fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ኤጀንሲው ከዛሬ ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ ሙሉ ቀን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ይፋ አደረገ አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2016 (ኢዜአ)፦ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከወረዳ ጀምሮ ባ
ኤጀንሲው ከዛሬ ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ ሙሉ ቀን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ይፋ አደረገ አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2016 (ኢዜአ)፦ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከወረዳ ጀምሮ ባለው መዋቅር ከዛሬ ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ ሙሉ ቀን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ይፋ አደረገ። ኤጀንሲው በ16 ሞዴል ወረዳዎች ስራ የማስጀመሪያ መርሃግብር እያካሄደ ይገኛል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን፣ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁና የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ታረቀኝ ገመቹ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በመገኘት መረሃ ግብሩን አስጀምረዋል። በዚህ ወቅት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን እንዳሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ፍጥነትና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል እየተሰራባቸው ካሉ ተቋማት መካከል የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አንዱ ነው። ኤጀንሲው እያደረገ ባለው ተቋማዊ ሪፎርም ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር እና አገልግሎቱን ለማዘመን ይረዳዋል ነው ያሉት።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በዛሬው እለት በወረዳ 5 እና 8 የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የሞዴል ወረዳ ፅ/ ቤቶች ምረቃ በፎቶ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በቂርቆስ ክፍለ ከተማና በልደታ ክ/ከተማ በዛሬው እለት የተመረቁ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ሞዴል የወረዳ ጽ/ ቤቶች በፎቶ:- ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን
+6
በቂርቆስ ክፍለ ከተማና በልደታ ክ/ከተማ በዛሬው እለት የተመረቁ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ሞዴል የወረዳ ጽ/ ቤቶች በፎቶ:- ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+1

photo content
+9

ሳምንታዊው የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች ተካሂደ። በየሳምንቱ ቅዳሜ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚካሄደው ብሎክን መሠረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሃግብር በሁሉም ክ/ከተሞችና ወረዳዎች እስከ ብሎክ ድረስ የዘለቀ የፅዳት ንቅናቄ ከማለዳው 12:30 ጀምሮ በሁሉም ከ/ከተሞች የተካሄደ ሲሆን እንደ ማዕከል በተመረጠው በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ልዩ ቦታው ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አካባቢ በድምቀት ተካሂዷል። ባለፉት አምስት አመታት የከተማዋን ፅዳት ለማስጠበቅ በተደረጉ ቅንጅታዊ የፅዳት ንቅናቄ ስራዎች በከተማዋ ፅዳት ዙሪያ ተጨባጭ ለውጥ መምጣት መቻሉን የገለፁት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ አካባቢያችንን ማፅዳት ብቻ ሳይሆን ዳግም የቆሻሻ መጣያ ቦታ እንዳይሆኑ ነዋሪው በባለቤትነት መጠበቅ እና መንከባከብ እንዳለበት በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ አብራርተዋል። አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍላችን ያፀዳውን አካባቢ ጥቂቶች አሁንም በግዴለሽነት በህገወጥ መንገድ የሚያቆሽሹ በመኖራቸው በተቀመጠው ደንብ መሠረት ተጠያቂ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። አክለውም ወርሃ ክረምቱ ከመግባቱ በፊት የተዘጉ ቱቦዎችን : የወንዝ ዳርቻዎችን : ማንሆሎችን : የውሃ ማስተላለፊያ መስመሮችን እና የመሳሰሉትን በማፅዳት አካባቢው ለጎርፍ አደጋ አስጊ እንዳይሆን የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች በቀጣይ በሚኖሩ ንቅናቄዎች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል:: ከፅዳት ንቅናቄ ስራው በኋላም ሞዴል በፅዳታቸው ብሎኮችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በፅዳት ንቅናቄው ላይም አመራሮችን ጨምሮ የፀጥታ አካላት : የፅዳት አምባሳደሮች : የተለያዩ አደረጃጀቶች : ተቋማት እና የአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ ተሳትፎ አድርገዋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በተቋማዊ ሪፎርም ፕሮግራሙ ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር እና አገልግሎትን ማዘመን አካል የሆነ በሰባት ክፍለ ከተሞች የሚገኙ 16 ሞዴል ወረዳዎችን በዛሬው እለት አስመረቀ:: በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በዛሬው እለት በለሚኩራ ክ/ ከተማ የወረዳ 8 ጽ/ቤትን ከኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ: ከለሚኩራ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ገመቹ እና በየደረጃው ካሉ አመራሮች ጋር በጋራ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል። ክብርት ሂክማ ከይረዲን በዚሁ ወቅት የመንግስት አገልግሎትን በፍጥነትና በጥራት ለመስጠት እየተሰሩ ካሉ ስራዎች የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት አንዱ የትኩረት መስክ ነው ብለዋል። ተገልጋይ የሚበዛባቸው ወረዳዎችና ክፍለከተሞችን ትኩረት በመስጠት ምቹ የማድረግ ፣በቴክኖሎጂ የታገዙና አሰራሮችን የማሻሻል ስራው የተገልጋዩን እርካታ እያሳደገ መሆኑንም አውስተዋል። ዜጎች የተሟላ አገልግሎት እንዲያገኙ የሁሉንም ተሳትፎ ይጠይቃል ያሉት ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዮችን እርካታ ከፍ ማድረግ ይገባል ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪውን የአገልግሎት ፍላጎት ግምት ውስጥ በማስገባት በኤጀንሲው ዘወትር ቅዳሜ ሙሉ ቀን የስራ ሰዓት መደረጉን ይፋ አድርገው የአገልግሎት ክፍያ አማራጮቹም ሙሉ ለሙሉ ወደ ቴሌ ብር የዲጂታል ስርዓት መሸጋገሩንም አመልክተዋል። የከተማችን ነዋሪዎች የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ፈልገው ከማእከል እስከ ወረዳ ጽ/ቤቶች ሲሄዱ አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልተው በመገኘት በስታንደርዱ መሠረት አገልግሎት በጥራትና በቅልጥፍና ማግኘት የሚችሉበትን ሁኔታ በሙሉ አቅም ተግባራዊ ለማድረግ ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም በዚሁ ወቅት አስገንዝበዋል:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የተቋሙን አዲስ መለያ (ሎጎ) በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ዓለም አቀፍ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን መሰረት ባ
+4
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የተቋሙን አዲስ መለያ (ሎጎ) በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ዓለም አቀፍ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን መሰረት ባደረገ መልኩ በአዲስ አበባ ዩንበርስቲ የስነጥበባት ት/ቤት እንዲዘጋጅ ያደረገውን አዲስ መለያ ሎጎና የብራንዲንግ ስራ ተጠናቆ በዛሬው እለት ርክክብ ተካሂዷል፡፡ አዲሱ የጽ/ ቤቱ ሎጎ የተቋሙን ራዕይ ፣ተልእኮና ፣ እሴት በሚገልፅ መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን የጽ/ቤቱን የተግባር ሙሉእነት፣ ተደራሽነት ፣የማያቋርጥ የለውጥ ሂደትን በሚገልጽ መልኩ የተዘጋጀ ነው፡፡ በተጨማሪም የሎጎና የብራንዲንግ ስራው አለምአቀፋዊነትን ሃሳብን ፣በጋራ ግንዛቤ መስራትን ክትትልና ድጋፍ ማድረግን ቅንጅታዊ አሰራር የማጎልበት የፅ/ቤቱ ተግባር የተገለጸበት ነው:: በሎጎው ውስጥ ያሉት ምስሎች ከትንሽ ክብ ወደ ትልቅ ክብ እየተዘረጋ እየሰፋ በሚሄድ ወካይ መስመር የተገለፀው ትርጉም ጽ/ ቤቱ የሚያከናውናቸውን ተግባርን በፍጥነት የማድረስና የማስረፅ ተግባር የተካተተበት ነው:: እንዲሁም ይህ መስመር ተደራሽነትን የስራ ፍጥነትንና በቴክኖሎጅ የሚታገዝ ፈጣንና ቀልጣፋ አሰራርንም የሚገልፅ ነው:: በምህፃረ ቃሉ ( CMO) የ"M" ፊደል አቀማመጥ ከፊደልነት ባሻገር ያለው ትርጉምና ምስል ከፍታን ፣ፅናትን ፣ዘመን የሚሻገር ስራ መስራትን፣ ህያውነትን፣ የተቋሙ ዋና ስራ የሆነውን የስራ ማስኬድን ተግባር ከሌሎች በጉልህነት ከሌሎች ፊደላት ከፍ በማድረግ ተገልጿል:: በተጨማሪም በአለምዓቀፍ ምልክት ውስጥ የ"M' ፊደል በሎጎው ውስጥ ያለው አቀማመጥ የእስትንፋስ ምልክት የሆነውን የልብ ምትን የያዘ ሲሆን የህያውነትና ዘመን ተሻጋሪ የስራ ውጤት የሚያስመዘግብ ተቋም መሆኑን ይገልጻል::

የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲን እና የእሳት አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ በዛሬው እለት አካሂዷል:: በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በመሩት በዚህ መድረክ ሁለቱ ተቋማት ባለፉት 9 ወራት ግንዛቤ ከመፍጠር ፣የማህበረሰብን ተሳትፎ ከማሳደግ በየተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ስራዎችን ከመስራት እና የበጎ ፈቃድ ስራዎችን ከማከናወን አንፃር የተከናወኑ ስራዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል:: በተጨማሪም የሪፎርም ስራዎችን ከመተግበር ፣ ቅንጅታዊ አሰራርን ከማጠናከር ፣ የኘሮጀክት አፈፃፀሞችን በተመለከተ፣ የቅድመ አደጋ መከላከልና የኮሙዩኒኬሽን ስራዎች ላይ የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል:: ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በዚሁ ወቅት እንደገለፁት ሁለቱም ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማዘመን ፣በእቅድ መሰረት ስራዎችን በመፈፀም ረገድ የተደረጉ ጥረቶችና የመጡ ውጤቶችና ለዉጦች መልካም የሚባል እንደሆኑ አስገንዝበዋል::በቀጣይም የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ መትጋት እንደሚገባ አሳስበዋል። አክለውም ከፅዳት አንፃር ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልፀዉ በቀጣይም ያለዉን የሰዉ ሀይል በሙሉ አቅም በመጠቀም የተሻለ ፅዱና ንጹህ ከተማ መፍጠር እንደሚገባ አስገንዝበዋል:: በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በኩልም ከተቋማት ጋር ተቀናጅቶ አደጋን አስቀድሞ ከመከላከልና የቅድመ አደጋ ስጋት ቅነሳ ረገድ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል:: ክብርት ወ/ሮ ሂክማ በቀጣይ ቀሪ ወራት ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራትን በትኩረት በመስራት የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ አሳስበዉ በተለይም በፅዳት አሰተዳደር ኤጀንሲ በቀሪ ወራት በግንዛቤ በመፍጠር ረገድና በሁሉም ክ/ከተሞች ሞዴል የፅዳት ወረዳዎችን የመፍጠር ሰራ በትኩረት እንዲሰራ አሳሰበዋል:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ” በሚል መሪ ሃሳብ በከተማችን የብክለት መከላከል ንቅናቄ አስጀምረናል። ተፈጥሮ ለአዲስ አበባ የለገሳትን ውበት ያመናመነውን አሰራር ለመቀየር እና የከተማውን ሰርዓተ ምህዳር ለማሻሻል የሚረዱ ሜጋ ፕሮጀክቶች በከፍተኛ ርብርብ ፣ በልዩ የአመራር ትኩረት እና በአጠረ ጊዜ ተፈጽመዋል። ከፍተኛ ለውጥ እያመጡ ካሉት ፕሮጀክቶች መካከል ዋነኞቹ ለሞቱት የከተማዋ ወንዞች ትንሳኤቸውን፤ ለተበከሉት ደግሞ ህክምናን ያበሰረው የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ ልማት አንዱና መሰረታዊ ሲሆን በከፍተኛ ፍጥነት እየቀነሰ የነበረውን የከተማችን የአረንጓዴ ሽፋን የታደገውና ከነበረበት 2.8 በመቶ ወደ 15 በመቶ ያሳደገው የአርንጓዴ አሻራ ማኖር ኢኒሼቲቫችንም ተጠቃሽ ነው። የተሰሩት ስራዎች አዲስ አበባን የቱሪስት መዳረሻና ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ያደረጓት ቢሆንም አሁንም ድረስ የድምጽ እና የፍሳሽ ብክለት እና አወጋገድ የከተማችን ፈተናዎች ሆነው ቀጥለዋል። በሕግና በአሰራር ችግሩን ለመፍታት ከምናደርገው ጥረት ባሻገር ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚቆይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በመስራት ለውጥ ለማምጣት ንቅናቄውን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እየተካሄደ ባለው ተቋማዊ ሪፎርም ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር እና አገልግሎትን ማዘመን ለ3ኛ ጊዜ በ7 ክ/ከተሞች ባሉ 16 ሞዴል ወረዳዎችን በነገው
+4
በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እየተካሄደ ባለው ተቋማዊ ሪፎርም ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር እና አገልግሎትን ማዘመን ለ3ኛ ጊዜ በ7 ክ/ከተሞች ባሉ 16 ሞዴል ወረዳዎችን በነገው እለት ቅዳሜ ሚያዚያ 12/2016ዓ. ም ስራ ያስጀምራል:: በዚሁ ዕለትም ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ ዘወትር ቅዳሜ ሙሉ ቀን የአገልግሎት ቀን እንዲሆን ማድረጉን ገልጿል:: የአገልግሎት ክፍያ አማራጮቹም ሙሉ ለሙሉ ወደ ቴሌ ብር የዲጂታል ስርዓት መሸጋገሩን ኤጀንሲው አስታውቋል:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

"አዲስ ፎረም" ክፍል ሁለት ... በአዲስ አበባ ከተማ የቅድመ አደጋ መከላከልና የከተማዋ ፅዳት ጉዳይ ላይ የከተማዋ ነዋሪዎች ምን ይላሉ? ኢቢሲ ኤፍኤም 97.1 "አዲስ ፎረም" ክፍል ሁለት ፕሮግራምን በፌስቡክ ገፃችን እንዲከታተሉ እነሆ ብለናል :: https://www.facebook.com/100063770933024/videos/3599520320361525

የኤሌክትሪከ መሰረተ ልማት የማዛወር ስራው 98 በመቶ ተጠናቀቀ በአዲስ አበባ ከተማ ከቀበና ድልድይ እስከ መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ክልል ውስጥ የነበረን የኤሌክት
+1
የኤሌክትሪከ መሰረተ ልማት የማዛወር ስራው 98 በመቶ ተጠናቀቀ በአዲስ አበባ ከተማ ከቀበና ድልድይ እስከ መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ክልል ውስጥ የነበረን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የማዛውር ስራ 98 በመቶ መጠናቀቁን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ማዛወር ስራው አስተባባሪ አቶ አስናቀው ፀሀይ ገለፁ፡፡ በዚህ የመስመር የማዛወር ስራ 3 ነጥብ 75 ኪ.ሜ መካከለኛ መስመር፣ 4 ነጥብ 1 ኪ.ሜ የዝቀተኛ መስመር፣ 16 ትራንስፎርመሮችና 3 ስዊቺንግ ስቴሽኖችን (የኤሌክትሪክ መስመር መቆጣጠሪያዎች) ቀድሞ ከነበሩበት በማንሳት ወደተመደበላቸው ቦታ ማዛወር ተችሏል ብለዋል፡፡ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የማዛወር ስራው 103 አዲስ የኮንክሪት ምሰሶዎች፣ 100 አዲስ የእንጨት ምሰሶዎች፣ አንድ ድራም የኤሌክትሪክ ኬብል እና 200 ሜትር የከፍተኛ ቮልቴጅ የመሬት ውስጥ ኬብል ከነባሩ በተጨማሪ ጥቅም ላይ መዋሉን ጠቁመዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ 98 ነባር የኮንክሪት ምሶሶዎችን የማንሳትና አንድ ስዊቺንግ ስቴሽን በአዲስ ለመቀየር የመሰረት ስራ መሰራቱን አስተባባሪው ገልፀዋል፡፡ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የማዛወር ስራው ሲከናወን በአካባቢው የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳይቋረጥ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ መደረጉን አቶ አስናቀው ተናግረዋል፡፡