fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ለ #ጽዱኢትዮጵያ 50 ሚሊየን ብር በአንድ ጀምበር ለማሰባሰብ የዲጂታል ቴሌቶን በዛሬው እለት ግንቦት 4 ቀን 2016 አ.ም ተጀምሯል፡፡ በንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248፣ በብሔራዊ ባንክ የዶላር አካውንት 0101211300016 እና በስዊፍት ኮድ NBETETAA የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ይቀላቀሉ። በዲጂታል ባንኪንግ ከንግድ ባንክ ወደ ንግድ ባንክ በአንድ ጊዜ 100,000 ብር በቀን 6 ጊዜ አንዲሁም ከሌላ ባንክ ወደ ንግድ ባንክ ሲላክ ደግሞ በአንድ ጊዜ 25,000 ብር በቀን 4 ጊዜ መላክ ይቻላል፡፡ ለ#ጽዱኢትዮጵያ For a #CleanEthiopia

አትሙቺ ያላት ነፍስ... በደቡብ አፍሪካ አንድ ሰው ከህንፃ ፍርስራሽ ውስጥ ከ5 ቀናት ቆይታ በኋላ በሕይወት ተርፎ ወጥቷል፤ ክስተቱም በርካቶችን አስገርሟል። ነገሩ እንዲህ ነው፤ የነፍስ አድን ሰራተኞች በህንፃ ፍርስራሹ ውስጥ በመዘዋወር ላይ ሳሉ ድምፅ ይሰማሉ። እናም ከ116 ሰዓታት ቆይታ በኋላ ዕድለኛውን ሰው ከፍርስራሹ ውስጥ ከነ ሕይወቱ አውጥተውታል። በደቡብ አፍሪካዋ ጆርጅ ከተማ በግንባታ ላይ የነበረው አፓርትመንት ህንፃ ሰኞ ዕለት በውስጡ 81 ሰራተኞችን እንደያዘ መደርመሱ ይታወሳል። እስካሁን በአደጋው 13 ሰዎች መሞታቸው ተረገጋገጠ ሲሆን፤ 29 ሰዎች በነፍስ አድን ሰራተኞች በሕወት ተገኝተዋል። ሌሎች 39 ሰዎች እስካሁን የደረሱበት ባለመታወቁ ፍለጋው እንደቀጠለ መሆኑን ከኤኤፍፒ እና ከሮይተርስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። Ethiopian Broadcasting Corporation

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ያስጀመሩት #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ለከተማችን ትልቅ አስተዋፅዖ ያለው ሲሆን መላው የከተማችን ነዋሪዎች ንፅህና የዘመናዊት ምልክት፣ ከዚያም አልፎ ክብር መሆኑን ልብ በሉ። ሜዳ ላይ መፀዳዳት ነውር በመሆኑ ይህን ለማስቀረት በተጀመረው የዲጂታል ቴሌቶን ዘመቻ ላይ እንድትሳተፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት 6:50 በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ገብርዔል ቤተክርስቲያን አጠገብ ተነስቶ የነበረዉ የእሳት አደጋ ከሌሌቱ 11ሰዓት ላይ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ዉሏል። በእሳት አደጋዉ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም በቤተክርስቲያኗም ሆነ በሰዉ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም ሲል የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ፈጥነዉ ይደዉሉ! ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የብልፅግና ስራ አስፈፃሚ አባላት የዘጠኝ ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ በጎርጎራ አካሂደናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት አስቀድሞ መከላከል አንደሚገባ ተገለፀ፡፡ በጉለሌ ከፍለ ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙና ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን የክፍለ ከተማዉ እና የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የጉለሌ ቅርንጫፍ አመራሮች ዛሬ ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓም የመስክ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ አንደተናገሩት ለአደጋ ስጋት የሆኑ ቦታዎች መለየታቸውና የተወሰኑት ምላሽ ማግኘታቸው መልካም ተግባር መሆኑን ገልፀው፤ ምላሽ ያላገኙት ቦታዎች ደግሞ በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት በፍጥነት መከላከል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለው ህብረተሰቡ የአከባቢውን ደህንነት እንዲጠብቅ ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንና ከሚመለከታቸዉ አካላት የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስበዋል። በመስክ ጉብኝቱ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑና መፍትሄ የተሰጣቸዉ እንዲሁም በሂደት ላይ ያሉ ስራዎች በአመራሮቹ ተጎብኝቷል። ለማንኛውም አደጋ በነጻ መስመር 939 ደውለው ያሳውቁ። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!

በቂርቆስ ክ/ከተማ ሳምንታዊ ከተማ አቀፍ የጽዳት ንቅናቄ ተካሄደ። የክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሰምሃል ገ/ መድህን የቂርቆስ ክ/ከተማን የአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ፈርጥ እናደርጋታለን ብለን እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ገልፀው በከተማ ውበት ስራዎች ረገድ ፊት ወጥቶ የሚታይና የሚተገበር ስራዎች መካከል አንዱና ዋነኛው ፅዳት ነው ሲሉ ተናግረዋል። በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ ጽዱ አዲስ አበባን ለመፍጠር እያንዳንዱ ሰው ከግሉ ጀምሮ የመኖሪያውንና የአካባቢውን ጽዳት መጠበቅ እንዳለበት ገልጸው ይህም በየእለቱ መተግበር ያለበትና የባህሪ ለውጥ ማምጣትን የሚጠይቅም ነው ሲሉም አስገንበዋል። ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ላይ ያሉ 37 ብሎኮች እንደ ክ/ ከተማ ሞዴል በማድረግ የከተማችንም ሞዴል ለማድረግ እየተሰራ ነው ሲሉ የገለጹት ደግሞ አቶ አብድልሃዲ ረሺድ የቂርቆስ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ ናቸው። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ለ#ጽዱኢትዮጵያ For a #CleanEthiopia #PMOEthiopia

#ፅዱ_ኢትዮጵያ_በተግባር_በፅዳት_የውበትና_ማራኪ_ገፅታ_መፍጠር_በቦሌ_ ወረዳ_12_አስተዳደር_ሸማች_ቀጠና_ፅዳት_ዘመቻ ። በቦሌ ወረዳ 12 አስተዳደር ምቹና ውብ ብሎኮችን በፅዱ ኢትዮጵያ ፕሮግራም በማካተት አጠቃላይ አመራር የብሎኩ ነዋሪዎች ባለሙያዎች በተገኙበት የፅዳት ንቅናቄ ተካሂዷል ። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

"አካባቢን ከብክለት መጠበቅ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነው!" "ብክለት ይብቃ፣ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው የአካባቢ ጥበቃ ንቅናቄ የአየር ብክለት መከላከል ወር ማስጀመሪያ በቦሌ ክፍለ ከተማ ተካሄደ። በወረዳ 14 በተካሄደው በዚህ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዲ ድሪባ ባደረጉት ንግግር የግንቦት ወር የአካባቢ ብክለት መከላከል ወር መሆኑን አውስተው፣ ኅብረተሰቡ አካባቢን ለብክለት የሚያጋልጡ ክስተቶችን አውቆ መከላከል እንዲችል የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸዋል። በከተማ ድርጅት የሚካሄደው የአካባቢ ብክለት ንቅናቄ በቦሌ ክፍለ ከተማ በይፋ መጀመሩን ያበሰሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ለንቅናቄው ግብ መሳካት ሁሉም አካላት በባለቤትነት መንፈስ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል። የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው በበኩላቸው አካባቢን ከብክለት መጠበቅ የማኅበረሰቡ የጋራ ኃላፊነት እንደሆነ ገልጸው፣ "ብክለት ይብቃ፣ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው አገር አቀፍ ንቅናቄ በኅብረተሰቡና በባለድርሻ አካላት ግብን እንዲመታ የተቀናጀ ርብርብ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በመርሐ ግብሩ ዘመናዊ የሊስትሮ መቀመጫዎች ለተደራጁ ወጣቶች ተበርክተዋል። የእግር ጉዞ እና የብስክሌት ውድድር የተደረገ ሲሆን፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት አስተባባሪነት የታደሰ የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤትም ተመርቋል። ከመርሐ ግብሩ ጎን ለጎን በክፍለ ከተማው እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶች በእንግዶች ተጎብኝተዋል። ግንቦት 3/2016 ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et