fa
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
አዲስ አበባ ሰርክ አዲስ !! ዛሬ ጥዋት ለአገልግሎት ክፍት ያደረግነዉ ከእንጦጦ - አራት ኪሎ ኮሪደር። ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የሁለተኛው ዙር ኮሪደር ልማት አካል የሆነውና ዛሬ የተመረቀዉ ከ4 ኪሎ እስከ እንጦጦ ኮሪደር ፕሮጀክቶች ምን አካቶ ይሆን? •ፕሮጀክቱ በአገሪቱ ዘመናዊ የአገር ግንባታ ሂደት ከፍተኛ ሚና ያላቸው ተቋማት የሚገኙበት ነዉ •የህዝብ እንደራሴዎች መቀመጫ •የምሁራን አምባ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መገኛ ፣ •በአገሪቱ የመጀመሪያው የህክምና ተቋም የካቲት 12 ዘመናዊ ሆስፒታል መገኛ •የመጀመሪያው የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ሙዚየሞችና የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማትና እንዲሁም የከተማዋ የእደ ጥበብ ውጤቶች ልህቀት ማዕከል የሆነው ሽሮሜዳ መገኛ •በአጠቃላይ በርካታ ግዙፍ መንግስታዊና ታሪካዊ ተቋማት የሚገኙበት መስመር የሚሸፍን እና 314 ሄክታር ስፋት ያለው መሬት ለምቷል • ቀድሞ 32 ሜትር ወደ 42 ሜትር መንገዱ ሰፍቷል • 3 ሜትር ስፋት ያለው የብስከሌት መንገድ • 11 የታክሲ እና የአውቶቡስ መጫኛና ማውረጃዎች • 20 አረንጓዴ ቦታዎች • 2 ፕላዛዎች • 10 ደረጃቸውን የጠበቁ የህጻናት መጫዎቻ • 7 ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች • 9 መጸዳጃ ቤቶች • ከ5-13 ሜትር ስፋት ያለው 11.4 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ • 2 (1 ዘመናዊ ሞልን ያካተተ በመንግስትና የግል አጋርነት እየተገነባ ያለ ተርሚናሎች እና 11 የታክሲ/ባስ መጫኛና ማውረጃዎች • 7 የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች • 417 ስማርት ፖሎች • ከ15 ሺ ለሚበልጡ ዜጎች ጊዚያዊ እና ቋሚ የስራ እድል • በአዲስ የተሰሩ 770 ሱቆች በመጨመር 1521 ሱቆች አካቷል ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ባለፈ በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለሚፈለገው ዓላማ ማዋል ከመቼውም ጊዜ በላይ ባህላችን እየሆነ መምጣቱ ዛሬ የምናስመርቃቸው 4 ኪሎ እስክ እንጦጦ ኮሪደር እውነተኛ ማሳያ ናቸው፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከሁሉ በላይ የረዳን ፈጣሪ ይመስገን! ዛሬ የሁለተኛው ዙር ኮሪደር ልማት አካል የሆነው ከ4 ኪሎ እስከ እንጦጦ ኮሪደር ፕሮጀክቶች መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል፡፡ ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ባለፈ በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለሚፈለገው ዓላማ ማዋል ከመቼውም ጊዜ በላይ ባህላችን እየሆነ መምጣቱ ዛሬ የምናስመርቃቸው 4 ኪሎ እስክ እንጦጦ ኮሪደር እውነተኛ ማሳያ ናቸው፡፡ በአገራችን ዘመናዊ የአገር ግንባታ ሂደት ከፍተኛ ሚና ያላቸው ተቋማት መገኛ ፣ የህዝብ እንደራሴዎች መቀመጫ ፣ የምሁራን አምባ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መገኛ ፣ በአገሪቱ የመጀመሪያው የህክምና ተቋም የካቲት 12 ዘመናዊ ሆስፒታል መገኛ ፣ የመጀመሪያው የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ሙዚየሞችና የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማትና እንዲሁም የከተማችን የእደ ጥበብ ውጤቶች ልህቀት ማዕከል የሆነው ሽሮሜዳ መገኛ ፤ በአጠቃላይ በርካታ ግዙፍ መንግስታዊና ታሪካዊ ተቋማት የሚገኙበት መስመር የሚሸፍነው እና 314 ሄክታር ስፋት ያለው መሬት የለማ ሲሆን :: ይህ ኮሪደር ልማት በፊት ከነበረው 32 ሚትር ስፍት ወደ 42 ሜትር የመንገድ የስፋው ፤ 3 ሜትር የብስከሌት መንገድ እንዲሁም 11 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጨምሮ 11 የታክሲ እና የአውቶቡስ መጫኛና ማውረጃዎች ተሰርተውለታል። ከዚህ በተጨማሪ 20 አረንጓዴ ቦታዎችና 2 ፕላዛዎች እንዲሁም 10 የህጻናት የመጫዎቻ እና 7 የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን ጨምሮ 9 መጸዳጃ ቤቶች ፣ ከ5 – 13 ሜትር ስፋት ያለው 11.4 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ፣ 2 (1 ዘመናዊ ሞልን ያካተተ በመንግስትና የግል አጋርነት እየተገነባ ያለ ተርሚናሎች እና 11 የታክሲ/ባስ መጫኛና ማውረጃዎች ያሉት እንዲሁም 7 የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እና 417 ስማርት ፖሎች አካቷል። ይህንን መስመር መልሶ ማልማት፤ማደሰና ማስዋብ ለአገራችንና ለህዝባችን ታሪክ ያለንን ክብር የሚገልፅ ከመሆኑም በተጨማሪ ከ15 ሺ ለሚበልጡ ዜጎች ጊዚያዊ እና ቋሚ የስራ እድል ለመፍጠር ችለናል፡፡ በፊት የነበረው 751 ሱቆች ሲሆኑ በአዲስ የተሰሩ 770 ሱቆች በመጨመር 1521 ሱቆች በዚህ ኮሪደር የኢኮኖሚ ልማት እና የንግድ ልውውጥ እንዲያድግ አድርጓል። በመጨረሻም ለፕሮጅክቶች ስኬትና በዚህ ደረጃ ዕውን መሆን ቀን ከሌሊት የደከማችሁ ብሎም በተለያየ መንገድ የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባላት ጋር በመሆን አዲሱን እና ከእንጦጦ እስከ አራት ኪሎ ፕላዛ ተሠርቶ የተጠናቀቀውን ኮሪደር ዛሬ ጠዋት ተመልክተናል። ይኽ አስደናቂ ለውጥ ከተካሄደባቸው የከተማችን ክፍሎች አንዱ ነው። Together with Prosperity Party Central Council members, we have reviewed the entire pathway of the Entoto to Arat Kilo Plaza corridor development that has been completed unveiling anothe section of our city rang has undergone a great transformation. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ

ለረዥም ጊዜ የህብረተሰቡ የቅሬታ ምንጭ የነበሩ የመንገድ ላይ መብራት ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ መደረጉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስ… See mor

ለረዥም ጊዜ የህብረተሰቡ የቅሬታ ምንጭ የነበሩ የመንገድ ላይ መብራት ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ መደረጉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ፡፡ ለዝርዝር ዘገባው በቀጣዪ ቪዲዮ ይመልከቱ 👉👉 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የህብረተሰቡን የረጅም ጊዜ የመንገድ መብራት ጥያቄ መፍታት የቻለ ተቋም መፍጠር መቻሉ ተገለፀ። ለረጅም ጊዜ የህብረተሰቡ የቅሬታ መንስኤ የነበሩ በርካታ የመንገድ መብራት ጥያቄዎችን በመፍታት ረገድ የከተማችን የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን እያከናወናቸው ያሉ ውጤታማ ስራዎች ከተማ አስተዳደሩ በመንገድ ዳር መብራት ላይ የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታት የተከተለውን ስትራቴጂካዊ ውሳኔ ትክክለኛነት ማሳያ እንደሆነ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ። ለረጅም ጊዜ የህብረተሰቡ ቅሬታ ሆኖ የቆየውን የአራራት- ኮተቤ - ካራን የመንገድ መብራት ሙሉ በሙሉ በማብራት አገልግሎት መስጠት እንደተቻለ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች የመንገድ መብራት ስራውን ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት አረጋግጠዋል፡፡ ለዚህም የአራራት ኮተቤ -ካራ መንገድ ላይ የተከናወነው የመብራት መሰረተ-ልማት ዝርጋታና ጥገና ስራ አንዱ መሆኑን አንስተው፤ የታየው ለውጥ ከተማችን የቀን ብቻ ሳትሆን ምሽትም ጭምር የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ በማቀላጠፍና አካባቢውን ብርሀን በማድረግ ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ ለመግባት ምቹ ሁኔታ መፍጠር መቻሉን ገልፀዋል፡፡ ኢንጂነር ወንድሙ አፅንኦት የሰጡት ጉዳይ በከፍተኛ የህዝብ ሀብት የለሙ መሰረተ-ልማቶች አገልግሎት የሚሰጡት ለራሳችን በመሆኑ ከሚፈፀም ማንኛውም ስርቆት፣ ብልሽትና የተሽከርካሪ ግጭት ግንባር ቀደም ሆነን መጠበቅ ይገባናል ብለዋል፡፡ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ያስጎበኙት የከተማው የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን፤ ይህን አካባቢ ጨምሮ በከተማዋ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ በርካታ ዋና መንገዶች፣ የጋራ መኖሪያ አካባቢዎች የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ላይ አስፈላጊውን የመስመር ዝርጋታ፣ ተከላና ጥገና ስራዎችን በማከናወን ለህብረተሰቡ ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ የምሽት እንቅስቃሴ በቂ ብርሀን እንዲሰጡ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡ በተለይም ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የተጎበኘው ይህ መንገድ፤ ህብረተሰቡ ለረጅም ጊዜ ቅሬታ ሲያቀርብበት የነበሩ መሆኑን አስታውሰው፤ ባለስልጣን መ/ቤቱ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማከናወን በአጠረ ጊዜ ውስጥ ባደረገው የጥገና ስራ በሁለቱም አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጥ አድርጓል ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሬ አሁንም ያልተሸገርነው ዋነኛ ችግር ብለው ያነሱት መሰረተ-ልማቱን በመጠበቅና በመንከባከብ ረገድ ሲሆን ለዚህም በተሰራ በአጭር ጊዜ ውስጥ በዚሁ መንገድ ላይ ከትራንስፎርመር ወደ ፖሎች የሚሄደውን የኬብል መስመር መንገዱን ቆፍረውና ኬብሉ ተቆርጦ መሰረቁ አንዱ ተጨባጭ ማሳያ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ከዚሁ አያዘው በለማው መሰረተ ልማት ላይ የሚፈፀም ስርቆት መልሶ ህብረተሰቡን ለዘርፈ ብዙ ችግር የሚዳርግ ከመሆኑ ባለፈ ከፍተኛ የህዝብ ሀብት እንዲባክን የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም ከምንም በላይ ህብረተሰቡ የመሰረተ-ልማቱ ባለቤት መሆኑና በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ ተሳታፊ በመሆን ከባለስልጣኑ ጎን እንዲቆሙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የእኛ ፖለቲካ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በዉጤት የታጀበ ስራ ነው ።… See more

የአዲስ አበባ ወንዞች ትንሣኤ ፤ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያዎች!! ትላንት ማምሻዉን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባላት ጉብኝት Ka'umsa laggeen Finfinnee, mul'istuuwwan bayyanachuu Itoophiyaa!! Kaleessa galgala kabajamoo muummichi ministeeraa Dr. Abiyyi Ahimad bakka argamanitti daaw'annaa miseensota mana maree Paartii Badhaadhinaa!