fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ዛሬ ጠዋት የ2016 በጀት ዓመት የመንግስትና የፓርቲ ስራ አፈጻጸም ግምገማ እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ማከናወን ጀምረናል። ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለማቅለል እና ከተማችንን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ በ2016 በጀት ዓመት ከያዝነው አጠቃላይ እቅድ በአማካይ ከ91% በላይ የሚሆነውን ማሳካት የቻልን ሲሆን ፤ ይህም አዲስ የስራ ባህል በመተግበር ያሳካነው ነው። በግምገማችንም በ2016 በጀት ዓመት ስኬቶቻችንን በማላቅና በማስፋፋት፣ የጥንካሬዎቻችንን ምንጭ በመለየት እንዲሁም ጉድለቶቻችንን በመሙላት እና በማረም ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት ለኑሮ የተመቸች ውብ አበባ የሆነች ከተማ ለመገንባት የጀመርነውን ስራ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ኮሙኒኬሽን ቢሮ “ የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የክረምት ወራት የአረንጓዴ አሻራ መረሀ-ግብር አካሄደ። የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ‹‹የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ›› በሚል መሪ ቃል ዛሬ ነሐሴ 2/2016 ዓ.ም በእንጦጦ ፖርክ ውስጥ 2ተኛ ምዕራፍ 2ተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለስ፣ክብርት ዘይነባ ሽኩር የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሴቶቸና ህጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ የአዲስ አበባ ከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ሃላፊ :የቢሮው ምክትል ኃላፊዎች ፣የኮሙኒኬሽን መዋቅር አመራሮችና ባለሙያዎች ፣አርቲስቶች ፣የሚዲያ ተቋማት :ባለሃብቶች ፣ ጋዜጠኞች እና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተው አሻራቸውን አኑረዋል ። በመርሀ -ግብሩ መክፈቻ ላይ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ እናታለም መለስ እንደተናገሩት ፦ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ስናኖር ሃገር በቀል ችግኞችን በብዛትና በጥራት በእንጦጦ ፓርክ አኑረናል ፤የዛሬው መርሃ ግብር አረንጓዴ አሻራችንን ብቻ ለማሳረፍ ሳይሆን ትላልቅ ሃሳቦችንና ታሪክን ጭምር በትዉልድና በሃገር ላይ ለመትከል ነዉ፡፡ ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም የአካባቢ ጥበቃ መርህን በመከተል ለአየር ንብረት መስተካከል አዎንታዊ አስተዋጽኦ የሚኖራቸውን ሀገር በቀል ችግኞች በህብረት ከመትከል ባለፈ መጽደቃቸውንም የምንከታተልም ይሆናል ብለዋል ። በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ያነጋገርናቸው ተሳታፊዎች በበኩላቸው• አገር በትውልድ ቅብብሎሽ ይቀጥላል ፣ ነገን በማሰብ ጎዳናዎቿ ንጹህና አረንጓዴ ፣ተራራዎቿ ለምለም የሆነች አገር ለመፍጠር እንደ መንግስት እየተከናወነ ያለውን ውጤታማ ሥራ ከግብ ለማድረስ የኮሙዩኒኬሽን መዋቅሩ የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል። በመረሀ ግብሩ ላይ 2 ሺህ አምስት መቶ በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት አገር በቀል ችግኞች ተተክለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አሰኪያጅ ጽ/ ቤት የ2016 የሴክተር ማጠቃለያ ጉባኤ በምስል ሲቃኝ

በጽዳት ዙሪያ የሚከሰት ህገወጥነትን በጋራ እንከላከል!

በጽዳት ዙሪያ የሚከሰት ህገወጥነትን በጋራ እንከላከል!

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አሰኪያጅ ጽ/ ቤት የ2016 የሴክተር ማጠቃለያ ጉባኤ በምስል ሲቃኝ

እንኳን ደስ አለን! በፈረንሳይ ፓሪስ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 33ኛው የኦሎምፒክ ውድድር አትሌት ፅጌ ዱጉማ በተወዳደረችበት የ800 ሜትር በታሪክ ለሀገራችን የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ አምጥታለች::
እንኳን ደስ አለን! በፈረንሳይ ፓሪስ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 33ኛው የኦሎምፒክ ውድድር አትሌት ፅጌ ዱጉማ በተወዳደረችበት የ800 ሜትር በታሪክ ለሀገራችን የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ አምጥታለች:: በድጋሚ እንኳን ደስ አለን! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት የሐምሌ ወር 2016 ዜና መጽሄት ለንባብ በቅታለች። በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይከታተሏት። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በብዙ ትጋት፣ በህዝብ ሀብትና ተሳትፎ የተሰራውን የኮሪደር ልማት በግዴለሽነት ጉዳት የሚያደርሱ አሽከርካሪዎችን በመጠቆም ህብረተሰቡ ለሚያደርገው ተሳትፎ ሊመሰገን ይገባል:: በቂርቆስ ክፍለ ከተማ እየ
+3
በብዙ ትጋት፣ በህዝብ ሀብትና ተሳትፎ የተሰራውን የኮሪደር ልማት በግዴለሽነት ጉዳት የሚያደርሱ አሽከርካሪዎችን በመጠቆም ህብረተሰቡ ለሚያደርገው ተሳትፎ ሊመሰገን ይገባል:: በቂርቆስ ክፍለ ከተማ እየተሰራ ባለው የኮሪደር መንገድ ላይ የተቀመጠውን የአጠቃቀም ህግ በመጣስ እንዲሁም መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አሽከርካሪዎች ቅጣት እንደቀጠለ ነው። በዛሬው እለትም ከመስቀል አደባባይ ቦሌ ባለው የኮሪደር ልማት ላይ ባልተፈቀደለት ቦታ በመቆም፣የመኪና እጥበት በመፈፀምና ሳሩ ላይ በማሽከርከር መሰረተ ልማቱ ላይ ጉዳት ያደረሱ 3 አሽከርካሪዎች በተደነገገው አሰራር መሰረት 5 ሺህ ፣20 ሺህ እና 50 ሺህ ብር መቀጣታቸውን አስተዳደሩ ገልጿል። አሽከርካሪዎቹ መሰረተ ልማቱ ላይ ጉዳት በማድረስ ለማምለጥና ለመሰወር ቢሞክሩም በህብረተሰቡ ክትትልና ጥቆማ ከተሰወሩበት ተይዘው ቅጣቱ እንደተወሰነባቸውም ተገልጿል። በብዙ ትጋት፣ በህዝብ ሀብትና ተሳትፎ የተሰራውን የኮሪደር ልማት በግዴለሽነት ጉዳት የሚያደርሱ አሽከርካሪዎችን በመጠቆም ህብረተሰቡ ለሚያደርገው ተሳትፎ አስተዳደሩ ምስጋናውን አቅርቧል። በቀጣይም ህግን የሚተላለፉ አካላትን በመጠቆም፣ እንዲሁም ፎቶ ጭምር ቀርፆ በመላክ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም አስተዳደሩ ጥሪውን ያቀርባል። ይህ የተቀመጠ ህግን የመጣስ ጉዳይ በየእለቱ እየተበራከተ መምጣቱን ቂርቆስ ሚዲያ እያስተዋለ በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፅ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ይጠናከር ዘንድ ያሳስባል።

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት " ይህ የሁላችንም ጉዳይ ነው" በሚል ርእስ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ኤፍኤም 98. 1 ጋር በመተባበር የሚያቀርብላችሁ ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም 3ኛውን ክፍል እነሆ ብለናል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የ2ኛው ምእራፍ የ2ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር በምስል ሲቃኝ

ከተማችን አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እንዲሁም ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እንደ ከተማ አስተዳደር ከጀመርናቸው የኮሪደር ልማት ስራዎች በተጨማሪ ስራው በሌሎች የግል እና የመንግስት ተቋማት በመስፋፋት ላይ ይገኛሉ:: በዛሬው ምሽትም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን(ኢኮስኮ) በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ለሕዝብ መዝናኛ አገልግሎት እንዲውል የገነባውን ፋውንቴይን መርቀን አገልግሎት አስጀምረናል:: ፒያሳ ዶሮ ማነቂያ አካባቢ በብራዘርስ ኮንስትራክሽን እና ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ ስር በአሰር ኮንስትራክሽን በተመሳሳይ ለሕዝብ መዝናኛ እንዲውሉ በራሳቸዉ ወጪ የገነቡልንን ፋውንቴኖችን ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ማድረጋችን ይታወሳል:: የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን(ኢኮስኮ) ፣ብራዘርስ ኮንስትራክሽን እና በአሰር ኮንስትራክሽን ከልብ እያመሰገንኩ ሌሎች የግል እና የመንግስት ተቋማትም ከዚህ ልምድ በመውሰድ አካባቢያቸውን ለነዋሪዎች ምቹ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ላቀርብ እወዳለሁ:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ