1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ተኛ አመት 7ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
1ኛ .በከተማዉ አስተዳደር በጀት ተመድቦላቸዉ የተገነቡ እና በመጠናቀቅ ላይ ያሉትን አዳዲስ ሆስፒታሎችን ዘመኑን በዋጀ የህክምና መሳሪያ ለማሟላት እና አለም አቀፍ ደረጃን የሚያሟላ አገልግሎት መስጠት ያስችላቸው ዘንድ በዘርፉ ትልቅ ልምድ ካካበቱ የግል ሴክተር ጋር በአጋርነት ለመስራት ዉሳኔ አሳልፏል።
2ተኛ .አንዳንድ የመንግስት አገልግሎቶችን በውል ለ3ተኛ ወገን ለማስራት የወጣውን ረቂቅ ደንብ መርምሮ በማየት ካቢኔዉ አፅድቋል።
3ተኛ .የተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ላላቸው እና ተኪ ምርቶችን ለሚያመርቱ ኢንዲስትሪዎች ባቀረቡት የማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎች ላይ በጥልቅ በመወያየት እና የአተገባበር አቅጣጫ በማስቀመጥ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
4ተኛ .የኮሪደር ልማት ውጤት ከሆኑት ሥራዎች አንዱ የብዙሀን ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ችግሮች የሚያቃልል እና የትራፊክ ፍስቱን የሚያሻሽለው የብስክሌት መጋራት አገልግሎት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብን በመመርመር አፅድቋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
'የካዛንቺስ ገጽታ በመልሶ ማልማትና በመታደስ ሂደት'
ከምንም በላይ ቅድሚያ የመንገድ ትስስሩን ማስፋት፣ የመንገዶቹን ደረጃ ማስጠበቅ፣ አገልግሎት ለማሳለጥ የሚረዱ መሰረተ ልማቶችን ከመሬት በታች መቅበር እና ሌሎች የመልሶ ማልማት ስራዎችን ለዘላቂ ልማት ምቹ የማድረግ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል::
የተከታታይ የምስል አቅርቦቱን ምንጀምረው በአዲስ አበባ ከተማ ነው።
በሁለተኛው ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ምን እየተከናወነ ነው?
👉ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራ በአዲስ አበባ በ8 አካባቢዎች እየተከናወነ ነው።
👉በሁለተኛው ምዕራፍ የሚከናወነው የኮሪደር ልማት በአጠቃላይ 2 ሺህ 879 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን፤ 240 ኪሎ ሜትር የአስፋልት እንዲሁም 237 ኪሎሜትር እግረኛ መንገድ በመገንባት ላይ ነው።
👉በስምንቱም የኮሪደር ልማት ስፍራዎች 32 የህጻናት መጫዎቻ ፤79 የሚሆኑ ህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች እንዲሁም 114 የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንግና የታክሲና አውቶብስ ተርሚናሎችን ያካተተ መሰረተ ልማት ይከናወናል።
👉ከትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች መካከል 58 በሚሆኑ አካባቢዎች ላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ጣቢያዎች ይኖራሉ።
👉ከ100 ኪሎሜትር በላይ የሚሆን የብስክሌት መንገድም በመገንባት ላይ ነው።
👉የከተማዋ ነዋሪዎች ጤናቸውን የሚጠብቁባቸው 17 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችም ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋሉ።
👉በኮሪደር ልማት ስራው ከእንጦጦ -ቀበና-ግንፍሌ ፒኮክ እንዲሁም ከእንጦጦ-ወዳጅነት-ፒኮክ የሚደርሱ ሁለት የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎችም እየተከናወኑ ነው።
"የትግራይ ህዝብ ቀዳሚ ምርጫ ሠላም ነው"
በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች
በመዲናዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ለሠላም ያላቸውን ድጋፍ እና ቁርጠኝነት የሚገልፅ ሰልፍ አካሂደዋል።
ነዋሪዎቹ ለትግራይ ልማት እንጂ ዳግም ጦርነት አያስፈልግም፣ በክልሉ ያለውን ሠላማዊ እንቅሥቃሴ እና መሠል ሥራዎች በማሥተጓጎል የሚገኝ ጥቅም የለም የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
ለትግራይ እና ነዋሪዎቿ ሠላም በምንም የማይተካ መሆኑንም ሰልፈኞቹ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ፖለቲከኞች ችግሮቻቸውን በመነጋገር እንዲፈቱ እና ለሠላም ጠንቅ ከመሆን እንዲታቀቡም አስገንዝበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀናት በፊት በትግርኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት፦ የትግራይ ክልል ሕዝብ ካለፈው ቁስሉ ሳያገግም አሁንም በጦርነት ስጋት እና ሽብር ላይ መሆኑን ገልፀው በትግራይ ልህቃን መካከል መከፋፈል መኖሩን በማንሳትም ልህቃኑ ልዩነታቸውን በመግባባትና የትግራይ ሕዝብን አንድነት በሚያረጋግጥ መንገድ ሊፈቱ እንደሚገባ መጠቆማቸው ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ራእይ፣ተልዕኮ እና ተግባርና ኃላፊነት ያውቃሉ?
ቀጣዪን ቪዲዮ ይመልከቱ:-
የፈረንሳይ ሊዮን ከተማ የእሳት አደጋ መከላከል አገልግሎት ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ተገኝተዉ ጉብኝት አካሄዱ።
የልዑካን ቡድኑ አባላት የኮሚሽኑን ዋና መ/ቤትና የአራዳን ቅርንጫፍ የጎበኙ ሲሆን በጉብኝት መርሀ -ግብሩ ላይ በኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮችና በባለሞያዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
በዚሁ ጊዜም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ እንደተናገሩት ኮሚሽን መ/ቤቱ አዲስ አበባ ከተማ ከአደጋ የተጠበቀች ሰላማዊ ከተማ እንድትሆን በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዉ የሊዮን ከተማ የእሳት አደጋ መከላከል አገልግሎት ካለዉ ልምድና አቅም አንጻር በተለያዩ አግባቦች ኮሚሽን መ/ቤቱን እንዲደግፍ ጠይቀዋል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በጉብኝታቸዉ ሰፊ መረጃዎችን እንዳገኙ ጠቅሰዉ ኮሚሽን መ/ቤቱ ያሉበትን ዉስንቶች ለመሙላት አስፈላጊዉን ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸዉ የገለጹ ሲሆን በቀጣይ በሚኖሩ ግንኙነቶች የድጋፎቹ አይነት እንደሚወሰኑ አብራርተዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት አዲስ ለተቋቋመው የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አሰተዳደር ባለስልጣን ሰራተኞች ለተሟላ አገልግሎት የስነልቦናና የሙያ ዝግጁነታቸውን የሚያጎለብት ሰልጠና በዛሬው እለት መሰጠት ጀመረ።
በሰልጠናው ማሰጀመሪያ መርሀግብር ላይ የባለስልጣን መ/ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን ለሰልጣኞቹ በስተላለፉት መልእክት ወደ ተቋሙ የተቀላቀሉ ሰራተኞች የከተማዋን የመብራት አገልግሎት ለነዋሪው ውጤታማ በሆነ መንገድ ተደራሸ ለማድረግ የመሰረተ ልማት ዲዛይን እና ግንባታን ጨምሮ መሰል አገልግሎቶችን በጎለበተ አቅምና እውቀት እንዲሁም ተነሳሺነት ሳትታክቱ ለህዝባችን አገልግሎት ለመሰጠት ቁርጠኝነት ሊኖራችሁ ይገባል ብለዋል።
አክለውም በተቋሙ የተለያየ የመመዘኛ መስፈርቶችን አልፈው የተቀላቀሉ ከፍተኛ ባለሙያዎች የተቋሙን ራእይ፣ ተልእኮ ተግባርና ሀላፊነት በሚገባ ተረድቶ በአገልጋይነት መንፈስ እቅድን በጥራትና በፍጥነት ወደተግባር በመቀየር የህዝባችንን እርካታ ለማረጋገጥ ይህን መሰል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ወሳኝ ነው ብለዋል።
አቶ ሰብስብ ሁሴን አያይዘውም የተቋሙ ሰራተኞች በጥሩ ሰነ-ምግባር ስልጠናውን በመከታተል ወደ ተግባር መተርጎም እንደሚገባቸው አሳስበው ስልጠናውን ያዘጋጀውን የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አሰኪያጅ ጽ/ቤትም አመሰግነዋል።
የባለሰልጣን መሰሪያ ቤቱ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘመኑ ደሳለኝ በበኩላቸው ሰልጣኝ ባለሙያዎች በተለያየ ቦታ ተከፋፍሎ ሲሰጥ የቆየውን የከተማዋን የመብራት አገልግሎት በአንድ ማአከል ለመሰጠት ከተማው ሀላፊነት ወሰዶ ያደራጀውን የባለሰልጣን መሰሪያቤት ተቀላቅላችሁ የከተማችንን ህዝብ ለማገልገል የበቃችሁ በመሆናችሁ በሰልጠናው የሚፈጠርላችሁን አቅም እንደተጨማሪ ግብአት በመጠቀም የከተማችን መብራት አቅርቦት የተሳለጠ እና ፈጣን ለማድረግ የተጣለባችሁን ሃላፊነት በብቃት መወጣት ይጠበቅባችሁዋል ሲሉም አስገንዝበዋል።
የሰልጠና መርሀ በሁለት ዙር የሚሰጥ ሲሆን የእቅድ እና በጀት ዝግጅት ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አሰኪያጅ ከፍተኛ የሰልጠና ባለሙያ አቶ ደሰታ ፈንታ እየተሰጠ ይገኛል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ቀን 2/5/2ዐ17 ዓ.ም
በስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የአቻ ሰራተኛ ፎረም የሳምንታዊ ውይይት ሪፖርት ማድረጊያ
የስራ ክፍል/ዳይሬክቶሬቱ ስም፡ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳሬክቶሬት
1. በስራ ክፍሉ የተደራጀ የአቻ ሰራተኞ ፎረም ብዛት 1 ውይይት ያደረጉ የአቻ ሰራተኛ ፎረም ብዛት 4
2. የሳምንቱ ይሥራሉ ተብለው የተያዙ እቅዶች-
• ከፌስ ቡክ ወደ-----ቴሌግራም፣ቲውተር፣ ፣ዩቱቭ ላይ አስፈላጊ መረጃ ማሠራጨት
• አይሲቲ እቃዎች ብልሽት ሲያጋጥም ድጋፍ ማድረግ
3. የተሰሩ ስራዎች
• ከፌስ ቡክ ወደ-----ቴሌግራም፣ቲውተር፣ ፣ዩቱቭ ላይ አስፈላጊ መረጃ ማሠራጨት
• መረጃ ማደራጀት
• የተለየዩ ክፍሎች ቴክኒካል ድጋፍ ማድረግ
• የዳነ ብክነት መተንተን
• የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የአይሲቲ እቃዎች ንብረት ቆጣራ ማድረግ
• 2ዐ17 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ሪፖርት
4. በእቅድ አፈፃፀም የታዩ ጠንካራ ጎኖች
የሚገጥሙ ስራዎችን በሕብረት መስራት
5. ያጋጠሙ ችግሮች
የመገልገያ ሶፍትዌር እጥረት
የድረገጽ መረጃ አለመሟላት/አለማለቅ
ፋይል ማኔጅመንት ከሰርቨር አለመስተካከል
6. የተወሰዱ መፍትሔዎች
ኢኖቨሽን ከቴሌ ጋር ያለውን ሥራ እስከሚጨርሱ መጠበቅ
7. በቀጣይ ሳምንት ይሰራሉ ተብሎ የታቀዱ ስራዎች
ፋይል ማኔጅመንት በአዲስ መልክ ስራው ክትትል ማድረግ
8. በጽ/ቤት ደረጃ ታይተው መፍትሔ እንዲሰጣቸው የሚፈለጉ ችግሮች
ለድረገጹ እና ለፋይል ማኔጅመንቱ አዋጭ የሆነ የሰርቨር ችግር ቢቀረፍ
9. ሪፖርቱን ያዘጋጅ ባለሙያ እፀገነት ተስፋሁን
10. ሪፖርቱን ያፀደቀው ኃላፊ ስም
ቀን 9/5/2ዐ17 ዓ.ም
የፈረንሳይ ሊዮን ከተማ የእሳትና አደጋ መከላከል አገልግሎት (Departmental-Metropolitan Fire and Rescue Service Lyon) የልኡካን ቡድን የመዲናችንን የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎችን የሚያጠናክር እገዛ ማድረግ በሚችሉበት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የፈረንሳይ ሊዮን ከተማ የእሳትና አደጋ መከላከል አገልግሎት የልኡካን ቡድን አባላትን በዛሬው እለት በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የልኡካን ቡድኑን በፈጣን እድገት ላይ የምትገኘው መዲናችን አዲስ አበባ የቅድመ አደጋ መከላከል ስራን ለማዘመንና ፈጣን ምላሽ ሰጭነት አቅም ለመገንባት የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ገለፃ. አድርገውላቸዋል።
የፈረንሳይ የእሳትና አደጋ መከላከል አገልግሎት የልኡካን ቡድን አባላት በበኩላቸው በኮሚሽኑ የመረጃና የማእከላዊ ማዘዣ ማእከልን በማዘመን፣ በሰው ሃይል ልማት፣ የከተማዋ አደጋ ስጋት ቦታዎች አስቀድሞ በመለየት (Risk Mapping) ላይ የሊዮን ከተማን ልምድ ለማካፈል፣ ቴክኒካዊ ቁሳዊ ድጋፍ ለማድረግ የከተማዋን ተጨባጭ ሁኔታዎች ለመዳሰስ የሚያስችል ጉብኝት በቆይታቸው እንደሚያደርጉ አስረድተዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ለልኡካን ቡድኑ ባደረጉት ገለፃ የአዲስ አበባ ከተማ የደረሰችበት ተጨባጭ ሁኔታ የመረጃና የማእከላዊ ማዘዣ ማእከልን አሁን ካለበት በይበልጥ በማዘመን ባጠረ ጊዜ ለአደጋ ምላሽ መስጠት የሚችልበት አቅም እንዲፈጠር የሚያደርግ እገዛና ድጋፍ እንፈልጋለን ሲሉም አስገንዝበዋል።
አክለውም አደጋ በሚያገጥምበትም ወቅት አደጋውን በፍጥነት ለመቆጣጠር የሚውሉ ግብአቶችን በሙሉ ከአንድ ማእከል (Command Center) ለመምራትና ለመቆጣጠር የሚቻልበትን ድጋፍ ከፈረንሳይ መንግስት ማግኘት ቢቻል ለከተማዋ የአደጋ ስጋት ቅነሳና መከላከል ብቃት መጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልፀውላቸዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
