fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
በአዲስ አበባ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ። አዲስ አበባ: ጥር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ "ጥምቀትን በጽዱ አዲስ አበባ" በሚል መሪ መልዕክት የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል። ጽዳቱ የተካሄደው በጃን ሜዳ የታቦታት ማደሪያ ላይ ነው። የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጸሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ አንዳችን የአንዳችን በዓል ደስታችን መኾኑን እና አክብሮታችንን ለመግለጽ ተገኝተናል ብለዋል። ክርስቶስ ትህትናን ያሳየበት የፍቅር፣ የአንድነት እና የአብሮነት በዓል በመኾኑ ይህንን የበዓሉን ሥፍራ በማጽዳት በዓሉን በጋራ በአንድነት ማክበር ይገባል ነው ያሉት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ወክለው የተገኙት አባ ወልደየስ በዓሉ የፍቅር ነው ብለዋል። ቤተክርስቲያኒቱም ይህንን ስታስተምር ኖራለች ነው ያሉት። ዋና ዓላማው መተባበርን፣ የጥላቻ እና መለያየትን ከአዕምሮ ማጽዳት ነው ብለዋል። በዓሉን ለማድመቅ እና ቦታውን ለማጽዳት የተገኙትን እና ያስተባበረውን ከተማ አሥተዳደሩንም አመሥግነዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማው ሥራ አሥኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የጥምቀት በዓል ለዘመናት ሲከበር የቆዬ ትልቅ በዓል መኾኑን ገልጸዋል። ሁሉም የኔ ብሎ የሚያከብረው በዓል መኾኑንም ተናግረዋል። ከተማ አሥተዳደሩም ጥምቀት በንጹሕ ሥፍራ፣ በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ሁሉ ማድረጉን ይቀጥላል ነው ያሉት። በዓሉ በአብሮነት እና በሰላም እንዲከበር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ዘጋቢ:- ድልነሳ መንግሥቴ የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ! 👇👇👇 https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

በአዲስ አበባ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ። አዲስ አበባ: ጥር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ "ጥምቀትን በጽዱ አዲስ አበባ" በሚል መሪ መልዕክት የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል። ጽዳቱ የተካሄደው በጃን ሜዳ የታቦታት ማደሪያ ላይ ነው። የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጸሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ አንዳችን የአንዳችን በዓል ደስታችን መኾኑን እና አክብሮታችንን ለመግለጽ ተገኝተናል ብለዋል። ክርስቶስ ትህትናን ያሳየበት የፍቅር፣ የአንድነት እና የአብሮነት በዓል በመኾኑ ይህንን የበዓሉን ሥፍራ በማጽዳት በዓሉን በጋራ በአንድነት ማክበር ይገባል ነው ያሉት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ወክለው የተገኙት አባ ወልደየስ በዓሉ የፍቅር ነው ብለዋል። ቤተክርስቲያኒቱም ይህንን ስታስተምር ኖራለች ነው ያሉት። ዋና ዓላማው መተባበርን፣ የጥላቻ እና መለያየትን ከአዕምሮ ማጽዳት ነው ብለዋል። በዓሉን ለማድመቅ እና ቦታውን ለማጽዳት የተገኙትን እና ያስተባበረውን ከተማ አሥተዳደሩንም አመሥግነዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማው ሥራ አሥኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የጥምቀት በዓል ለዘመናት ሲከበር የቆዬ ትልቅ በዓል መኾኑን ገልጸዋል። ሁሉም የኔ ብሎ የሚያከብረው በዓል መኾኑንም ተናግረዋል። ከተማ አሥተዳደሩም ጥምቀት በንጹሕ ሥፍራ፣ በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ሁሉ ማድረጉን ይቀጥላል ነው ያሉት። በዓሉ በአብሮነት እና በሰላም እንዲከበር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ዘጋቢ:- ድልነሳ መንግሥቴ የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ! 👇👇👇 https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን! በአዲስ አበባ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ። አዲስ አበባ: ጥር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ "ጥምቀትን በጽዱ አዲስ አበባ" በሚል መሪ መልዕክት የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል። ጽዳቱ የተካሄደው በጃን ሜዳ የታቦታት ማደሪያ ላይ ነው። የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጸሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ አንዳችን የአንዳችን በዓል ደስታችን መኾኑን እና አክብሮታችንን ለመግለጽ ተገኝተናል ብለዋል። ክርስቶስ ትህትናን ያሳየበት የፍቅር፣ የአንድነት እና የአብሮነት በዓል በመኾኑ ይህንን የበዓሉን ሥፍራ በማጽዳት በዓሉን በጋራ በአንድነት ማክበር ይገባል ነው ያሉት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ወክለው የተገኙት አባ ወልደየስ በዓሉ የፍቅር ነው ብለዋል። ቤተክርስቲያኒቱም ይህንን ስታስተምር ኖራለች ነው ያሉት። ዋና ዓላማው መተባበርን፣ የጥላቻ እና መለያየትን ከአዕምሮ ማጽዳት ነው ብለዋል። በዓሉን ለማድመቅ እና ቦታውን ለማጽዳት የተገኙትን እና ያስተባበረውን ከተማ አሥተዳደሩንም አመሥግነዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማው ሥራ አሥኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የጥምቀት በዓል ለዘመናት ሲከበር የቆዬ ትልቅ በዓል መኾኑን ገልጸዋል። ሁሉም የኔ ብሎ የሚያከብረው በዓል መኾኑንም ተናግረዋል። ከተማ አሥተዳደሩም ጥምቀት በንጹሕ ሥፍራ፣ በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ሁሉ ማድረጉን ይቀጥላል ነው ያሉት። በዓሉ በአብሮነት እና በሰላም እንዲከበር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ዘጋቢ:- ድልነሳ መንግሥቴ የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ! 👇👇👇 https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

በኤጀንሲው የበጀት አመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት የመደበኛና የሪፎርም ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ። ጥር 09/2017 ዓ.ም በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና የጽ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት የመደበኛና የሪፎርም ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀም በየደረጃው ካሉ የዘርፉ አመራሮች ጋር በጋራ በዛሬው እለት ተገምግሟል። ለውይይት መነሻ የሆነውን ሪፖርት ያቀረቡት የኤጀንሲው የፋይናንስ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሳድቅ ሽኩር ሲሆኑ ባለፉት 6ወራት እንደ ኤጀንሲ የተከናወኑ በርካታ መደበኛ እና የሪፎርም ተግባራትን በሪፖርቱ አቅርበዋል። የውይይት መድረኩን የመሩት በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት መዲናችን ፅዱ ፣ ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ እየተከናወነ ያለው ዘርፈብዙ ተግባር የከተማዋ ነዋሪዎች የፅዳቱ ባለቤት እስኪሆን ድረስ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል። ለዚህም ለህብረተሰቡ ግንዛቤን የማስረጹን ስራ ማጎልበት እንደሚገባ አመልክተው ከዚህ ጎን ለጎንም በፅዳቱ ዘርፍ የወጡ ህግና መመሪያዎች ተግባራዊ የማድረጉ ስራም ትኩረት ሊሰጥበት እንደሚገባም አብራርተዋል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ በበኩላቸዉ በግማሽ ዓመቱ የስራ አፈፃፀም አበረታች ዉጤት እንደተመዘገበ ገልፀው በቀጣይ ቀሪ ጊዚያት በስራ አፈጻጸም ክፍተት በታየባቸዉ የስራ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል። አክለውም ዋና ዳይሬከተሩ በፅዳት ስራው ላይ የህ/ሰቡ ተሳትፎና የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ተሳትፎ ውጤታማ እንደነበር አብራርተዋል። በቀጣይ ቀሪ ጊዚያት ሞዴል ተቋማትና ብሎክ ማፍራትን፣ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ብልሹ አሰራርን መከላከልና መቆጣጠር ላይ አጠናክረን የምንሰራበት ይሆናል ብለዋል። የዉይይቱ ተሳታፊዎችም የቀረበዉን ሪፖርት መነሻ በማድረግ በመደበኛና በሪፎርም ትግበራ ሂደት ላይ እየገጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች ላይ አተኩረዉ ላቀረቡት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል። በውይይቱ ላይም በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታን ጨምሮ የከተማ ስራ አስኪያጅ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የኤጀንሲው በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ የክ/ከተማ ዋና ስራ አስኪያጆች እና እንዲሁም እስከ ወረዳ ድረስ ያለው የፅዳት አስተዳደር መዋቅር ኃላፊዎች ታድመዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በመዲናችን የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ልዩ ልዩ መዋቅሮች እና መላ ህብረተሰቡን በስፋት ማሳተፍ ዉጤታማ እንደሚያደርግ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አሰኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ!

photo content
+6

በመዲናችን የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ልዩ ልዩ መዋቅሮች እና መላ ህብረተሰቡን በስፋት ማሳተፍ ዉጤታማ እንደሚያደርግ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አሰኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ! የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመአራር ኮሚሽን የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የመደበኛና የሪፎር ም ስራዎች የ6ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ዛሬ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም ቀርቦ በየደረጃዉ ያሉ አመራሮች በተገኙበት ዉይይት ተካሂዷል። የዉይይት መድረኩን የመሩት በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት በከተማዉ የሚያጋጥሙ አደጋዎችን አስቀድሞ መከላከል ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል። ከተማዋን ከማናቸዉም አደጋ ለመጠበቅ በሚደረገዉ ጥረት የኮሚሽኑ አመራርና ሠራተኞች ለሚከፍሉት መስዋዕትነት ክብር እንደሚሰጡም አስታውቀዋል። አያይዘዉም ከተማዋን ከአደጋ ለመጠበቅ እና የኮሚሽን መ/ቤቱን ተደራሽነት ለማስፋት የከተማ አስተዳደሩን አቅምና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም አበረታች ዉጤት እንደተመዘገበ አስታዉሰዉ በቀጣይ ቀሪ ጊዚያት በስራ አፈጻጸም ዉስንነት በታየባቸዉ የስራ ዘርፎች ላይ በትጋት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። የዉይይቱ ተሳታፊዎችም የቀረበዉን ሪፖርት መነሻ በማድረግ በመደበኛና በሪፎርም ትግበራ ሂደት ላይ እየገጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች ላይ አተኩረዉ ላቀረቡት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና በኮሚሽኑ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ !

በመዲናዋ ለከተራና የጥምቀት በዓል በሁሉም የታቦታት ማደሪያ ቦታዎች የጽዳት መርሐ ግብር እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ገልጸዋል።

መጪው የጥምቀትና የከተራ በዓል ምክንያት በማድረግ በታቦታት ማደርያ ጥምቀተ ባህር ቦታ የፅዳት ንቅናቄ ተካሄደ። ጥር 09/2017 ዓ.ም የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር በመጪው ቀናት የሚከበረዉን የጥምቀትና የከተራ በዓል ምክንያት በማድረግ በልዩ ስሙ መሿለኪያ በሚገኘው የታቦታት ማደሪያ እና የባህረ ጥምቀት ቦታ ላይ የፅዳት ንቅናቄ ተካሂዷል። በፅዳት ዘመቻው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አብርሀም ታደሰ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የፀጥታ ሀይሎች እንዲሁም የክ/ከተማው ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አብርሀም ታደሰ የጥምቀት በዓል የአለም የማይዳሰስ ቅርስ፣የቱሪስት መስህብ በመሆን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዉ ከፍ ያለ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበርና በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ የሚሳተፍበት ታላቅ የአደባባይ በዓል መሆኑን አንስተው በዓሉ በሰላም እንዲከበር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ሊሰራ እንደሚገባ ገልፀው በዓሉን በአብሮነት፣ በፍቅርና በሰላም ማክበርና በክ/ከተማው በርካታ ሀብት የፈሰሰባቸውን የአረንጓዴ ልማት ስራዎች መጠበቅ እንደሚገባ ተናግረዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው የጥምቀት በዓል በአለም ቅርስነት በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበ የሀገር ኩራትና የአለም ህዝብ በዓል መሆኑን ጠቅሰው በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የመከባበር ፣ የአንድነትና የሰላም በመሆኑ በዓሉ ሲከበር ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ እንዲከበር ማድረግ እንዲሁም በክ/ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎችን መጠበቅ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል ። Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2017 ከተራና ጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ በክፍለ ከተማው በሚገኙ የታቦታት ማደሪያ ቦታዎች የጽዳት ዘመቻ አካሄደ ጥር 9/2017 ዓ.ም አስተዳደሩ የ2017 የከተራና ጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ በወረዳ 2፣በወረዳ 5፣በወረዳ 8 እና በወረዳ 11 በታቦታት ማደሪያ ቦታዎች ላይ የጽዳት ዘመቻ ዛሬ ማለዳ አካሂዷል። በክፍለ ከተማው ስር በሚገኙ የታቦት ማደሪያ በተካሄደው ፅዳት ዘመቻ ላይ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ፣የክፍለ ከተማው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ብስራት ማጆሬ ፣ የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት፣የየካ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አቶ ተራማጅ ተረፈን ጨምሮ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣የፀጥታ አካላት ፣የተለያዩ የሐይማኖቶች አባቶችና ተከታዮች እንዲሁም ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ በመርሀ ግብሩ እንደገለፁት የጥምቀት በዓል የአደባባይ በዓልና በርካታ የሀገር ውስጥና የውጪ ዜጎች የሚታደሙ በመሆኑ እሴቱንና ቱፊቱን በጠበቀ ሁኔታ ሁሉም በአብሮነት፣ በአንድነት ፣አብረን የተጋመድን በመሆናችን፣ አንዳችን ለሌላው ጥላ ከለላ ሆነን ፣ በመከባበርና በመተሳሰብ ሁሉም እንዲያከብር አሳስበው የ2017 ከተራና ጥምቀት በዓል በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መውጣት እንዳለበት አሳስበዋል። የፅዳት ዘመቻ መርሀ ግብሩ አብሮነትን በሚያሳይ መልኩ በወረዳ 2፣በወረዳ 5፣በወረዳ 8 እና በወረዳ 11 በሚገኙ የታቦታት ማደሪያ ቦታዎች ተካሂዷል። የጥምቀት በዓል በዓለም አቀፍ ደረጃ (በዩኔስኮ) የማይዳሰሱ ቅርሶች ተብለው ከተመዘገቡ በዓላት መካከል አንዱ መሆኑ ይታወቃል። Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በመዲናዋ ለከተራና የጥምቀት በዓል የሁሉም ታቦታት ማደሪያ ቦታዎች ጽዳት እየተካሄደ ነው ****************** በመዲናዋ ለከተራና የጥምቀት በዓል በሁሉም የታቦታት ማደሪያ ቦታዎች የጽዳት መርሐ ግብር እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ገልጸዋል። በጃን ሜዳም "የጥምቀት በዓል በፅዱ አዲስ አበባ" በሚል መሪ ሀሳብ የፅዳት መርሐ ግብር ተከናውኗል። በመርሐ ግብሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፣ የሁሉም ሃይማኖቶች ተወካዮች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣የአበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፤ በዓሉን ለማክበር ወደ ከተራና ጥምቀት ለሚጓዙ እግረኞችና ለተሽከርካሪዎች መንገዶችን የማስተካከል ሥራዎች መከናወናቸውንም አንስተዋል። አዲስ አበባን ውብና ፅዱ የማድረግ ሥራ ትኩረት እንደተሰጠውም ነው የገለጹት። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የፕሮጀክት መምሪያ ኃላፊ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ወልደኢየሱስ ሰይፉ፥ የጥምቀት በዓል ፍቅርንና አብሮነትን የሚያስተምር ነው ብለዋል። የጥምቀት በዓል የሚከበርበትን ስፍራ በአብሮነት በማጽዳት የተባበሩትን የሁሉንም ሃይማኖት ተወካዮችና የህብረተሰብ ክፍሎች አመስግነዋል። የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ፥ ሃይማኖታዊ በዓላት ሁሉም ህብረተሰብ አንድነቱንና ትብብሩን የሚያጠናክርባቸው መልካም እሴቶቻችን ናቸው ብለዋል። ይህም በዓላቱ ደምቀውና አምረው እንዲከበሩ በማድረግ የሀገር ገፅታ እየገነባ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል። በዛሬው ዕለትም የሁሉም ሃይማኖት ተከታዮች አንድነታቸውን ለማሳየት በጥምቀት በዓል የታቦታት ማደሪያ የፅዳት ዘመቻ ላይ በመሣተፋቸው ምስጋና አቅርበዋል።

በመዲናዋ ለከተራና የጥምቀት በዓል የሁሉም ታቦታት ማደሪያ ቦታዎች ጽዳት እየተካሄደ ነው ****************** በመዲናዋ ለከተራና የጥምቀት በዓል በሁሉም የታቦታት ማደሪያ ቦታዎች የጽዳት መርሐ ግብር እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ገልጸዋል። በጃን ሜዳም "የጥምቀት በዓል በፅዱ አዲስ አበባ" በሚል መሪ ሀሳብ የፅዳት መርሐ ግብር ተከናውኗል። በመርሐ ግብሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፣ የሁሉም ሃይማኖቶች ተወካዮች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣የአበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፤ በዓሉን ለማክበር ወደ ከተራና ጥምቀት ለሚጓዙ እግረኞችና ለተሽከርካሪዎች መንገዶችን የማስተካከል ሥራዎች መከናወናቸውንም አንስተዋል። አዲስ አበባን ውብና ፅዱ የማድረግ ሥራ ትኩረት እንደተሰጠውም ነው የገለጹት። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የፕሮጀክት መምሪያ ኃላፊ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ወልደኢየሱስ ሰይፉ፥ የጥምቀት በዓል ፍቅርንና አብሮነትን የሚያስተምር ነው ብለዋል። የጥምቀት በዓል የሚከበርበትን ስፍራ በአብሮነት በማጽዳት የተባበሩትን የሁሉንም ሃይማኖት ተወካዮችና የህብረተሰብ ክፍሎች አመስግነዋል። የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ፥ ሃይማኖታዊ በዓላት ሁሉም ህብረተሰብ አንድነቱንና ትብብሩን የሚያጠናክርባቸው መልካም እሴቶቻችን ናቸው ብለዋል። ይህም በዓላቱ ደምቀውና አምረው እንዲከበሩ በማድረግ የሀገር ገፅታ እየገነባ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል። በዛሬው ዕለትም የሁሉም ሃይማኖት ተከታዮች አንድነታቸውን ለማሳየት በጥምቀት በዓል የታቦታት ማደሪያ የፅዳት ዘመቻ ላይ በመሣተፋቸው ምስጋና አቅርበዋል።