1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
እንገነባለን! እናጸዳለን !! "
የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማሳደግ በጽዳት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ የሚገኘው የተለያዩ ተረፈ ምርቶች እና የግንባታ ዕቃዎችን በማስወገድ ጽዱና ውብ ክፍለ ከተማ መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ህገ ወጥ የግንባታ ተረፈ ምርቶችን እና ግብዓቶችን ስርዓት ለማስያዝ የንቅናቄ ማስፈጸሚያ ዕቅድ ዙሪያ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።
የንቅናቄው ዋና ዓላማ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በተለያዩ ቦታዎች ተከማችቶ በክፍለ ከተማችን ጽዳት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ የሚገኘው የተለያዩ ተረፈ ምርቶች እና የግንባታ ዕቃዎችን በማጽዳት ጽዱና ውብ ክፍለ ከተማ መፍጠር መሆኑን ተገልጿል።
ውይይቱን የመሩት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማን አንዱዓለም እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው በሚገኙ 10ሩም ወረዳዎች በሚገኙ መንግስታዊ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር በክፍለ ከተማችን የጽዳት ስራዎቻችን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ተረፈ ምርቶችን በመከላከልና በመቆጣጠር ንቅናቄውን ተፈጻሚ እንዲሆን ማስቻል ነው ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ይትባረክ በበኩላቸው ከተማችን ጽዱና ውብ ለነዋሪዎቿ ተስማሚ ለማድረግ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል በመሆኑ በዘርፉ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ተግባራቶች የከተማዋን ጽዳት የተፈለገበት ደረጃ ማድረስ ባለመቻሉ የሚወጡ ከተለያዩ ቦታዎች የሚወጡ ተረፈ ምርቶችንና የግንባታ ዕቃዎችን ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ አወጋገዱን ስርዓት በማስያዝ የከተማዋን ገጽታ ማሳደግ ነው ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ሰምሃር ንጉሴ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በግንባታ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች በሚያከማቹት የግንባታ ዕቃዎች የሚያሳድሩትን አሉታዊ ተጽዕኖ ግንዛቤ በመፍጠር እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
Gullele communication-ጉለሌ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በመዲናዋ የግንባታ ተረፈ ምርት አያያዝና አወጋገድን ስርዓት የሚያሲዝ አሰራር ከነገ ጀምሮ ሊተገበር ነው
ከአዲስ አበባ ከተማ ውበትና ፅዳት ጋር የሚጣጣም የግንባታ ተረፈ ምርት አያያዝና አወጋገድን ስርዓት የሚያሲዝ አሰራር ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በተገመገመበት ወቅት በኮሪደር ልማቱ የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን በአግባቡ ማስተዳደር እንደሚገባ ገልጸው ነበር።
የግንባታ ተረፈ ምርት አያያዝና አወጋገድ በተለይም ተረፈ ምርት በተሽከርካሪ ሲጓጓዝ ስርዓት የከተማዋን ገፅታና መሰረተ ልማት በማያበላሽ መልኩ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
በከተማዋ የሕገ ወጥ የግንባታ ተረፈ ምርቶች እና ግብዓቶችን ስርዓት ለማስያዝ የተዘጋጀው ማስፈፀሚያ ዕቅድ ዙሪያ የባለድርሻ አካላት የንቅናቄ መድረክ ዛሬ ተካሂዷል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከተማ አቀፍ የልማት ስራዎች የሀገር ገፅታ እየለወጡ መሆኑን ተናግረዋል።
ከተማዋን ውብና ጽዱ ለማድረግ ከሚደረገው ጥረት ጋር የሚጣጣም ለግንባታ ተረፈ ምርቶች አያያዝና አወጋገድ ስርዓት ማበጀት እንደሚጠይቅ ገልፀዋል።
በዚህም የግንባታ ተረፈ ምርት የሚያንቀሳቅሱ የጭነት ተሽከርካሪዎች የከተማዋን ውበትና ጽዳት በማይጎዳ መልኩ እንዲከውኑ የሚያስገድድ አሰራር ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
ይህ አሰራር የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ከጉዳት ለመጠበቅ፣ የተሳለጠ እንቅስቃሴና ጤናማ ከባቢ መፍጠር እንደሚያስችል ጠቁመው፤ አሰራሩ ሳይሸራረፍ መተግበር ይገባዋል ነው ያሉት።
የከተማ አስተዳደሩ ፅዳት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙላት ተገኝ በበኩላቸው፤ ከህዝብ ቁጥር፣ ከከተማው መስፋፋትና የኢንዱስትሪ ዕድገትን ተከትሎ የቆሻሻ መጠንና አይነት እየጨመረ ነው ብለዋል።
ኤጀንሲው ቆሻሻን በወቅቱና በተደራጀ መልኩ የመሰብሰብ፣ የማስወገድና መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በግንባታ ሂደት የሚመነጩ ተረፈ ምርቶችና ግብዓት አያያዝና አወጋገድ ስርዓት የጎደለው በመሆኑ ለከተማ ውበት፣ ለእንቅስቃሴ እንዲሁም ለማህበረሰቡ የጤና ጠንቅ እንደሆነ አንስተዋል።
በመዲናዋ በ66 ወረዳዎች ሕገ ወጥ የግንባታ ተረፈ ምርት መከማቸቱን ያነሱት አቶ ሙላት፤ አዲሱ አሰራር እንዲህ ዓይነት ሕገ ወጥ የግንባታ ተረፈ ምርት አያያዝ ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስቸል መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የመዲናችን አዲስ አበባን ጽዳት በዘላቂነት ለመጠበቅ እንዲቻል የግንባታ ተረፈ ምርቶችን በተደራጀ ንቅናቄ ማስወገድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በጋራ የግንባታ ተረፈ ምርቶችን እና ግብአቶችን ስርዓት ለማስያዝ ከሚመለከታቸው ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር የዉይይት መድረክ በዛሬው እለት ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ዉብና ፅዱ ለማድረግ እንዲሁም የብልፅግና ተምሳሌትና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በከተማዋ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የግንባታ ተረፈ ምርቶች ያሉባቸዉ ቦታዎችን በመለየትና ግንዛቤ በመፍጠር የከተማዋን ፅዳት ከማስጠበቅ አንፃር ሁሉም ተቋምና ባለድርሻ አካላት በፍጥነት ወደ ተግባር መግባት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
አክለውም የፅዳት ንቅናቄዉ በትናንትናው እለት የተጀመረ ቢሆንም ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ተቋማት የተቋማቸዉን ሀላፊነት በማወቅና ወደ ተግባር በመግባት እንዲሁም የቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር በተለይም የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ የተሰማሩ ተቋማት፣አገልግሎት የማይሰጡ መኪናዎች፣ቆሻሻዎችን ለይቶ የመስጠት ፣ስታንዳርድ ያልጠበቁ የማስታወቂያ የመለጠፍ፣የከተማዉን ፅዳት ከማቆሸሽ አንፃር ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር በሁሉም ተቋማት በኩል መደረግ ስላለበት የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ አክለውም ፅዳት በሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ባህል እንዲሆን ሰፊ እና ተከታታይነት ያለው ስራ መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በዚሁ መድረክ ከአዲስ አበባ ደንብ ማስከበርና ቁጥጥር ባለስልጣን አቶ ገዛኸኝ የከተማዋ የፅዳት እንቅስቃሴዎች በይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሁሉም ተቋማት ሃላፊነት እንደሆነ ጠቅሰው በተለያዩ የከተማዋ ቦታዎች የሚስተዋሉትን የግንባታ ተረፈ ምርቶችን ባለቤቶች እንዲያስነሱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ከመስራት ባሻገር ተግባራዊ በማያደርጉ አካላት ግን ህጉን ታሳቢ ያደረገ ቅጣት ተግባራዊ እንደሚደረግ አመልክተዋል።
ህዳር 23 ቀን 2017 አ.ም
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የሳር ቤት-ላፍቶ-ፉሪ የኮሪደር ልማት
ከሳር ቤት፣ ላፍቶ አደባባይ እስከ ፉሪ አደባባይ የሚካሄደው የኮሪደር ልማት ሥራ በፍጥነት እየተከናወነ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ…
See more
ከመካኒሳ እስከ ፉሪ ሀና በመገንባት ላይ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት የስራ ሂደት ገምግመናል።
18 ኪ.ሜ የሚሸፍነው ይህ የኮሪደር ልማት ስራ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለል የመንገድ ደረጃውን ማሻሻል፣ የአረንጓዴ ልማት፣ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች፣ የህጻናት መጫዎቻዎች፣ ሰፊ የእግረኛ መንገድ፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የታክሲና አውቶቡስ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናሎች እንዲሁም ለረዥም ጊዜ ግንባታቸዉ ሳይጠናቀቅ የቆዩ ህንጻዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ወደ አገልግሎት የማስገባት እና ነባር ህንፃዎችን የማደስ ስራዎችን ያካተተ ነዉ።
በከተማ ደረጃ ከጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራ በተጨማሪ የንፋስስልክ ላፍቶ ክፍለከተማም ማህበረሰቡን በማስተባበር ተጨማሪ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም በአቃቂ ቃሊቲ ከተጀመረው ጋር የሚገጥም ይሆናል።
በዛሬው ጉብኝታችን አንዳንድ ቅሬታ የቀረበባቸዉ ጉዳዮችን በቦታዉ በመገኘት ከባለ ጉዳዩቹ ጋር ተመካክረን የፈታን ሲሆን፣ ስራው በፍጥነት እና በጥራት እንዲከናወን ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም እየደገፋችሁ ያላችሁ ማህበረታትን እና የአካባቢውን ነዋሪዎች በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
