fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ፤ በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬቾ ቀበሌ ለደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወጎኖቻችን ግምታቸው 45.5 ሚሊዮን የ ገንዘብ ፤የህክምና ግብአቶች የአስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ ወደ ቦታው መላኩን አስታወቁ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በድጋፉ ሽኝት ሰነ ሰርዓት ላይ እንደተናገሩት ለወገን ቀድሞ መድረስ ቀዳሚ ተግባራችን ነው ያሉት በከተማው ህዝብና አስተዳደር ስም ከጎናቸው መሆናችንን ለመግለፅ የከተማው አመራሮችን ወደ ቦታው በአካል የሄዱ ሲሆን የጉዳቱን ልክ በቦታው በአካል በማየት ድጋፉን ለመቀጠል እንስራለን ሲሉም አብሮነታቸውን ተናግረዋል። ከተላኩት የድጋፍ አይነቶቹ ውስጥ አንቡላንስ፣ የህፃናት አልሚ ምግቦች ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ህክምና እርዳታ መስጫ መሣሪያዎች ፣ መድሀኒቶች ፣ እንሶላዎች፣ በርድልብሶች ሲሆኑ በገንዘብ 25 ሚሊየን እና በቁሳቁስ ደግሞ 20 ሚሊዮን ግምት እንዳላቸው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ራእይ፣ ተልእኮ እና አሴቶች ያውቃሉ? ይህችን አጭር ጽሁፍ ይመልከቱ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በጎፋ ዞን ጎዝዲ ቀበሌ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ በበርካታ ዜጎቻችን ሕይወት ላይ በደረሰው አስከፊ አደጋ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እገልጻለሁ። አደጋው ለደረሰባቸው ዜጎችና ቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እየተመኘዉ በቀጣይ ከክልሉ አስተዳደር ጋር በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ የምናደርግ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በጎፋ ዞን ጎዝዲ ቀበሌ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ በበርካታ ዜጎቻችን ሕይወት ላይ በደረሰው አስከፊ አደጋ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እገልጻለሁ። አደጋው ለደረሰባቸው ዜጎችና ቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እየተመኘዉ በቀጣይ ከክልሉ አስተዳደር ጋር በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ የምናደርግ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በ''አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ'' የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ጎን ለጎን ከተለያዩ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቋማት ለተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮች ለስድስት ወራት የኤክስኪዩቲቭ ሊደርሺፕ ሥልጠና ለመስጠት የታለመበት መርሃግብር ተዋውቋል። ሥልጠናው በኢትዮዽያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥታት በትብብር የሚሰጥ ነው።

አረንጓዴ አሻራ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያግዝ ለትውልድ የሚተርፍ ቅርስ ነው”-በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ተጠሪ ተቋማቱን እና መላ መዋቅሩን በማስተባበር በአቃቂ / ቃሊቲ ክ/ ከተማ በሚገኘው የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (አስቱ) ዩንቨርስቲ የ2ኛው ምእራፍ 2ኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂዷል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን "የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ!" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው መርሃ ግብር እንደ ጽ/ቤት በክረምቱ ወራት በዛሬው እለት የምንተክለውን የ10 ሺህ ችግኝ ጨምሮ በአጠቃላይ 50 ሺህ ችግኞች ይተከላሉ ብለዋል። በዛሬው እለትም ሃምሌ 16/ 2016 አ.ም በስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት የተጠሪ ተቋማቱን እና ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለው መላው መዋቅሩን በማስተባበር በአቃቂ ክ/ ከተማ በሚገኘው የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአንድ ጀምበር ብቻ 10 ሺህ ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እንደተካሄደ ተገልጿል ። “አረንጓዴ ልማት ለምንኖርበት አካባቢም ሆነ ለምድራችን ሁሉ ውበት፣ ድምቀት፣ እስትንፋስ እና ህይወትም ነው” ያሉት ክብርት ሂክማ አረንጓዴ አሻራ ለከተማዋ ውበትን የሚያጎናጽፍ፣ የአረንጓዴ ልማትን እና የደን ሽፋንን በማሳደግ መዲናችንን አለም አቀፍ ደረጃዋን የጠበቀች እንድትሆን የሚያደርጋት እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም አዲስ አበባን አረንጓዴ፣ ውብ እና ከአየር ብክለት የፀዳች ለማድረግ የከተማው ነዋሪ የነቃ ተሳትፎውን በማድረግ ለትውልድ የሚሻገር ደማቅ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በበኩላቸው፣ ክፍለ ከተማው በርካታ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙበት እንደመሆኑ ሀገር በቀል ችግኞችን መትከል ከኢንዱስትሪዎች የሚወጡ በካይ ጋዞችን በመቋቋም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመከላከል ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል። በአቃቂ ክ/ከተማ የሚገኘው የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተመስገን ወንድሙ፣ በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ የሚተከሉት ችግኞች ሙሉ በሙሉ የፍራፍሬ መሆናቸውን በመግለጽ በአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አማካኝነት በግቢው የተተከሉ ችግኞችም ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ ሐምሌ 16/ 2016 አ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የክፍለ ከተሞች ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤቶችን የ2016 በጀት አፈፃፀምና የ2017 እቅድን በጋራ ገመገመ :: የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የክፍለ ከተሞች ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤቶችን የ2016 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀምና የ2017 እቅድ ላይ የጋራ ዉይይት አካሂዷል። በመድረኩም በ2016 በጀት አመት የክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤትና በተጠሪ ተቋማት የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች፣ የቅንጅታዊ አሰራር ፣የድጋፍ እና ክትትል፣የአገልግሎት አሰጣጥን ከማሻሻል፣በፅዳት ሞዴል ወረዳዎችን ከመፍጠር አንፃር፣ ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር፣ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ እና በስታንዳርድ ከመስጠት አንጻር እና ብልሹ አሰራሮችን ከመፍታት አንጻር የተሰሩ ስራዎችን የሚያሳይ ራፖርት ቀርቦ የጋራ ውይይት ተካሂዶበታል :: በመድረኩ በቢሮ ሀላፊ ማአረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ሰራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በበጀት አመቱ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ከማድረግ፣ቅንጅታዊ አሰራርን ከመተግበር፣የስራ ከባቢን ምቹ ከማድረግ እና የህብረተሰብ ተሳትፎን ከማሳደግ አንፃር አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን አመልክተዋል። ከድጋፍና ክትትል፣የኘሮጀክት አፈፃፀምን በተመለከተ፣ብልሹ አሰራርን ከመቅረፍ አንፃር አመርቂ ዉጤት የተመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ተፈራ አክለውም በ2016 በጀት አመት በሁሉም ክፍለ ከተሞች የስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤቶች ያልተተገበሩ ስራዎችን በመለየት በ2017 በጀት አመት ተግባራዊ በማድረግ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ እንሚገባቸዉም አቅጣጫ አሳስበዋል። በቢሮ ሀላፊ ደረጃ የስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ በሁሉም ክ/ ከተሞች በበጀት አመቱ የተሻለ አፈፃፀም እንደነበር ገልፀዉ በተለይም አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ከማዘመን አንፃር የአገልግሎቱን አሰጣጥን ቀላል የሚያደርጉ የተጀመሩ ስራዎችን በቀጣይ በጀት አመት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ለተሽከርካሪ የማይፈቀድ ቦታ ላይ መኪናውን ያቆመ አሽከርካሪን ጨምሮ ቆሻሻን በኮሪደር ልማቱ ላይ የጣሉ ተቋማት ተቀጡ ዛሬ ሀምሌ 15/2016 ከረፋዱ 5:45 አከባቢ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለተሽከርካሪ በማይፈቀድ ቦታ ላይ መኪናውን ያቆመው ግለሰብ 5 ሺህ ብር በደንብ ማስከበር ተቀጥቷል። ፍቅር ባርና ሬስቶራንት ድርጅት በተከለከለ ቦታ ተረፈ ምርትን እና ደረቅ ቆሻሻ በመጣላቸው ብር 50,000 እና ይደምቃል ወርቅነሽና ጓደኞቿ ቆሻሻን በአግባቡና በወቅቱ ባለማንሳት ብር 20,000 ተቀጥተው ቆሻሻውንም እንዲያነሳ ተደርገዋል። እንዲሁም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኦላ ኢነርጂ የነዳጅ ማደያ ያመነጨውን ቆሻሻ በአግባቡ ባለማስወገዱ / የጥፋት አይነት ተ.ቁ 1.2 / መሰረት 50,000 ተቀጥቷል:: በጥቅሉ በልማት ኮርደሩ ላይ የደንብ መተላለፍ የፈፀሙ ሁለት ድርጅቶችና አንድ የጽዳት ማህበር በድምሩ 125,000 ብር ተቀጥቷል። የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ከመንግሥት ጋር እጅና ጓንት ሆኖ በልማቱ ላይ በባለቤትነት እንደሚሳተፍ ሁሉ በመሰረተ ልማት ጠበቃ ዙሪያም በንቃት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህዝቡ ጋር በመተባበር መሰረተ ልማቶች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያገኙ የማድረግ ስራውን በሁሉም አማራጮች ትምህርት መስጠትን ጨምሮ ህጉን የሚተላለፉትን አሽከርካሪዎች እና እግረኞችን በህጉ መሰረት አስፈላጊውን መቀጮ እየሰጠ መሄዱን የሚቀጥል ይሆናል።

በእግረኛ መንገድ ላይ ባልተፈቀደ ቦታ ሽንት ሲሸና ተገኝቶ በደንቡ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ሊፈፅም ባለመቻሉ ስፓርት እንዲስራ በማድረግ የተቀጣው ግለሰብ

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ሞዴል የፅዳት ወረዳዎችን አስመረቀ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) እንደተናገሩት አዲስ አበባን እንደ ስሟ ፅዱ ውብና አረንጓዴ ለማድረግ ተባብረን መስራት አለብን ብለው ይህ እንዲሳካ ሁሉንም ወረዳዎች በፅዳት ሞዴል ማድረግ አለብን ሲሉ ተናግረዋል። የከተማችንን ውበትና አረንጓዴነት በማስጠበቅ ረገድ ሁላችንም በባለቤትነት ልንሰራ ይገባል ያሉት ዶ/ር ጀማሉ ፅዳትና የቆሻሻን ለይቶ የማስቀመጥ ስርዓትን ሁሉም ነዋሪ ባህል እንዲያደርግ ለማስቻል የጀመርነውን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰዒድ ዓሊ እንደተናገሩት ከተማችን ውብ ጽዱና ለኑሮ ምቹ እንድትሆን እየሰራን ነው ያሉ ሲሆን በቀጣይ የህ/ሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ 10ሩንም ወረዳዎች ሞዴል እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል። መተጋገዝና መደጋገፍ ለስኬት ስለሚያበቃ አንድነታችንን አጠናክረን በሁሉም ዘርፍ ውጤት ማምጣት አለብን ያሉት አቶ ሰዒድ ክፍለ ከተማችንን የአገልግሎትና የልህቀት ማዕከል እናደርጋታለን ሲሉ ተናግረዋል። የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ተረፈ በበኩላቸው ሞዴል የፅዳት ወረዳዎችን ለመፍጠር በትኩረት እየሰራን ነው ብለው ክፍለ ከተማችንን ለመኖሪያ ምቹ ለማድረግ የጀመርነውን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ገልፀዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et