1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ዛሬ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ያስገነባናቸውን 1 ሺህ 671 ያህል ቤቶች ለአገር ባለውለታዎች ፣ ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለከፋ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ እና በወንዝ ዳርቻዎች ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አስረክበናል።
የቤት ግንባታዎቹ አብሮነትን እና ጉርብትናን የሚያጠናክሩ፣ የህፃናት መጫዎችን ፣ የስፓርት ማዘዉተሪዎችን የያዙ፣ በአጠቃላይ ንፁህና ሰው ልጅ የሚገባውን የከበረ የአኗኗር ዘይቤ የሚያዳብሩ ናቸው።
ይህን በጎ ተግባር በእውቀታቸው፣ በሃብታቸው፣ በጉልበታቸው የደገፉ ልበ ቀና ባለሀብቶችን እና ያስተባበሩ አመራሮቻችንን ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አ
በአዲስ አበባ ከተማ በሚኪሊላንድ ኮንደሚንዬምና አካባቢው ከሰሞኑ ያጋጠመው የመሬት መሰንጠቅ መንስኤዎችና የከተማ አስተዳደሩ የቅድመ አደጋ ጥንቃቄ ምላሽን አስመ…
See more
ፕሬስ_ሪሊዝ 🧹🧹🧹
ዘንድሮ ለ8ኛ ጊዜ "Don' t trash fashion Rethink, Reuse,Reduce" በሚል መሪ ቃል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የአለም የፅዳት ቀን በአዲስ አበባም በነገው እለት በአይነቱ ልዩ የሆነ የጽዳት ንቅናቄ መርሀግብር በማካሄድ ይከበራል።
የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የዓለም የፅዳት ቀንን ምክንያት በማድረግ በሁሉም ክ/ከተማ እስከ ብሎክ የዘለቀ የጽዳት ንቅናቄ መርሀግብር የሚያካሂድ ሲሆን እንደ ማዕከል በተመረጠው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 15 አፍሪካ ሲዲሲ ሴንተር አካባቢ በነገው እለት ቅዳሜ መስከረም 10/2018 ዓ.ም ከማለዳው 12፡30 ጀምሮ በአይነቱ ልዩ የሆነ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በድምቀት እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡
የዓለም የፅዳት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ8ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ6ኛ ጊዜ የሚከበር መሆኑም ተገልፅዋል።
የጽዳት ንቅናቄው ዋና ዓላማም የከተማችንን ነዋሪዎች በሙሉ እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የፅዳት ስራን በህብረተሰቡ የተቀናጀ ተሳትፎ እና ባለቤትነት እንዲመራ ማስቻል እንደሆነ ተገልጽዋል፡፡
በንቅናቄው ላይም ከፍተኛ የመንግሰት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ፣ የጸጥታ አካላት፣ የጽዳት አምባሳደሮች፣ የተለያዩ አደረጃጀቶች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ነዋሪው ህብረተሰብ በታደሙበት እንደሚከናወን ተገልጽዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም አካባቢ በተከሰተው የመሬት መሰንጠቅ አደጋ ዙሪያ ጥናት ሲያደርጉ የነበሩ የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች የጥናቱ ዉጤቱን ይፋ አደረጉ
AMN- መስከረም 8/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ልዩ ስሙ ሚኪሊላንድ ኮንዶሚንየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተከሰተውን የመሬት መሰንጠቅ ተከትሎ የተከሰተዉ አደጋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦሎጂ ሳይንስ ባለሙያዎች ቡድን ጥናት አስጠንቷል፡፡
የጥናት ቡድኑም የደረሰበትን የጥናት ውጤት በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲቲዩት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ነገሰ ሞላ በአካባቢው የደረሰው የመሬት መሰንጠቅ መንስኤ ኮንዶሚኒየሞቹ ሲገነቡ የተቆፈረ ምልስ አፈር በአካባቢው መኖሩና፣ የኮንስትራክሽን ተረፈ ምርቶችም የተደፉበት ስፍራ እንደሆነ በጥናት መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡
እንደ ተመራማሪው ገለፃ፣ በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎችን ከአደጋው ለመከላከል የሚያስችሉ ጊዜያዊና ዘላቂ የመፍትሄ ሀሳቦችም በጥናቱ ተመላክተዋል፡፡
የመሬት መሰንጠቅ ከደረሰበት በቅርብ እርቀት የሚኖሩ ነዋሪዎችን ወደ ሌላ ቦታ ማዛዎር ጊዚያዊ መፍትሄ መሆኑን የጠቆሙት ከፍተኛ ተመራማሪው፣ የአካባቢውን የፍሳሽ አወጋገድ በአግባቡ ማስተካል ደግሞ ዘላቂ መፍትሄ እንደሆነ በጥናቱ መረጋገጡና ተናግረዋል፡፡
አሁን የተከሰተው የመሬት መሰንጠቅ አደጋ የበለጠ እንዳይስፋፋ አካባቢውን ከተሸከርካሪም ሆነ ከሰዎች እንቅስቃሴ መገደብ ተገቢ መሆኑንም ከፍተኛ ተመራማሪው ነገሰ ሞላ አሳስበዋል፡፡
በአስማረ መኮንን
በመዲናዋ 29 አባወራዎችን ከመኖሪያቸው እንዲነሱ ያደረገው የመሬት መንሸራተት አደጋ
**********************
በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ብርጭቆ ሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የመሬት መሰንጠቅና መንሸራተት ማጋጠሙን ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲዘዋወር ነበር፡፡
ኢቢሲ ዶትስትሪም ጉዳዩን አስመልክቶ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታን ማብራሪያ ጠይቋል፡፡
ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በማብራሪያቸውም፤ ነሀሴ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዙሪያ ባለው አስፓልት ላይ የመሬት መሰንጠቅ ምልክት አጋጥሞ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
በሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም 4 ሺህ 242 አባወራዎች የሚኖሩ ሲሆን፤ በዚህ ግቢ ውስጥ ካሉ ብዛት ያላቸው ህንፃዎች የሚወጣው የውኃ ፍሳሽ፤ የዝናብ ውኃ ታሳቢ ያላደረገ የውኃ ፍሳሽ የግንባታ ችግር እንደነበረበት ተናግረዋል።
በኮንዶሚኒየሞቹ ዙሪያ ያሉ የጎርፍ ማፍሰሻ ቱቦዎች በተለያየ ቆሻሻ የተደፈኑ በመሆናቸው ውኃው ወደ ወንዙ እንዳይሄድ እንዳደረገውም ነው ያነሱት፡፡
እነዚህ ችግሮች እንዳሉ ሆነው በሌላ በኩል ክረምቱን ተከትሎ የመጣው ከባድ ዝናብ የመሬት መንሸራተት አደጋው እንዲከሰት ማድረጉን የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢኒስቲትዩት ባደረገው ጥናት መረጋገጡን ኢንጂነር ወንድሙ ገልፀዋል፡፡
በዋናነት ሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም በሚገነባበት ወቅት ከስፍራው የሚወጣው አፈር የሚወገደው አቅራቢያው ባለ ወንዝ እንደነበረ ጠቅሰው፤ ወንዙም ከአፈር ጋር የተደባለቀ ውኃ እንዲያቁር ስለማድረጉም አመልክተዋል፡፡
ይህን ተከትሎ ከሰሞኑ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 በሚገኙ ሚኪሊላድ ትምህርት ቤት አጥር ላይ፣ እቃ ማከማቻ ጊዜያዊ መጋዘን እንዲሁም የምገባ ማዕከል ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ነው የገለጹት፡፡
በጋራ መኖሪያ ቤት ብሎክ 13 ህንጻ ላይ ጉዳት ባይከሰትም የህንጻው ዙሪያውን የመሸሽ ሁኔታ እንዳጋጠመ አክለዋል፡፡
በወረዳ 14 ባለ የእምነት ተቋም ቢሮዎች፣ በቅጥር ጊቢው ባለ መዋእለ ህጻናት የመማሪያ ክፍሎች እና መጸዳጃ ላይ ጉዳት እንዳደረሰም ጠቅሰዋል፡፡
የአደጋ ስጋት ያለባቸውን አካባቢዎች የመለየት ስራ እየሰሩ እንዳለ የገለጹት ኢንጂነር ወንድሙ፤ ብሎክ 13 ህንጻ ላይ የሚገኙ 29 አባወራዎች እና 150 ነዋሪዎችን ከስፍራው እንዲወጡ በማድረግ ቤቶቹ እንዲታሸጉ መደረጋቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በተሽከርካሪም ሆነ በሰዎች እንቅስቃሴ ምክንያት የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመከላከል ቦታውን ለእንቅስቃሴ ዝግ የማድረግ ስራ መሰራቱንም ኢንጂነር ወንድሙ ተናግረዋል፡፡
ጉዳቱ እየተባባሰ እንዳይሄድም በአካባቢው ላይ ተጨማሪ ውኃ እንዳይኖርና የመሰጠንቅ አደጋዎች እንዳይከሰቱ በቀጣይ የማቅለያ እርምጃ የሚወሰድ ስለመሆኑም ዋና ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
በሜሮን ንብረት
#ebc #ebcdotstream #AddisAbaba #landslide
በመጪው ሳምንታት በታላቅ ድምቀት የሚከበሩትን የመስቀል ደመራና የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ ክብረ በአላትን በማስመልከት በፅዱና ውብ በሆነ ቦታ እንዲከበሩ ለማስቻል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወነ ነው።
በመጪው ሳምንታት በታላቅ ድምቀት የሚከበሩትን የመስቀል ደመራና የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ ክብረ በአላትን በማስመልከት በፅዱና ውብ በሆነ ቦታ እንዲከበሩ ለማስቻል ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬከተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ ገልፀዋል።
በዓላቶቹ የሚከበሩባቸውን ስፍራዎች ከወዲሁ የማፅዳት ስራ እየተከናወነ አንደሆነ የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ በዓላቱን ምክንያት በማድረግ ህብረተሰቡ የሚያመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ እንዲይዙ ለማድረግና በከተማዋ ፅዳት ዙሪያ ህገወጥነትን ለመከላከል የሚያስችል የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰራዎች ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው የፅዳት አስተዳደር መዋቅር እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
ይህንንም ታሳቢ ያደረገ የፅዳት ንቅናቄ ስራ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ደሲሳን ጨምሮ የክ/ከተማ አመራሮች፣የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ፣የጸጥታ አካላት፣ ደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች እና የዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት በቂርቆስ ክ/ከተማ የመሰቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የሚከበሩበትን ቦታዎች በጋራ አፅደተዋል።
ይህ የፅዳት ንቅናቄ ስራም በዓሉን ምክንያት በማድረግ በቀጣይ ተከታታይ ቀናትም እንደሚከናወን ተጠቁሟል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በመጪው ሳምንታት በታላቅ ድምቀት የሚከበሩትን የመስቀል ደመራና የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ ክብረ በአላትን በማስመልከት በፅዱና ውብ በሆነ ቦታ እንዲከበሩ ለማስቻል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወነ ነው።
በመጪው ሳምንታት በታላቅ ድምቀት የሚከበሩትን የመስቀል ደመራና የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ ክብረ በአላትን በማስመልከት በፅዱና ውብ በሆነ ቦታ እንዲከበሩ ለማስቻል ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬከተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ ገልፀዋል።
በዓላቶቹ የሚከበሩባቸውን ስፍራዎች ከወዲሁ የማፅዳት ስራ እየተከናወነ አንደሆነ የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ በዓላቱን ምክንያት በማድረግ ህብረተሰቡ የሚያመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ እንዲይዙ ለማድረግና በከተማዋ ፅዳት ዙሪያ ህገወጥነትን ለመከላከል የሚያስችል የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰራዎች ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው የፅዳት አስተዳደር መዋቅር እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
ይህንንም ታሳቢ ያደረገ የፅዳት ንቅናቄ ስራ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ደሲሳን ጨምሮ የክ/ከተማ አመራሮች፣የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ፣የጸጥታ አካላት፣ ደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች እና የዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት በቂርቆስ ክ/ከተማ የመሰቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የሚከበሩበትን ቦታዎች በጋራ አፅደተዋል።
ይህ የፅዳት ንቅናቄ ስራም በዓሉን ምክንያት በማድረግ በቀጣይ ተከታታይ ቀናትም እንደሚከናወን ተጠቁሟል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በሚኪሊላንድ ኮንደሚንየምና አካባቢው ለተከሰተው የመሬት መሰንጠቅ ዘለቄታዊ መፍትሄ ለማስገኘት የከተማ አስተዳደሩ በኢትዮጵያ ጂኦሎጅካል ኢንስቲትዩት በኩል ያስጠናው ጥናትና የተገኘው ውጤት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ለሚደረገው ጥረት ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስታወቁት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲቲዩት በሚኪሊላንድ ኮንደሚንየም አካባቢ ያጋጠመውን የመሬት መሰንጠቅ አስመልከቶ ያስጠናውን የጥናት ውጤትና ግኝቱ በቀረበበት ወቅት ነው።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በኢንሲቲትዩቱ የተካሄደው ጥናት ከተማ አስተዳደር ዋነኛ ትኩረት የሆነውን የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል የቅድመ አደጋ መከላከል ስርአቱን ለማጠናከር ከፍተኛ የሆነ አቅም እንደሚፈጥርለት ገልፀዋል።
የኢንሲቲትዩቱ ባለሙያዎች ያቀረቡት ጥናት በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዚያት የመሬት መሰንጠቅ፣ መስመጥ እና መንሸራተት ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት አስቀድሞ ለመከላከልና ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችሉ ማደማደሚያዎችና የውሳኔ ሃሳብ የቀረበበት ነው።
የኢንስቲትዩቱ የጥናት ውጤት እንዳመለከተውም ከሰሞኑ የተከሰተዉ የመሬት መሰንጠቅ፣ መስመጥና መንሸራተት ዋነኛ ምክንያት በቦታዉ ላይ የተገነቡት የዉሃ ማፋሰሻ ቱቦዎች መዘጋታቸዉ፣ ተገቢ የሆነ የጎርፍ ውሀ ቅብብሎሽ መሰረተ ልማት ችግር፣ ብዛት ያለው ምልስ አፈር መኖሩና በዚሁ አፈር ላይ የመሰረተ ልማትና ሌሎች ግንባታዎች መከናወናቸው፣ በአካባቢው በውሃ ስርገት ምክንያት የተፈጠሩ የምንጭ ዉሃ መኖሩ፣ አስቀድመው የተገነቡት መንገዶች የጎርፍ ውሃ ተፋሰስና የአካባቢውን የመሬት አቀማመጥ ታሳቢ ተደርገው የተሰሩ አለመሆናቸውና እንዲሁም የመሬት አቀማመጥ ሁኔታን ያላገናዘቡ ግንባታዎች መሆናቸውን የጥናቱ ውጤቱ አመላክቷል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የጥናቱ ውጤትና ምክረ ሃሳቡ ከቀረበ በሁዋላ እንደተናገሩት በተለይም ከቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎች ጋር በተያያዘ የተዘጉ የዉሀ የመፋሰሻ ቱቦዎችን ከማፅዳትና የተዘጉትን የመክፈትና የመፋሰሻ አቅጣጫ ለአደጋ ከሚያጋልጡ ቦታዎች የማስቀየስ፣ በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራበት ያለውን የወንዞች ዳርቻ (Buffer Zone) ልማትና ጥበቃ ህግ ተግባራዊ ማድረግ እና ስለአደጋ ስጋቱ ለነዋሪዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራን እና የተቋማትን እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራን በማጠናከር ሊከናውኑ እንደሚገባ አስምረውበታል።
ለዚህም በከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት አስተባባሪነት የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን፣ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እንዲሁም የከተማው ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ እና የአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ያካተተ ግብረሐይል በአፋጣኝ እንዲቋቋም ኢንጅነር ወንድሙ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ከዚህ ጎን ለጎንም ኢንስቲትዩቱ በአጭር ጊዜ መፍትሄነት ያስቀመጣቸው የቅድመ ጥንቃቄ ተግባራት በሚመለከታቸው ተቋማት በአስቸኳይ እንዱተገበሩም አሳስበዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በሚቀጥሉት አስር ቀናት አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የክረምቱ ዝናብ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ
በሚቀጥሉት አስር ቀናት አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የክረምቱ ዝናብ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡
የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቷ አካባቢዎች መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚኖራቸው የ2017/18 ዓ.ም ትንበያ ማመላከቱን በኢንስቲትዩቱ የትንበያ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል፡፡
ይህ የተከሰተውም በተለይም ከደቡባዊ የህንድ ውቅያኖስ በመነሳት ወደ ኢትዮጵያ ሲነፍስ የነበረው እርጥበት አዘል የአየር ሁኔታ ከእለት ወደ እለት እየተስፋፋና እየተጠናከረ በመምጣቱ መሆኑንም ነው ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡
አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ 464 በሚደርሱ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ እጅግ ከባድ መጠን ያለው የዝናብ መጠን መመዝገቡንም አንስተዋል፡፡
በቀጣዮቹ አስር ቀናትም እስከ 250 ሚሊ ሜትር የሚደርስ ዝናብ እንደሚስተዋል ያነሱት አሳምነው (ዶ/ር)፤ ከዕለት ወደ እለት ወደ አርብቶ አደሩ እና ከፊል አርብቶ አደሩ የዝናብ ስርጭቱ እንደሚስፋፋ አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ተናግረዋል፡፡
በእነዚህ ቀናት አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለይም በምዕራብ ሸዋ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በሰሜን ምዕራብ እንዲሁም በአዋሽ ተፋሰስ አካባቢዎች ላይ ዝናቡ ቀጣይነት ስለሚኖረው ማህበረሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
AMN-Addis Media Network
.
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም ማለዳ ላይ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ማለዳ ላይ አንድ ሚኒባስ ታክሲ አፍንጮ በር ድልድይ ውስጥ በመግባቱ ሚኒባሱ ውስጥ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መካከል ዕድሜዋ 22 ዓመት የምትገመት ህይወቷ አልፏል።
ሌሎች 12 ሠዎች ከባድና መካከለኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ተጎጂዎች በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አምባላንሶች እየተረዱ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ።
ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጂዎች 6 ወንዶች እና 6 ሴቶች ሲሆኑ ከተጎጂ ዎቹ መካከል 12 ዓመት ታዳጊ ትገኝበታለች ።
የአደጋውን ምክንያት ፖሊስ እያጠራ መሆኑ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን Fire and Disaster Risk Management Commission አስታውቋል ።
በሌላ በኩል በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሾለ ገበያ ማዕከል ላይ ትላንት መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 5 30
በአጋጠመ የእሳት አደጋ በተወሰኑ የንግድ ሱቆች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን የእሳት አደጋውን ለመቆ ጣጠር አምስት የእሳት አደጋ ተሽካርካሪ ሁለት አምቡላንስና ሁለት ቦቴ
እንዲሁም 60 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ተሰማርተዋል ።
የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የእሳት አደጋው ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መቆጠጠር የቻሉ ሲሆን በሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል ።
።
በአደጋው በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳትና የአደጋ መንስኤ ፖሊስ እየጠራ ይገኛል።
ሾላ የገበያ ማዕከል የተገነባበት ግብዓትና የግብይት ስርዓቱ ለአደጋ የተጋለጠና በአደጋ ጊዜ የአደጋ ጊዜ ተሸከርካሪ የሚያስገባ የገበያ ስፍራ ሲሆን ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ አደጋ አገጥሟል ።
በገበያ ማዕከሉ ያሉ ነጋዴዎች ከኤሌክትሪክ አጠቃቀም እንዲዚሁም በገበያ ማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ካፍቴሪያና መሠል አገልግሎት የሚሰጡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዳያደርጉ ኮሚሽን ያሳስባል ።
ለእሳት ለሌሎች ድንገተ ኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳውቁ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
