fa
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የጥንቃቄ መልእክት ድንገት የመሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰት ምን ያደርጋሉ? ****** ከአስፈሪ የተፈጥሮ ክስተቶች ውስጥ አንዱ ርዕደ መሬት ነው፡፡ በእርግጥ በመሬት ከመከዳት በላይ ምን ሊያስፈራ ይችላል፡፡ ዓለማችን በርዕደ መሬት መለኪያ የተለያየ መጠን ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጦችን በየጊዜው ታስተናግዳለች፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ ባለንበት ሥፍራ ቢከሰት ድንጋጤን ውጦ እኚህን ነገሮች ለማድረግ መሞከር የራስንም ሆነ የወዳጅን ህይወት ለመታደግ ያግዛል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ የሚሰጥ አደጋ ባለመሆኑ እራስን ለማዳን ከቦታ ቦታ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ባሉበት ቦታ ከታች ያሉትን የአደጋ መከላከያ ነጥቦች ይተግብሩ፡፡ • የመሬት መንቀጥቀጡ እንደተሰማዎ አንገትዎን በሁለት እጅዎ አጥብቀው በመያዝ በጉልበትዎ ይንበርከኩ • በቀላሉ የማይንቀሳቀሱ ጠንካራ ነገሮችን አጥብቀው ይያዙ • እንደ ጠረጴዛ ያሉ ከላይ መከለያ ያላቸው ዕቃዎች ሥር መግባት በሚወድቅ ዕቃ ሊደርስ የሚችልን ጉዳት ይቀንሳል፡፡ - የሚይዙት ዕቃ እንዳይንቀሳቀስ ከጠንካራ ነገር ጋር በደምብ ያስጠጉት (ለምሳሌ ከቤት ምሰሶ ጋር) • እንደ መስታውት ያሉ በቀላሉ ረግፈው ጉዳት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ነገሮች ይራቁ • ቤት ውስጥ ከሆኑ ሲሊንደር ጋዝ፣ የተለኮሰ ሻማ አሊያም ሌላ እሳት ሊፈጥር የሚችል ነገር ካለ ያጥፉ • አሳንሰር ከመጠቀም ይቆጠቡ • ወጪ ከሆኑ ኤሌክትሪክ የተሸከሙ ፖሎች፣ ዛፎች አሊያም ሌሎች የተተከሉ ነገሮች እንዳይወድቁብዎ መራቅ እና በተቻለ መጠን ሜዳማ በሆነ ግልጽ ቦታ ላይ መገኘት እራስን ከአደጋው ለመጠበቅ ያግዛሉ፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ትናንት ምሽት በአፉር ክልል ባራህሌ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ደርሷል። በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የክልባቲ ራሱ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ከትናንት ጀምሮ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ አጋጥሞታል። በክልባቲ ራሱ ዞን የበራህሌ ወራዳ አስተዳዳሪ አቶ አሊ ሁሴን ለኤኤምኤን እንዳሉት በመሬት መንቀጥቀጡ አንድ የ12 አመት ህጻን ሲሞት ሌሎች 6 ሰዎች ቆስለዋል ብለዋል። በአደጋዉ በተለይ በቡሬ እና አስ ጉቢ አላ ቀበሌዎች በንብረትና በሰው ላይ ጉዳት ማድረሱንም ተናግረዋል። ተጎጂዎቹ ወደ ጤና ተቋማት እየተወሰዱ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል። ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም AMN-Addis Media Network ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ባለስልጣኑ አደገኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ 2 ድርጅቶች የ600 ሺህ ብር መቅጣቱ አስታወቀ በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አደገኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ 2 ድርጅቶች እያንዳንዳቸው 300 ሺህ ብር በድምሩ 600 ሺህ ብር መቅጣቱ አስታወቀ ። ድርጅቶቹ ሮያል ከረሚላ ፋብሪካ እና ዲኤም ሲ ሪል እስቴት ሲሆኑ ባልተገባ መንገድ ከፋብሪካ አደገኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ሲለቁ በመገኘታቸው ቅጣቱ ተላልፎባቸዋል ። በክፍለ ከተማው የኮሪደር ልማት እየለማ በሚገኝበት ጀሞ ወረዳ ፣ለቡ ወረዳ እንዲሁም ወረዳ 12 መዳረሻውን ያደረገው በተለምዶ አርሴማ ወንዝ አካባቢ የተለቀቀ አደገኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ፈሳሽ መሆኑ ተመላክቷል ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለትን ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት ተቀጥተዋል ። ባለስልጣኑ አሁን ላይ በወንዞች ዳርቻ ልማት መርሃ ግብር መሰረት የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማት ለከተማዎ ነዋሪዎች ምቹና ሳቢ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል ፡፡ A.A City Administration Code Enforcement Authority ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

አዲስ ገጽ

አዲስን እንደ ስሟ ዉብና ለነዋሪዎቿ ምቹ የማድረግ ምዕራፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል ! Finfinnee akkuma maqaashee miidhagduu fi jiraattota isheef mijattuu boqonnaan taasisuu cimee itti fufera. !

አዲስ ገጽ’ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፌዴራል እና ክልል አመራሮች ጋር የገጠር ኮሪደር ስራዎች ላይ ያደረጉት አጭር ውይይት ዛሬ ምሽት 2:30 ይጠብቁ። #PMOEthiopia

"ድንገተኛ አደጋዎችን አስቀድሞ በመከላከል ህይወትና ንብረት ከአስከፊ ጉዳቶች እንከላከል!" የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኪሽን ጽ/ቤት ከክከተማዉ ስራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ድንገተኛ አደጋን አስቀድሞ በመከላከል ህይወትና ንብረት ከአስከፊ ጉዳቶች ለመታደግ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ የፓናል ውይይት መድረክ አካሄዷል። በፓናል ውይይቱ የክ/ከተማው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ንጋቱ፣ የክ/ከተማዉ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማናዬ ጫኔ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ስጋት ቅነሳና ትግበራ ጥናት ዋና ዳሬክተር አቶ ዴሲሳ ጦናን ጨምሮ በጎ ፍቃደኞችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የአደጋ ደህንነት የሙያ ምክር ቴክኒክ ድጋፍና የክትትል ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት በአቶ እንዳለ ከተማ ለፓናል ውይይት መነሻ የሆነውን ሰነድ በስፋት የቀረበ ሲሆን፤ የእሳት፣ የትራፊክ፤ የጎርፍ አደጋ የስጋት የሆኑ ቦታዎች በጥናት እንደተለዩ፣ የቅድመ መከላከል፣ ድንገተኛ አደጋዎችን መቆጣጠር፣ የቅድመ ሆስፒታል ህክምናና የአንቡላስ አገልግሎቶችና ስልጠና አገልግሎት እንደሚሰጥ አመላክተዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማናዬ ጫኔ ድንገተኛ አደጋዎችን አስቀድሞ መከላከል ዋና ትኩረት እንደሆነ ጠቁመው፣ ህብረተሰቡ አደጋን በመከላከል የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበት፣ ግንዛቤ መፍጠር፣ አደጋ መቀነስና መከላከል እንደሆነ፣ አደጋ ለመከላከል ሌላውን አካል ከመጠበቅ ከእኔ ምን ይጠበቃል በሚል ስሜት የዜግነት ሀላፊነትን መወጣት እንደሚገባ ገልጸዋል ። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ንጋቱ በአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራዎች ውድና መተኪያ የሌለውን የሰው ህይወትን እና ንብረት ከድንገተኛ አደጋ በቅድሚያ ለመከላከል ታስቦ መሆኑን ጠቁመው፣ ድንገተኛ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት ህብረተሰቡን ማስገንዘብ እንደሚገባ፣ የእሳት፣ የጎርፍ፣ የትራፊክ፣ ሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ በቅንጅት መቀነስ እንደሚጠበቅ፣ ለሌሎችን ማስገንዘብ የሁሉም ሰው ኃላፊነት መለሆኑን መልዕክት አስተላልፈዋል። በመጨረሻም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ስጋት ቅነሳና ትግበራ ጥናት ዘርፍ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ዴሲሳ ጦና በአደጋ መከላከልና ቅነሳ ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት መስራት ትልቅ አቅም እንደሆነ ገልፀው፣ የአደጋ ሰጋት ቦታዎችን በመለየት በርካታ መፍትሔ እርምጃ እንየተወሰደና በአቃቂ ወንዝ ዙሪያ በተሰራው የመከላከል ስራ ህብረተሰቡን ጎርፍ አደጋ መታደግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡ Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት የመስከረም ወር የስራ እንቅስቃሴን ያካተተውን የዜና መፅሄት በቀጣዩ ሊንክ በቴሌግራም ገፃችን ይከታተሉ። https://t.me/aacitymanager/23858 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በየሳምንቱ ቅዳሜ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚከናወነው ከተማ አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሏል። የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በየሳምንቱ ቅዳሜ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚያከናውነው ብሎክን መሠረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች ያካሄደ ሲሆን እንደ ማዕከል በተመረጠው በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 አካባቢ አካሂዷል። በጉለሌ ክ/ከተማ በተካሄደው የፅዳት ንቅናቄ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አሰተዳደር ኤጀንሲ ዋና አማካሪ ወ/ሮ ሀዳስ ኪዱ እንዳሉት ወርሀ ክረምቱን አስመልክት "ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ መንኤ ሊሆን አይገባም!" በሚል መሪ ቃል መጠነ ሰፊ የፅዳተት ንቅናቄ መካሄዱን ጠቁመው ይህም ለጎርፍ ተጋላጭ የነበሩ አካባቢዎችን መታደግ መቻሉን ገልፀዋል በየሳምንቱ በሚካሄዱ የፅዳት ንቅናቄ ስራዎች ብቻ የአካባቢ ፅዳት አይጠበቅም ያሉት ወ/ሮ ሀዳስ ፅዳትን ባህል አድርጎ የአካባቢን ፅዳት ማስጠበቅ ላይ የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል የጉለሌ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መሠለ አያሌው በበኩላቸው በበኩላቸው በክ/ከተማቸው ላይ በተሰሩ የፅዳት፣ የውበት እና አረንጓዴ ስራዎች ምክንያት በርካታ ሞዴል ብሎኮች መፍጠር መቻላቸውን ጠቁመው የተፈጠሩ ሞዴል ብሎኮች ዳግም የአካባቢን ገፅታ እንዳያባላሹ ለነዋሪው ህብረተሰብ በባለቤትነት እንዲጠብቁ የማስተላለፍ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም አብራርተዋል። በፅዳት ንቅናቄው ላይም አመራሮችን ጨምሮ የፅዳት አምባሳደሮች፣ አርቲስቶች፣ የፀጥታ አካላት፣ የተለያዩ አደረጃጀቶችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፎ አድርጓል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የመልሶ ግንባታ ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት ዛሬ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ስራ ለማከናወን ሲባል በአዲስ አበባ እና ሸገር ሲቲ ሀይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች 👉ከጠዋቱ 4፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 አምባሳደር አካባቢ፣ ሸራተን ፣ የውጭ ጉዳይ ፣ ታችኛው ቤ/መንግስት፣ ባሻወልዴ ኮንዶሚኒየም ፣ ቱሪስት ጀርባ ኮንዶሚኒየም 👉 ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት ቻይና ቱቦ፣ ቆሼ ፊጽለፊጽ፣ ረጲ መድሃኒዓለም ቤ/ክ፣ ፋና ሬዲዮ፣አየር ጤና ፣ ሳሚ ካፈ ጀርባ ፣ ታቦት ማደሪያ፣ መሐንዲስ ሰፈር፣ ፈመ ሬሲዮ፣ ቴሌ፣ ስልጤ ሰፈር መውጫ፣ ፋኑኤል ቤ/ክ፣ አጃንባ ኮንዶሚኒየም፣ አየር ጤና ፣ናትራን ፣ ለማ ነገዎ ሰፈር፣ ሞቢል ጋዝ፣ ካራ መድህንዓለም መውጫ፣ ኢንዱስትሪ መንደር ፣ አየር ጤና ት/ቤት ፣አየር ጤና መስጊድ፣ ኪዳነምህረት ቤ/ክ፣ 👉 ከ2፡30 እስከ 9፡30 ሰሚት ኮንዶሚኒየም ሙሉውን፣ አራብሳ ኢንዱስት መንደር እና አካባቢያቸው ላይ የኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ Ethiopian Electric Utility -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል። አገልግሎቱ በጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቹ የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁም በትህትና እንጠይቃለን ሲል መልእክቱን አስተላልፏል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የመዲናችን የስማርት ሲቲ ግንባታና ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን በተጀመረው መንገድ ለማስቀጠል አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ዘላቂነትን የማረጋገጥ ጉዳይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩበት እንደሚገባ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስገነዘቡት በዛሬው እለት በመዲናችን የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት መሠረተ ልማት አስተማማኝነትና ጥበቃ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል፣ ከከንቲባ ጽ/ ቤት፣ ከአዲስአበባ ከተማ ፕላን ቢሮና ከግንባታና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ ነው። ኢንጅነር ወንድሙ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት በሁሉም መስክ በፈጣን የእድገት ግስጋሴ ላይ የምትገኘው መዲናችን አዲስ አበባ የተዋጣለት የስማርት ሲቲ ግንባታ ሂደት ላይ እንደመሆኗ ይህንኑ የሚመጥን ስማርት የመሠረተ ልማት ዝርጋታና ዘመናዊ የአስተዳደር ሰርአት ተግባራዊነትን ማጠናከር ስለሚያስፈልግ ተቋማት በዚህ ረገድ ቅንጅታዊ አሰራርን በይበልጥ ሊያጠናክሩ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የስራ ሃላፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ ነባር የኤሌክትሪክ ሀይል መሠረተ ልማት የነባር መስረተ ልማት ሁኔታ፣ ደረጃ የማሻሻልና ተጨማሪ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ዝርጋታ ስራዎች፣ አዳዲስ ግንባታ፣ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ ባቀረቡት ሰነድ ላይ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች መሠረተ ልማቶችን ለአደጋ የሚያጋልጡ ግንባታዎችና ጥብቅ ቦታዎች ማስከበር እና መሠል ችግሮች እየፈጠሩት ያለውን ጫናና ተግዳሮት አቅርበዋል። ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የተወከሉ የስራ ሃላፊዎች የከተማ አስተዳደሩ የተቋማት ቅንጅትን በማጠናከር በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት አስተማማኝነትና እንዲሁም በመሠረተ ልማት ጥበቃና ማስፋፋት ላይ ተግዳሮት የሆነውን ችግር በአፋጣኝ ለመፍታት የሚመለከታቸው ተቋማት ቅንጅታዊ የአሰራር ስርአት መዘርጋቱንም አድንቀዋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አክለውም የአፍሪካ ህብረትና የአለም የዲፕሎማሲ ማእከል፣ ከፍተኛ የቱሪዝምና ኢንቨስትመን ስበት ማእከል በሆነችው መዲናችን አዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ሃይል መሠረተ ልማቷን አደጋ ላይ የሚጥሉ ማንኛውንም አይነት ጉዳቶችና ተግዳሮቶች የመሠረተ ልማት አቅራቢ ተቋማትና የሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት በአፋጣኝ የመፍትሄ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል። ይህንኑ የመሠረተ ልማት ጥበቃ ለማጠናከርና ተግባሩን በአፋጣኝ እንዲፈፀምም በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አስተባባሪነት፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይልና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከፕላን ቢሮ፣ ከመሬት ልማት ቢሮ፣ ከአካቢ ጥበቃ፣ ከግንባታ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣንን ጨምሮ ሌሎች የመሠረተ ልማት ቅንጅት ተቋማት የተካተቱበት ግብረ ሐይል ተቋቁሟል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡- ቴክኖሎጂ መር አዘማኝነት ላይ የሚያተኩረው የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ በስኬት መጠናቀቅን ተከትሎ አሁን በበለጠ የማሽን ግብዓት (አቶሜሽን) በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጥን የሚያጠናክረውን ዲጂታል 2030ን አስጀምረናል። የፍትኅ ተደራሽነት ለዜጎች እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ መሆኑን እውቅና በመሥጠትም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፈጣን፣ ግልጽ እና ውጤታማ የሆነ ሥርዓት ለመገንባት በጽናት እየሠራ ይገኛል። ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት የፍርድ ሂደቶች በአግባቡ መቀዳታቸውን ለማረጋገጥ ድምጽን ወደ ጽሁፍ የሚቀይር ብሎም በአስተማማኝ ሁኔታ ተጠብቀው የሚቆዩበትን ስማርት የፍርድ ሥርዓት አልምቶ በመመልከቴ ደስታ ተሰምቶኛል። ሥርዓቱ ፍትኅ ፈላጊዎች ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው በአካል በችሎት መገኘት ሳይጠበቅባቸው ካሉበት ሆነው ጉዳያቸውን ለመከታተል ያስችላቸዋል። በተጨማሪም የለሙት የNetwork Operation Center እና Integrated Case Management System የፍርድ ሂደት ባለጉዳዮች በዲጂታል አውታሮች ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ያስችላሉ። በአሁኑ ወቅት 24 የፌደራል ቅርንጫፎች በሥርዓቱ የተሸፈኑ መሆኑ አበረታች ሲሆን በቅርቡ ወደ ክልሎችም እንደሚስፋፋ ተስፋ አለን።