fa
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
Baga Ayyaana Irreechaa bara 2018 nagaan geessan! እንኳን ለ2018 ዓ.ም የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል አደረሳችሁ ! Happy 2018 Irreechaa Holiday! በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ከማናቸውም አደጋ ተጠብቆ እንዲያልፍ በቂ ዝግጅት ተደርጓል:: የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሆረ ፈንፊኔ ኢሬቻ በዓል ከአደጋ ክስተት ተጠብቆ እንዲከበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ወደስራ መገባቱን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ አስታውቀዋል። ኮሚሽኑ በአደጋ ቅነሳ ዘርፉ በተለየዩ አማራጮች የጥንቃቄ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ መቆየቱን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ በዓሉ በሚከበርበት ቦታም ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር የተቀናጀ የቅድመ ሆስፒታልና የአንቡላንስ አገልግሎትን ጨምሮ የአደጋ ምላሽ አመራርና ባለሞያዎች በዓሉ በሚከበርበት ቦታ በተለያዩ አቅጣጫዎች አስፈላጊውን ጥበቃ በማድረግ ላይ እንደሆኑ ኮሚሽነር አህመድ ገልጸዋል:: በሌላ በኩልም በማናቸውም ስፍራ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል በአስራ አንዱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና በማዕከል በቂ ዝግጅት እንደተደረገም ኮሚሽነሩ አስታው ቀዋል። ለእሳትና ለሌሎች ድንተገኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳውቁ ! ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት እንኳን ለ2018 የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በአል በሰላም አደረሰን/አደረሳችሁ እያለ የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ ሪጅን ኦፕሬሽን ኮርዴኔሽን ፅ/ቤት በስሩ የሚገኙ ሪጅንና አገልግሎት መስጫ ማእከላት አድራሻ እንደሚከተለው ይፋ አድርጓል። የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ ሪጅን ማስተባበሪያ ቢሮ ለመዲናችን ነዋሪዎች ለማንኛውም ከኤሌክትሪክ ጋር ለተያያዙ አገልግሎቶች በነፃ መስመራችን 905 ይደውሉ ሲልም አስታውቋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

እንኳን ለ2018 የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በአል አደረሳችሁ! ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ለፈጣሪ አምላክ ምስጋና የሚቀርብበት፤ ከሰው ጋር ሰላም፣ ፍቅር እና አብሮነት የሚከናወንበት፤ አዲስ ተስፋና ብሩህ ዘመን የሚበሰርበት በዓል ነው። በዩኔስኮ የተመዘገው የኦሮሞ ገዳ ሥርአት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል የሀገራችንን መልከ-ብዝሃነት፤ ጥልቅ ዉበት ለመላዉ ዓለም ካሳዩ እና ካስተዋወቁ በዓላት መካከል አንዱ ነው። የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ወንድም እህት ህዝቦች ጋር በመሆን ባካሄደዉ መራር ትግል ከተቀዳጃቸው ድሎች መካከል አንዱ የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔን ክብረ በዓል በጥንታዊ ስፍራው ማክበር መቻል ሲሆን ይህም ባለፉት 7 አመታት በከፍተኛ ድምቀት ባህላዊ እሴቱን እና ቱፊቱን ጠብቆ በመዲናችን አዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል። የመዲናችን አጠቃላይ ህዝብም ከወንድም እህቱ የኦሮሞ ህዝብ ጋር በአብሮነት በሚያከብረው በዚህ ታላቅ በዓል ላይ እንደወትሮው ሌሎች የአደባባይ በዓላት ሲከበሩ ለበዓላቱ ድምቀት እና ባማረ መልኩ መጠናቀቅ እንደሚያደርገው ሁሉ አብሮነትን፣ ወንድማማችነትን፣ እህትማማችነትን በሚያጸና መልኩ፤ በከተማው ውስጥ ከሚኖሩ የኦሮሞ ሕዝቦችም ሆነ በእንግድነት ከሚመጡት ወገኖቹ ጋር በመሆን በዓሉ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ለማድረግ በመንገድ ጽዳት፣ በአደባባይ ማስዋብ እና በሌሎችም በርካታ በጎ ፈቃድ ስራዎች ከምንጊዜውም በላቀ መልኩ ለአገር ገጽታ ግንባታ፣ ለዘላቂ ቱሪዝም መስህብነት፣ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሚያመች መልኩ በሕብረ ብሄራዊ አንድነት መንፈስ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቋል። መላው የከተማችን ነዋሪዎች በከተማችን የአደባባይ በዓላት ሲከበሩ በዓላቱ ከዋዜማዉ አንስቶ እስኪጠናቀቁ ድረስ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት በመሳተፍ እያበረከታችሁ ላለዉ እጅግ የላቀ ሚና እያመሰገንኩ፣ ይህ ተግባር ውብ እና ድንቅ ባህሎቻችን ከእኛ አልፈው ለመላዉ ዓለም የምናበረክታቸው፤ የእኛነታችን መለያ ጌጥ በመሆናቸው እንደወትሮው ሁሉ የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል በድምቀት ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ ባማረ መልኩ ለማክበር ያደረግነውን ቅድመ ዝግጅት ከዋዜማው ጀምሮ በጋራ በምናከናውነው ተግባር የከተማችንን የሰላም ተምሳሌትነት፣ የህዝባችንን የሰላም ዘብነት እና እንግዳ ተቀባይነት በማረጋገጥ ይሆናል። በድጋሚ እንኳን ለ 2018 ኢሬቻ ሆረ-ፊንፊኔ ክብረ በዓል አደረሳችሁ! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ Baga Kabaja Ayyaana Irreechaa bara 2018tin Isin gahe, nuun gahe! Ayyanni Irreecha Ummanni Oromoo sirana waaqa umaa umaatiif galata ittin dhiyessudha. Jaarmiyaalee Sirna Gadaa; kan Yuuneeskon Galmaahe, keessaa tokko kan ta'ee Ayyaanni Irreechaa calaqqeewwan bifa danuu, Bareedinaa fi Hawwata Addaa, Adunyaaf agarsiisan keessaa isa tokko yoo ta'u, mallattoo Nageenyaa, Kan jaalalaa, Kan waloominaa, Araara fi sirna Injifannoowwan Uummatni Oromoo, Uummattoota Obbolaa, Sabaaf sablammoota hunda waliin ta'uun Qabsoo hadhaahaa adeemsiseen goonfate keessaa inni tokko Ayyaana Irreecha Hora Finfinnee iddoo ganamaa isaatti deebihee akka kabajamu gochuu isaati. Kanaanis uummatni Oromoo waggootan 7n darban Magaalaa Finfinnee keessatti Karaa Seenaa, Aadaa, fi Duudhaa isaa eeggateen sadarkaa olaanan Sabaaf Sablammoota hunda waliin kabajaa jira. Aadaa Waloon jiraachuu cimaa, fi waldanda'uun kan beekkaman jiraattotni Magaalaa Finfinnees, Ayyaana Obboleeyyan isaa Uummatni Oromoo Kabaju kana akkuma kana dura ayyaanotni uummataa kanneen biroo bifa hawwataa ta'een karaa nagaahan kabajamii akka xumuramaniif hijjechaa ture, Bifa Obbolummaa, fi Waliin jireenya keenya dagaagsu fi itichuu danda'uun uummata Oromoo Magaalaa keenyaa fi keessummootaa fageenya irraa dhufan waliin ta'uun, Ayyaanichi Duudhaa isaa eeggatee akka kabajamuuf, Hojii qulqullinaan, Adabaabayiiwwan adda addaa Bareechun, kenna tajaajilaani, fi hojiilee gocha gaarii adda addaatin kan kanaan dura ture caalatti bifa Hawwata turizimii walitti fufaa fi Sochii diinagdee olaanaf oolun Afuura Obbolummaa Sabdaneessummaan socho'uun kabajuuf qophii isaa xumuree jira. Jabana kana Jiraattotni Magaalaa Keenyaa hundi Ayyaanotni Uummataa kanneen Adabaabayii irratti kabajaman hunda jala bultii irraa kaasee hanga xumuramanitti hojiilee Gocha gaarii adda addaa irratti hirmaachun nageenya fi miidhagina isaaniif shoora olaanaa waan taphattaniif maqaa koo fi maqaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinneetin isin galateeffachuun barbaada.Hanga xummura ayyanichattii gocha fakkenyummaa kana cimsuin akka ittifuftan amantaan qaba. Irra deebihuun, Baga Kabaja Ayyaana Irreechaa Bara 2018tin isin gahe! Waaqayyo Itoophiyaa fi Uummattoota ishee haa eebbisu! Kantiibaa Adaanech Abeebee.

አዲስ አበባ ሆረ ፊንፊኔ በታላቅ ድምቀት ለማክበር ዝግጅቷን አጠናቃለች! በኮሪደር ልማት በተዋበችዉ ፣ በደመቀችዉ ፣ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የጋራ መኖሪያ ቤት ፣ የአደባባይ ክብረ በአሎቻችን ተጨማሪ ድምቀት ፣ ለበአሉ ታዳሚያን ፣ ለ ቱሪስቶች የበለጠ ምቹ እና ሳቢ በሆነችዉ አዲስ አበባ ፣ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በታላቅ ድምቀት ዝግጅቷን አጠናቃለች።

እንኳን ለኢሬቻ መልካ በሰላም አደረሳችሁ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢሬቻ የኦሮሞ የምስጋና ስርዓት ነው፡፡ ኦሮሞ የሰው ዘር አፍርቶ የሚባዛው የተዘራው ሞቶ በመነሣት ፍሬ የሚያፈራው በፈጣሪ ድጋፍና እርዳታ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ለዚህ ነው ኢሬቻ ሲደርስ ኦሮሞ ልበ ንፁህ የሆነውን ታላቅ ፈጣሪ ላደረገለት ሁሉ በማመስገን ለሚመጣው ጊዜ ደግሞ ምህረትን በመለመን ውዳሴ ያቀርባል፡፡ በጥንት የኦሮሞ ፍልስፍና ውስጥ ኦሮሞ ለውሃ ትልቅ ስፍራ አለው፡፡ ውሃ የንጽህና ምንጭ ፣ የፍጥረትና የህይወት መሠረት ነው ብሎ ያምናል፡፡ ለዚህም ነው ሲፀልይ ፈጣሪ አምላክ ፣ የፍጥረታት አምላክ ፣ የቡርቃ ወላቡ (የላቡ ምንጭ) አምላክ ብሎ ነው የሚፀልየው፡፡ የዘንድሮው ኢሬቻ ኢትዮጵያ የዜጎቿን የኢነርጂ ፍላጎት ለማሟላት የዓባይን ወንዝ በመገደብ ታላቁን የህዳሴ ግድብ ባስመረቀችበት ማግስት የሚከበር መሆኑ ደስታችንን ድርብ ያደርገዋል፡፡ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! ኦሮሞ መልካ የሌለው ህዝብ ራስ እንደሌለው ህዝብ ነው እንደሚል የባህር በር የሌላት አገር ኑሮ የሌላት አገር ናት ብለን ለህዝባችን ብልጽግና ስንል በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የባህር በር ለማግኘት እየሠራን እንገኛለን፡፡ በዚህ ረገድ እያደረግን ያለነው እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት በማግኘት ላይ ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት አዲስ እሳቤ በሆነው የመደመር ፍልስፍና በመመራት አገር ያላትን ሀብት፣ ልምድና እውቀት ከህዝባችን ጋር በመሆን ቁርጠኛና በሳል አመራር በመስጠት ፣ ፈጣሪም አግዞን በበርካታ ችግሮች ውስጥ ሆነን አስደናቂ ለውጦችን አስመዝግበናል፡፡ በ2018 ዓመተ ምህረትም የኢሬቻ እሴቶች የሆኑትን ሰላም፣ ምህረትና አንድነትን አጥብቀን በመያዝ የአገራችንን ማንሠራራት ለማረጋገጥ በፈተናዎች ሳንበገር ተግተን እንድንሠራ አደራ ለማለት እወዳለሁ፡፡ በድጋሚ የመከናወን ኢሬቻ ይሁልን እላለሁ! መልካው ሰላም ይሁን! ገዳው የጥጋብና የስኬት ይሁን! ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ፣ በልጽጋ ለዘላለም ትኑር! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ! መስከረም 23 ፤ 2018

Irreechaa ፥ Olkaiinsa Biyyaaf ! ኢሬቻ ለሃገር ማንሰራራት !… See more

የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ለማክበር በሁሉም አቅጣጫዎች ወደ መዲናችን እንግዶች የሚገቡባቸውን መንገዶች የማፅዳት ስራ በዛሬው እለትም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

አዲስ አበባ ከተማ የኢሬቻ በዓልን ስታከብር የኢትዮጵያን ማህበራዊ መስተጋብር ለዓለም በሚያስተዋውቅ መልኩ መሆን እንደሚገባ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ AMN - መስከረም 22/2018 ዓ. ም አዲስ አበባ ከተማ የኢሬቻ በዓልን ስታከብር የኢትዮጵያን ማህበራዊ መስተጋብር ለዓለም በሚያስተዋውቅ መልኩ መሆን እንደሚገባ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናግረዋል፡፡ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል የዋዜማ ዝግጅት መርሃ ግብር ተካሂዷል። አዲስ አበባ ከተማ በርካታ በዓላትን እሴታቸውን በጠበቀ ሁኔታ ስታከብር መቆየቷን የተናገሩት ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ መስከረም 24 በሆረ ፊንፍኔ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል ለማክበር ወደ ከተማችን የሚገቡ እንግዶችን በተለመደው የእንግዳ አቀባበል ስሜት በመቀበል እና በማስተናገድ በዓሉን የኢትዮጵያዊያን ማህበራዊ መስተጋብራችንንና አንድነታችንን ለዓለም ማሳየት ይኖርብናል ብለዋል። የሆረ ፊንፍኔ የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ወደ ከተማው የሚመጡ እንግዶችን ተቀብለው ለማስተናገድ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎችም አስፈላጊውን ዝግጅት በማጠናቀቅ እየተጠባበቁ መሆናቸውንም ተናግረዋል። በአለሙ ኢላላ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኢሬቻ በአል አከባበር ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ያስተላለፉትን መልእክት በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ👉👉 ለ… See more