fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ ያደረሰውን ጉዳት ተመለከቱ

photo content
+2

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ ያደረሰውን ጉዳት ተመለከቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ያደረሰውን ጉዳት በስፍራው ተገኝተው ተመልክተዋል። የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የእሳት ቃጠሎ የደረሰበትን ሕንፃ ግማሽ አካልን ከአደጋው ማትረፍ ተችሏል። የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና የፀጥታ አካላት በተቀናጀ መንገድ አደጋውን ለመቆጣጠር እና አደጋው እንዳይዛመት ያደረጉት የተቀናጀ ርብርብ የሚመሰገን መሆኑንም ገልጸዋል። የከተማ አስተዳደሩ በተከሰተው የእሳት አደጋ የንብረት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በትኩረት እንደሚሠራም አቶ ሞገስ ገልጸዋል። AMN

ትናንትና ምሽት በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር እንዲውል ከፍተኛ እገዛና አስተዋጽኦ ላደረጉ የፌዴራል እና የክልል ተቋማት በም/ከንቲባ ማእረግ የከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ምስጋና አቀረቡ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በትናንትናው እለት ጥቅምት 11 ምሽት የተከሰተውን የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር በማዋሉ ሂደት የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ የጸጥታ አካላት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን፣የአዳማ ከተማ እና የሞጆ ከተማ አስተዳደር ላደረጉት እገዛና ከፍተኛ አስተዋጽኦ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል። በተለይም የመዲናችን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የሰዎችን ህይወት ከአደጋ ለመታደግና በንብረትም ላይ ጉዳት እንዳይደርስ በከፍተኛ የሙያ መስጠት እና ቁርጠኝነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ክብር ይገባችሁዋል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ኢንጅነር ወንድሙ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና በየደረጃው ያሉ የፌዴራል መንግስት አመራሮች እንዲሁም የከተማችን ነዋሪዎች የእሳት አደጋው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር እንዲውል ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይ መሠል አደጋዎች እንዳይከሰቱ የቅድመ አደጋ መከላከል ስርአቱን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያግዙ ስራዎች ላይ በከፍተኛ ትኩረት ልንሰራ ይገባል ሲሉም በአጽንኦት አስገንዝበዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል:: የ እሳት አደጋዉን በቁጥጥር ስር በማዋል ርብርብ ያደረጋችሁ ፤ በርካታ ሎጀስክ በማቅረብ የደገፋችሁን እና ከዚህ በላይ ሊደርስ የነበረዉን ጉዳት የቀነሳችሁ አካላትን በሙሉ በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ:: በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ያሳዝናል ፤ መንስኤዉን በማጣራት የምናሳዉቅ ሲሆን ህብረተሰቡ ሁሌም መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እዲያደርግ አደራ እላለሁ። Markaatoo naannawa shaamaa taraatti balaan ibiddaa ka'ee ture guutumaan guututti too'annoo jalaa ooleera. Ibiddicha too'annoo jala oolchuuf hirmaannaa kan taasistan,loojistikii baay'ee dhiheessitanii kan nu deeggartan fi miidhaa kanaa ol qaqqabuu danda'u qaamolee hir'istan hundaa maqaa koo fi bulchiinsa magaalaatiin isin galateeffachuun barbaada. Miidhaa qabeenya irra gahee gaddisiisaadha. Ka'uumsa balichaa qorachuun kan beeksisnu yennaa ta'u,hawwasni balaa walfakkaataan akka hin uumamneef of-eeggannoo barbaachisaa akka taasisu amaanaa jedha.

44775209_548863247753894_5710473467826748147_n.mp4.crdownload9.44 MB

አካባቢው አስቸጋሪ በመሆኑ ጊዜ ቢወስድም እሳቱ በቁጥጥር ስር ውሏል- ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው ማምሻውን በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ ሸማ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው ገልጸዋል፡፡ እሳቱን ለመቆጣጠር የኮሚሽኑ ሰራተኞችና አመራሮች፣ የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ያደረጉት ርብርብ ከፍተኛ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ አደጋው የደረሰበት አካባቢ አስቸጋሪ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ጊዜ ወስዶብናል ያሉት ኮሚሽነሩ አሁን በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል፡፡ አካባቢው አስቸጋሪ በመሆኑ ከፍተኛ ርብርብ ባይደረግ የከፋ ጉዳት ያደርስ እንደነበር አንስተዋል፡፡ ለዚህም ህብረተሰቡን እና የሚመለከታቸውን አካላት አመስግነዋል፡፡ AMN-Addis Media Network ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ ነው ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር

በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ በተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት እጅግ አዝነናል። የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ከእሳት አደጋ እና ስጋት መከላከል እንዲሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ርብርብ እየተደረገ ሲሆን አደጋውን ቶሎ ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለዉን ጥረት አዳጋች ያደረገዉ የአካባቢው መንገድ የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት በሄሊኮፕተር ለመጠቀም እየጣርን ነው። ይህንን አደጋ ለመቀነስ ርብርብ እያደረጋችሁ ያላችሁ አካላት ሁላ ጥረታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ አሳስባለሁ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአዲስ መልክ በግሩም ሁኔታ የታደሰውን የአፍሪካ አዳራሽ ለመመረቅ በመብቃታችን አፍሪካዉያን ሁሉ እንኳን ደስ አለን። ህንፃዎች፣ ግድግዳዎች እና ኮሪደሮች መናገር ቢችሉ በአፍሪካ ለዘመናት የተገኙ ድሎችን እና ፈተናዎችን ያስተጋቡ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በዛሬው እለት ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ማምሻዉን በመርካቶ ሸማተራ አየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በንግድ ሱቆች ላይ የተነሳዉን የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ለማዋል የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችና ባለድርሻ አካላት ርብርብ እያደረጉ ነዉ። የአደጋው መከሰት ጥሪ ለኮሚሽኑ እንደደረሰ የእሳት አደጋው ሰፋ ያለ ስለነበረ ሁሉም የቅርንጫፍ ጣቢያዎች የአደጋ መቆጣጠር ማሽነሪዎች፣ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና አንቡላንሶች በቦታው ላይ እንዲሰማሩ እና እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እንዲያደርጉ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!

ተቋርጦ የቆየው የኃይል አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ተመልሷል ******************* በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት በትላንትናው ዕለት የኃይል አቅርቦቱ ያልተመለሰላቸው የለገጣፎ ከተማ፣ 44 እና ኢንዱስትሪ መንደር እንዲሁም አባዶ ኮንድምኒየም አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ የኃይል አቅርቦቱ ተመልሶላቸዋል፡፡ ስለሆነም የጥገና ስራው ሙሉ በሙለ ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት ለጠበቃችሁ ሁሉ ምስጋናችንን እናቀርባለን ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጿል። #የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት