fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የኮሪደር ልማት ዕሳቤ ዜጎችን ለመጪው ዘመን የከተሜነት ኑሮ ማዘጋጀት ዘመንንም ለህዝብ ማዘጋጀት ነው

በመጀመሪያ የረዳን ፊጣሪ ይመስገን! የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ስለሰጡን እውቅና እና ስላደረጉልን የምስጋና ፕሮግራም በራሴ ፣ በከተማ አስተዳደሩ አመራር እና ህዝብ ስም አመሰግናለሁ። በእርሶ ሃሳብ አመንጪነት እና ቀዳሚ መሪነት ከተማችን አዲስ አበባ እንደስሟ ውብ አበባ ለማድረግ ከለውጡ ማግስት ጀምረን እስከ ኮሪደር ልማት ደረስ በርካታ ጥረቶችን አድርገናል ።በተለይ በኮሪደር ልማት ከሶስት እስከ አራት ወራት ውስጥ የተሰራው ግን የከተማችንን አጠቃላይ ገፅታ የቀየረ ፣አዲስ የስራ ባህልን ያዳበረ እና ለከተማችን ነዋሪዎች ምቹ መኖሪያ እንደትሆን የአደረገ ድንቅ ስራ ነው። በዚህ በኩል የከተማ አመራር ብቻ ሳይሆን መላው የከተማችን ነዋሪዎች በተለይ በኮሪደር ልማት አከባቢ የሚገኙት ተባብረዋል ፣ ሰርተዋል ፣ኮንትራክተሮችና ኮንሰልታንቾች አብረውን ለነበሩ ሁሉ ዛሬ የቀረበው ምስጋና የሁላችንም እንደሆነ ማስመር እወዳለሁ። አሁንም ተሰባስበን እና እጅ ለእጅ ተያይዘን የማንቀይረው እና የማንለውጠው ሁኔታ አይኖረም :: ለህዝባችን ተጠቃሚነት የዛሬው እውቅና የበለጠ ሞራል እና ትጥቅ ሆኖን ዝቅ ብለን የምናገለግል መሆኑን ማረጋገጥ እወዳለሁ ። ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከተሞቻችንን ለወደፊቱ ለዜጎቻችን ክብር የሞላበት የኑሮ ዘይቤን ለማጎናፀፍ የሚመቹ እንዲሆኑ ማዘጋጀት ይኖርብናል። ከተሜነት እየተስፋፈ የሚሄድ መሆኑ የታወቀ ነው። እኛም ዘላቂ እና ምቹ ከተሞችን ለመፍጠር ሁሉም መሳሪያዎች አሉን። የከተማችንን ኮሪደሮች ለማልማት የተረባረቡትን ሁሉ ማመስገን እፈልጋለሁ። የዛሬው የእውቅና መርሃግብር የተሻለ የከተማ ከባቢ ለመፍጠር ያሳያችሁትን ትጋት እና ጠንካራ ሥራ የሚያንፀባርቅ ነው። ከመጀመሪያው የሥራ ምዕራፍ ብዙ ትምህርቶች ቀስመናል። አሁን ለሚቀጥለው ምዕራፍ ባላሰለሰ የመሻሻል ሂደት እና የሥራ ሥነምግባር በቀደመው ያሳካነውን ለማላቅ ተነስተናል። ዛሬ የአዲሶቹን ኮሪደሮች ልማት በይፋ ስናስጀምር ልማቶቹ እና ጥገናዎቹ ከደረስንበት ምዕራፍ አልፈው የሚሻገሩ መሆናቸውን ማስታወስ ይገባናል። በተጨማሪም ይህን ጠቃሚ ሥራ ለማስፋፋት በምናደርገው ጥረት የተሰሩት ኮሪደሮች የሥራ መሪዎች በመላው ሀገራችን ተመሳሳይ ሥራ ለጀመሩ አስራ አንድ ከንቲባዎች ረዳት በመሆን ያገለግላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዛሬው እለት ቀደም ሲል ከተማውን በም/ ከንቲባ ማእረግ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲመሩ ከነበሩት ከክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ጋር በዛሬው እለት በጽ/ ቤቱ የስራ ርክክብ አድርገዋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው እስከተሾሙበት ጊዜ ድረስ የኢፌዴሪ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ዜና ሹመት በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት ክብርት ሂክማ ከይረዲን የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል። ክብርት ሂክማ ከይረዲን በስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት በነበራቸው ቆይታ ላበረከቱት ግንባር ቀደም የመሪነት ሚና በጽ/ ቤቱ ስም እጅግ አድርገን እያመሰግንን አዲስ በተሾሙበት ሃላፊነት ውጤታማና ስኬታማ የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ዛሬ ማለዳ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታዉ ሰላም ሰፈር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ከከፍታ ቦታ ላይ አለት በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ተንዶ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው ገለፁ። በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ሰላም ሰፈር እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ከከፍታ ቦታ ላይ የተናደዉ አለት በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ተንዶ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደረጉት ጥረት የስምንት ሰዎች ህይወት ማትረፍ መቻሉ ኮሚሽኑ አስታወቋል። አደጋዉ የደረሰዉ ሟቾቹና ጉዳት የደረሰባቸዉ ሰዎች በቤታቸዉ እያሉ ሲሆን ህይወታቸዉ ያለፈዉ ሰዎች ሁሉም ወንዶች መሆናቸዉን ተገልጿል ። በሀገራችን በተለያዩ ክልሎች ተመሳሳይ አደጋዎች እየተከሰቱና ወቅቱ የክረምት ወቅት በመሆኑ የጎርፍ ስጋት እንደሚኖር የአየር ትንበያ ያመላከተ ስለሆነ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ከወዲሁ መልዕክታችን ነው።

ከሳሊተ ምህረት እስከ የተባበሩት የተሰራው የኮሪደር ልማት ስራ ምልከታ ተደረገ። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ በወ/ሮ ሂክማ ከይረድን የተመራ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የተሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ ምልከታ አድርጓል። ወ/ሮ ሂክማ ከምልከታው በሁዋላ ለ/ከተማው አመራሮች በጉብኝቱ ዙሪያ ግብረ መልስ የሰጡ ሲሆን መደበኛ ስራዎችንና የኮሪደር ልማት ስራዎችንም አጣጥሞ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል። የኮሪደር ልማቱ የተሰራባቸውን አካባቢዎች በተገቢው መንከባከብና ከጉዳት መታደግ እንደሚገባ በማውሳት አጠቀላይ የኮሪደር ስራው የተሰራበትን የጊዜ ፍጥነት፣ጥራትና የተቀናጀ አሰራር አድንቀዋል፡፡ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ገመቹ በበኩላቸው ምልከታ የተደረገባቸውን የኮሪደር ልማት ስራዎች ክ/ከተማ አስተዳደሩ ርክክብ ከማድረጉ በፊት በጥንቃቄ አይቶና በባለሙያ ገምግሞ እንደሚቀበላቸው በመግለጽ ቀሪ የኮሪደር ስራዎችንም ከዚህ በላቀ ጥረትና ቅንጅት እንዲሁም ፍጥነት ለመጨረስ መረባረብ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም Lemi Kura Communication ለሚ ኩራ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በተለያዩ የሀገራችንን አካባቢዎች በመሬት መንሸራተት ወገኖቻችን በመጎዳታቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ። ለብዙ ዘመናት ተፈጥሮን ባለመከባከባችን አሉታዊውን ውጤት አያየነው ነው። አረንጓዴ ዐ
በተለያዩ የሀገራችንን አካባቢዎች በመሬት መንሸራተት ወገኖቻችን በመጎዳታቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ። ለብዙ ዘመናት ተፈጥሮን ባለመከባከባችን አሉታዊውን ውጤት አያየነው ነው። አረንጓዴ ዐሻራ በዘላቂነት ችግሩን የመፍቻ ቁልፍ መፍትሔ ነው። የሚመለከታቸው አካላት ለተጎጂዎች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ መመሪያ ተሰጥቷል። ማኅበረሰቡም የተጎዱ ወገኖችን በሚቻለው ሁሉ እንዲደግፍ አደራ እላለሁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት " ይህ የሁላችንም ጉዳይ ነው" በሚል ርእስ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ኤፍኤም 98. 1 ጋር በመተባበር የሚያቀርብላችሁ ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም 6 ተኛውን ክፍል እነሆ ብለናል ።

በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረገ ያለው የአዘርባጃን መንግስት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በኤጀንሲው ጉብኝት አደረገ በአዘርባጃን መንግስት የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ሞሃመድ አሊ ኩዳቬርዴቭ የተመራው ልዑካን ቡድን ዛሬ ነሃሴ 22 በአዲስ አበባ ከተማ ቆይታ ያደረገ ሲሆን ቡድኑ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲን አጠቃላይ አገልግሎት እና የዲጂታላይዜሽን ስራ ጎብኝቷል። በዕለቱ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር በኤጀንሲው በመገኘት እንግዶቹን የተቀበሉ ሲሆን በከተማው የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለመቀየር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን መሰረት ያደረገ ማብራርያ ሰጥተዋል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተቋሙን በተመለከተ ለቡድኑ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ከተማዋ በዘርፉ የጀመረችውን የዲጂታላይዜሽን እንቅስቃሴ ስራም አስጎብኝተዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et Boost this post to reach up to 14208 more people if you spend $14. You're commenting as Etsegene