fa
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
በመዲናዋ 716 ሺህ 318 ዜጎች የዲጅታል አገልግሎት አግኝተዋል +++++++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ |በአዲስ አበባ ከተማ ለ716 ሺህ 318 ዜጎች የዲጅታል አገልግሎት መሰጠቱን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ። ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልከተው እንደገለጹት፤ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ለ716 ሺህ 318 ዜጎች በዲጅታል አገልግሎት መስጠት ተችሏል። የዲጅታል አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነት በመሥፋፋቱ የተጨበረበሩ መረጃ አጠቃቀምና ለብልሹ አሰራር ተጋላጭነትን ከአንድ በመቶ በታች ዝቅ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። ለአንድ ነጥብ 56 ሚሊዮን የከተማዋ ነዋሪዎች የነዋሪነትና ወሳኝ ኩነት ምዝገባ አገልግሎት ተሰጥቷል ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ በፋይዳ መታወቂያ ሶስት ነጥብ አንድ ሚሊዮን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተመዘገበ ነው ብለዋል። በ2018 በጀት ዓመት በከተማዋ የፋይዳ መታወቂያ የሌለው ሰው እንዳይኖር የሚል እቅድ ተይዞ፤ ከሁለት ነጥብ 85 በላይ ነዋሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዷል ሲሉ አስታውቀዋል። በሄለን ወንድምነው #ዲጂታልመታወቂያ #ዲጂታልኢትዮጵያ #አረንጓዴዐሻራ #digitalethiopia

የ 4 ቢሊዮን ብር በጀት ወጪ የተደረገባቸዉ 22 የጤና ተቋማት ምርቃት መርሃግብር። Sagantaa eebbaa dhaabbilee fayyaa 22 baajatni birrii biliyoona 4 baasii itti ta'ee ijaarame.

በየካ ክፍለ ከተማ ተገንብተው የተጠናቀቁ የጤና ተቋማት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደረጉ! በበጀት ዓመቱ ከተጀመሩት 28 የጤና ፕሮጀክቶች 22ቱ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርጏል:: በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እንደገለፁት የህዝባችንን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሁሉም ዘርፍ በርካታ ፕሮጀክቶችን ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ የህዝባችንን ተጠቃሚ እያረጋገጥን እንገኛለን። በዛሬው ዕለትም የሚመረቁት የጤና ተቋማት ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሲሆን በጤናው ዘርፍ እምርታዊ ለውጥ ከማምጣት ባለፈ የታካሚዎችን ምቹና አስፈላጊው ግብዓት በማሟላት ወደ ስራ በማስገባት ቃልን ወደ ተግባር የቀየርንባቸው ናቸው ብለዋል። አክለውም ከተማ አስተዳደሩ የጤና መሰረተ ልማትን ለማሟላት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝና ጥራት ያለው አገልግሎት ለህብረተሰባችን ለመስጠት በበጀት ዓመቱ ከተጀመሩት 28 የጤና ፕሮጀክቶች 22ቱ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን አክለዋል። የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በበጀት ዓመቱ በመንግስት ካፒታል እና በህብረተሰብ ተሳትፎ በርካታ ፕሮጀክቶች ሰርቶ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን በመግለፅ ፕሮጀክቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ ለተባበሩ አካላትን አመስግነዋል። ለረጅም ዓመት የመልካም አስተዳደር ችግር የነበረው የየካ ወረዳ 03 G+4 ጤና ጣቢያ እና ወረዳ 12 G+4 ጤና ጣቢያ የማስፋፊያ ህንፃ ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸው የነዋሪዎችን ጥያቄ ከመመለስ ባለፍ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለህብረተሰባችን የሚሰጡ መሆኑን እና የሆስፒታሎችን ጫና የሚያቃልል መሆኑን አብራርተዋል። በመጨረሻም ከፍተኛ አመራሮቹ በየካ ቤላ ጤና ጣቢያ ቅጥር ግቢ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ከተማችንን የምንሰራት ፣ ጤናማ ትውልድ እንዲገነባ፣ እንዲረከባት እና እንዲያበለፅጋት ነው ! በ2017 በጀት ዓመት ከገነባናቸዉ 28 የጤና ፕሮጀክቶች መካከል 22 ያህሉን በዛሬው እለት አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ። በሁሉም ክፍለ ከተሞች ዛሬ አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት ያደረግናቸው የጤና ጣቢያዎች ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት ጋር እኩል ደረጃ ያላቸው ሲሆን የሚሰጡት አገልግሎት ጥራት ከፍ እንዲል ከ4 ቢልዮን በላይ ወጪ የተደረገባቸዉ በዘመናዊ የህክምና መሳሪያ ግብአት እና ባለሙያዎች ጭምር እንዲደራጁ ተደርገዋል ። እነዚህም ለከተማችን ነዋሪዎች ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ፤ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎትን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንዲሁም በቅንነት፣ በትጋት እና በታማኝነት የማገልገል ማሳያችን ናቸው። ፕሮጀክቶቹ በጥራትና በፍጥነት ተጠናቅቀው ለህዝብ አገልግሎት እንዲበቁ ያደረጋችሁ በሙሉ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም የላቀ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ Magaalaa teenya kan hojjennuuf; Dhaloonni fayya-qabeessi akka ijaaramuuf, akka fudhatuuf fi akka badhaadhomsuufi dha. Piroojektoota fayyaa 28 bara baajataa 2017 ijaarre keessaa 22 guyyaa har'aa eebbisnee tajaajilaaf banaa taasisnee jirra. Kutaalee magaalaa hundatti giddu galoonni fayyaa har'a eebbisnee tajaajilaaf banaa taasisne haala kana dura baratame irra adda ta'een tajaajila hospitaala sadarkaa tokkoffaa waliin waliqixaa kan qaban yemmuu ta'u, qulqullinni tajaajila laatanii akka ol guddatuuf Birriin biliyoona 4 ol baasii kan itti ta'e bu'aa meeshaalee yaalaa ammayyaa'ootiinii fi abbootii ogummaatiinis akka gurmaa'an taasifameera. Kunniinis gaafilee jiraattota magaalaa keenyaaf deebii kan laatan; fayyadamummaa tajaajila fayyaa haqa qabeessa kan mirkaneessan akkasumas gaarummaan, ciminaan fi amanamummaan tajaajiluu keenya kan mul'usaniidha. Piroojektoinni qulqullinaa fi saffisaan xumuramanii tajaajila uummataaf akka qaqqaban kan taasistan hundi maqaa koo fi bulchiinsa magaalaatiin galatni koo guddaan isin haa qaqqabu. Waaqni Itoophiyaa fi Uummata Ishee Haa Eebbisu

በ2017 በጀት አመት በህዝብ ዘንድ ተአማኒነትን ያተረፉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መገንባታቸውን በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ።

በአዲስ አበባ ከተማ በክረምት ወቅት የሚከሰተውን ጎርፍ በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችል የጎርፍ ማስተርፕላን አጠናቆ ተግባራዊ ስራ መጀመሩ በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዛሬው እለት ሐምሌ 18 /2017 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አመልክተዋል ።የዜናውን ዝርዝር ዘገባ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ባዘጋጀው ቀጣዩ ቪዲዮ ይከታተሉ👉👉

የአዲስ አበባ የጎርፍ ሥጋትና ጥንቃቄዎቹ

የተጠናቀቀው በጀት አመት መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ መሰረት የተጣለበት ነው አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2017(ኢዜአ)፦ በተጠናቀቀው በጀት አመት በተከናወኑ ስራዎች መዲናዋን ስማርት ሲቲ ማድረግ የሚያስችል መሰረት መጣሉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን አስመልክቶ የ2017 በጀት አመት የስራ አፈጻጸምና የ2018 ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ መግለጫ ተሰጥቷል። በመግለጫው ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት በተጠናቀቀው በጀት አመት ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል። በበጀት አመቱ የህዝብ አመኔታን ያተረፉ፣ የተሻለ አገልግሎት መስጠትና ተወዳዳሪ መሆን የሚያችሉ ተቋማት መፍጠር መቻሉን አስታውቀዋል። የህብረተሰብ ተሳትፎን በተሻለ መልክ ከማሳደግ እንዲሁም በጽዳትና ደህንነት ሞዴል አፍሪካዊ ከተማ ከማድረግ አኳያ ውጤቶች መገኘታቸውን ገልጸዋል። እንዲሁም የተሳለጠ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ማቅረብ የተቻለበት መሆኑንም አስታውቀዋል። በተጠናቀቀው በጀት አመት በተከናወኑ ስራዎች መዲናዋን ስማርት ሲቲ ማድረግ የሚያስችል መሰረት የተጣለበት ነውም ብለዋል። የመዲናዋ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ንጉሴ በበኩላቸው በበጀት አመቱ ወቅታዊ ሁነቶችን የመመዝገብ አቅም መጨመሩን አንስተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ገዛሀኝ ደሲሳ፤ ቆሻሻን ወደ ሀብት ምንጭነት ለመቀየርና የስራ ዕድል ፈጠራን ከማሳደግ አንጻር ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳዳር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሰብስቤ ሁሴን በበኩላቸው፤ ተቋሙ በአዲስ አበባ ለመንገድ መብራት መሰረተ ልማቶች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የመንገድ መብራት በመትከልና የተበላሹ ፖሎችን በመጠገን ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ለህብረተሰቡ ቅሬታ ምላሽ መሰጠቱን አንስተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ እንደገለጹት፤ ተቋሙ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራ በመስራት ለሁሉም ጥሪ ምላሽ እየሰጠ ይገኛል። ጥሪ ከተደረገ ጀምሮ የስራ እንቅስቃሴ መከታታል የሚያስችል ግልጽ አሰራር ለመፍጠር በቴክኖሎጂ የመደገፍ ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ #Ethiopia #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ

አዲስ አበባ በአመት ምን ያህል ቆሻሻ ትሰበስባለች? አዲስ አበባችን በ2017 በጀት አመት 983ሺህ 944 ቶን ቆሻሻ ሰብስባለች። ከዚህ ውስጥም 100,585 ቶን ደረቅ ቆሻሻን ወደ ሀብትነት በመቀየር ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ በዘርፉ የተሰማሩ ማህበራት ገቢ ማገኝት ችለዋል። በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ከተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር በጋራ ለሚዲያ ባለሙያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ለሚዲያ ባለሙያዎች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት የከተማዋን ፅዳት ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከ675ሺህ 684 ነዋሪዎችን በየሳምንቱ በጽዳት ንቅናቄ ስራዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። እንደዚሁም 2ሺህ 540 ተቋማትም በጽዳት ስራው ላይ መሳተፋቸውን አብራርተዋል። በዚህም ከተማዋ ንጽህናዋ የተጠበቀ እንዲሆን ከማድረግ በተጨማሪም ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት ምሳሌ ለመሆን የቻለች ከተማ መፍጠር መቻሉን ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አክለው ገልፀዋል። እንደዚሁም በጽዳት አስተዳደር ስርአታችን ወንዞቻችን ከብክለት መታደግ ችለናልም ብለዋል። ህብረተሰቡም ለጽዳት ያለው አመለካከት መሻሻሉን የተናገሩት ስራ አስኪያጁ ህዝቡ የጽዳት ባለቤት እንዲሆን ተደርጓልም ብለዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዘኻኝ ዴስሳ በበኩላቸው ወርሀ ክረምቱ ከመግባቱ ቀደም ብሎ "ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ መንስኤ ሊሆን አይገባም!" በሚል መሪቃል መላው የከተማችንን ነዋሪ ህብረተሰብ እና ተቋማትን ባሳተፈ መልኩ የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮችን፣ ቱቦዎችን ፣ የወንዝ ዳርቻዎችን እና ማን ሆሎችን ከደረቅ ቆሻሻ የፀዱ እንዲሆኑ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል። ይህም የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች በቆሻሻ ምክንያት ተዘግተው የጎርፍ መንስኤ ሲሆን የነበረውን ችግር መቅረፍ መቻሉን እና ይህ ተግባርም በሁሉም ክ/ከተሞች እስከ ብሎክ የዘለቀ የፅዳት ንቅናቄ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል። አክለውም ዋና ዳይሬክተሩ ብዙኋኑ ያፀዷትን ፅዱ ከተማ ጥቂቶች በግዴለሽነት የሚያቆሽሹትን ግለሰቦችና ተቋማትን ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት በህግ ተጠያቂ የማድረጉ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

አዲስ አበባን የአፍሪካ ሞዴል ከተማ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፦ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ **** አዲስ አበባን የአፍሪካ ሞዴል ከተማ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ። ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ተጠሪ የሆኑ አራት ተቋማት በ2017 ዓ.ም. የሰሯቸውን ሥራዎች እና የቀጣይ የትኩረት መስኮችን በተመለከተ ዛሬ በዐድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ መግለጫ ሰጥተዋል። የከተማ አስተዳድሩ ከሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ኀብረተሰቡም ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ኢ/ር ወንድሙ ሴታ ጥሪ አቅርበዋል። በመግለጫው በከተማዋ በክረምት ወቅት የሚከሰተውን ጎርፍ በዘላቂነት ለማከላከል የሚያስቸል የጎርፍ ማስወገጃ ማስተርፕላን ማስተር ፕላን አጠናቆ ተግባራዊ መደረግ በመጀመሩ ጅምር ውጤት ተገኝቷል ተብሏል። በከተማዋ ለጎርፍ እና ጎርፍ ነክ ተጋላጭ በሆኑ 247 ቦታዎች በተሰሩ 64 የጎርፍ ማስወገጃ ግንባታዎች አደጋዎችን መቀነስ እንደተቻለ ኢ/ር ወንድሙ ተናግረዋል። በከተማዋ በተሰሩ የቅድመ የጎርፍ መከላከል ዝግጅት ሥራዎች ሰሞኑን በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር መቻሉንም ነው የገለፁት። በዓመቱ 490 የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎችን ጥቆማ ከህብረተሰቡ በመቀበል 12.7 ቢሊዮን ብር ሀብት ማዳን መቻሉንም ነው ኢንጂነሩ የተናገሩት። የአዲስ አበባን የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት ለማዘመን በተሰሩ ሥራዎች ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ከ20 ሺ በላይ ለሆኑ ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም አስታውቀዋል። በከተማዋ በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ የመንገድ ዳር መብራቶች የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ የወንጀል ምጣኔን በመቀነስ ነዋሪዎች ያለምንም ስጋት በምሽት እንዲንቀሳቀሱ አስችሏል ተብሏል። በአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባን በዲጂታል ስርዓት ማከናወን በመጀመሩ ሃሰተኛ ማስረጃዎችን መቀነስ እንደተቻለ በመግለጫው ተነስቷል። ከዚህ ጋር በተያያዘ 221 ወንጀለኞች የተሳሳተ መረጃ በማቅረባቸው በሕግ እንዲጠየቁ መደረጉ ተገልጿል። በላሉ ኢታላ #ebc #ebcdotstream #addisababa #smartcity

Engineer Wondimu Seta, Addis Ababa City General Manager with the rank of Deputy Mayor, announced that a citywide public works mobilization is underway to reduce the risk of flooding during the rainy season. Addressing the press, he emphasized that the city is prioritizing early preparedness and risk mitigation, guided by data collected during the dry season. As part of these efforts, the city has already constructed 64 new flood protection structures in various vulnerable areas, in addition to the flood control works incorporated into the major riverbank development projects. These structures are designed to prevent recurrent hazards and protect both lives and infrastructure. The City Administration, working in close coordination with technical institutions and sub-city administrations, is strengthening its emergency response capabilities. This includes operational readiness, deployment of machinery, and mobilization of technical teams to deliver rapid and coordinated action in case of emergencies. Engineer Wondimu further revealed that for the first time, Addis Ababa has developed a comprehensive flood risk management master plan. This plan addresses legacy infrastructure challenges and provides a new framework for resilient urban development. It is designed to protect the city from flood hazards on a long-term basis while laying the groundwork for sustainable drainage and stormwater systems. He also announced that a legally binding riverbank buffer regulation has now entered into force. This regulation prohibits construction within a minimum of 30 meters from any riverbank, with wider buffer zones applied based on specific local conditions such as river size, surrounding topography, and zoning classifications. The regulation has been integrated into the city’s structural plan and is currently being enforced. Many of the city’s riverbanks that were once occupied by informal structures and filled with waste are now being cleared and rehabilitated. The buffer zone enforcement is critical in preventing runoff blockages, sedimentation, and flood damage—particularly in densely populated and environmentally sensitive areas. Going forward, any construction activity near riverbanks must comply with the buffer zone requirements. This is essential to safeguarding natural waterways, preventing future disasters, and ensuring ecological sustainability. Engineer Wondimu concluded by calling on residents, developers, and institutions to support the city’s efforts. He urged collective responsibility in upholding the riverbank protection regulations and fostering a culture of environmental stewardship—key to building a flood-resilient and livable Addis Ababa. For More Information https://linktr.ee/aacitymanager