንድ ሙስሊም ፆመኛ ሲሆን አላህን      መገዛትን አስቦ  ከምግብ ከመጠጥ      እንደሚከለከለው ሁሉ  ✅ 👉ከዛሬ ጀምሮ አስከ ሮብ ያሉት 3ቱ      አያመተሽሪቅ ቀናቶች ላይ      ሁሉም ሙስሊም በመብላትና      በመጠጣት ለአላህ ኢባዳ      ያደርጋል በዚህም ላይ      የመልክተኛው ትእዛዝ      መከተልም አለበትና.👍            ‼️ ያ ጀመዐ ነቃ እንበል‼️ ❌ዛሬ ፣ ነገና ሮብ የሱና ፆምም ይሁን❌ ቀዳእም ይሁን ❌የስለት ፆምም ባጠቃላይ ምንም አይነት ፆም ❌ መፆም የተከለከለ ነው አይቻልም 👌በዚህ ፆም ክልከላ ላይ ግን አንድ      አካል ብቻ አይካተትም እሱም ሀጅ      ላይ ያለና ሀድይ ማረድ ያልቻለ ወይም      ያላገኘ ሰው ከእርዱ ቀን ቡሀላ      3ቱ የአያመተሽሪቅ ቀን ኢዚያው      ፆሞ ሰባቱን ደግሞ ወደ ሀገሩ      ሲመጣ ይፆመዋል። ☁ 🌟 🌟 🌟 ☁
نمایش همه...
👍 6
ቁርስ ከ በ3:00 ሗላ ነው
نمایش همه...
ዒድ የሚሰገደው ኮዬ ንፋስ ስልክ ስለሆነ ከኮዬ አደባባይ ንፋስ ስልክ ታክሲ በመያዝ መሄድ ትችላላችሁ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
🔊ለሁሉም የአዲስ አበባ  ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ  ተማሪዎች እንዲሁም በዙሪያው ያላችሁ ነዋሪዎች በሙሉ ፦ 🎆እንኳን ለ1445ኛው ዒድ አል-አድሃ🐑🐑 በዓል በሰላም አደረሳችሁ! 💧عيد أضحى مبارك عليكم وعلى من تحبون، تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
نمایش همه...
👍 21
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.