1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ዛሬ ኢትዮጵያ 1500 ድሮኖችን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በመታገዝ አየር ላይ የማብረር ትዕይንት አሳይታለች።
ይህ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ትልቅ አቅም እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ገልጸዋል።
በአህጉሪቱ ግዙፍ እንደሆነ የተነገረለት የድሮን ትርዒት በአዲስ አበባ ሰማይ
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2025 አካል የሆነው የድሮን ትርዒት ተካሂዷል።
በትርዒቱ 1 ሺህ 500 ድሮኖች ወደ ሰማይ የተለቀቁ ሲሆን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የደረሰችበት አቅም መንጸባረቁ ተነግሯል።
ይህ ትርዒት ከትዕይንትነት ባለፈ ኢትዮጵያ ለሀገራዊ ብልጽግና እና ለአፍሪካ ትስስር ያላትን ጠንካራ አቋም ያሳየችበት መሆኑ ተገልጿል።
የምሽቱ የድሮን ትርዒት በአፍሪካ ትልቁ የድሮን ትዕይንት መሆኑ ተነግሯል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ‘ኢቴኤክስ 2025’ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል ።
ይህ ኤክስፖ፤ የሳይበር ደህንነት፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ፋይን ቴክ፣ ስማርት ሲቲ እና የቴክኖሎጂ ትምህርትን መሰረት ያደረገ አምስት የትኩረት መስኮችን የያዘ ነው።
ከዛሬ ግንቦት 8 እስከ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በሚካሄደው ኤክስፖ ከ10 ሺህ በላይ ታዳሚዎች እንደሚሳተፉም ተገልጿል።
በወረዳ እየተሰጠ ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ምልከታ ተደረገ
የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የተገልጋይ እና የሰራተኛ የመስተንግዶ እንዲሁም የስታንዳርድ አፈፃፀም የሁኔታን ለመመልከት የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 2፣ 13 እና 14 ጽ/ቤት እንዲሁም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 1 እና 12 ጽ/ቤት ምልከታ አድርገዋል።
በድጋፍ እና ክትትሉ ላይ ተቋሙ እየሰጠ ባለው አገልግሎት ላይ ከክ/ከተማዎቹ ጽ/ቤት ሃላፊዎች እና ወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የተገልጋይ የአገልግሎት ሁኔታ እና የሰራተኛ የመስተንግዶ ሁኔታን በተመለከተ ተገልጋዮችን አነጋግረዋል።
ተቋሙ ዘወትር ሃሙስ እና ቅዳሜ መደበኛ የአመራር የወረዳ ድጋፍ እና ክትትል ቀን ያደረገ ሲሆን አገልግሎት እና የተቋም ግንባታ እንዲሁም የቅሬታ አፈታት የክትትል ዓለማዎች መሆኑ ተመላክቷል።
ግንቦት 8/ 2017 ዓ.ም
መዲናችን አዲስ አበባ በፅዳት ዘርፍ እያስመዘገበችው ያለው ስኬት እና ከአለም አገራት ጽዱ ከተሞች ተሞክሮ ምን ትምህርት ትቀሰማለች በሚለው ርእሰ ጉዳይ ዙሪያ:-
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከ#AMN ጋር ያካሄዱትን ሙሉ ቃለምልልሱን በቀጣዩ ቪዲዮ ይከታተሉ👉
በወቅታዊ የጤና አገልግሎት ዙሪያ ከጤና ሚኒስቴር የተሰጠ መረጃ
የጤና ሚኒስቴር ለማኅበረሰባችን ጥራቱን የጠበቀ እና ፍትሐዊ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የጤና ፖሊሲ እና ስትራቴጂ በመቅረጽ የኅብረተሰቡን ባለቤትነት ባረጋገጠ መልኩ ሥራዎችን በትኩረት እያከናወነ መሆኑ የዐደባባይ ሐቅ ነው።
ምክንያቱም መቼምና በምንም ሁኔታ መቋረጥ ከሌለባቸው ማኅበራዊ አገልግሎቶች አንዱ የጤና አገልግሎት በመሆኑ፤ ስለዚህም ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት በመላ ሀገራችን በሚገኙ የጤና ተቋማት እንደ ወትሮው ሁሉ መደበኛ የጤና አገልግሎቶች ለማኅበረሰባችን ያለምንም መቆራረጥና መስተጓጎል እየተሰጡ ይገኛሉ።
ይሄንን የተረዳው የጤና ባለሞያ በማኅበራዊ ሚዲያ በሚሠራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች ጫና ሳይገፋ የገባውን የሞያ ቃል ኪዳን እና መሐላ ጠብቆ ማኅበረሰቡን እያገለገለ በመሆኑ ምስጋና ይገባዋል።
ይሁን እንጂ በጥቂት የማስተማሪያ የጤና ኮሌጆች/ተቋማት በመደበኛ የሥራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ የተወሰኑ ባለሞያዎች እንዳሉ መረጃዎች ደርሰውናል። ከእነዚህ የጤና ባለሞያዎች መካከል ብዙዎቹ በሐሰተኛ መረጃ የተወናበዱ ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ ጥፋትን ዓላማቸው ያደረጉ ናቸው።
ድርጊቱ የራስን ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ወገን እና መላውን ማኅበረሰብ ከመጉዳት ባለፈ ከሞያ ሥነ ምግባር፣ ከሰብአዊነት አኳያ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።
ከሕግ አኳያም የጤና ሞያ የሥራ ማቆም አድማ ከማይደረጉባቸው የሥራ ዘርፎች መካከል አንዱ መሆኑ በግልጽ ተደንግጓል። የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ እንኳን ቢኖራቸው በሥራ ገበታቸው ተገኝተው መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ ጉዳያቸውን ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
በመሆኑም እነዚህ የጤና ባለሞያዎች ወደ ሥራ ገበታቸው ተመልሰው ማኅበረሰባቸውን እንዲያገለግሉ በየተቋማቸው ጥሪ ተደርጓል።
መንግሥት የጤና ባለሞያውን ዘላቂ ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ በጥናት ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ለመስጠት ቀደም ብሎ የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ 1362 /2017 አጸድቆ ደንብና መመሪያዎችን በማውጣት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል።
በጎ ኅሊና ያላቸው የጤና ባለሞያዎች ይህንን በመገንዘብ ሥራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ ያቀርባል።
በሌላ በኩል ደግሞ ኅብረተሰቡ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች በሚሠራጩ የሐሰት መረጃዎች ሳይረበሽ የሚፈልገውን የጤና አገልግሎት በተለመደው መልኩ በጤና ተቋማት ማግኘት እንደሚችል እናሳውቃለን።
መንግሥት በሆደ ሰፊነት ችግሩን ለመፍታት ያሳየውን ትዕግሥት ወደጎን በመተው በሥራ ገበታቸው ላይ ባልተገኙ እንዲሁም በጤና ተቋሙም ሆነ ከጤና ተቋሙ ውጭ ሆነው ሁከትና ብጥብጥ በሚፈጥሩት ላይ አስፈላጊ የሆነ ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ቀድመን እናሳውቃለን።
የጤና ሚኒስቴር
ግንቦት 07፣ 2017 ዓ.ም
በመዲናችን አዲስ አበባ የጎርፍ አደጋን ለመከላከል ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቅንጅታቸውን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል - በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የወቅታዊ ቅድመ አደጋ መከላከል ዝግጁነትን አስመልክቶ የተካሄደውን የምክክር መድረክ ላይ ያተኮረ የኢሳት ቴሌቪዥን ዘገባን በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ
ለከተማችን ፅዳት ተቆርቋሪ ህብረተሰባችን እያመሰገንን በግዴለሽነት መንገድ ላይ ቆሻሻ አውጥተው የሚጥሉትን ግለሰቦች እና ተቋማትን ደግሞ በደንብ ቁጥር 167/2016 መሠረት ተጠያቂ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል::
ውብ መዲናችንን ጥቂት ህገ ወጦች እንዲያቆሽሹ አንፈቅድላቸው!!
የተበለሹ የመንገድ ዳር መብራቶች አገልግሎት እንዲሰጡ የጥገና ስራ በመከናወን ላይ ነው
ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ከቅድስተ ማርያም በተለምዶ መቻል ክለብ ተብሎ በሚጠራው መንገድ ላይ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ የመንገድ ዳር መብራቶችን በኦፕሬሽና ጥገና ዘርፍ የነበረውን ችግር በመለየት አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡
በአካባቢው ላይ በሚገኙ የመብራት ምሰሶዎች ላይ በተከናወነ የጥገና ስራ ማቀፊያዎችን የመቀየርና በአዲስ መልኩ ወደ ኤል. ኢ.ዲ. የመቀየር ስራ ተከናውኗል፡፡ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሳይሰጥ የቆየውን የመብራት አገልግሎት የተሟላ የጥገና ስራ በመከናወኑ የህብረተሰቡን የምሽት እንቅስቃሴ ጤናማ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ለእይታ ምቹ ማድረግ ተችሏል፡፡ በዚህም የከተማ አስተዳደሩ ከተማችን ቀን ብቻ ሳይሆን ምሽትም ለስራና ለኑሮ የተመቸች ለማድረግ የተሰራውን የተቀናጀ የልማት ስራ የሚያጠናክር ይሆናል፡፡
በመጨረሻም ባለስልጣኑ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በአገልግሎት እድሜ፣ ባጋጠመ ብልሽት፣ በሚደርስ የተሸከርካሪ ግጭት፣ በመሰረተ ልማቱ ላይ በሚፈፀም ስርቆትና በሌሎች ህገወጥ ተግባራት ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የመንገድ ዳር መብራቶችን በመጠገንና ወደ ኤል.ኢ.ዲ በመቀየር የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የመንገድ ዳር መብራት መሰረተ-ልማት ሀብትን ከጉዳት እንጠብቅ!
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- ነፃ የስልክ ቁጥር 9101 ወይም
በቀጥታ ስልክ መስመር +251-11-1127775
በልደታ ክ/ከተማ "ትውልድ በመምህር ይቀረፃል፤ ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል" በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው የትምህርት ማህበረሰብ ውይይት የማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ነው
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ሀገር የምትገነባው በትውልድ ነው ፥ትውልድን ደግሞ የሚያንፀው መምህር ነው ብለው ስለዚህ መምህራን ነገ ለምንገነባት ኢትዮጲያ ሚናቹህን ልትወጡ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
ሀገርን በመገንባት ረገድ ሁሉም ዜጋ የየድርሻውን መወጣት ይኖርበታል ያሉት ኢንጅነር ወንድሙ የመምህራን ሚና ደግሞ ትውልድ ላይ በትጋት መስራት እና መቅረፅ በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ኢትዮጲያ በለውጥ ጎዳና ላይ ትገኛለች ያሉት ኢንጅነሩ ነገ ለምናልማት ኢትዮጲያ ግንባታ በተሰማራንበት የስራ መስክ ሁሉ ውጤታማ መሆን አለብን ሲሉ ገልፀዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃፍቱ ብርሀኑ እንደተናገሩት በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት የመምህራን ሚና ከፍተኛ ነው ብለው መምህራን ትውልድን የሚያንፁ ስራዎችን በቁርጠኝነት በመስራት እና በስነ-መግባሩ ምስጉን የሆነ ትውልድን በማፍራት ለብልፅግና ጉዞው አስተዋፆ ማድረጋቹህን ማጠናከር አለባቹህ ሲሉ ገልፀዋል።
