1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የመጋቢት ወር የስራ እንቅስቃሴን የሚያስቃኝ ዜና መጽሄት ከታች በተቀመጠው ሊንክ እንዲያነቡ ተጋብዘዋል።
https://t.me/aacitymanager/18408
በአደጋ ተጋላጭነት በተለዩ ቦታዎች ላይ የማቅለያ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ተገለጸ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የባለፉት 9 ወራት የቅንጅት ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸምን አስመልክቶ የባለድርሻ ተቋማት አመራርና ተወካዮች በተገኙበት ዛሬ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ተገምግሟል።
በግምገማ መድረኩ ኮሚሽኑ ባለፉት 9 ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ያከናወናቸዉ ተግባራትና በሂደቱም ጥንካሬና ዉስንነት የታየባቸዉ ተግባሮች በዝርዝር ቀርበዉ ዉይይት ተካሂዶባቸዋል።
የዉይይት መድረኩን የመሩት የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሀመድ እንደተናገሩት ኮሚሽን መ/ቤቱ በተለይም የአደጋ ተጋላጭ ጥናትን መሰረት ያደረገ የቅድመ አደጋ መከላከል ስራን በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዉ በተጋላጭነት በተለዩ ቦታዎች ላይ መፍትሄ በማሰጠት ረገድ የባለድርሻ ተቋማት ሚና የላቀ በመሆኑ የተጀመሩ የማቅለያ ስራዎች ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
የባለድርሻ ተቋማቱ አመራሮች በበኩላቸዉ እንደተናገሩት ኮሚሽን መ/ቤቱ የአደጋ ተጋላጭ ቦታዎችን አስቀድሞ በጥናት በመለየት ጊዜዉን የጠበቀ ረፖርት በማቅረብ ባለድርሻ ተቋማት የመፍትሄዉ አካል እንዲሆኑ ማድረጉ አደጋን ለመቀነስ የሚደረገዉን ጥረት እንደሚያግዝ ጠቅሰዉ ተቋማቱም እንደየተልዕኳቸዉ ኃላፊነታቸዉን ለመወጣት በትኩረት እንደሚሰሩ አስታዉቀዋል።
በግምገማ መድረኩ በኮሚሽኑ የማዕከልና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አመራርና ባለሞያዎች ተገኝተዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ውበት የገለጠ ነው - የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና ግለሰቦች
የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ውበት ያሳየና የቱሪዝም መስህብነቷን ያሳደገ መሆኑን የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ግለሰቦች ገለጹ፡፡
የኮሪደር ልማት ስራዎችን በባለቤትነት መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በአዲስ አበባ የተገነቡ እና እየተገነቡ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች ከተማዋን እንደ ስሟ ውብና ሳቢ በማድረግ ተመራጭነቷን ያሳደገ ነው፡፡
የከተማዋ የኮሪደር ልማት የነዋሪዎችን የአኗኗር ዘይቤ ያሻሻለ፣ ከተማዋን የሚመጥን፣ ዘመኑን የዋጀ የመሰረተ ልማት አቅርቦት የጨመረና የከተማዋን ገጽታ የቀየረ ፕሮጀክት ነው፡፡
ኢዜአ ያነጋገራቸው የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የኮሪደር ልማት ስራ የከተማዋን የዕድገት ደረጃ ይበልጥ የሚያሣልጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል መንሱር ጀማል እንደገለጸው በሀገር ደረጃ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ዜጎች ምቹና ዘመናዊ የሆነ ከባቢ እንዲኖራቸው ያስቻለ፤ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ያሳደገ ነው፡፡
በመዲናዋ የተከናወኑና እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችም አዲስ አበባ እንደስሟ ውብ፣ ጽዱና ደረጃዋን የጠበቀች እንድትሆን ማስቻሉን ገልጿል፡፡
መንግስት የዜጎችን የልማት ጥያቄ ለመመለስና የሀገርን ገጽታ ለመገንባት የሚያከናውናቸው ተግባራት ከግብ እንዲደርሱ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብሏል፡፡
አርቲስት ሙሉነህ ዘለቀ በበኩሉ በሀገር ደረጃ እየተተገበሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች የቱሪስት መዳረሻነትን ያሳደጉ መሆናቸውን ተናግሯል፡፡
በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የተገነቡ የህጻናት መጫወቻዎች፣ የመዝናኛ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ጨምሮ ሌሎች ልማቶች መጪውን ትውልድ የሚመጥኑ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን የመለሱ መሆናቸውን ገልጿል፡፡
የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በባለቤትነት መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባም ጠቁሟል፡፡
የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በከተማዋ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን ለረጅም ዓመታት አገልግሎት እንዲሰጡ ሁሉም አካል መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባው የገለጸው ደግሞ አርቲስት ኤልያስ ተባባል ነው፡፡
የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ሌሎችም ከተሞች ልምድ እየቀሰሙበት የሚገኝ መልካም ተሞክሮ ነው። ኢዜአ
#Ethiopian_News_Agency
#ኢዜአ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ፣
የተዛባና ሚዛናዊነት የጎደለው መረጃን ግልፅ ስለማድረግ፣
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በመጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም "በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤና ተሳትፎ ማሳደግን" አላማው ያደረገ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱ ይታወሳል። መድረኩ የታለመለትን አላማ እንዲያሳካም በእለቱ የውይይት መድረኩን እንዲዘግቡ በጽ/ ቤታችን ከተጠሩት ከ15 በላይ የሚሆኑ የመደበኛና የዲጂታል ሚዲያዎች ተገኝተው ዘገባቸውን አሰራጭተዋዋል።
ተቋማችን ከመድረኩ መጠናቀቅ በሁዋላ ባካሄደው የሚዲያ ዳሰሳና ቅኝት ላይ ግን ሪፖርተር ጋዜጣ በትናንትናው እለት ሰኞ መጋቢት 29/ 2017 ዓ.ም "የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የኑሮ ውድነቱ አናታቸው ላይ ወጥቷል" የሚል ርአስ የያዘ ዘገባ ማውጣቱን ተመልክተናል።
በመሠረቱ በጽ/ ቤታችን በተጠራው መድረክ ላይ ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው የመወያያ ርእሰ ጉዳዪ " የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ላይ የህዝብ ተሳትፎን ማሳደግ" እንጅ የንግድ አሊያም የገቢ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ አልነበረም።
ሆኖም ግን በወቅቱ በመድረኩ ላይ ከተሳተፉት ከ200 በላይ ታዳሚዎች በርካቶች መድረኩ የተዘጋጀበትን ርእሰ ጉዳይ መሠረት በማድረግ ሃሳባቸውን እና አስተያዬታቸውን በነፃነት ያንሸራሸሩበት ሁኔታ ተስተውሏል።
ይሁንና በወቅቱ በመድረኩ ላይ ተገኝቶ ዘገባውን ያወጣው ሪፖርተር ጋዜጠኛ ከመድረኩ አውድ ውጭ በርእሰጉዳይነት ያልተካተ፣ የመድረኩን ሙሉ ስእል የማያሳይ፣ ቁንፅል፣ ስሜት ቀስቃሽ፣ ተጨባጭ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ እና ከጋዜጠኝነት የሙያ ስነምግባር ያፈነገጠ ዘገባ ማሰራጨቱ ተቋማችን በህዝብ ዘንድ ያለውን አመኔታ ሆን ተብሎ ለማሳጣት የተፈፀመ እኩይ ተግባር መሆኑን ተገንዝበናል።
በተለይም ደግሞ የሪፖርተር ጋዜጣ ዋነኛ የዜና ርእስ የሆነው አስተያዬት የዜናው ቀዳሚ ርእስ (Headline) በማድረግ ማውጣቱ ስሜታዊነት የተንፀባረቀበት፣ ሃላፊነት የጎደለው እና በምንም አይነት መስፈርት ተቀባይነት የሌለው እንዲሁም የጽ/ቤታችን የህዝብ ቅቡልነትና ተአማኒነት ሆን ተብሎ ለመሸርሸር የተፈፀመ በመሆኑ ሪፖርተር ጋዜጣ ይህንኑ በአስቸኳይ እንዲያርምና ማስተባበያ እንዲያወጣ እያሳሰብን ይህ ካልሆነ ግን ጽ/ ቤታችን ህጋዊና አስተዳደራዊ መንገዶችን በመከተል ተጠያቂነትን እንደሚያረጋግጥ በጥብቅ እናሳውቃለን ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
በመዲናችን አዲስ አበባ የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ አፈፃፀም 96 በመቶ መድረሱ ተመለከተ።
በከተማችን ተጽእኖ ፈጣሪና ታዋቂ ግለሰቦች በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ላይ በቂ ግንዛቤ ተፈጥሮላቸው በቅድመ አደጋ መከላከል፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በከተማ ፅዳትና ውበት ላይ በማህበረሰቡ ዘንድ ያላቸውን አዎንታዊ ተጽእኖ በመጠቀም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል የተካሄደውን የውይይት መድረክ
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ያለፉት ስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ምዘና ተካሄደ
የስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ያለፉት ስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የተመዘነው ከከንቲባ ፅ/ቤት፣ ከፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና ከኘላን ልማት ቢሮ በተውጣጡ መዛኝ አካላት ነው።
በምዘናው ጽ/ቤቱ በአዋጅና በተልእኮ በተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት መሠረት በእቅድ የተያዙና የተከናወኑ ስራዎች ፤ የመልካም አስተዳደር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የቅንጅት ስራዎች፣ የክረምትና የሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ ስራዎች በተለይም አገልገሎቶች በቴክኖሎጂ መታገዛቸው፣ ምቹ የስራ ከባቢን ከመፍጠር አንፃር እና ሌሎች በርካታ ዝርዝር ተግባራትን በሰነድ እና በአካል ምልከታ ተደርጓል።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና ስትራቴጂክ አመራሮች እንዲሁም ዳይሬክተሮች ተገኝተው በዛሬው እለት የተቋሙን የስራ ክንውኖች አስመዝነዋል።
የመዛኝ ቡድኑ አባላት በተቋሙ የተከናወኑ ጠንካራ ስራዎች መመዝገባቸውን ገልፀው በስራ ሂደቱ የታዩ አንዳንድ በቀጣይ መስተካከል ይገባቸዋል ባሉት ክፍተቶቸ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።
በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በጽ/ ቤቱ ባለፉት ስድስት ወራት አበረታች ስራዎች መሰራታቸውን በምዘናው ማጠቃለያ ገልፀው ምዘናው በዚህ ወቅት መካሄዱ በቀሪ ወራቶች ያልተጠናቀቁ ስራዎች ላይ ለመረባረብ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
የመዛኝ ቡድኑ ከሶስቱ ተቋማት መዋቀሩ ከዚህ ቀደም የነበረውን የምዘና ድግግሞሽ እና የጊዜ ብከነትን የሚቆጥብ እንደሆነ ተመላክቷል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ዛሬ "ከሸማችነት ወደ አምራችነት" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን ከተማ አቀፍ የኢትዮጵያ - አዲስ አበባ ታምርት የ2017 ዓ.ም የአምራች ኢንዱስትሪዎች አውደ ርዕይ የኢኮኖሚ ልህቀት ማዕከል በሆነው አዲስ ዓለምአቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል አስጀምረናል።
የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ቀዳሚ ትኩረት ከተሰጣቸው የኢኮኖሚ መስኮች መካከል አንዱ በመሆኑ አዲስ አበባ ከተማን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ ፈጠራን በማበረታት፣ አመራቾችን በመደገፍ፣ ፋይናንስ በማቅረብ፣ የመስሪያ ቦታዎችን በማመቻቸት፣ መሠረተ ልማትን በማሟላት፣ አስፈላጊ ሙያዊ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም ለአመራቾች ድጋፍ በማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ እንገኛለን።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዘርፉን ከማነቃቃት ባለፈ በተለያዩ ምክንያቶች ማምርት አቁመው የነበሩ ኢንዱስትሪዎች ወደ ምርት ስራቸው እንዲመለሱ እንዲሁም አምራቾች ምርታቸውን ለሸማቹ እንዲያስተዋውቁ፣ የገበያ ትስስር አንዲፈጥሩ፣ ሽያጭ እንዲያከናውኑ እና አምራቾች ከፍ ባለ መድረክ ተገኝተው ልምድ እንዲለዋወጡ የሚያደርግ መድረክ ነው።
የከተማችን ነዋሪዎች ይህን ከ250 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች የተሳተፉበትን አውደ ርዕይ እንድትጎበኙ እንዲሁም በሀገር ምርት በመጠቀም፣ የሀገር ውስጥ አምራቾችን በመደገፍ እና የሀገር ውስጥ ምርት በመግዛት አምራች እንዱስትሪዎችን እንድታበረታቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የታለመላቸውን አላማ እንዲያሳኩ እና ለትውልድ እንዲተላለፉ ባለድርሻ አካላት እና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ኃላፊነታቸውን መወጣት ይገባቸዋል - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ
በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የታለመላቸውን አላማ እንዲያሳኩ እና ለትውልድ እንዲተላለፉ ባለድርሻ አካላት እና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ኃላፊነታቸውን መወጣት ይገባቸዋል - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ
AMN-Addis Media Network ዝርዝር ዘገባ
በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ 👉👉
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቱን በማዘመን የከተማዋን ነዋሪዎች እርካታ ከፍ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዝርዝር ዘገባ ቀጣዩን ቪዲዮ ይመልከቱ 👉👉
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
