cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Health. Com/ጤናን በቴሌግራም

👉 ይህ የTelegram channel ስለ ጤናዎ በጥቂቱ ግንዛቤ ያስጨብጣል። 👉 ማንኛውንም ጤና ነክ ጉዳይ እናማክራለን

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
293
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የስኳር ህመም / Diabetes Mellitus /DM የስኳር ህመም በደም ውስጥ በሚፈጠር ከልክ ያለፈ የስኳር መጠን ሳቢያ የሚከሰት የእድሜ ልክ የጤና ችግር ነው።ይህም በደማችን ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን፡- 1.በባዶ ሆድ ለ 8 ሰዓት ምግብ ሳይበላ የሚሰራ የስኳር መጠን ፣126 እና ከዚያ በላይ ሚ.ግ/ ደ.ሊ ሲሆን ወይም 2. ሽንት ቶሎ ቶሎ የሚሸኑ ከሆነ፤ዉሃ ቶሎ ቶሎ የሚጠማዎት ከሆነ ፣ ከወትሮ የተለየ የረሃብ ስሜት የሚያስቸግሮት ከሆነ እና በማንኛውም ሰዓት የሚለካ የስኳር መጠን ፣200 እና ከዚያ በላይ ሚ.ግ/ ደ.ሊ ሲሆን ወይም 3.በ 3 ወር የሚሰራ አማካኝ የደም ውስጥ የስኳር መጠን( hemoglobin A1C (HgA1c test)) ከ 6.5% በላይ ሲሆን የስኳር ህመም አለበት እንላለን። የስኳር ህመም አይነቶች • Type I DM (1ኛው አይነት የስኳር ህመም) የሚከሰተው ቆሽት ሙሉ በሙሉ ኢንሱሊን ማመንጨት ሲያቆም ነው። አብዛኛውን ጊዜ በህፃናት ላይና እድሚያቸው ከ 30 ዓመት በታች በሆኑ ሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን የስኳር ህመም ቆሽት ኢንሱሊን ማምረት ስለሚያቆም የሚታከመው በ ኢንሱሊን ብቻ ነው። •Type II DM( 2ኛው አይነት የስኳር ህመም ) ሰውነታችን ከቆሽት የሚመነጭዉን ኢንሱሊን መጠቀም ሳይችል ሲቀር ወይም ለሰውነታችን በቂ የሆነ ኢንሱሊን ቆሽት ማመንጨት ሳይችል ሲቀር የሚፈጠር የስኳር ህመም አይነት ነው። ሁለተኛው አይነት የስኳር ህመም በመድሃኒት፣ ጤናማ አመጋገብ በመከተልና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ማከም እና የደም ውስጥ የስኳር መጠንን መቆጣጠር ይቻላል። ለስኳር ህመም አጋላጭ ሁኔታዎች ለሁለተኛው አይነት የስኳር ህመም የሚያጋልጡ ጉዳዮች • የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ • ከመጠን ያለፈ ውፍረት • የእድሜ መግፋት • በቤተሰብ ውስጥ የስኳር ህመም ታሪክ መኖር የስኳር ህመም ምርመራ መደረግ ያለበት ምን ዓይነት ምልክቶች ሲታዩ ነው? 1. ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት 2. ቶሎ ቶሎ ዉሃ መጠማት 3. የሰዉነት ክብደት መቀነስ 4. ከወትሮ የተለየ የረሃብ ስሜት 5. ቶሎ የማይድን ቁስል ካለ 6. ዕይታ ላይ ብዥታ ካለ 7.ተደጋጋሚ ኢንፌክሽን ( የኩላሊት፣ የሽንት ቱቦ፣ የቆዳ ኢንፌክሽን) 8.የነርቭ ህመም (እጅና እግር መደንዘዝ፣ የሽንት መቆጣጠር ችግር፣ ስንፈተ- ወሲብ)
نمایش همه...
የስኳር ህመም ተጋላጭነት ** 👉 ለዓይነት 2 ስኳር ህመም የሚያጋልጡ ሁኔታዎች #ሊቀየሩ የሚችሉ እና መለወጥ የማንችላቸው #የማይሻሻሉ ተብሎ በሁለት ይከፈላል። 1) መለወጥ የማንችላቸው ተጋላጭነት ሁኔታዎች (#Non-modifiable Risk Factors) 👉 ለአይነት 2 የስኳር ህመም የመጋለጥ እድልን የሚጨምሩ ሊቀየሩ የማይችሉ ሁኔታዎች፡- ✅ በቤተሰባቸው ውስጥ የስኳር ህመም ያለባቸው (#FamilyHistory) ✅ እድሜ ከ40 ዓመት እና ከዚህ መሆን ➬ በእድሜዎ በጨመረ መጠን የመጋለጥ እድል ከፍ ያለ ይሆናል። ✅ በእርግዝና ጊዜ የስኳር ህመም (#GestationalDiabetes) ➬ ከዚህ ቀደም በእርግዝና ጊዜ የስኳር ህመም ካጋጠመዎት በወደፊት ህይወትዎ ውስጥ እንደገና የመከሰት እድልዎ ከፍ ያለ ነው። 2) ሊቀየሩ የሚችሉ ተጋላጭነት ሁኔታዎች (#Modifiable Risk Factors) 👉 አንዳንድ ለስኳር ህመም የሚያጋልጡ ሁኔታዎች እርስዎ በመረጡት የአኗኗር ዘይቤ ሊቆጣጠሩ ይችላሉ። እነዚህም፦ ✅ ከፍተኛ የሰውነት ክብደት (BMI: ≥25 Kg/m2) (#Overweight or #Obesity) ✅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (Physically Activity) ➬ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የኢንሱሊን መቋቋምን ኃይል (Insulin Resistance) ለመቀነስ ይረዳል። ይህ ማለት ደግሞ ሰውነትዎ የራሱን ኢንሱሊን በብቃት እንዲጠቀም ያግዛል። ➬ በሳምንት ቢያንስ ለአምስት ቀናት የ30 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ የስኳር በሽታ እና የልብ ህመም ተጋላጭነትን በእጅጉ እንደሚቀንስ ተረጋግጧል። ✅ የደም ግፊት (#Hypertension) ➬ በልብና በደም ሥር (cardiovascular system) ላይ ጉዳት ከማድረስ በተጨማሪ ሕክምና ያልተደረገለት ከፍተኛ የደም ግፊት ከስኳር በሽታ ጋር ተያይዞ ልመጣ ይችላል። ➬ የስኳር እና የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ከ130/80mmHg በታች የሆነ የደም ግፊትን መጠበቅ አለባቸው። መደበኛ የደም ግፊት ከ 120/80 mmHg በታች ነው። ✅ በደም ውስጥ የቅባት (#Cholesterol /#Lipid) መጠን መቆጣጠር ✅ ማጨስ (#Smoking) ✅ አመጋገብ (#Diet) ✅ አልኮል (#Alcohol) ➬ አልኮልን በብዛት መጠቀም የቆሽት (#Pancreas) ቁስለት በማስከተል በቂ ኢንሱሊን ለማምረት ያለውን አቅም ይገድባል። ➬ እንዲሁም አልኮሆል በጉበት ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፤ ይህም ስኳር ጉበት ውስጥ ተከማችቶ እንዳይቀመጥ ያደርገዋል። ➬ ስለዚህ አልኮሆል የመውሰድ መጠን መጠነኛ ያድርጉ። ይህም ማለት ለሴቶች በቀን አንድ መጠጥ እና ለወንዶች ሁለት መጠጦች። (አንድ መጠጥ = 1 ጠርሙስ ቢራ = 330 ሚሊ ሊትር) ✅ ውጥረት / ጭንቀት (#Stress) ➬ በህይወታችን ውስጥ ያለውን ጭንቀት መቆጣጠር ለስኳር በሽታ ብቻ ሳይሆን ለልብ ህመም እና ለሌሎች በርካታ የጤና ችግሮች አስፈላጊው የጤና ኑሮ አካል ነው። ✅ እንቅልፍ (#Sleep) ➬ አዋቂዎች በቀን ከሰባት እስከ ዘጠኝ ሰአታት መተኛት አለባቸው። እንቅልፍ ልብዎን እና አዕምሮን ጨምሮ መላውን ሰውነትዎን ይጠቅማል፤ ስሜትን, ትውስታን እና ምክንያታዊነትን ያሻሽላል። ❤ የእኛን ጤናማ የኑሮ ምክሮች በመከተል፣ ሊቀየሩ የሚችሉ ተጋላጭነት ሁኔታዎች መቆጣጠር ይችላሉ። አሁኑኑ ቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን በመውሰድ የስኳር በሽታን መከላከል ወይም ማዘግየት እንዲሁም ህይወትዎን ማሻሻል ይችላሉ።🙏🙏🙏 መልካም ጤንነት ምንጭ፦ ✍️ American Heart Association ✍ American Diabetes Association ሌሎችም ይወቁ ለወዳጅ ዘመዶ #ሼር ያድርጉ! #diabetes #hypertension #riskmanagement Vai medicinedaily
نمایش همه...
CHOLERA OUTBREAK ALERT ❗️⚠️❗️ የኮሌራ(Cholera)/ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት(አተት) በሽታ ወረርሽኝ በህብረተሰቡ ውስጥ እየተከሰተ ይገኛል ___⚠️____ እስከ ሰኔ 28, 2015 ዓ.ም በተደረሰው መረጃ መሠረት በደቡብ ክልል 6 ዞኖችና( ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ጌድዖ ና ሀድያ) ፤ 4 ልዩ ወረዳዎች (አሌ፣ አማሮ፣ ባስኬቶና ቡርጂ) 4087 ሰዎች በበሽታው እንደተጠቁና 55 ሰዎች እንደሞቱ መረጃዎች ያሳያሉ። ስለዚህም በሽታው በአከባቢው ባሉት አጎራባች ዞኖችና ባልተጠቁ አከባቢዎችንም የመሰራጨት እድል ከፍተኛ ስለሆነ ተገቢውን የመከላከያ ዘዴዎችን በመከተል ህብረተሰቡ ከፍተኛ ርብርብ እንዲያደርግ ያስፈልጋል። አያይዞም በህፃናት፣ በአረጋዊያን፣ የምግብ እጥረት(መቅጨጭ) ችግር ላለባቸው ፣ ተጓዳኝ የቆየ በሽታ ባለባቸው( ኤችአይቪ ኤድስ ፣ ስኳር ፣ የደም ግፍት ) ላይ ከፍተኛ ጉዳትና የሞት አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል የታወቀ ምልክት ያለበት ሰዉ አቅራቢያ ወደሚገኝ ጤና ተቋም ቶሎ በመሄድ/በመዉሰድ አስፈላጊውን ህክምና እንዲያገኝና በሽታው ወደሌሎች እንዳይሰራጭ የሚደረግ የህክምና የባለሙያ ምክር እንዲተገብር።
نمایش همه...
🌙   ኢድ ሙባረክ!!  🌙 ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ የHealth.Com/ጤናን በቴሌግራም ቤተሰቦች እንኳን ለኢድ አል አድሀ /አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።       ⭐️     ⭐️     ⭐️ በዓሉ የጤና፣ የሰላምና የደስታ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን። 🌙  መልካም በዓል! 🌙      
نمایش همه...
ጥርስ ከተነቀለ በኋላ የሚፈጠር ህመም | Alveolar Ostitis ጥርስ በተለያዩ ምክንያቶች ሊነቀል ይችላል ከተነቀላ በኋላ ግን የከፋ ህመም በብዙ ምክንያት ሊከሰት ይችላል ይህም የሚፈጠረው ሐኪምዎ እንዲተገብሩ ያዘዝዎትን ትዛዝ ሳያከብሩ ሲቀሩ፣ ሴቶች በወር አበባ መምጫ ሰዓት ጥርስ የሚነቀሉ ከሆነ፣ የወሊድ መቆጣጠርያ መድኃኒት እየወሰዱ የሚነቀሉ አሆነ፣ ጥርስ ከተነቀለ በኋለ በአንድ ሳምንት ውስጥ ትምባሆ የሚያጨሱ ከሆነ የተባለው ህመም ሊከሰት ይችላል። የህመሙ ዓይነት የሚጠዘጥዝ ህመም ሲሆን የተነቀለበት ቦታ ቁስሉ ወደ ግራጫ መልክ የመቀየር፣ የአፍ ጠረን የማምጣት እና ብሎም እብጠትም ጭምር ሊኖረው ይችላል። ነገር ግን ጥርስ ከተነቀለ በኋላ ሊተገበሩ የሚገቡ የጥንቃቄ ዓይነቶች አሉ እነሱም 1. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ቢያን ለ 30 ደቂቃ ያህል ሐኪምዎ ያስነከሰዎትን ጥጥ በተነቀለበት ቦታ ነክሰው ማቆየት 2. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ለተከታታይ 24 ሰዓታት ትኩስ ነገር መብላትም ሆነ መጠጣት አይመከርም መመገብ ካለብዎ በረድ ወይም ለብ ያለ ነገር መሆን አለበት 3. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ለተከታታይ 24 ሰዓታት ደምም ይሁን ምራቅ መዋጥ እንጂ መትፋት በፍፁም የተከለከለ ነው 4. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ለተከታታይ 24 ሰዓታት የትኛውም ዓይነት ፈሳሽ ነገር ሲጠጡ መምጠጫ(Straw) መጠቀም አይመከርም 5. ቁስሉ እስኪድን ድረስ ጥርስ የተነቀለበትን ቦታ በእጅ፣ በምላስ እና በተለያዩ ቁሳቁሶች መነካካት አይመከርም 6. ምግብ ከበሉ በኋላ የበሉት ምግብ በቁስሉ በመከማቸት ለኢንፌክሽን የማጋለጥ ዕድሉ የሰፋ ስለሆነ እንደተመገቡ ጨው በውኃ በመቀላቀል ለብ አድርገው ተጉሞጥምጦ መትፋት 7. ቁስሉ እንዲድን አጋዥ ይሆናሉ ተብሎ በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶች ካሉ በትዕዛዙ መሰረት መውሰድ 8. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ቢያንስ ለተከታታይ 10 ቀናት ትምባሆ ማጨስ አይመከርም። 9. ከላይ የተጠቀሱትን ትዕዛዛት ሁሉ ተግብረው ነገር ግን ህመም እየበረታ ከሔደ እና እብጠት ካመጣ ፈጥነዉ ሐኪምዎትን ያማክሩ። እነዚህን ትዕዛዛት ከተገበሩ ሊመጣ የሚችለውን ህመም መከላከል ይችላሉ። የሙያዬን ድጋፍ እና የማማከር አገልግሎት ካስፈለገዎ በ +251943305035 ወይም የ ቴሌግራም ማስፈንጠሪያዬን t.me/AbdilnurShifa ተጠቅመው ያለዎትን ጥያቄ ማድረስ ይችላሉ። መልዕክቱ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩት። በ ዶ/ር አብዲልኑር ሺፋ ፡ Dental Surgeon #HakimEthio
نمایش همه...
Woodpecker DC

{وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ}

ሱስ ያሲዛሉ? ቤተሰብ ከሚጠይቃቸው ተደጋጋሚ መድሀኒት ነክ ጥያቄዎች አንዱ ‹‹መድሀኒቶቱ ሱስ ያሲዛል ወይ›› የሚል ነው፡፡ ፨ መልስ ፨ በስነ አእምሮ ህክምና ውስጥ የሚያገለግሉ ወደ 150 የሚጠጉ መድሀኒቶች ሲኖሩ ለህክምናው የሚሰጡ ቅድሚያ ተሰላፊ መድሀኒቶች (first lines) ለረጅም ጊዜ ቢወሰዱም ሱስ አያሲዙም፡፡ በአእምሮ ህክምና ትልቅ ክብደት የሚሰጣቸው እና ተኝቶ ወይም በተመላላሽ ህክምና የሚያስፈልጋቸው (ለሁለት ዋልታ [bipolar], ለድብርት፣ ለሱስ፣ ከእውን ለሚነጥሉ ህመሞች [psychosis]... የሚሰጡ መድሀኒቶች ሱስ አያሲዙም፨ ስለዚህም ህክምናዎን ያለጭንቀት መከታተል ይችላሉ፡፡ ነገር ግን…. ከዋናው መድሀኒት በተጨማሪ አብረው የሚታዘዙ መድሀኒቶች ሱስ ሊያሲዙ ይችላሉ 1 ቤንዞዲያዜፓም - በአብዛኛዎቹ ህመሞች ዘንድ የመጀመሪያ አማራጭ አይደሉም - ቁጥጥር በሚደረግበት የተለየ ማዘዣ ወረቀት የሚታዘዙ - አስገዳጅ የሆኑ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ለአጭር ቀናት ወይም ሳምንታት የሚሰጡ - ከአልኮል ጋር ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸው፤ ከ3 ወራት በላይ በተከታይ ወይም ከሀኪም ትዕዛዝ ውጭ ከተወሰዱ ሱስ ያሲዛሉ - አስቸኳይ ለውጥ ሲፈለግ ወይም አስገዳጅ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ የሚታዘዙ። እነርሱም * የእንቅልፍ ችግር፡- አብዛኛው የእንቅልፍ ችግሮች በሌሎች የአእምሮ ህመሞች ምክንያት የሚመጣ ሲሆን ዋናው ህመም ሲስተካከል ይስተካከላሉ፡፡ ዋናውን ህመም የሚያክመው መድሀኒት ስራ እሰኪጀምርና መሻሻል እስኪመጣ ቀናት ወይም ሳምንታት ሊፈጅበት ስለሚችል እስከዚያ ድርስ ታካሚው እንቅልፍ እንዲያገኝ ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡ ከቀናት ወይም ሳምንታት በኋላ ዋናው መድሀኒት መስራት ስለሚጀምር እና የስነ ልቦና ህክምናዎች ስለሚጨመሩ ይህኛው መድሀኒት ይቆማል፡፡ ስለዚህ ‹‹በመድሀኒት ሀይል የተኛ መድሀኒቱን ሲያቆም አይቸገርም ወይ›› የሚለው ጥያቄ እዚህ ላይ መልስ ያገኛል፡፡ * የአልኮል መጠጥ በድንገት ማቆም፡- የብዙ አልኮል ተጠቃሚ የነበረሰ ሰው መጠኑን ሲቀንሰው ወይም ሲያቆመው ምቾት የማይሰጡ ምልክቶችን ያሳያል (አንዳንዶቹ እስከሞት የሚያደርሱ)፡፡ ይህ እንዳይፈጠር የሚከላከሉት መድሀኒቶች እነዚህ ናቸው፡፡ ይህ ህክምና ከ3 እስከ 5 ቀን ብቻ የሚቆይ ስለሆነ ሱስ አያሳስበንም፡፡ * አስቸኳይ መሻሻል ሲፈለግ፡- ለምሳሌ ድንገተኛ ሽብረት (panic disorder) ወይም የማህበር ፍራቻ (social phobia) የመሳሰሉ የጭንቀት ህመሞች በሚነሱበት ጊዜ እጅግ አስጨናቂ ስለሆኑ እና አስቸይ መፍትሔ ስለሚሹ፤ ሌሎች ህክምናዎች (SSRI or SNRI and psychotherapy) መስራት እስኪጀምሩ ድረስ ሊሰጡ ይችላሉ * ለህይወት አስጊ የሆኑ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ፡- ታካሚው በሌላ ማረጋጊያ ዘዴዎች አልረጋጋ ያለ ከፍተኛ መታወክ ውስጥ ሲገባና ራሱን ወይም ሌላ ሰው ላይ ጉዳት ሊያደርስ ከሆነ እነዚህ መድሀኒቶች ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ሲያስፈልግ ብቻ በመርፌ ስለሚሰጥ ሱስ አያሳስበንም፡፡ * ጡንቻ ገትር (catatonia)፡- በከፍተኛ ሁኔታ የታመሙ ታካሚዎች ለተከታታይ ቀናት ምግብና ውሀ ላይወስዱ፣ ላይንቀሳቀሱ፣ ሰውነታቸው ድርቅርቅ ሊልና መንቀሳቀስ ሊያቆሙ፣ መናገር ሊያቆሙ…. ይችላሉ፡፡ ይህንን የሚያክሙት እነዚህ መድሀኒቶች ሲሆኑ ለጥቂት ቀናት ብቻ ስለሚሰጥ ሱስ አያሳስበንም * የማያቋርጥ የሚጥል በሽታ፡- የዚህ ህመም ታካሚ በመሀል ሳይነቃ በተደጋጋሚ ከጣለው ከፍተኛ አደጋ ላይ ይጋለጣል ይህንን የሚያስተካክሉ እነዚህ መድሀኒቶች ናቸው፡፡ * እና ሌሎችም… - በጠቅላላው፤ በሀኪም ትዕዛዝ መሰረት ከተወሰዱ ሱስ አያሳስበንም፡፡ 2. ማርከሻ መድሀኒቶች - ለአእምሮ መታወክ የሚሰጡ አንዳድ መድሀኒቶች የእንቅስቃሴ ችግር ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ይህንን ለማርከስ የሚሰጠው መድሀኒት ሱስ እንደሚያሲዝ ሪፖርት ተደርጓል፡፡ ስለዚህም ታካሚው በታዘዘው መሰረት ብቻ (የእንቅስቃሴው ችግር ሲፈጠር ብቻ አንድ ጊዜ) መውሰድ ይኖርበታል፡፡ ፨ለማጠቃለል፡ በሀኪም ትዕዛዝ መሰረት ከተወሰዱ ሱስ አያሳስበንም፡፡ ስለ ህክምናዎ ጥያቄ ካለዎት በህክምና ቡድኑ ውስጥ ያለውን የጤና ባለሙያ ለመጠየቅ አያንገራግሩ!፨ ጋሻው አወቀ (የስነ አእምሮ ባለሙያ) @HakimEthio
نمایش همه...
*ጉበት ከሰባ ምን ረባ* ሲባል ሰምተው ያውቃሉ?        ሰላም ዉድ የInfo Health Center ቤተሰቦች ለዛሬ ስለ #ጉበት #መስባት (በጉበት ላይ ስለሚከማች ስብ) ጠቃሚ መረጃ እናጋራችሗለን። • ለመሆኑ የጉበት መስባት ምን ማለት ነው?        ከፍተኛ የሆነ የስብ ክምችት በጉበት ላይ ሲኖር የጉበት መስባት(Fatty Liver) ይባላል። ትንሽ መጠን ያለው የስብ ክምችት እንደ ችግር አይቆጠርም። • እንደሚታወቀው ጉበት ከሰውነታችን አካል ክፍሎች በትልቅነቱ 2ኛ ደረጃ ሲሆን በምግብና መጠጥ አማካኝነት ወደ ሰውነታችን የገቡ ነገሮችን በማጣራትና በመፈተሽ ሰውነትን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን በማስወገድና የጉዳት መጠናቸውን በመቀነስ ሰውነት ላይ ሊደርስ የሚችልን ከባድ ችግር ያስቀራል። • ባጭሩ ጉበታችን ለሰውነታችን ዋና #የጉሙሩክ ጣቢያና ባትሪም ነው። ሞባይልም ሆነ ኮምፒውተር ያለባትሪ ዋጋ እንደሌለው ሰውነትም ያለጉበት ባትሪ ሎው ብሎ ህይዎትን ያቆማል። • መጠኑ የጨመረ የስብ መጠን ለጉበት መጠቃትና መመረዝ ያጋልጣል። ይህም ጉበት ላይ ጠባሳ እንድፈጠር ያደርጋል። ይህ ደግሞ ጉበት ስራውን በአግባቡ እንዳያከናውን ያደርገዋል። • የጉበት ስብ እንድፈጠር መጠኑ የጨመረ የአልኮል መጠን ትልቁን ድርሻ ይይዛል። #በጉበት ውስጥ ስብ ሲከማች ሊታዩ የሚችሉ ምልክቶች • ብዙ ጊዜ ቶሎ አያሳይም። እየቆየ ግን በቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል ላይ ህመምና መጥፎ ስሜት • የጉበት ጠባሳ መፈጠር #የጉበት ጠባሳ ካለ የሚታዩ ምልክቶች 1. የምግብ ፍላጎት መቀነስ 2. የክብደት መቀነስና ድካም ስሜት 3. አቅም ማነስ 4. በአፍንጫ ደም መፍሰስ 5. የቆዳ ማሳከክ 6. ቆዳና አይን ቢጫ መሆን 7. የሆድ ህመም 8. የሆድ ማበጥ 9. የእግር ማበጥ 10. በወንዶች ላይ ጡት ማበጥ 11. ግራ መጋባት #የጉበት ጠባሳ በጣም ከባድ ችግር ነው። ለህይዎትም አስጌ ስለሆነ የጤና ባለሙያ ክትትልና እንክብካቤ በእጅጉ አስፈላጊ ነው። #በጉበት ላይ ለምን ስብ ይጠራቀማል? • ሰውነት ስብን መጠቀም አለመቻል። • ብዙ ጣፋጭ ተጠቃሚ መሆን • መጠኑ ከፍ ያለ አልኮል መጠጣት #ችግሩን የሚያባብሱ ነገሮች • ውፍረት • ከፍተኛ ደም ግፊት • ስኳር በሽታ • ብዙ ስብ በሰውነት ውስጥ መከማቸት • የጉበት ቫይረስ ሲ • መድሀኒቶች(methotrexate, tamoxifen, amiodorone and valproic) • ለመርዛማ ነገሮች መጋለጥ • እርግዝናና ሌሎችም ናቸው። #መመርመሪያ መንገዶች • የተለያዩ ጥያቄዎች በመጠየቅ • የተለያዩ ምልክቶችን በማየት • አካላዊ ምርመራ በማድረግ • የደም ናሙና በመውሰድ • የተለያዩ የማያ መሳሪያዎች በመጠቀም • ከጉበት ናሙና በመውሰድ #ህክምናው • የሚታዘዝ መድሀኒት ባይኖርም አልኮልን ባለመጠጣት፡ ክብደትን በመቀነስና የባለሙያ ምክርንና ክትትልን በማክበር መቀነስና ከችግሩ መላቀቅ ይቻላል። #ለተጨማሪ መረጃ ከHealth.Com/ጤናን በቴሌግራም ጋር ቤተሰብ ይሁኑ። መልእክቱን ያጋሩ። ጤናችሁ ይብዛ! #IHC
نمایش همه...