1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የህዝባችንን ጥያቄዎች የምንመልሰዉ የሚታዩ ፣ የሚጨበጡ እና ዘላቂ መፍትሄዎች ላይ በማተኮር ነዉ።
ዛሬ ጠዋት ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የኢንዱስትሪ ክላስተር ጎብኝተናል። 93 ሄክተር መሬት በመመደብ በ7 ቢሊዮን ብር ወጪ ግንባታው እየተከናወነ ያለዉ ይህ የኢንዱስትሪ መንደር የመጀመሪዉ ምዕራፍ ከ120 በላይ ሼዶች ያሉት ሲሆን ለብረታብረት ሥራ፣ ለእንጨት ውጤቶች፤ ለጨርቃ ጨርቅ ፣ ለፕላስቲክ እና ለኬሚካል ማምረቻነት፣ የምርት ማሳያ እና መሸጫ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ናቸዉ።
ይህ ግዙፍ የኢንዱስትሪ መንደር ግንባታ፤ የመስሪያ ቦታ ችግርን ከማቃለል ባሻገር የማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመፍታት፣ ሰፊ የስራ ዕድልን ለመፍጠር የኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥ ረገድ ሚናው የጎላ ነው። የግንባታው ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ምርቶች የሚሆኑ ሼዶችን የያዘ ነው።
ይህ የኢንዱስትሪ መንደር ከዚህ ቀደም ከነበሩት ሼዶች በተለየ ሁኔታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግብአቶችን እንዲጠቀም ተደርጎ እየተገነባ ነዉ።
በተጨማሪም ከቦሌ ኤርፖርት በጥቂት ደቂቃ መድረስ የሚያስችል አዲሱ የአቃቂ ቦሌ ካርጎ መንገድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ምርት ማጓጓዝን ታሳቢ ያደረገ እና ስትራቴጂክ ስፍራ ላይ የሚገኝ ፕሮጀክት ነው።
አዲስ አበባን የኢትዮዽያ ብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን !
ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን እና ህዝቧቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
"የፎቶ አውደ-ርዕዩ የመጡ ውጤቶችን መለስ ብሎ ለማየት ይጠቅማል" ኢንጂነር መንድሙ ሴታ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተካሄደው የፎቶ አውደ-ርዕይ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የፎቶ አውደ-ርዕዩ የመጡ ውጤቶችን መለስ ብሎ ለማየት እንደሚጠቅም ገልጸዋል፡፡
የፎቶ አውደ-ርዕዩ በክፍለ ከተማው የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት የተዘጋጀ ነው፡፡
አውደ-ርዕዩ ብልጽግና ፓርቲ ላለፉት 7 አመታት በልማትና በመልካም አስተዳደር የተሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ በ13ቱም ወረዳዎች የተከናወኑ ተግባራት ያካተተ ነው ፡፡
የእለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሲታ፥ የፎቶ አውደ-ርዕዩ መሬት ላይ የወረዱ ስራዎች እና የመጡ ተጨባጭ ውጤቶችን መለስ ብሎ ለማየት ይጠቅማል ብለዋል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ አዲስ የታሪክ ምእራፍ እያሳየ እና አዳዲስ ትርክቶችን እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልጸው የሚከናወኑ ተግባራትን በኮሚኒኬሽን አግባብ ሊደገፉ እንደሚገባ ገልጸዋል ፡፡
የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ፥ አውደ-ርዕዩ ብልጽግና ፓርቲ ምን ያህል የህዝብ ችግር ነቅሶ በማውጣት የሚታይ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንዱ አሰፋ በበኩላቸው ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ሰባት ዓመታት በሁሉም መስኮች በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ መቻሉን ጠቅሰዉ ስኬቶቻችንን በሁሉም የሚዲያ አማራጮችና አውደ ርዕዮችን በማዘጋጀት ለዜጎቻችን ይበልጥ በማሳወቅ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማፅናት አጋዥ እንዲሆኑና በሁሉም ተግባሮቻችን እያደረጓቸው ያሉትን ቀጥተኛ ተሳትፎዎች እንዲጎለብቱ ለማስቻል ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።
በፎቶ አውደ-ርዕዩ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ እራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሲታ፥ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፋጻሚ ወ/ሮ ካባ መብራቱ፣ የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ፥ እንዲሁም የከተማና የክፍለ ከተማ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈውበታል፡፡
#LaftoCommunication
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የህዝብ እና የግል ሚዲያ ባለሞያዎች ጋር ያካሄዱት ውይይት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የህዝብ እና የግል ሚዲያ ባለሞያዎች ጋር ያካሄዱት ውይይት፤
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ የህዝብ እና የግል ሚዲያ ባለሞያዎች ጋር ያካሄዱትን ውይይት ዛሬ ምሽት ሰኔ 17 በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ከምሽቱ 2:30 ላይ ይከታተሉ።
ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረጉ ውይይቶች የመጨረሻው የሆነው ውይይት ዛሬ ከሕዝብ እና የግል ሚዲያዎች ከተወጣጡ ባለሞያዎች ጋር ተካሂዶ በኢንደስትሪው ያሉ ልዩ ጉዳዮችን እና ተግዳሮቶችን ዳስሷል። ሚዲያ በኢትዮጵያ የልማት ሥራዎች ውስጥ ሕዝብን በማሳወቅ፣ ውይይትን በማዳበር እና ብሔራዊ የእድገት ርምጃን በመደገፍ ቁልፍ ሚና አላቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የ90 ቀናት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች እና የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ልዩ የንቅናቄ አጀንዳ እቅድ ከከተማ የሚመለከታቸው ተቋማት እና ከክፍለ ከተማ መዋቅር ጋር የተካሄደው ውይይት በምስል:- 👉👉👉
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጤና ባለሙያዎች ጋር ያደረጉት ቆይታ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጤና ባለሙያዎች ጋር ያደረጉት ቆይታ፤
#Ethiopia
#addisababa
#AMN
#linkaddis
#developmentopportunity
See less
እንኳን ደስ አላችሁ!
ከአንጋፋው ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ዛሬ የተመረቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ።
ውድ ተመራቂዎች፤ የትምህርት ዘርፍ ተመራቂ እንደመሆናችሁ መጠን ትምህርት ትውልድን የሚቀርጽና የሚያንጽ መሳሪያ መሆኑን፣ መማር ደግሞ የአስተሳሰብ እና የአሰራር ለውጥ ማምጣት የሚስችል እንዲሁም የትምህርት ባለሞያነት ትውልድን በማነጽ ሃገርን የመገንባት የማይተካ ታላቅ ሃላፊነት ስለሆነ ስራ ላይ ስትሰማሩ ለአፍታም ሳትዘነጉ ለዉጤታማነቱ ልትተጉ ይገባል።
ተመራቂ ተማሪዎቻችን ወጣቶች ናቸሁ፤ መጪው ጊዜ ደግሞ የወጣቶች ነው። ከዛሬው የተሻለ ብሩህ ተስፋ ይጠብቃችኋል። ለሚጠብቃችሁ ብሩህ ዘመን የተማራችሁትን ወደተግባር መለወጥ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜም ተማሩ፤ እየተለወጠ ላለዉ ነገ ራሳችሁን ይበልጥ አዘጋጁ።
የስራ ዘመናችሁ ስኬታማ እንዲሆን ከልቤ እመኛለሁ !
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የግንባታ ተረፈ ምርት የማስነሳት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከለሚ ኩራ ክ/ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት እንዲሁም የጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት የግንባታ ተረፈ ምርት የማስነሳት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ህይወት ሳሙኤል ፣ኢ/ር አበበ እሸቱ የባለስልጣኑ የክትትል ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ፣ አቶ ወንድማገኝ ታደሰ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ እንዲሁም የ11ዱም ክ/ከተማ የግንባታ ፍቃድ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በዕለቱ መልዕክት ያስተላለፉት የየአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሂወት ሳሙኤል እንዳሉት የግንባታ ተረፈ ምርቶችን በአግባቡ ማስነሳት እንደሚገባ የገለጹ ሲሆን ይህም በተቀናጀ አግባብ በቀጣይ በሁሉም ክ/ከተሞች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ታደሰ በበኩላቸው የግንባታ ተረፈ ምርቶችን በወቅቱ በማንሳት የመሠረተ ልማት ስራዎችን በሚገባ ማከናዎን እንደሚገባና አካባቢውን ውብና ጽዱ ብሎም ለኑሮ ምቹ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር ሰለሞን እንደገለጹት የግንባታ ተረፈ ምርቶችን የማስነሳት ተግባር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
Lemi Kura Communication ለሚ ኩራ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ የጤና ባለሞያዎች ጋር ያካሄዱትን ውይይት ዛሬ ምሽት ሰኔ 15 በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ከምሽቱ 2:30 ላይ ይከታተሉ።
#PMOEthiopia
