cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ፍኖተ ቅዱሳን ዘ ተዋህዶ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
189
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33 #ስንክሳር ዘጥቅምት #ሃያ ስድስት (፳፮)     ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
نمایش همه...
ጥቅምት 26.mp33.98 MB
----------------------------------------------- ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ! " አንድ ሃይማኖት " [ ኤፌ.፬፥፭ ] [   ፰   ] ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ " ሥጋን ነሥቶ ሰው ቢሆን እርሱስ ሕማምን ሞትን ድል የሚነሣ ነው፡፡ ያልፋል ይለወጣል በማይባል ባሕርይ ለዘላለሙ ጸንቶ ይኖራል፡፡ በኋላ ዘመን በተለየ አካሉ ሥጋን የተዋሐደ እርሱ ነው። [ ዮሐ.፩፥፩-፲፬ ፣ ገላ.፬፥፬] ዓላም ሳይፈጠር በሁሉ በምልአት የነበረ ነው፡፡ እርሱ ሁሉን ይጠብቃል፡፡ መላእክትን ከመፍጠሩ አስቀድሞ የአባቱ የእግዚአብሔር ጌትነት ገንዘቡ ነው፡፡ በማይለወጥ ባሕርዩ ጸንቶ የሚኖር እርሱ ነው፡፡ ለርሱ ከቸር አባቱ ከመንፈስ ቅዱስም ጋር ክብር ይግባው፡፡ ሦስቱ በሥራ ሁሉ አንድ ናቸው፡፡ ፍጡር አይደለም፡፡ አይለወጥም፡፡ ጥንት ፍጻሜ የለውም፡፡ በአካል በገጽ በመልክ ሦስት ሲሆን በባሕርይ አንድ አምላክ ነው። ከዚህ ወጥቶ ሌላ ሃይማኖት የሚያስብ ቢኖር ለዘላለም ፡ የተለየ የተወገዘ ይሁን ። ሰው የሆነው እግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ከቅድስት ድንግል ማርያም በቤተልሔም በተወለደው የማያምን ቢኖር በቃላችን በእውነት የተለየ ይሁን፡፡ ሰውን ሁሉ ይልቁንም ያመኑበትን ያዳነ ነውና እግዚአብሔር ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ' አምላክ የማይለወጥ የዘለዓለም ሕይወት ነው። [ዮሐ.፬ ፣ ገላ.፩፥፷፯ ፣ ፩ጢሞ.፬፥፲] [ ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ ] ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🕊                     💖                       🕊
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
➯ በዚህ ዓለም ሳለን የእኛ ማዕረግ የሚወሰነው እንደ እድሜያችን እንደ ተሰጥኦአችን ወይም እንደ ችሎታችን ነው፤ በዘላለማዊው ሕይወት ግን ማዕረጋችን የሚወሰነው እግዚአብሔርን የበለጠ በምታውቅ ልብ ነው፤ ምናልባት ብዙዎች የተናቁ የተጠሉና ችላ የተባሉት እነዚያ ተሰጥኦ ወይም ሥልጣን ያላቸውን ሊበልጧቸው ይችላሉ፤ ስለዚህ ታናናሽ የተባሉትን በሙሉ እንዳትንቁ ይሁን። ➯ እግዚአብሔር ኢያሪኮን ለማዳን በወደደ ጊዜ የመረጠው ጋለሞታዋን ረዓብን ነበር፤ ከዚህ የተነሳ ረዓብ በጌታ የዘር ሐረግ ውስጥ ከተጠቀሱት የእግዚአብሔር  ሰዎች መካከል አንዷ ሆና እንድትቆጠር ሆኗል፤ ያለፈው ሕይወቷ ስለ ተረሳና ቅድስት ስለ ሆነች ለሚያስታውሳት ሁሉ ሕያው ምሳሌ ወይም አርአያ ሆናለች። 📖ማቴ 1፥1 ➯ እግዚአብሔር  ጋለሞታዋንና አጋንንት የነበሩባትን ሴት ምን ያህል እንደተንከባከባት ስትመለከት ልትደነቅ ትችላለህ፤ እርሱ እንዲህ ያለውን እንክብካቤ ለተናቁት ለተጠሉትና ምንም ዓይነት ነገር አይገባቸውም ለተባሉት ሁሉ ያደርጋል። 📖1ኛ ቆሮ 1፥27-28 📌 ምንጭ ✍ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
نمایش همه...
  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33 #ስንክሳር ዘጥቅምት #ሃያ አምስት (፳፭)     ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
نمایش همه...
ጥቅምት 25.mp37.17 MB
🕊 [  ለጀማሪ ታሐራሚ የተሰጠ ምክር   ] ------------------------------------------------- ......... " ወዳጄ ሆይ ! በሙሉ ልብህ መዝሙራትን ለመድገምና ቅዱሳት መጻሕፍት ለማንበብ ትጋ፡፡ ሕፃን ከእናቱ ጡት የተነሣ እንዲፋፋ እንዲሁ ነፍስህ ከቃሉ ወተት ጠጥታ ትፋፋ ዘንድ ቅዱሳት መጻሕፍትን ዘወትር በማንበብ ትጋ፡፡ ከእነርሱ የመልካም ሥነ ምግባርን ዋጋ ትረዳለህ ፤ ለነፍስህም ደስታና ሐሴት ትሰጣታለህ፡፡ ወዳጄ ሆይ የዋህ ፣ ታዛዥና ትሑት ሁን፡፡ እንደ ሕፃናት የዋህ ከሆንህ እርሱን መከተልና ፈቃዱን መፈጸም ይቻልሃል። በበአትህ [በመኖሪያህ በቤትህ] ሆነህ አርምሞን ገንዘብህ አድርገህ ኑር፡፡ ብዙ ከመናገር ተከልክለህ አርምሞን ውደድ፡፡ በልብህ ግን ወደ አምላክህ ጸልይ ለቃሉም ታዛዥ ሁን ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሰውነትህ ቅድስናን ገንዘብ ታደርግ ዘንድ በጌጠኛ ልብስ ሥጋህን አታስጊጣት፡፡ ባለጸጋ ዘመድ ስላለህም ራስህን አታስታብይ፡፡ ሊመካ የሚወድ በእግዚአብሔር ይመካ ይላልና፡፡ ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር የሰው ሁሉ ክብር እንደ ምድር አበባ ነውና፡፡ ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል የእግዚአብሔር ቃል ግን ለዘለዓለም ይኖራል፡፡ ተወዳጆች ሆይ ! በጌታችን ሆኜ ሌላ ተጨማሪ መመሪያን እሰጣችኋለሁ፡፡ እርሱን ፈጽማችሁ ከተገኛችሁ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ደስ ያሰኛችኋል፡፡ ከንቱ የሆነውን ሕይወት ክደህ ወደ ቅዱሳን ሕብረት ከገባህ በኋላ ማኅበሩን ጥለህ ትወጣ ዘንድ የጠላት ዲያብሎስን ምክር አትስማ፡፡ በፍጹም ትሕትና ሆነህ ሥራህን ጀምር፡፡ ከጠላትህ የተነሣብህን ፈተና እንደ በቀቀን መልሰህ አታስተጋባው። ብፁዓን ከሆኑት ቍጥር ትሆን ዘንድ ታጋሽ ሁን፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ “በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው ፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና፡፡” [ያዕ.፩፥፲፪] " 🕊 [   ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ    ] ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
نمایش همه...
✞ እናቴ እመቤቴ እናቴ እመቤቴ/ የማትጠፊው ከአፌ/2/ በረከቴ አንቺ ነሽ/ የመስቀል ስር ትርፌ /2/ አምላኬ ሸልሞኝ ለዘላለም ያዝኩሽ ጌታን የማይብሽ ብሌኔ አደረኩሽ በልቤ ላይ ይፍሰስ የፍቅርሽ ፀዳሉ የሚጣፍጥ ስምሽ መድኃኒት ለሁሉ ተወዳጁ ልጅሽ ፀጋውን ያብዛልኝ እድሜዬ እስኪ ፈፀም ለክብርሽ እንድቀኝ /አዝ==== ነፍሴ እንዳትጎዳ እንዳትቀር ባክና ብርታት ሆኖልኛል የስምሽ ምስጋና እኖራለሁ ገና ንኢ ንኢ ስልሽ ክብሬ ነሽ ጌጤ ነሽ ከአፌ የማልነጥልሽ /አዝ ===== ሲነጋም ጠራሁሽ ሲመሽም ጠራሁሽ ስዕልሽ ፊት ቆሜ ሰአሊ ለነ እያልኩሽ አሜን የምልብሽ መነጋገሪያዬ የአማኑኤል እናት አንቺ ነሽ ቋንቋዬ /አዝ===== መች በስጋ ጥበብ ሰው ለአንቺ ይቀኛል ከአምላክ ከአልተላከ ከፊትሽ ይቆማል አንቺን ማመስገኔ አንቺን ማወደሴ በልቡ ያሰበሽ ፈቅዶ ነው ስላሴ /አዝ===== ብዙ ተቀብዬ ጥቂት አልዘምርም ለእናትነት ፍቅርሽ ከቶ ዝም አልልም እኔን በእደ ፍቅርሽ የምትባርኪ ኦ ምልዕይተ ፀጋ ድንግል ሰላም ለኪ
نمایش همه...
ድንግል_ማርያም_ብዬ_ሊቀ_መዘምራን_ኪነጥበብ_@DNZEMA_ዜማ_ቅዱስ_ያሬድ.mp36.63 MB
Photo unavailableShow in Telegram
በዝምታው ፥ በቅድስና ሕይወቱና በብቸኝነት የሚታወቁት ጻዲቅ ዝምተኛው መነኩሴ "አባ ዮስጦስ" በገዳመ እንጦስ ከተናገሯቸው በጥቂቱ፦ <ስለ ዝምታ> ☞ ከማድረግ መናገር ይቀላል ነገር ግን ልብ ወደ ሰማይ የሚወጣው በመናገር አይደለም ፤ ወደ ጌታችን መቅረብ የምትችለው በቃላት አይደለም፡፡ ☞ አንዳንድ ጊዜ ዝምተኛ ነኝ ነገር ግን ዝምታዬ ከእንባዬ ይልቅ ኃይል እንዳለው ይሰማኛል፡፡ ☞ ዝምተኛ ብሆንም ልቤ ግን በቃላት የተሞላ ስለሆነ እግዚአብሔር ሳልናገር ይሰማቸዋል ፤ የእግዚአብሔር ልብ ግን የርኅራኄ ፏፏቴ ነው፡፡ ☞ ቅድስና ቆሽሾ ከመታየት ጋር የማገናኘው ነገር የለም ፤ ከልብ ንጽሕና ጋር እንጂ፡፡ ☞ ማናችንም በራሳችን መልካም አይደለንምና ፤ የእግዚአብሔር ምሕረት ያስፈልገናል፡፡ ☞ እኔ መነኩሴ ስለሆንኩ ከእናንተ የምሻል ይመስላችኃል? አልሻልም ፥ጠባቡ በር ግን በመስቀል የተሞላ ነው ፤ለእያንዳንዱ ሰው አንድ መከራ አለው፡፡ ☞ እግዚአብሔር ግን ሁላችንንም ይፈልገናል ፤ እርሱ ማናችንንም ከእርሱ ተነጥለን እንድንጣል አይፈልግምና፡፡ ☞ እኔ ግን ማድረግ የምችለው ብቸኛ ነገር ዝምታ መማሬ ነው ፤ እግዚአብሔርን አመስግኑ፡፡ <"አሁን ስንት ሰዓት ነው?????????>" አባ ዮስጦስ ዝምተኛው መነኩሴ የአባታችን በረከት አትለየን፡፡ https://t.me/eotcy https://t.me/eotcy https://t.me/eotcy
نمایش همه...
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ =>+"+ እንኩዋን ለታላቁ "ጻድቅና ሰማዕት አቡነ አቢብ": "ለአባ ዕብሎይ" " ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+ +*" አቡነ አቢብ (አባ ቡላ) "*+ =>ይህን ታላቅ ቅዱስ በምን እንመስለዋለን! ¤እኛ ኃጥአን ጣዕመ ዜናውን: ነገረ ሕይወቱን ሰምተን ደስ ተሰኝተናል! ¤ቅዱሱ አባታችን:- "ቡላ - የእግዚአብሔር አገልጋይ" ብለን እንጠራሃለን:: ¤ዳግመኛም "አቢብ - የብዙኃን አባት" ብለን እንጠራሃለን:: ¤እርሱ ቅሉ አባትነትህ አንተን ለመሰሉ ቅዱሳን ቢሆንም እኛን ኃጥአንን ቸል እንደማትለንም እናውቃለን:: ¤አባ! ማነው እንዳንተ የክርስቶስን ሕማማት የተሳተፈ! ¤ማን ነው እንዳንተ በፈጣሪው ፍቅር ብዙ መከራዎችን የተቀበለ! ¤ማንስ ነው እንዳንተ በአንዲት ጉርሻ አማልዶ ርስትን የሚያወርስ! ¤የፍጡራንን እንተወውና በፈጣሪ አንደበት ተመስግነሃልና ቅዱሱ አባታችን ላንተ ክብር: ምስጋናና ስግደት በጸጋ ይገባሃል እንላለን:: +"+ ልደት +"+ =>አባታችን አቡነ አቢብ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ ሮሜ ናት:: ወላጆቹ ቅዱስ አብርሃምና ቅድስት ሐሪክ እጅግ ጽኑ ክርስቲያኖች ነበሩ:: ልጅ ግን አልነበራቸውም:: ዘመነ ሰማዕታት ደርሶ ስደት በሆነ ጊዜ እነርሱም በርሃ ገቡ:: +በዚያም ሳሉ በቅዱስ መልአክ ብሥራት ሐሪክ ጸንሳ ብሩሕ የሆነ ልጅ ወለደች:: ቅዱሱ ሕጻን ሲጸነስ ማንም ሳይተክለው የበቀለው ዛፍ ላይ መልአኩ እንዲህ የሚል የብርሃን ጽሑፍ ጽፎበት ወላጆቹ ዐይተዋል:: "ቡላ ገብሩ ለእግዚአብሔር: ወቅዱሱ ለአምላከ ያዕቆብ: ዘየኀድር ውስተ ጽዮን" +"+ ጥምቀት +"+ =>ቅዱሱ ሕጻን ከተወለደ በሁዋላ ሳይጠመቅ ለ 1 ዓመት ቆየ:: ምክንያቱም ዘመኑ የጭንቅ ነውና ካህናትን እንኩዋን በዱር በከተማም ማግኘት አይቻልም ነበር:: እመቤታችን ግን ወደ ሮሙ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሰለባስትርዮስ ሒዳ "አጥምቀው" አለችው:: +ወደ በርሐ ወርዶ ሊያጠምቀው ሲል ሕጻኑ ተነስቶ: እጆቹንም ዘርግቶ:- "አሐዱ አብ ቅዱስ: አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ አመስግኖ ተጠመቀ:: ከሰማይም ሕብስትና ጽዋዕ ወርዶላቸው ሊቀ ዻዻሳቱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የሕጻኑ ወላጆች "ለልጃችን ስም አውጣልን" ቢሉት "ቡላ" ብሎ ሰየመው:: እነርሱም ምሥጢሩን ያውቁ ነበርና አደነቁ:: +"+ ሰማዕትነት +"+ =>የቅዱሱ ቡላ ወላጆች ለ10 ዓመታት አሳድገውት ድንገት ሕዳር 7 ቀን ተከታትለው ዐረፉ:: ሕጻኑን የማሳደግ ኃላፊነትን የአካባቢው ሰዎች ሆነ:: ሕጻኑ ቡላ ምንም የ10 ዓመት ሕጻን ቢሆንም ያለ ማቁዋረጥ ሲጾም: ሲጸልይ ክፉ መኮንን "ለጣዖት ስገዱ" እያለ መጣ:: +በዚህ ጊዜ በሕጻን አንደበቱ አምልኮተ ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ የተበሳጨ መኮንኑ ስቃያትን አዘዘበት:: በጅራፍ ገረፉት: በዘንግ ደበደቡት: ቆዳውን ገፈፉት: በመጋዝ ቆራርጠውም ጣሉት:: ነገር ግን ኃይለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና 2 ጊዜ ከሞት ተነሳ:: በመጨረሻ ግን ሚያዝያ 18 ቀን ተከልሎ ሰማዕት ሆኗል:: +"+ ገዳማዊ ሕይወት +"+ =>ቅዱስ ቡላ ሰማዕትነቱን ከፈጸመ በሁዋላ ቅዱስ ሚካኤል በአክሊላት አክብሮ ወስዶ በገነት አኖረው:: ከሰማዕታትም ጋር ደመረው:: በዚያም ቡላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተመልክቶ ተደነቀ:: መንፈሳዊ ቅንዐትን ቀንቷልና "እባክህን ወደ ዓለም መልሰኝና ስለ ፍቅርህ እንደ ገና ልጋደል" ሲል ጌታን ለመነ:: +ጌታችን ግን "ወዳጄ ቡላ! እንግዲህስ ሰማዕትነቱ ይበቃሃል:: ሱታፌ ጻድቃንን ታገኝ ዘንድ ግን ፈቃዴ ነውና ሒድ" አለው:: ቅዱስ ሚካኤልም የቅዱስ ቡላን ነፍስ ከሥጋው ጋር አዋሕዶ: ልብሰ መነኮሳትንም አልብሶ ግብጽ በርሃ ውስጥ አኖረው:: +"+ ተጋድሎ +"+ =>አባ ቡላ ወደ በርሃ ከገባ ጀምሮ ዐርብ ዐርብ የጌታን ሕማማት እያሰበ ራሱን ያሰቃይ ገባ:: ራሱን ይገርፋል: ፊቱን በጥፊ ይመታል: ሥጋውን እየቆረጠ ለአራዊት ይሰጣል: ከትልቅ ዛፍ ላይ ተሰቅሎ ወደ ታች ይወረወራል:: +በጭንቅላቱ ተተክሎ ለብዙ ጊዜ ጸልዮ ጭንቅላቱ ይፈሳል:: ሌላም ብዙ መከራዎችን የጌታን ሕማማት እያሰበ ይቀበላል:: ስለ ጌታ ፍቅርም ምንም ነገር ሳይቀምስ ለ42 ዓመታት ጹሟል:: ጌታችንም ስለ ክብሩ ዘወትር ይገለጥለት ነበር:: +የሚታየውም እንደ ተወለደ: እንደ ተጠመቀ: እንደ ተሰቀለ: እንደ ተነሳ: እንዳረገ እየሆነ ነበር:: አንድ ቀንም ጌታችን መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! እንዳንተ ስለ እኔ ስም መከራ የተቀበለ ሰው የለም:: አንተም የብዙዎች አባት ነሕና ስምህ አቢብ (ሃቢብ) ይሁን" አለው:: "እስከ ይቤሎ አምላክ ቃለ አኮቴት ማሕዘኔ: ረሰይከኑ ለባሕቲትከ ኩነኔ: ዘመጠነዝ ታጻሙ ነፍስከ በቅኔ" እንዲል:: +" ዕረፍት "+ =>አቡነ አቢብ ታላቁ ዕብሎን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ:: ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት እየተጨዋወተ ዘለቀ:: በተጋድሎ ሕይወቱም ከ10 ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል:: በዚህች ቀን ሲያርፍ ገዳሙ በመላእክት ተሞላ:: +ጌታም ከድንግል እናቱ ጋር መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! ስምህን የጠራውን: መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ:: አቅም ቢያጣ "አምላከ አቢብ ማረኝ" ብሎ 3 ጊዜ በዕለተ ዕረፍትህ የሚለምነኝን: በስምሕ እንኩዋ ቁራሽ የሚበላውን ሁሉ እምርልሃለሁ" ብሎት ነፍሱን በክብር አሳረገ: በሰማይም ዕልልታ ተደረገ:: +"+ ታላቁ አባ ዕብሎይ +"+ =>ይህ ቅዱስ የአቡነ አቢብ ደቀ መዝሙር ሲሆን በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳንም ቀዳሚው ነው:: ብዙ መጻሕፍት "ርዕሰ ገዳማውያን" ይሉታል:: የቅዱሱ ተጋድሎ እጅግ ሰፊ በመሆኑ በዕለተ ዕረፍቱ (የካቲት 3 ቀን) እንመለከተዋለንና የዚያ ሰው ይበለን::
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.