fa
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
"የኮሪደር ልማት ስራው በፍጥነትና በጥራት ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት በቀሪ ስራዎች ላይ ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል" ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የኮሪደር ልማት ስራው በፍጥነትና በጥራት ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት በቀሪ ስራዎች ላይ ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለፁ። በዛሬው ለት በተደረገው ምልከታ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፥የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ፤የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ሐፍቱ ብርሀኑ ፥የክ/ከተማ ደጋፊ አመራሮችና የወረዳው አመራሮች ተገኝተዋል። በ2ኛው ዙር የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት 7ኛ ኮሪደር ከሳር-ቤት አረቄ ፋብሪካና ከካርል አቦ ማዞሪያ ኮሪደር በልደታ ክፍለ ከተማ እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል። በዛሬው ዕለትም የኮሪደር ልማት ስራው የደረሰበትን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፥የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ፤የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ሐፍቱ ብርሀኑ ፥የከተማና የክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመስክ ጉብኝትና ቅኝት ተካሂዷል። በመስክ ምልከታው የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የኮሪደር ልማት ስራው በሚፈለገው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ኢንጂነር ወንድሙ አክለውም የኮሪደር ልማት ስራው በፍጥነትና በጥራት ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት በቀሪ ስራዎች ላይ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቅሰው ኮንትራክተሩን፣ ማህበራትንና የአካባቢውን ማህበረሰብ በተለያየ መንገድ ማገዝ እንደሚገባ ተናግረዋል። ከሳር ቤት አረቄ ፋብሪካ እና ከካርል አቦ አደባባይ ኮሪደር ልማት ስራ ላይ የመንገድ ደረጃ ማሻሻልና ምቹ ማድረግ፣ ሰፊ የእግረኛ መንገድ፣ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች፣ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የህፃናት መጫዎቻ ስፍራዎችና የታክሲና የአውቶቢስ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናሎች ይገኙበታል። በተጨማሪም የህንፃዎች እድሳት፣ የቆዩ ህንፃዎችን በማጠናቀቅ ወደ አገልግሎት ማስገባት፣ የሳይክል መንገድ፣ ዘመናዊ የፍሳሽ ማሶገጃ መስመር ዝርጋታ፣ የደህንነት ካሜራ መስመር ዝርጋታ፣ የትራፊክ ፍሰት መቆጣጠሪያ እና የስፖርት ሜዳ የልማቱ አካል ናቸው። Lideta sub-city communication office ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች የኤጀንሲውን የሪፎርም እና ቴክኖሎጂ ስራዎች ምልከታ አደረጉ በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የተመራው የአመራር እና የስራ ክፍል ሃላፊዎች ቡድን የኤጀንሲውን የሪፎርም እና ቴክኖሎጂ ስራዎች ጉብኝት አደርገዋል። በኤጀንሲው ዋና መስርያ ቤት ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ተቋሙ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ እያደረገ ያለውን ሪፎርም ተመልክተዋል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በተቋም ሪፎርም ስራ የተሰሩ ስራዎችን ያስጓበኙ ሲሆን ወደ ተግባር ለማስገባት በመልማት ሂደት ላይ ያለውን የተቋሙን አዲስ የሲስተም የቴክኖሎጂ ስራን ጨምሮ በዋና ዋና የተቋሙ ነባራዊ ሁኔታ ላይ ዝርዝር ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። የአገልግሎት መስርያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላም ዳዊት በበኩላቸው የተቋሙ የሪፎርም ስራ እንደ ሃገር በዘርፉ ተሞክሮ መሆን የሚችልና እንደ ሃገር ውጤቱን አስፍቶ ማጠናከር ይገባል ያሉ ሲሆን እንደ ፌደራል ተቋም ዘርፉ በከተማው እያመጣ ያለውን ለውጥ መሰረት ያደረገ ድጋፍ በማድረግ የተጀመሩት የቴክኖሎጂ ስራዎችን ጨምሮ ለማስቀጠል ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። ለበለጠ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 7533 ይደውሉ መጋቢት 9 / 2017 ዓ.ም ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የባሕር ዳር ልምድ ዛሬ የባሕርዳርን ከተማ የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴ ተመልክቻለሁ። ተፈጥሮ እና የሰው ጥበብ ተዋሕደው ባሕርዳርን ይበልጥ ውበቷን እያወጡት ነው። ከተማዋን የንግድና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ አመራሩ ከሚያደርገው ጥረት የምንማራቸው ብዙ ነገሮች አሉ። 1. ባሕር ዳር በፈተና ውስጥ የመጽናት ምሳሌ ናት፤ ባለፉት ዓመታት የነበረው ፈተና እያለፈ ነው። ባሕር ዳር በፈተናው ውስጥ ሥራዋን አላቋረጠችም። እንዲያውም ለፈተና የተወረወረውን ድንጋይ ለግንባታ ተጠቅማበታለች። 2. የጣና መከፈት የማስተሣሠር(ኮኔክቲቪቲ) መርሐችን መገለጫ ነው። የልማት ሥራዎቻችን መመጋገብ እና መተሣሠር እንዳለባቸው የባሕር ዳር ኮሪደር ምሳሌ ይሆናል። ለብዙ ዘመናት ከከተማው ተለያይቶ የነበረው ጣና ወደ ስምንት በሚደርሱ ቦታዎች ከኮሪደሩ ጋር ተገናኝቷል። ይሄም ከመዝናኛነቱ ባሻገር ከተማዋን ነፋሻማ አድርጓታል። 3. ነባር ዕሴት ላይ አዲስ ዕሴት መጨመር። በመደመር መንገድ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በነባር ዕሴቶቻችን ላይ አዳዲስ ዕሴቶችን ጨምረን መገንባት አለብን። ባሕርዳር የጣና ሐይቅና የዓባይ ወንዝ መገናኛ ናት። ከግማሽ ምእተ ዓመት በላይ ያስቆጠሩ የዘንባባ ዛፎች አሏት። በዚህ ላይ የኮሪደር ልማቱ ተጨማሪ ውበት ሰጥቷታል። 4. የአካባቢ ተቋማት ፈጠራ እየጨመሩ ልማትን እንዲያሣልጡ ማድረ፤ በባሕር ዳር ኮሪደር የለበሱት ንጣፎች እና የቆሙት መብራቶች በአካባቢው ተቋማትና ባለሞያዎች የተዘጋጁ ናቸው። በቀጣይም አካባቢያዊ ክሂሎትንና ዐቅምን መጠቀም የበለጠ መለመድ አለበት። 5. ባሕርዳርን የስፖርትና የቅርስ ቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ፦ በጣና ዙሪያ ያሉት ታሪካዊ ሥፍራዎች፤ ከጣናና ከዓባይ ጋር ተያይዘው የተሠሩት ወደቦችና መናፈሻዎች፤ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም፣ የዓባይ ዘመናዊ ድልድይ እና ሌሎቹም ልማቶች ባሕር ዳርን የ22ኛው መክዘ የንግድና ቱሪዝም ማዕከል እያደረጓት ነው። 6. የአመራር አርአያነት፦ አመራር ሠርቶ የሚያሠራ ፣ ቀድሞ የሚያስከትል መሆን አለበት። የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት የራሳቸውን ጽቤት አካባቢ አስተካክለው ኮሪደሩን በመሥራት አርአያ መሆናቸው ትምህርት የሚሆን ነው። ባሕርዳር ከዚህም በላይ መሥራት የምትችል ናት። ይሄ መጀመሪያዋ እንጂ የመጨረሻዋ አይደለም። ጽዳቱን ባህል ማድረግ፤ የተሠሩ አካባቢዎችን ጥንቅቅ ማድረግ፤ ተቋማት አካባቢያቸውን እንዲቀይሩ ማትጋት፤ ንግድን፣ ቱሪዝምን ና ኢንቨስትመንትን ይበልጥ ማበረታታት፣ ከሕዝቡም ከአመራሩም ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ (ዶ/ር)

መጋቢት 1 ቀን 2017 “በትምህርት፣ በጤና፣ በኢኮኖሚ ጉዳዮችና በሌሎች አምራች ዘርፎች ያሏችሁን ጥያቄዎች እና ማብራሪያ የሚሹ ጉዳዮችን ይላኩልን” በማለት ባሳወቅነው መሰረት የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች የሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ በዚህ ሳምንት እናቀርባለን። #PMOEthiopia

በኢትዮጵያ በሬክተር ስኬል 5.1 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ ምሽት ተከስቷል በኢትዮጵያ በሬክተር ስኬል 5.1 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ እሁድ 3 ሰዓት ከ53 ደቂቃ ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ተቋም አስታውቋል። ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየው የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ በስተሰሜን 50 ኪሜ ርቀት ላይ የተከሰተ ሲሆን ንዝረቱ በመዲናዋ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል። AMN-Addis Media Network ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ድንገት የመሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰት ምን ያደርጋሉ? ****** ከአስፈሪ የተፈጥሮ ክስተቶች ውስጥ አንዱ ርዕደ መሬት ነው፡፡ በእርግጥ በመሬት ከመከዳት በላይ ምን ሊያስፈራ ይችላል፡፡ ዓለማችን በርዕደ መሬት መለኪያ የተለያየ መጠን ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጦችን በየጊዜው ታስተናግዳለች፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ ባለንበት ሥፍራ ቢከሰት ድንጋጤን ውጦ እኚህን ነገሮች ለማድረግ መሞከር የራስንም ሆነ የወዳጅን ህይወት ለመታደግ ያግዛል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ የሚሰጥ አደጋ ባለመሆኑ እራስን ለማዳን ከቦታ ቦታ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ባሉበት ቦታ ከታች ያሉትን የአደጋ መከላከያ ነጥቦች ይተግብሩ፡፡ • የመሬት መንቀጥቀጡ እንደተሰማዎ አንገትዎን በሁለት እጅዎ አጥብቀው በመያዝ በጉልበትዎ ይንበርከኩ • በቀላሉ የማይንቀሳቀሱ ጠንካራ ነገሮችን አጥብቀው ይያዙ • እንደ ጠረጴዛ ያሉ ከላይ መከለያ ያላቸው ዕቃዎች ሥር መግባት በሚወድቅ ዕቃ ሊደርስ የሚችልን ጉዳት ይቀንሳል፡፡ - የሚይዙት ዕቃ እንዳይንቀሳቀስ ከጠንካራ ነገር ጋር በደምብ ያስጠጉት (ለምሳሌ ከቤት ምሰሶ ጋር) • እንደ መስታውት ያሉ በቀላሉ ረግፈው ጉዳት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ነገሮች ይራቁ • ቤት ውስጥ ከሆኑ ሲሊንደር ጋዝ፣ የተለኮሰ ሻማ አሊያም ሌላ እሳት ሊፈጥር የሚችል ነገር ካለ ያጥፉ • አሳንሰር ከመጠቀም ይቆጠቡ • ወጪ ከሆኑ ኤሌክትሪክ የተሸከሙ ፖሎች፣ ዛፎች አሊያም ሌሎች የተተከሉ ነገሮች እንዳይወድቁብዎ መራቅ እና በተቻለ መጠን ሜዳማ በሆነ ግልጽ ቦታ ላይ መገኘት እራስን ከአደጋው ለመጠበቅ ያግዛሉ፡ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በአቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ከ16500 በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በይፋ ተጀመረ። በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ (DPO) ከመንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በክ/ከተማው ሁሉም ወረዳዎች የሚተገበረው የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተካሄደ። በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ፣ የክ/ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና ስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ዉቢት ዮሐንስ፣ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ፣ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል የተውጣጣጡ ነዋሪዎች እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በዛሬው ዕለት የሚጀመረው ፕሮግራም መንግስት በሀገሪቱ ያስጀመረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ተከትሎ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ካሉበት የኑሮ ደረጃ ሰርተው እንዲለወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን በመግለፅ ሁሉም የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች የሀገሪቱ ብልፅግና ዕውን ለማድረግ ተግቶ በመስራት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ሊሸጋገሩ እንደሚገባ ተናግረዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ከዚህ በፊት የነበሩ ፕሮግራሞች በውጭ ሀገራት ድጋፍ ሲደረጉ የነበሩ መሆኑን በማንሳት በዛሬው ዕለት የሚጀመረው ፕሮግራም በዓይነቱ ልዩና በመንግስት አቅም ብቻ የሚተገበርና በርካታ ዜጎች የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያሰጋሰጠለ የሚያስችልና የስራ ዕድል የሚፈጥር ከድህነት አረንቋ በመውጣት ወደ ብልፅግና ጉዞን የሚያሳካ መሆኑን በማንሳት የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች በዕድሉ በመጠቀም በሀገሪቱ እድገት ላይ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ገልፀዋል ። የክ/ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዉቢት ዮሐንስ በዛሬው ዕለት የተጀመረው ፕሮግራም ከዚህ ቀደም ከነበሩት በጥራት በብዛትም የተለየ መሆኑንና በከተማ ደረጃ ለ154 ሺ ዜጎችን በክ/ከተማው ደግሞ ከ16500 በላይ ዜጎችን በአካባቢ ልማት ፣ በደረቅ ቆሻሻ ፣ በአረንጓዴ ልማትና በተፉሰስ ልማት ዘርፎች ተጠቃሚ የሚያደርግና መሆኑን በመጥቀስ ዜጎች የተፈጠረላቸው ዕድል በአግባቡ በመጠቀም ራሳቸውንና ሀገራቸውን ሊጠብቁ እንደሚገባ ተናግረዋል። Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በብሔራዊ ቤተመንግሥት በተደረገው ሁለተኛው የኢፍጣር ምሽት ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ሁለት መቶ የሚሆኑ ስደተኞች ተስተናግደዋል። የኢፍጣሩ ተሳታፊዎችም የታደሰውን ብሔራዊ ቤተመንግሥት ጎብኝተዋል። #PMOEthiopia

ፅዳት የሥልጡን ማህበረሰብ መገለጫ በመሆኑ ባህል ሊሇን እንደሚገባ ተገለፀ። በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 1 የአንድ ማዕከል የፅዳት ንቅናቄ የተካሔደ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አማካሪ ወ/ሮ እፀገነት እዮብ እንዳሉት ጽዳት የስልጡን ማህበረሰብ መገለጫ በመሆኑ ባህል ልናደርገው ይገባል ብለዋል። የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳለ ተሰማ አካባቢውን ለማፅዳት ማልዶ የተገኘውን ነዋሪ አመስግነው በወረዳው በሚገኙ በሁሉም ብሎኮች የፅዳት ስራ ባህል እየሆነ መሆኑን ገልፀው በራስ አገዝ የጀመርነውን የኮሪደር ልማት ስራ አጠናክረን በመቀጠል ውጤታማ እናደርጋለን ብለዋል አያይዘው የወንዞቻችንን ውበት እና ፅዳት እንዲጠበቅ ሁላችንም የወጣውን ደንብ ማክበርና ማስከበር ይኖርብናል ብለዋል። በእለቱ የክ/ከተማው የጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንየው ዘላለምን ጨምሮ የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል። Arada communcation/አራዳ ኮሙኒኬሽን ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et