fa
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ለመዲናችን የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች በሙሉ እንኳን ለአለም ዓቀፉ የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች ቀን (International Fire Fighters day) አደረሳችሁ! የዘንድሮው ዓለም ዓቀፉ የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች ቀን "ህዝባቸውን ከአደጋ ለመታደግ በጀግንነት፣በቆራጥነት እና በመሥዋእትነት ስራቸውን ለሚያከናውኑት የእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞቻችን ክብር እንስጣቸው!" በሚል መሪ ቃል በመላዉ ዓለም እየተከበረ ይገኛል። እለቱ በመላው አለም የሚከበረው የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች በስራቸው የሚያጋጥማቸውን አደጋ ተጋፍጠው የሰው ልጅ ህይወትንና ንብረትን ለመታደግ ለሚከፍሉት ዋጋና ለህዝብ ለሚሰጡት ክቡር አገልግሎት እውቅና ለመስጠት በማለም የሚከበር ቀን ነው። በመሆኑም በመዲናችን አዲስ አበባም እለቱን በተለያዬ ዝግጅቶች በድምቀት ለማክበር ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ይገኛል። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ለመዲናችን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች እንኳን አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል! ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ እንዲሁም ለአንቡላንስ አገለሰግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

የኮሪደርና መሰረተ ልማቶች ቅንጅት በ2ኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እየተከናወነ ያለው የመሰረተ ልማት ዝርጋታ በተናበበ እና ቅንጅታዊ አሰራርን ተከትሎ በፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ AMN - ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም See less

በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዙሪያ የህዝብ ተሳትፎን ለማጠናከር እየተሰሩ ያሉ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችና የተግባቦት ስራዎች የፈጠሩትን የአመለካከት ለውጥ እና ያስገኙትን ውጤት ለማወቅ ለሚካሄድ ሳይንሳዊ ጥናት የኦሬንቴሽን መድረክ ተካሄደ። ሳይንሳዊ የዳሰሳ ጥናቱ በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ፣በተጠሪ ተቋማት እና እንዲሁም በክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አስከ ወረዳ ድረስ ባለው መዋቅር ባሉ ሙያተኞች የሚካሄድ ሲሆን የጥናቱ ናሙናም የተለያዩ የከተማው የህብረተሰብ ክፍሎችን ስብጥር በጠበቀ መልኩ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል ። በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ በመሩት በዚሁ የኦሬንቴሽን መድረክ ላይ ከማዘጋጃ ቤታዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ከነዋሪው ጋር የሁለትዮሽ ተግባቦቱን ለማጠናከር በመላው መዋቅር በበጀት አመቱ 10 ወራት የተከናወኑ ስራዎች እና ያመጡት የአመለካከት ለውጥ ላይ ሳይንሳዊና ሙያዊ በሆነ ጥናት ማስደገፍ ለቀጣይ ስራዎች ወሳኝ እንደሆነ ተመላክቷል። የኦሬንቴሽን መድረኩ ዋነኛ አላማ የሚሰበሰበዉ መረጃን ጥራቱን የጠበቀ ለማድረግና በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የህበረተሰቡን የግንዛቤ ደረጃ ለመለካትና በዚህ መነሻነት የቀጣይ ስራዎችን አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነም ተገልጿል። በዚህ መነሻነት የሚካሄደው የፋይዳ ጥናት በዋናነት የከተማችንን ነዋሪዎች በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዙሪያ ያላቸውን የግንዛቤ ደረጃ በተጨባጭ እና ትክክለኛ መረጃ ላይ በመመስረት እና በመለካት ያሉ ጥንካሬዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ክፍቶችን በማረም ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለዉም ተጠቁሟል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

" ፋይዳ ለኢትዮጵያ " የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ በመጪው እሁድ ግንቦት 3/2017ዓ.ም በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን ተገለፀ " ፋይዳ ለኢትዮጵያ " የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ በመጪው እሁድ ግንቦት 3/2017ዓ.ም በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን በዛሬው ዕለት በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና መስርያ ቤት ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር የጋራ መግለጫ ተሰጥቷል። በፋይዳ ምዝገባ ላይ ያለውን የህብረተሰብ ግንዛቤ እና አረዳድ በስፖርት ንቅናቅኔ ማጠናከረ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ቴክኒካል ድጋፍ " ፋይዳ ለኢትዮጽያ " በሚል መሪ-ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ በመስቀል አደባባይ እሁድ ግንቦት 3/ 2017ዓ.ም ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በዛሬው ዕለት በኤጀንሲው ዋና መስርያ ቤት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ዋና ስራ-አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ አርዓያ ስላሴ በመግለጫው እንደገለፁት ሩጫው የምዝገባ ንቅንናቄውን ያግዛል ተብሎ የታመነበትና የፋይዳ ምዝገባን በህብረተሰቡ ውስጥ በስፋት ለማስረፅ በሌሎች ክልሎች ይህ የስፖርት ንቅናቄ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። አቶ ዮዳሄ የፋይዳ ምዝገባ እንደ ሃገር ጅማሮው መልካም የሚባል ቢሆንም በስፋት ከመመዝገብ አኳያ አሁንም የሁሉም አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ አክለዋል። በጋዜጣዊ መግለጫው ቴክኒካል ገለፃ ያደረጉት የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በላይ ደጀን ሩጫው ግንቦት 3/2017ዓ.ም መነሻ እና መዳረሻውን መስቀል አደባባይ እንደሆነና በመርሃ-ግብሩ አትሌቶችን ጨምሮ ነዋሪዎች በስፋት በሩጫው እንደሚሳተፉ ገልፀዋል። ቢሮ ሃላፊው ለሯጮች የሚሰጠው ቲ-ሸርት ነፃ መሆኑን እና ሁሉም ተወዳዳሪዎች ሜዳልያ ሽልማት እንደሚኖር የገለፁ ሲሆን ለወንዶች ፣ በሴቶች እና በፓራ ለሚወዳደሩ አሸናፊ አትሌቶች በየደረጃው ሽልማት እንደተዘጋጀ ጠቁመዋል። በሩጫ መርሃ ግብሩ ነዋሪዎች፣ ሰራተኞች ፣ ታዋቂ ሰራተኞች፣ አትሌቶች ፣ አመራሮች ፣ የውጭ ዲፕሎማቶች እና ተጋባዥ እንግዶች የሚሳተፉ ይሆናል። የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ከየሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት ምዝገባ ኤጀንሲ የፋይዳ ምዝገባ በጋራ ለመምራት መግባብያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በከተማው ባደረጉት ንቅናቄ 2.3 ሚልዮን አዲስ ተመዝጋቢዎችን ላለፉት ወራት መመዝገባቸውን በዛሬው ዕለት ያስታወቁ ሲሆን ይህም በከተማው ላለፉት ሁለት ዓመት ከተመዘገበው ቁጥር አንፃር በአጭር ግዜ ከግማሽ በላይ ብልጫ እንዳለው ተነግሯል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager " ፋይዳ ለኢትዮጵያ " የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ በመጪው እሁድ ግንቦት 3/2017ዓ.ም በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን ተገለፀ " ፋይዳ ለኢትዮጵያ " የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ በመጪው እሁድ ግንቦት 3/2017ዓ.ም በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን በዛሬው ዕለት በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና መስርያ ቤት ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር የጋራ መግለጫ ተሰጥቷል። በፋይዳ ምዝገባ ላይ ያለውን የህብረተሰብ ግንዛቤ እና አረዳድ በስፖርት ንቅናቅኔ ማጠናከረ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ቴክኒካል ድጋፍ " ፋይዳ ለኢትዮጽያ " በሚል መሪ-ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ በመስቀል አደባባይ እሁድ ግንቦት 3/ 2017ዓ.ም ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በዛሬው ዕለት በኤጀንሲው ዋና መስርያ ቤት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ዋና ስራ-አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ አርዓያ ስላሴ በመግለጫው እንደገለፁት ሩጫው የምዝገባ ንቅንናቄውን ያግዛል ተብሎ የታመነበትና የፋይዳ ምዝገባን በህብረተሰቡ ውስጥ በስፋት ለማስረፅ በሌሎች ክልሎች ይህ የስፖርት ንቅናቄ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። አቶ ዮዳሄ የፋይዳ ምዝገባ እንደ ሃገር ጅማሮው መልካም የሚባል ቢሆንም በስፋት ከመመዝገብ አኳያ አሁንም የሁሉም አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ አክለዋል። በጋዜጣዊ መግለጫው ቴክኒካል ገለፃ ያደረጉት የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በላይ ደጀን ሩጫው ግንቦት 3/2017ዓ.ም መነሻ እና መዳረሻውን መስቀል አደባባይ እንደሆነና በመርሃ-ግብሩ አትሌቶችን ጨምሮ ነዋሪዎች በስፋት በሩጫው እንደሚሳተፉ ገልፀዋል። ቢሮ ሃላፊው ለሯጮች የሚሰጠው ቲ-ሸርት ነፃ መሆኑን እና ሁሉም ተወዳዳሪዎች ሜዳልያ ሽልማት እንደሚኖር የገለፁ ሲሆን ለወንዶች ፣ በሴቶች እና በፓራ ለሚወዳደሩ አሸናፊ አትሌቶች በየደረጃው ሽልማት እንደተዘጋጀ ጠቁመዋል። በሩጫ መርሃ ግብሩ ነዋሪዎች፣ ሰራተኞች ፣ ታዋቂ ሰራተኞች፣ አትሌቶች ፣ አመራሮች ፣ የውጭ ዲፕሎማቶች እና ተጋባዥ እንግዶች የሚሳተፉ ይሆናል። የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ከየሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት ምዝገባ ኤጀንሲ የፋይዳ ምዝገባ በጋራ ለመምራት መግባብያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በከተማው ባደረጉት ንቅናቄ 2.3 ሚልዮን አዲስ ተመዝጋቢዎችን ላለፉት ወራት መመዝገባቸውን በዛሬው ዕለት ያስታወቁ ሲሆን ይህም በከተማው ላለፉት ሁለት ዓመት ከተመዘገበው ቁጥር አንፃር በአጭር ግዜ ከግማሽ በላይ ብልጫ እንዳለው ተነግሯል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager