fa
Feedback
EECSF

EECSF

رفتن به کانال در Telegram

ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::

نمایش بیشتر
508
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
photo content

✍ Word of God | Sunday ይሄ ዘመን ምን አይነት ዘመን እንደሆነ እናውቃለን? ልክ እንደኖህ ዘመን ያለ ጊዜ ነው። እግዚአብሔር አስቀድሞ ልክ እንደኖህ ዘመን ተመለሱ እያለን ነው ወደእርሱ መርከብ እንድንገባ እየጠራን ነው። ግን ለዚህ ጊዜ የጌታ ጥሪ ሶስት አይነት መልስ የሚመልሱ አሉ፡- አንደኛው ሰምቶና አስተውሎ በዝግታ ወደጌታ መርከብ የሚሳፈር ሲሆን። ሁለተኛው ደግሞ ሰምተው የሚያፌዙ ናቸው። ሶስተኛው ደግሞ የሚያሳዝነው በተመሳሳይ መርከቦች ነገር ግን ውሃ በመጣ ጊዜ በሚሰምጡ መርከቦች ጥሪ የሚታለሉት ናቸው። ይህ እዳይሆን ግን ትክክለኛዋ መርከብ የቷ እንደሆነች ጌታ አስቀድሞ በቃሉ ተናግሯል። እናም ይህ ጊዜ ጌታ ወደመርከቡ እየራጠን ያለበት ጊዜ ነው አስተውሎ ወደመርከቢቱ የሚገባ እርሱ ይድናል። ነገር ግን ችላ ላለ የንስሀውን በር ጌታ ከውጪ የሚዘጋበት ቀን ይመጣል። የዛኔ ማንም ምህረት ቢለምንም የማይከፈትበት ጊዜ ይሆናል። ቀን ሳለ በጌታ እጅ ሰለመሆናችን እርግጠኛ እንሁን! By: #Abebayehu ******************************* Join and share EECSF Channel: @EECSF @EECSF @EECSF

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫 "እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ" 📌 ይህ በዓይነቱ ለየት ያለ ተከታታይ የቴሌግራም ሾው ዘወትር ሰኞ ምሽት በ @EECSF ቻናል ይተላለፋል። 📌 በዚህ
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫 "እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ" 📌 ይህ በዓይነቱ ለየት ያለ ተከታታይ የቴሌግራም ሾው ዘወትር ሰኞ ምሽት በ @EECSF ቻናል ይተላለፋል። 📌 በዚህ ሾው ላይ የሚቀርቡ ፕሮግራሞች : 👉 ቃለ እግዚ (የመ/ቅ ጥናት ማጠቃለያ) 👉 ቅኔ (የዝማሬ ግብዣ) 👉 ትዝታ(ቆየት ያሉ ትውስታዎች) 📌 ይህን ሾው ስፖንሰር ለማድረግ የምትፈልጉ ሰዎች በ @Am2nddd ልታገኙን ትችላላችሁ። 📌 ሀሳብና አስታየት ካላችሁም በ @Am2ndd ማድረስ ትችላላችሁ። 📌 ፕሮግራማችን በመጪው ሰኞ (19-08-2012) ይጀምራል። 🙌 #Stay_Home #Stay_Tuned 🙌

✍ Word of God | Saturday 2nd Corinthians 13 "Last Advice of St.Paul" 📌 ምክር 1 👉 እኛ እናንተን ስንመክር እና ስንገስፅ ደካሞች ብንመስላችሁ እንኳን በእኛ አቅም ሳይሆን ብርቱ በሆንንበት በክርስቶስ መንፈስ ስለሆነ የምንናገረው ይህን ምክራችንን መቀበል እና በመንፈሳዊ መንገድ መኖር ይጠበቅባችኋል።(ቁ.4) 👉 ይህ ማለት በህብረት ውስጥ ስላለው መቀባበል እና መደማመጥ አመልካች ነው። ክርስቶስ ራስ በሆነበት ህብረት አገልጋዩ የራሱን ነገር ሊያንፀባርቅ አይችልም። ስለዚህ እርስ በራስ መወቃቀስ እናመደማመጥ አስፈላጊ ነው።(ቁ.5) በአንዱ ወንድም ውስጥ ሆኖ የሚናገረው በውስጡ ያለው መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ። 📌 ምክር 2 👉 ፀሎት እርስ በእርሳችን አንዱ ለሌላው እንዲፀልይ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። በዚህ ምንባብ መሠረት በሁለት ነገሮች ላይ እንፀልያለን። 1: በህይወታችን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ የሆነ እና ክርስቶስን የማያከብር (ክፉ ነገር) እንዳናደርግ መፀለይ ነው። 2: ማንም ብርቱ የለም : ነገር ግን ብርቱ የሆነው ክርስቶስ ወደ እርሱ ፍፁም ሙላት እንዲያደርሰን አንዱ ለሌላው መፀለይ ነው። 📌 ምክር 3 👉 አገልግሎት ለማነፅ እንጂ ለማፍረስ አይደለም 👉 አገልግሎት ማለት ከእግዚአብሔር የተቀበልነውን ብቻ እርሱ በሚፈልገው መንገድ ለህብረቱ ማድረስ ነው። ይህም ለክርስቶስ ህንፃ ግንባታ አስተዋፆ ማድረግ ነው። ከእኛ የሆነውን ነገር ስንጨምር ከህንፃው ተግባብቶ መቶም ስለማይችል እያፈረስን ነው ማለት ነው። 📌 ምክር 4 👉 ፍፁማን ሁኑ ፣ አንድ ሀሳብ ይኑራችሁ ፣ በሰላም ኑሩ 👉 እነዚህ ሶስት ነገሮች ተያይዘው የሚሄዱ ናቸው። ሰዎች ወደ ክርስቶስ ፍፁምነት(ፍፁም ሙላት) እና እርሱን ወደመምሰል በሚያደርጉት ሩጫ ተመሳሳይ ነገርን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር በአንድነት እና በህብረት + በመያያዝ እና በመገሳሰፅ + በመደጋገፍ እና በመረዳዳት አንድ ላይ ይሰራሉ። ይህ ደግሞ የሰዎችን ትኩረት ሁሉ በመስቀሉ እና በክርስቶስ ላይ ስለሚያደርግ በህብረት ውስጥ ሊፈጠር የሚችለውን የሠላም አለመኖር ያጠፋዋል። 📌 አንድ የመጨረሻ 👉 በተቀደሰ አሳሳም ሰላም ተባባሉ። በአሁኑ ጊዜ አባባል ርቀታችሁን ጠብቃችሁ ሰላም ተባባሉ 🤝❌ 🖐 🖐🏾 ✅ እኔም ርቀቴን ጠብቄ ሰላምታዬን አደርሳለው። 🖐🏾 By: #አማኑኤል አበራ ******************************* Join and share EECSF Channel: @EECSF @EECSF @EECSF

😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተከታታይ ፕሮግራም ማቅረብ ይችላሉ:: 🤔Just contact us on: @DETAE1 @Caleb_24
😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተከታታይ ፕሮግራም ማቅረብ ይችላሉ:: 🤔Just contact us on: @DETAE1 @Caleb_24

#Chain_prayer(Chain48)_update 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 👉 የተወደዳችሁ ቅዱሳን ከሁለት ሳምንት በፊት ጀምረነው የነበርነው የፀሎት ሰንሰለት ከ ሰኞ(ሚያዚያ 19) ጀምሮ የሚቀጥ
#Chain_prayer(Chain48)_update 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 👉 የተወደዳችሁ ቅዱሳን ከሁለት ሳምንት በፊት ጀምረነው የነበርነው የፀሎት ሰንሰለት ከ ሰኞ(ሚያዚያ 19) ጀምሮ የሚቀጥል ይሆናል:: 👉ይህ ፀሎት ከ “smart coordinators “ እና ከተለያዩ ተማሪዎች በተቀበልነው ገንቢ ሀሳብ መሠረተ ሳይቋረጥ የሚቀጥል ይሆናል:: 👉እንደ ቅሬታ የተነሱት ሀሳቦች: * በሰዓታችን ከፀለይን በኃላ ለቀጣዩ ሰው አለመደወል🤷‍♂ * የማንቂያ ደውል(Alarm) ሳይሞሉ መዘናጋት😉 * የተነሣሽነት ጉድለት😮 * የፀሎት ርዕሶች በጊዜ post አለማድረግ😉 * ቋሚ የ bs ጊዜ ቢኖር 📌 የመፍትኄ ሀሳቦች ☑️ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር እናንሳ ☑️ ወገባችንን በእውነት እንታጠቅ ☑️ የጽድቅን ጥሩር እንልበስ ☑️ በሰላም ወንጌል እግሮቻችን ይጫሙ ☑️ የእምነትን ጋሻ እናንሣ ☑️ የመዳንን ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ እንያዝ 😁 እንግዲያውስ በቀረው አለመፀለይ አይቻልም:: 👉 Alarm ይሞላ✊ 👉 ስልክም ይደወል✊ 👉 የፀሎትም ርዕስ በጊዜ post ይደረግልን ✊ 👉 እየተነሳሳን እንንቃ 👊 👉 ዘወትር ሰኞ ሁላችንም በ የ#teamu bs እናድርግ:: • <If there is a will,there is a way> 🔺በክርስቶስ ኢየሱስ ያመነ ሰው ሁሉ አሁን ኩነኔ የለበትም። For any of your comment: @Caleb_24 @DETAE1 🙏🙏🙏ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ:: Join and share EECSF Channel: @EECSF @EECSF @EECSF

መሳይ እምሩ "ከቃሉ ጋር መገናኘት”/ "(Scripture Engagement)" በሚል ርዕስ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ለመገናኘት ልባችን እንዲነሳሳ ይመክረናል:: በዚህም "ቃሉና እግዚአብሔርን መውደድ" ፤ "ቃሉና የሕይወት ተሃድሶ" ፤ "ቃሉና የመንግሥቱ ወንጌል መረዳት" የሚሉ ሀሳቦችን ያብራራል:: ቪዲዮውን ይመልከቱ፡፡ተጠቀሙበት አካፍሉትም::https://youtu.be/LRwUnwNIn6M

ውድ የኢቫሱ ሕብረቶች ውስጥ ያላችሁ ተማሪዎች ይህ አጭር ቪዲዮ በቤት ውስጥ ሳለን ጊዜያችንን በተሻለ እንዴት ለመጠቀም እንደምንችል ለተማሪዎች ምክር ይሰጣል ፡፡ እባክዎን ቪዲዮውን ይመልከቱ፡፡ ተጠቀሙበት አካፍሉትም:: https://youtu.be/IRO0f0FCTTc

[@12] #EECSF_Graphics Join and share EECSF Channel: @EECSF @EECSF @EECSF
[@12] #EECSF_Graphics Join and share EECSF Channel: @EECSF @EECSF @EECSF

📌 #ዝማሬ{ሳሙኤል ጋሻው} 🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼 EECSF: -[@12]>>_graphics -inspirations -poem -motion graphics -Gospel Songs -word of God #እዚህ ያገኛሉ #Share በማለት ለሌሎችም ያጋሩ ። Click here 👇👇👇👇 https://t.me/EECSF Click here 👇👇👇👇 https://t.me/CSFEiABC

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ******************************* እንዴት ናችሁ የተወደዳችሁ እህቶችና ወንድሞች? በያላችሁበት የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ! በሚሆነው ሁኔታ ከልክ በላይ እየተናወጣችሁ እንዳልሆነ እናምናለን ምክንያቱም ❝አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።❞ ፊልጵስዩስ 4: 7 ባልጠበቅነው ሁኔታ ለጊዜው ተራርቀን ለመቆየት ብንገደድም በፀሎትና ቃሉን በማጥናት በአንድነት ወደ ጌታ እንድናድግ እየተደረገ ባለው ጥረት ሁላችሁም እየተካፈላችሁ እንደሆነ እናምናለን! በአካል አብረን ስንሆን የአንድነታችን ምክንያት የሆነው መንፈስ ቅዱስና የምንተባበርበት ዓላማ አሁንም በያለንበት አብሮን አለ! በጋራ ስንሰባሰብና በአገልግሎት ዘርፎች (teams) በኩል የምናደርገውን ፀሎት ፣ ዝማሬ ፣ ቃሉን መከፋፈል ፣ ፍቅርን የማካፈል ተግባራት ፣ እምነታችንን የሚገልጡ የጥበብ ስራዎችን መስራት ወዘተ. በያለንበት እንዲቀጥል እናበረታታለን! አገልግሎት የሚጀምረው የጌታን ቤተ መቅደስ ከመጠበቅ ስለሆነ ራሳችሁን እየተንከባከባችሁ ፣ በአጠገባችሁ ላሉ ሁሉ ፍቅራችሁን በተግባር እየገለጣችሁ ፣ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ነገር በማሳደግ ጊዜውን ለመልካም እንድትጠቀሙበት እናበረታታለን! ❝እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።❞ ሮሜ 8: 28 ይህን ቃሉን በማመን ይህ ጊዜ አልፎ ሁላችንም በአንድነት ጌታን እንድናመሰግን ፀሎታችሁን አታቋርጡ! 🔺በክርስቶስ ኢየሱስ ያመነ ሰው ሁሉ አሁን ኩነኔ የለበትም። Join and share EECSF Channel: @EECSF @EECSF @EECSF

📌 #ዝማሬ{አማኑኤል አበራ} 🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼 EECSF: -[@12]>>_graphics -inspirations -poem -motion graphics -Gospel Songs -word of God #እዚህ ያገኛሉ #Share በማለት ለሌሎችም ያጋሩ ። Click here 👇👇👇👇 https://t.me/EECSF Click here 👇👇👇👇 https://t.me/CSFEiABC

እግዚአብሄርን መፈለግ ------------------- እግዚአብሔር ፈልጉ ስል ይገኛል እያልኩ ነው። እሱ የሌለ ነገር አያስፈልገንም። የሚያስፈልገንን ከፈለግን እናገኛለን። መፈለግ፣ ጊዜ፣ ጉልበት ፣ትጋትና ትግዕስት ይጠይቃል። ሆኖም በዚህ ሁሉ የምንፈልፈው ማግኘትን አልመን ነው። እግዚአብሔረር መፈለግ፣ መጠጋት መቅረብና ፈቃዱን ማድረግ ነው። አሁን እግዚአብሔርን ብዙዎቻችን እየፈለግን ነው። ከዚህ በፊት ፈልግልኝ እከፍልሃለው ነበር። አሁን ግን ሁሉም ወደ ቦታው ተመልሷል። ♥ መፈለግ ማጣትም አለበት። ነገር ግን እግዚአብሔርን ፈልጎ ያጣ የለም። እግዚአብሔርን የምንፈልገው በውስን ቦታ ስለሚገኝ አይደለም፤ ልምምዳችን እሱን እንዲሆን ስለሚፈልግ እንጂ። እግዚአብሔርን ፈልጎ ያጣ የለም፣ + በእሳት ውስጥ + በእስር ቤት + በአንበሳ ጉድጓድ ውስጥ ሁሉ እግዚአብሔር ተገኝቷል። በደጉ ጊዜ ያወቁት በመከራም አብሮአቸው ነበር። ዛሬም እኛ እየለመድን ያለው እሱን የመፈለግ ነገር ይቀጥላል። ======== እርዳው ጴጥሮስ ደቡብ_ኢቫሱ ========= ይቀላቀሉ 👉🏿 @EvaSUE58

The RESURRECTION of Christ *ሁለቴ ተወለድኩ* *** አበባየሁ አናቶ ** ልዩ የበአል ዝግጅት ** Presented by RESURRECT crew * Join and share EECSF Channel: @EECSF @EECSF @EECSF

The RESURRECTION of Christ **Rap** * MD * ልዩ የበአል ዝግጅት **** Presented by RESURRECT crew **** Join and share EECSF Channel: @EECSF @EECSF @EECSF

The RESURRECTION of Christ **ቃል** *** ካሌብ አለማየሁ (ችዋ) *** ልዩ የበአል ዝግጅት **** Presented by RESURRECT crew **** EiABC fellowship

አዳንከኝ(8) በፍቅርህ ገዛኸኝ ልጅህ አደረከኝ(2) The RESURRECTION of Christ አዳንከኝ**** ሳሙኤል ጋሻው ********** ልዩ የበአል ዝግጅት ********** Presented by RESURRECT crew ******** ** EiABC fellowship

The RESURRECTION of Christ **የኢየሱስ ደም********** ሳሙኤል ጋሻው ****************** ልዩ የበአል ዝግጅት ****************** Presented by RESURRECT crew ****************** Join and share EECSF Channel: @EECSF @EECSF @EECSF

The RESURRECTION of Christ *ፀሎት* * ሱራፌል ፈቀደ ልዩ የበአል ዝግጅት ** Presented by RESURRECT crew * EiABC fellowship

እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ መታሰቢያ ቀን በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፡፡ ሁላችንንም በምህረቱ እና በቸርነቱ ጠብቆ እንዲሁም ለወደደን ከሀጢአታችንም በደሙ ላጠበን ለእ
እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ መታሰቢያ ቀን በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፡፡ ሁላችንንም በምህረቱ እና በቸርነቱ ጠብቆ እንዲሁም ለወደደን ከሀጢአታችንም በደሙ ላጠበን ለእርሱ ከ ዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ሀይል ይሁን፤አሜን፡፡ እነሆ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው በ ቡድን "Resurrect" የተዘጋጀው መርሃግብር አሁን እነሆ እንላችኃለን፡፡ መልካም ቆይታ!