fa
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሰጡት አስተያየት !!

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በመዲናችን እተካሄደ ባለዉ የኮሪደር ልማት ዙሪያ ከአዲስ አበባ ዩኒቨር… See more

ዳጉ ዳጉ - የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት…

የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አንፃር ከከተማዋ ነዋሪዎች ምን ይጠበቃል? በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ … See more

አዲስ አበባ በአለም አደባባይ ሌላኛዋ የኩራታችን ምንጭ ! ባለፉት የለዉጥ አመታት ከተማችን አዲስ አበባን በሁለንተናዊ መልኩ ለነዋሪዎቿ የተመቸች ፣ ለጎብኚዎቿ የተመረጠችና እንደ ስሟ ዉብ አበባ እናደርጋታለን ብለን ከነዋሪዎቻችን ጋር ሌት ተቀን የሰራናቸዉ ስራዎች ይኸዉ ዛሬ ፍሬ አፍርተዉ በአለም አደባባይ አሸናፊ እያደረጉን ይገኛል ። በተለያዩ መወዳደሪያ መስፈርቶች እየመዘነ እዉቅና እና ደረጃ የሚሰጠዉ የብሉምበርግ ፍላንተሮፒስ ግብረ ሰናይ ድርጅት በከተማችን አዲስ አበባ የነዋሪዎቻችንን የአደጋ ተጋላጭነት ለመቀነስና ለመቆጣጠር በመንገድ ደህንነትና ፍጥነት ማስተዳደር ላይ በአጭር ጊዜ የሰራነዉን ስራና በተጨባጭ ያስመዘገብነዉን ዉጤት በመገምገም በአለም አቀፍ የከተምች የዘርፉ ዉድድር ላይ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ አድርጎናል ። ይህንን እዉቅናና ክብር የሰጠንን ብሉምበርግ ፍላንተሮፒስን በከተማ አስተዳደራችን ስም ከልብ እያመሰገንኩ በቀጣይም መዲናችንን በሁሉም መመዘኛዎች የተሻለች አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን የበለጠ መትጋታችን ይቀጥላል ። ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ The Addis Ababa City Administration is sincerely grateful to Bloomberg Philanthropies for the worldwide recognition of our dedication to improving road safety and speed control. This honor is a great motivator for our future efforts and a clear testament to the success of our initiatives. On behalf of the city administration and its residents, I want to express my profound thanks once more. #Bloomberg #Philanthropies.#AddisAbaba.#RoadSafety.

የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አንፃር ከከተማዋ ነዋሪዎች ምን ይጠበቃል? በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ … See more

የኤሌክትሪክ አገልግሎትን በማዘመን፤ ይነሱ የነበሩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ሪፎርም ተግባራዊ በመደረጉ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ነው። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የሚያስችል የሪፎርም ትግበራ ለከተማው የሚሰጠውን አገልግሎት ማዘመን አስችሏል ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናግረዋል፡፡ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቀደም ብሎ ከአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ጋር ተያይዞ ይነሱ የነበሩ የደንበኞች መንገላታት፣ አገልግሎት መስጪያ ዴስኮች ምቹ አለመሆን፣ በተገልጋዩ ይነሱ የነበሩ እንግልቶችን ተግባራዊ ባደረገው ሪፎርም መቀረፍ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ አክለውም በአገልግሎቱ ላይ የሚስተዋሉ የነበሩ አሰራሮችን ወደ ወረቀት አልባ አሰራር በመተካት፣ የደንበኞች የጥሪ ማዕከላትን አውቶሜትድ በማድረግ ከጥገና ስምሪት ጋር አብሮ በማስተሳሰር የቀላጠፈና ውጤታማ ስራ መከናወኑ፣ ከደንበኞች በአገልግሎቱ ላይ ግብረ መልስ የመቀበል ስርዓት መፍጠር መቻሉን አስረድተዋል፡፡ ኢንጅነር ወንድሙ አያይዘውም እንዲሁም የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቱንና ሀይል ስርጭት ጋር ተያይዞ ያለውን አሰራር በቴክኖሎጂ በማስደገፍ በማዕከል ማስተዳደር አስተማማኝ ስርዓት መፍጠር ተችሏል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ደንበኞች በየትኛውም ሰዓትና ቦታ ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት መምጣት ሳያስፈልጋቸው በሚኖሩ የክፍያ አማራጮች ሀይል መሙላት የሚችሉበት ስርዓት መፍጠር መቻሉንና በፓይለት ደረጃ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ ቀጣይ ደንበኞችን የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ከእንግልት እንደሚያስቀር አስታውቀዋል፡፡ በከተማ አስተዳደሩ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን ሁለቱም ተቋማት ለከተማው ነዋሪዎች ከሀይልና ከመሰረተ ልማት አቅርቦት ጋር ተያይዞ በቅንጅት የሚሰሩ በመሆናቸው በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት በመቅረፍና በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ግብዓት ለመውሰድ እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያካሄደው ሪፎርም የከተማውንና የህብረተሰቡን የአሁንና መጪውን እድገት ታሳቢ ያደረገና የከተማዋን እድገት ጋር በሚመጥን ደረጃ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ዘላቂ የሀይልና የመሰረተ ልማት አቅርቦት በቴክሎጂ የተደገፈ ስርዓት መተግበሩን ማየት መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በዚህም በጋራ ጥምረትና ትብብር ለከተማው የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችሉ ስራዎች ከማዕከል አገልግሎት መስጪያ፣ በመሰረተ ልማት ማዘመን በተለይም በኮሪደር ልማት መሰረተ-ልማቱን ከመሬት በታች በመዘርጋት፣ የሀይል አቅርቦቱን በአንድ ማዕከል ለማስተዳደርና ስርጭቱ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመፍታት የሚያስችል በሲስተም የተደገፈ ስራ መሰራቱን፣ የደንበኞችና የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሪፎርም መተግበሩን በመልካም ተሞክሮ ሊወሰዱ የሚችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኔትወርክ መሠረተ-ልማት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ገበየሁ ሊካሳ በበኩላቸው በከተማዋ የሚከሰተውን የሀይል መቆራረጥ ለመፍታት የአጭር፣ የመካከለኛና ረጅም ጊዜ ዕቅድ በመያዝ የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማቱን ለማሻሻልና አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘርፉ ብዙ የመሰረተ ልማት ስራዎች መሰራቱን ገልፀዋል፡፡ በመሰረተ-ልማቱ በኮሪደር ልማቱ ላይ ከመሬት በታች በመቅበር የተገኙ መልካም እድሎችን በማስፋትና የተዳከሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ በማልማትና በቴክኖሎጂ የተደገፈ በማድረግ የተሰሩ ስራዎች ይከሰቱ የነበሩ የሀይል መቆራረጦችን በመቀነስና በቀጣይ ወደ ዜሮ ለማድረስ እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

አጠቃላዩ የኮሪደር ልማት አሠራር ለመጪው ጊዜ ታላቅ ተስፋ የሚሰጠን ነው። በመጀመሪያው ምዕራፍ በአራት ኮሪደሮች ጀምረን በሁለተኛው ምዕራፍ በስምንት ኮሪደሮች ቀጥለናል። የተጠናቀቀውን እና 12.74 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን ከአዲስ ኮንቬንሽን መዐከል-ጎሮ-ቪአይፒ ኤርፖርት ኮሪደር ዛሬ ተመልክተናል። በኮሪደሩ 29 ኪሎሜትር የእግረኛ መንገድ እና 15.27 ኪሎሜትር የብስክሌት መጋለቢያ ተሰርቷል። ይኽ የኮሪደር ሥራ ሰፋፊ የተሽከርካሪ መንገዶችን፣ ከጎሮ እስከ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ መንገድ እንዲሁም በአካባቢው ሰፊ የወንዝ ልማትን ያካተተ ነው። ሰባት የስፖርት ማዕከላት፣ የመኪና ማቆሚያዎች፣ የታክሲ እና አውቶቡስ መናኸሪያዎች፣ ካፌዎች፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች እና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎች የተካተቱበት ነው። እነኚህ ግንባታዎች ሥራ ፈጥረዋል፣ መገናኛ እና መዳረሻዎችን አስፋፍተዋል፣ የከተማዋን መሠረተ ልማት አጠናክረዋል። በሁሉም መስክ ኢትዮጵያ መበርታቷን ቀጥላለች። ወደ ብልጽግና የምናደርገው ጉዞ አይደናቀፍም። አይቆምም። የእነኚህ ሥራዎች ስኬት ይኽንን ያስቻለውን የተለወጠ ርዕይ እና የሥራ ባሕል ያንፀባርቃል። እስከአሁን የከተማዋ ግማሽ ያህል የተለወጠ ሲሆን የበለጠ ለማሻሻል የምንተጋባቸው ከባቢዎች አሁንም ይቀራሉ። ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ ር አቢይ አህመድ

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ የሪፎርም ተግባር በአራቱ የከተማዋ ሪጅን ቢሮዎች ያመጣው ለውጥና ያስገኘው ውጤት የመስክ ምልከታን AMN-Addis Media Network ይከታተሉ

የኮሪደር ልማት በመዲናዋ የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀነስና የተሳለጠ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ለመስጠት አስችሏል

በኮልፌ ክፍለ ከተማ ማህበረሰቡን በማስተባበር የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮች ተግባራዊ በማድረግ ለህብረተሰቡ ምቹ የመኖሪያ አከባቢ መፍጠር መቻሉን ተገለፀ። ክፍለ ከተማው በ90 ቀናት ውስጥ ለማከናወን በዕቅድ ከተያዙት ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮችን የመፍጠር ስራ ያለበትን የአፈፃፀም ደረጃ ለመመልከት የክፍለ ከተማው ዋና አመራሮች፣ የማዘጋጃ ቤታዊ እና የክረምት የበጎ ፍቃድ ግብረ ሃይል አባላት በተገኙበት በጋራ በወረዳ 06 እና 07 አስተዳደር የተሰሩ ስራዎች ምልከታ ተካሄደዋል ። የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሚ ሙሄ ዓሊ የመስክ ምልከታውን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት በክፍለ ከተማው ውጤታማና የተቀናጀ የሞዴል ብሎኮች መፈጠራቸውን በማስታወስ የተፈጠሩ ሞዴል ብሎኮች ለህብረተሰቡ ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ከመፍጠር ባሻገር የሰላም ሁኔታን በተሻለ ሁኔታ በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆናቸውን ገልፀዋል። ሀላፊው ጨምረውም ማህበረሰቡን በማስተባበር አካባቢውን ከማልማት አንፃር እያደረገው ያለው አስተዋፅኦ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባዋል ብለዋል። በመስክ ምልከታው የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮችን ከመፍጠር አንፃር የተከናወኑ ስራዎች፣ ፅዳና ውብ አከባቢን ከመፍጠር አኳያ፣የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራሞች አፈፃፀም እንዲሁም ደረጃውን የጠበቀ የኮሪደር ስራዎች ማለትም ስታንዳርዳይዜሽን የማስጠበቅ ስራዎች፣ በማህበረሰብ ተሳትፎ የተሰሩ የመብራት ማስበራት፣ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች፣ የተሟላ የህፃናት መጫወቻና ሌሎች ስራዎች ምልከታ ተደርጎባቸዋል ። Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሰጡት አስተያየት !!

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በመዲናችን እተካሄደ ባለዉ የኮሪደር ልማት ዙሪያ ከአዲስ አበባ ዩኒቨር… See more

1221684913319019 (2).mpd0.10 KB

1221684913319019.mpd0.10 KB