1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
በምግብ ዋስትና ሴፍቲኔት ፕሮግራም የስራ እድል አግኝተው ሲሰሩ የነበሩ ከተረጂነት ወደ አምራችነት የተሸጋገሩ 31ሺ 2 የከተማችንን ነዋሪዎች አስመርቀናል።
የከተማችን ነዋሪዎች ሰርቶ በመለወጥ፣ በትጋት፣ የተገኘውን እድል ወደ ድል በመቀየር፣ ኑሯቸውን በማሻሻል እና ከተረጂነት በመላቀቅ አምራች ዜጋ እና ተወዳዳሪ በመሆን ከራሳችሁ አልፋችሁ ለሌሎች ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ተተኪ የሌለው ሚናችሁን እንድትወጡ ጥሪ አቀርባለሁ።
ከተረጂነት ወደ አምራችነት የተሸጋገራችሁ ነዋሪዎቻችን ኑሯችሁን በራሳችሁ አቅም በዘላቂነት ለመምራት በመቻላችሁ እና ለምረቃ በመብቃታችህ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፣ ከጥር 1 ጀምሮ በመንግስት በጀት 154 ሺሕ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የምናደርግ ሲሆን ማህበራዊ ፍትህን በማረጋገጥ ለብዙ ዘመን አንገት ያስደፋንን እና ለተረጂነት የዳረገንን ድህነትን በማሸነፍ በልተን ማደር ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋጥ በትጋት የምንሰራ ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በምግብ ዋስትና ሴፍቲኔት ፕሮግራም የስራ እድል አግኝተው ሲሰሩ የነበሩ ከተረጂነት ወደ አምራችነት የተሸጋገሩ 31ሺ 2 የከተማችንን ነዋሪዎች አስመርቀናል።
የከተማችን ነዋሪዎች ሰርቶ በመለወጥ፣ በትጋት፣ የተገኘውን እድል ወደ ድል በመቀየር፣ ኑሯቸውን በማሻሻል እና ከተረጂነት በመላቀቅ አምራች ዜጋ እና ተወዳዳሪ በመሆን ከራሳችሁ አልፋችሁ ለሌሎች ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ተተኪ የሌለው ሚናችሁን እንድትወጡ ጥሪ አቀርባለሁ።
ከተረጂነት ወደ አምራችነት የተሸጋገራችሁ ነዋሪዎቻችን ኑሯችሁን በራሳችሁ አቅም በዘላቂነት ለመምራት በመቻላችሁ እና ለምረቃ በመብቃታችህ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፣ ከጥር 1 ጀምሮ በመንግስት በጀት 154 ሺሕ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የምናደርግ ሲሆን ማህበራዊ ፍትህን በማረጋገጥ ለብዙ ዘመን አንገት ያስደፋንን እና ለተረጂነት የዳረገንን ድህነትን በማሸነፍ በልተን ማደር ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋጥ በትጋት የምንሰራ ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ከመሬት ንዝረት/መንቀጥቀጥ ክስተት ጋር ተያይዞ ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች፣
የመሬት ንዝረት ከመከሰቱ በፊት
• አደጋው ሲከሰት በህንፃዎች/ክፍሎች ውስጥ የት ቦታ መቆየት እንደሚቻል ማወቅና መዘጋጀት
• በአደጋ ወቅት ከጣራ ከሚወድቁ ቁሳቁሶች በቀላሉ የማይሰበሩ መከላከያዎችን (ጠረጴዛ፣ ዴስክ፣ ግድግዳ፣ ወዘተ) ማዘጋጀት
• በቤት/ህንፃ ውስጥ ከሆነ በአደጋው ምክንያት የሚረግፉና ጉዳት የሚያደርሱ ቁሳቁሶችን (መስኮችን፣ መስታወቶችን፣ ተንጠልጣይ ዕቃዎችን፣ ወዘት) ማወቅና ከእነሱ መራቅ
• የነዳጅ፣ የጋዝ፣ የውሃ፣ የኤሌክትሪክ መስመሮች እንዴት ቶሎ እንደሚዘጉ እና እንደሚቋረጥ አስቀድሞ መለማመድ
• በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት የሚወድቁና ጉዳት የሚያደርሱ ትላልቅ ዕቃዎችን መለየት አስቀድሞ ማስወገድ
• ሊቀጣጠሉ ወይም አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ፈሳሾችና ኬሚካሎች ዝቅ ባሉ ካቢኔቶች/ሼልፎች ውስጥ ማስቀመጥ
• በአስቸኳይ ጊዜ የሚያስፈልጉ ምግብ፣ ውሃ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን (የእሳት ማጥፊያ፣ መብራት፣ ሬዲዮ፣ መድሐኒት፣ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ፣ አልባሳት) መለየትና ማዘጋጀት
• በአስቸኳይ ጊዜ የሚያስፈልጉ የስልክ ቁጥሮችን ዝርዝር መያዝ
• በአደጋው ምክንያት የሚበተነው ቤተሰብ እንዴትና የት ቦታ እንደሚገናኝ አስቀድሞ መወሰን
በመሬት ንዝረት ክስተት ወቅት
• በሀንፃ/ቤት ውስጥ ከሆነ
- ከሚወድቁ ቁሳቁሶች ለመከላከል በቀላሉ በማይሰበሩ (በጠረጴዛ፣ በዴስክና በግድግዳ፣ በአልጋ) ስር ጎንበስ ብሎ መንበርከክ
-በመስኮት ወይም በሊፍት ለማመለጥ/ለመውረድ አለመሞከር
- ፊትን ወደ በር በማዞር ከመስኮት፣ መስታወቶች በመራቅ መቆም
-ከሚወድቁና ከሚወረወሩ ቁሶች ጭንቅላትንና ሰውነትን መጠበቅ
- የመሬት መንቀጥቀጡ እስከሚቆም ድረስ አለመንቀሳቀስ
- ከአንዱ ክፍል/ህንፃ ወደ ሌላ ክፍል/ህንፃ መሮጥ/መንቀሳቀስ አለመሞከር
-ከከቤቱ/ከህንፃው ውስጥ እንዴት መውጣት እንደሚቻል ማወቅ
• ከቤት ውጪ ከሆነ
- ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሮጥ/መንቀሳቀስ አለመሞከር
- የመሬት መንቀጥቀጡ እስከሚቆም ድረስ አለመንቀሳቀስ
-ከህንፃዎች፣ ከዛፎች ከግድግዳዎች፣ ከኃይል ማመንጫ መስመሮች፣ ወዘት በመራቅ ከፍት ቦታ ዝቅ በማለትና ሚዛንን በመጠበቅ መቁመጥ/መቆም
- ወደ ቤት/ህንፃ፣ በኃይል ማመንጫ መስመሮች ስር፣ ህንፃዎች ስር፣ ተሸከርካሪዎች መሀል፣ ዛፎች ውስጥ እና በሌሎች ለአደጋ በሚያጋልጡ አካባቢዎች መገኘት ወይም መንቀሳቀስ ወይም መሮጥ አለመሞከር፣
• በማሽከርከር ላይ ከሆነ
- የሚነዳውን ተሸከርካሪ ክፍት ቦታ መምረጥ፣ በፍጥነት ማቆም፣ ሞተር ማጥፋትና የአስቸኳይ ጊዜ ህጎችን በመጠበቅ በተሸከርካሪው ውስጥ መቆየት፣
- ተሸከርካሪውን በመተላለፊያ መንገድ ወይም ድልድይ ላይ ወይም በኃይል ማንጫ መስመር ስር አለማቆም
- አስቸጋሪ ሆኖ የግድ ከተሸከርካሪው መውጣት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከተሸከርካሪው በመውጣት ወደ ክፍት ሜዳ መሄድ
ከመሬት ንዝረት ክስተት በኋላ
• የተጎዱ/የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን ማረጋጥ፣ የመጀመሪያ እርዳት መስጠት፣ የተጎዱ/የቆሰሉ ሰዎችን ያለጥንቀቄ በፍጥነት አለማንቀሳቀስ
• ሌሎች አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ (የኃይል ማመንጫ መስመሮች፣ እሳት፣ ኬሚካል፣ መርዛማ ነገሮች፣ ሊወድቁ የሚችሉ ነገሮች) መኖራቸውን ማረጋገጥና ማስወገድ
• የውሃ፣ የጋዝ፣ የኤሌክትሪክ መስመሮች መኖራቸውን ማረጋገጥና መዝጋት/ማቋረጥ
• የህንፃ መሠረቶች፣ ግድግዳዎች፣ ጣራዎች፣ የጭስ መውጫዎች፣ መሰነጣጠቃቸውንና መጎዳታቸውን ማረጋገጥና ጥንቃቄ ማድረግ
• በቤት ውስጥ ክብሪት፣ ላይተር፣ ሻማ፣ ስቶቭ ወዘተ በጭራሽ ለመጠቀም አትሞክር
• ሬዲዮ በመክፈት የአደጋ ጊዜ መረጃን፣ ሪፖርትንና የጥንቃቄ መልዕክቶችን ማስማትና ተግባራዊ ማድረግ፣ ከደህንነትና ከአደጋ መቆጣጠር ሰዎች ጋር መተባበር
• ከአደጋ መቆጣጠርና አምቡላንሶች በስተቀር ማንኛውንም ተሸከርካሪን አለመጠቀም
• ያለህበት ህንፃ ለደህንነት የሚያጠራጥር ከሆነ ከህንፃው በመራቅ ሌላ ጊዜያዊ መጠለያ (ማቆያ ቦታ) ማዘጋጀት
• ለአስቸኳይ ጊዜ የሚያስፈልጉ ምግብ፣ ውሃ፣ አልባሳት መኖራቸውን ማረጋገጥ፣
ወቅታዊ መረጃ
በአፋር፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ማዕከላቸውን አድርገው የተለያየ መጠን ያላቸው የርዕደ መሬት ክሥተቶች በተደጋጋሚ መከሠታቸው ይታወቃል።
ክሥተቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠን እና በድግግሞሽ እያደጉ ይገኛሉ። በተለይም በዚህ ሳምንት በርዕደ መሬት መለኪያ እስከ 5.8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ መንቀጥቀጥ መከሠቱን መረጃዎች ያሳያሉ።
መንግሥት ክሥተቶቹን በዘርፉ ባለሞያዎች በቅርብ እየተከታተለ ይገኛል።
በተጨማሪም በተለይ የርዕደ መሬቱ ማዕከል (epicenter) የሆኑት አካባቢዎችን በመለየት በ12 ቀበሌዎች ላይ መንግሥት ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሠሣ እያደረገ ይገኛል።
በእነዚህ ቀበሌዎች ከሚኖሩ 80ሺህ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ከአካባቢው በማራቅ ለማሥፈር ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ነው።
በተጨማሪም ርዕደቱ በማኅበራዊ አግልግሎት ሰጭ ተቋማት፣ በኢኮኖሚ ተቋማት እና በመሠረተ ልማት ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽዕኖ በመከታተል ላይ እስካሁን ባለው ሁኔታ በዋና ዋና ከተሞች የጎላ ተጽዕኖ ያላደረሰ ቢሆንም ዜጎች በባለሞያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ መልእክቶችን እንዲከታተሉና በጥብቅ እንዲተገብሩ ለማሳሰብ እንወዳለን።
በቀጣይም ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል አስፈላጊ መረጃዎችን በሚመለከታቸው ተቋማት አማካይነት የሚያደርስ መሆኑን መንግሥት ያስታውቃል።
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ከፊታችን ለሚከበሩ በዓላት የተቋማት ዝግጅት
ከፊታችን የሚከበሩ በዓላት በጥሩ ሁኔታ እንዲያልፉ የመዲናዋ ተቋማት ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡…
የገና እና የጥምቀት በአላት እና የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በጥሩ ሁኔታ እንዲከበሩ አስፈላጊው የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የዝግጅት ስራ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ከተጠሪ ተቋማቱ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ፣የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ ከአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማስተባበሪያ ሪጅን እና ከመብራት አገልግሎት ባለስልጣን ጋር በጋራ የበዓላት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የዝግጅት ስራዎችን አስመልክቶ በዛሬዉ እለት መግለጫ ሰጥተዋል።
በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በመግለጫው ላይ እንዳስታወቁት የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማቱ የገናና የጥምቀት በዓላት ህብረተሰቡ በተሟላ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በዓሉን ባማረ ፣በደመቀ እና ከአደጋ ነፃ ሆኖ እንዲያሳልፍ አስፈላጊው የቅንጅት ስራዎች በአግባቡ መከናወናቸውን ገልፀዋል።
አያይዘውም ከአቅም በላይ በሆኑ ጉዳዮች የአገልግሎት መቆራረጥ ቢያጋጥም ደግሞ ፈጣን የሆነ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ግብረሐይል መቋቋሙንም አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ በበኩላቸው ከበአል ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ የሚመነጨዉ ቆሻሻ የከተማችንን ጽዳት እንዳያጓድል ስለቆሻሻ አወጋገድ ለህብረተሰቡ ሰፋፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሠራቱን ተናግረዋል።
ከበአሉ አከባበር ጋር ተያይዞ የሚኖረው የእርድ ተረፈ ምርቶችን አካባቢን እንዳያቆሽሽ ህብረተሰቡ ተረፈ ምርቶችን በአግባቡ ለሚመለከተው አካል ሊሰጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ገና፣ለጥምቀት እና የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎች በልዩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ አመልክተው ከዚህ ጎን ለጎንም በተለያዩ የአማራጮች ለህብረተሰቡ ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መከናወኑንም አስታውቀዋል።
አክለውም ህብረተሰቡ በበኩሉ በአሉን ሲያከብር ለአደጋ ከሚዳርጉ ተግባራት በመቆጠብ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበው ከዚህ አልፎ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል በሁሉም ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታዉቀዋል።
ኮሚሽነሩ ማንኛውም አደጋ ቢከሰት ነዋሪው 939 ነፃ የስልክ መስመር በመጠቀም በፍጥነት እንዲያሳውቅም ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ ሪጅን ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ጂሳ ካሳ እንደገለፁት በበዓላት ወቅት ሰፊ የሆነ የሀይል ፍላጎት ስለሚኖር ይህንን ከግምት ዉስጥ በማስገባት ተቋሙ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማከናወኑን ተናግረዉ ከሀይል መቆራረጥ ጋር ተያይዞ ለሚያጋጥሙ ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥ ክፍል ዝግጁ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የበዓል ቀናትን ጨምሮ አገልግሎት እንደሚሰጥም አሳዉቀዋል።
የአዲስ አበባ የመብራት አገልግሎት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን እንደተናገሩት መጪዎቹ በአላትም ሆነ ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የመንገድ እና የአደባባይ መብራቶች ለከተማችን ተጨማሪ ውበት እና ድምቀት እንዲሆኑና ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ አስፈላጊው የዝግጅት ስራዎች መከናወኑን አስገንዝበዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በቻይና ጂያንግሱ በነበረን የሁለት ቀን ጉብኝት ከያንጆ ከተማ የሲፒሲ ሴክሬተሪ ከሆኑት ሚስተር ዋንግ ጅንጂአን ጋር ተገናኝተን በሁለትዮሽ ጉዳዮች ለይ በትብብር ለመስራት ተወያይተናል።
በተጨሜሪም ከዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ እና ቴክኒክ ትብብር ጉዳዮች ሊቀ መንበር ሚስተር ሶንግ ቺንቦ ጋር ተገናኝተን በትብብር አቅጣጫዎች እና ዘርፎች ዙሪያ የተወያየን ሲሆን በቀጣይ አብሮ ለመስራት ተግባብተናል።
በናንጂን እና በያንጆ ከተሞች ባደረግነዉ ጉብኝት በከተማችን እየተካሄደ ለሚገኘው የኮሪደር ልማት ግብዓት የሚሆኑ ልምዶች የቀሰምን ሲሆን ትላልቅ የወንዝ ዳርቻ እና የከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክቶችን፤ የመኖሪያ ቤቶችን በስፋት ለመገንባት ለያዝነዉ እቅድ ግብአት የሚሆኑ ፣ በፍጥነት እና በጥራት ለማከናወን የሚያስችሉ የግባታ ቴክኖሎጂዎችን እንዲሁም በጥራት እና ስፋት እየተገበሩ ያሉትን የከተማ ግብርና ስራዎችን ጎብኝተናል።
በጉብኝታችን የተመለከትነዉ እና ለሀገራችን ተስማሚ የሆኑትን የግንባታ የቴክኖሎጂዎች እና የእዉቀት ሽግግር ላይ ለመስራት ተግባብተናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከቃል እስከ ባህል በሚል መሪ መልዕክት 2ኛው የብልፅግና ፓርቲ አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ውይይት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የኢንስፔክሽንና ሥነ ምግባር ኮምሽን ባቀረበው ረቂቅ ሪፖርት ላይ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል።
በውይይቱ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እሳቤዎች እና ልምምዶችን በተለወጠ እና አዲስ የሆነ የስራ ባህል በመተግበር የነዋሪውን ህይወት መለወጥ ያስቻሉ ስኬቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡
ፓርቲው ከምስረታው ጀምሮ በሁለንተናዊ መስኮች ለውጦችን ለማምጣት የህዝቦችን ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የገባውን ቃል ከስኬት ለማድረስ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡
ከነባር እሳቤዎች በመውጣት ተጨባጭ ለውጥ ያመጡ አሰባሳቢ እና አሳታፊ የፖለቲካ እሳቤን በመተግበር፣ የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚን ስርዓትን ወደ ስራ በማስገባት፣ በሰው ተኮር ተግባራት እና በአጠቃላይ ማህበራዊ ዘርፎች የህዝቦችን ተጠቃሚነት ቅድሚያ በመስጠትና በማረጋገጥ፣ ፕሮጀክቶችን አቅዶ በፍጥነት በመተግበር እና ወደ ስራ በማስገባት፣ ስኬታማ ዲፕሎማሲን በማካሄድ እና በመሰል መስኮች ቃል በተግባር የተለወጠበት እና አዲስ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ባህል ለውጥ መምጣቱን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች ብልጽግና ፓርቲ በአንደኛው ጉባኤው የገባቸውን ቃሎች በተጨባጭ ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
ለቀጣይ ሶስት ቀናት በሚካሄደው የቅድመ ጉባኤ ውይይት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠል ብሎም የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ ለማረም በሚያስችል ደረጃ በጥልቀት የሚወያዩ ይሆናል፡፡
የቅድመ ጉባኤ ውይይቶችና የአባላት ኮንፍረስ እስከ ጉባኤው መዳረሻ ድረስ በድምቀትና በከፍተኛ መነሳሳት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
ከዓመት በፊት ወደ ጎዴ መጥቼ ነበር። ከዚያ ወዲህ እየተካሄደ ያለው ለውጥ አበረታች ነው። በጽኑ ሃሳብ ማተኮር ያለብን በልማት ላይ ነው። ይኽ መንገድ ለእድሎች በር የሚከፍት፣ የሕይወት ደረጃን የሚያሻሻልና ማኅበረሰብን የሚያሻግር ጎዳና ነው።
በምዕራብ ጎዴ የመስኖ ፕሮጀክት በተለይ ደስታ ተስምቶኛል። በአንድ ወቅት ገላጣ የነበረው በረሃማ መሬት በመስኖ አሁን ታርሶ በተስፋ ሰጪ አቅም የሰሊጥ፣ ስንዴ፣ በቆሎ አዝርዕት ምርት እና በተለያዩ የፍራፍሬ ምርቶች የተሞላ ስፍራ ሆኗል።
Waggaa tokko dura gara Godee dhufeen ture. Yeroo sanaa as jijjiiramni adeemsifamaa jiru jajjabeessaadha. Yaada jabaataadhaan xiyyeeffachuu kan qabnu misooma irrattidha. Daandiin kun carraawwaniif kan balbala banu, sadarkaa jireenyaa kan foyyeessuufi daandii hawaasa kan ceesisudha.
Keessumaa piroojektii misoomaa Godee Lixaatti gammadeera. Lafti kanaan dura golgolaa'aafi gammoojjii ture amma jallisiidhaan qotamee misooma min'aanii akka saliixii, qamadii, boqqolloo akkasumas muduraalee garaagaraatiin uwwifamee humna abdii namatti horu ta'eera.
I came to Gode last year, and it’s encouraging to see the progress taking place since then. Our focus must remain steadfast on development — the path that unlocks opportunities, improves livelihoods, and transforms communities.
I am particularly pleased with the success of the West Gode Irrigation Project. What was once barren land is now being cultivated, with promising potential for producing sesame, wheat, corn, and a variety of horticultural crops.
