fa
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን በማዘመን ግልጽነትና ተጠያቂነትን ማስፈን ተችሏል አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2018(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር መዘርጋት መቻሉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ፡፡ ዋና ስራ አስኪያጁ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በመዲናዋ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተጨባጥ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ውጤቶች አስመዝግበዋል፡፡ የመኪና፣ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገዶች፣ የውሃ፣ የመብራትና የቴሌኮም አገልግሎቶች እንዲሁም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የሚጠቀሙባቸው የህዝብ መናፈሻዎች አዲስ አበባን ጽዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ እያደረጓት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የተቋማት ሪፎርሞች፣ ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም ግልጽ፣ ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት መስጠት ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡ በተቋማት ሪፎርም ከፍተኛ ለውጥ ካስመዘገቡ ተቋማት መካከል የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አንዱና ግንባር ቀደሙ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከሪፎርሙ በፊት የህዝብ ቅሬታ የሚነሳበት፣ አገልግሎት በገንዘብ የሚለወጥበት ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ ተቋም እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ በተከናወነ ሪፎርም የህዝብ ቅሬታዎች በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰው በአገልግሎት አሰጣጥ ሞዴል ተቋም መሆን ችሏል ብለዋል፡፡ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላቱን እስከ ወረዳ በማስፋት 119 ማድረስ መቻሉን የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ የተሳለጠ አገልግሎት መስጠት በሚያስችል መንገድ መደራጀታቸውን ተናግረዋል፡፡ በአገልግሎት መስጫ ማዕከላቱ ሥራ ላይ የዋሉ ቴክኖሎጂዎች መረጃዎችን በቀላሉ ማደራጀት፣ ብልሹ አሰራርን መከላከልና ግልጽነትና ተጠያቂነትን ማስፈን አስችለዋል ብለዋል፡፡ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያልተገባ ድርጊት በሚፈጽሙ አካላት ላይ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ ለመውሰድ አንድ ማዕከል ላይ ሆኖ የአገልግሎት አሰጣጡን እንቅስቃሴ መቆጣጠርና መከታተል የሚያስችል ቴክኖሎጂም መተግበሩን ገልጸዋል፡፡ #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ

"ምስጋና ለክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ይሁንና አይቼው የማላውቀው የብርሀን አለም አየሁ። ወ/ሮ አረጋሽ ተሾመ የቤት ተጠቃሚ

የመስቀል አደባባይ የመስቀል ደመራ በዓል ማክበሪያ ቦታ የማጽዳት ዘመቻ ተካሄደ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዓለም የአቶሚክ ሳምንት (World Atomic Week) ጉባኤ ለመሳተፍ ሩሲያ ገብተዋል። Prime Minister Abiy Ahmed is currently attending the World Atomic Week conference in Moscow, Russia. #PMOEthiopia

የአደባባይ በአላቶቻችን ብሄርና እምነት ሳንለይ ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን የምናጠናክርባቸው እሴቶቻችን ናቸው- በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስ… See more

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መጪውን የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በአላት በማስመልከት ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ቀድሞ የመከላከል ግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች እየተሰራ ነው የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት መጪውን የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በአላት በማስመልከት ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ቀድሞ መከላከል የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል። በመድረኩ የተገኙት የየካ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አቶ ብስራት ማጆሬ እንደገለፁት የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በአላት የአብሮነት ፣ የፍቅር ፣ የአንድነትና የመተሳሰብ እንዲሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መልዕክት ያስቀመጡ ሲሆን ለበአላቱ ቅድመ ዝግጅት ተግባር ብርቱ አስተዋፅኦ እያደረጉ ላሉ አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናቸውን በማቅረብ የግንዛቤ ፈጠራ ፕሮግራሙ በይፋ ተጀምሯል ። የየካ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መርክነህ ያዕቆብ በበኩላቸው በሁለት ቀናት ውስጥ በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ ስጋት መከላከል ኮሚሽን ፣ ትራፊክ ማኔጅመንት ፣ መንገድ ትራንስፖርት እንዲሁም ጽዳት አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን ከበአሉ ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቀልበስ የሚያስችሉ የቅድመ መከላከል የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል ። በፕሮግራሙ ለአደጋ ቅድመ መከላከል የሚሆኑ በድምፅ ቀረፃ ፣ በብሮሸርና በበራሪ ወረቀቶች አማካኝነት የተዘጋጁ መልዕክቶችን በብዛት በማዘጋጀት በዋና ዋና መንገዶች ፣ በአደባባዮችና በገበያ ማዕከላት በመዘዋወር ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ ላይ ስለመሆናቸው አቶ መርክነህ ያዕቆብ ጨምረው ተናግረዋል ። Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

አደባባይ በዓላት ኢትዮጵያዊ መልኮቻችንና አብሮነታችንን ለዓለም የምናሳይባቸው መድረኮች ናቸው አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2018(ኢዜአ)፦ የአደባባይ በዓላት ኢትዮጵያዊ መልኮቻችንና አብሮነታችንን ለዓለም የምናሳይባቸው መድረኮች ናቸው ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ፡፡ የመስቀል ደመራ በዓል የሚከበርበት የመስቀል አደባባይን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ዛሬ ጠዋት የማጽዳት መርሃ ግብር ተከናውኗል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት፤ የመሰቀል ደመራ በዓል በአደባባይ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ ነው ብለዋል፡፡ የአደባባይ በዓላት ኢትዮጵያዊ መልኮቻችንና አንድነታችንን ለዓለም የምናሳይባቸው መድረኮች ናቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ የመስቀል ደመራ በዓል በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለም ቅርስ በመሆን የአብሮነት በዓል መሆኑን ገልጸው፤ ሀብትነቱ ከእምነቱ ተከታዮች ባሻገር የመላው ኢትዮጵያውያን ነው ብለዋል። በመሆኑም ከተማ አስተዳደሩ በዓሉን በድምቀት እንዲከበር እቅዶችን አዘጋጅቶ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ ለሙሉ ዘገባው 👉 https://www.ena.et/web/amh/w/amh_7395785

የደመራ/መስቀልና ሌሎች በዩኔስኮ የተመዘገቡ የአደባባይ በአላት የአገር ውስጥና በርካታ የውጭ ቱሪስቶች የሚታደሙበቸው እንደመሆኑ ውብና አዲስ የሆነችውን የከተማችን ገጽታ ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በሚገባ ለማስተዋወቅ ያስችላሉ ሲሉ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስታወቁት በዛሬው እለት "በእምርታና ማንሰራራት የታጀበ በዓላትን እናክብር!" በሚል መሪ-ቃል የደመራ/መስቀል በአላት የሚከበርበትን የመስቀል አደባባይ ስፍራ የሃይማኖት አባቶች፣ወጣቶች፣ ተፅእኖ ፈጣሪዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተሳተፉበት በተካሄደ የፅዳት ንቅናቄ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ነው። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በመስከረም ወር የሚከበሩ ተከታታይ በአላትን ባማረና በደመቀ መልኩ እንዲከበር አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ገልፀው ሁላችንም የከተማችን ገጽታ በይበልጥ ጎልቶ እንዲታይ የድርሻችንን ገንቢ ሚና መወጣት ይኖርብናል ሲሉም አስገንዝበዋል። ዘንድሮ ይህንን በዓል ስናከብር ልዩ የሚያደርገው ለዘመናት ስንቆጭበት የቆየነውን የህዳሴ ግድብን ገድበን ባጠናቀቅንበት ማግስት የሚከበር በመሆኑ በአሉን የተለዬ ያደርገዋል ሲሉም አክለዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ በበኩላቸው ፅዳት የመዲናችን ነዋሪዎች ባህል እስኪሆን ድረስ የዘወትር ተግባር መሆን እንዳለበት ገልፀው የዛሬው ፅዳት ንቅናቄ መርሀ ግብር ግን የደመራ/መስቀል በዓል ፅዱና ውብ በሆነ ስፍራ እንዲከበር ለማስቻል በዕቅድ እንደተዘጋጀ ገልፀዋል። መላዕከ ይሁን አባ ወ/የሱስ ሰይፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርክስቲያን ዕቅድና ልማት መምሪያ ኃላፊ ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ የምናከብረው የመስቀል ደመራ በዓል ፍቅር፣ የአብሮነትና የመቻቻል መገለጫ የሆነውን የመስቀል ደመራ በዓል የሚከበርበትን ቦታ ዘርና ሐይማኖት ሳይገድባቸው አብረው ለማጽዳት በመምጣታቸው አመስግነው ለዚህ በዓል በድምቀት መከበር የከተማ አስተዳደሩ ላደረገው ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ወክለው ንግግር ያደረጉት ሃጂ አወል ሃምዛ በበኩላቸው፣ በዩኔስኮ የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል የኢትዮጵያውያን የጋራ ጌጥና ውበት በመሆኑ አክብረን ለትውልድ ማስተላለፍ አለብን ብለዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ እና፣ የቂርቆስ ክ/ከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሐይማኖት አባቶችና የጽዳት እምባሳደሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡፡

የመስቀል ደመራ በዓል የሚከበርበት ስፍራን የማፅዳት መርሃግብር ተከናወነ አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2018(ኢዜአ)፦ የመስቀል ደመራ በዓል የሚከበርበት የመስቀል አደባባይን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ዛሬ ጠዋት የማጽዳት መርሃ ግብር ተከናውኗል። በመርሃ ግብሩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የተለያዩ እምነት ተከታይ ወጣቶችና የጽዳት ሰራተኞች ተገኝተዋል። ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት፤ መስቀል ደመራ በዓል ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለም ቅርስ የሆነና የአብሮነት በዓል ነው ብለዋል። በመሆኑም ሀብትነቱ ከእምነቱ ተከታዮች ባሻገር የመላው ኢትዮጵያውያን እንደሆነ ነው የገለፁት። በዚህም ከተማ አስተዳደሩ የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር የተለያዩ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል። የዛሬው የጽዳት መርሃ ግብርም የዚሁ አካል መሆኑን ጠቁመው፤ አሁን ላይ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር የዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥቷል ። በዚህም መሰረት:- (1) አቶ ሐፍታይ ገብረእግዚያብሔርን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ፣ (2) አቶ ሙሉነህ ደሳለኝን የቄራዎች ድርጅት ስራ አስኪያጅ ፣ (3) አቶ ዋለልኝ ደሳለኝን :የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን ም/ኃላፊ . (4) ወይዘሮ ነስትሆ አብዲ ኮይሬን :-የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን ፅ/ቤት ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል:: መልካም የስራ ዘመን! #Mayor office of Addis Ababa.

የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብፁእ አቡነ ሳዊሮስ ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁህ አቡነ ዲዎስቆሮስ እንዲሁም የአ/አ አገረ ስብከት ሊቀ ዻዻስ ብፁህ አቡነ ህርያቆስ እና የመስቀል በአል አዘጋጅ ኮሚቴ በተገኙበት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ከከተማዉ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ጋር በበአሉ ቅድመ ዝግጅት እና በከተማዉ አስተዳደር ስለሚደረገዉ ድጋፍ ዙሪያ ተወያይተዋል ። የመስቀል ደመራ በአል መስቀል አደባባይን ጨምሮ በ 2375 ደብሮችና ቦታዎች ላይ የሚከበር መሆኑ በመጥቀስ ሃይማኖታዊ ቱፊቱን እና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በደመቀና ባማረ መልኩ እንዲከበር የከተማዉ አስተዳደር ከማእከል እስከ ወረዳ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን በመግለፅ አባቶች እና የኮሚቴዉ አባላት እየተረገ ላለዉ ድጋፍ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዉይይቱ የበአሉ ዋና ባለቤትና በአሉን የምትመራዉ ፣ የምታስተባብረዉ የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ብትሆንም የመስቀል ደመራ በአል ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ህዝብ በአደባባይ የሚያከብረዉ የአገር ሀብት ፣የከተማችን ድምቀት ፣ የቱሪዝም መስህብ ነዉ ያሉ ሲሆን ሃይማኖታዊ ቱፊቱን እና እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት እንዲከበር፣ አብሮትን በሚያጠናክር መልኩ እና በሰላም እንዲጠናቀቅ ለሌሎችም የአደባባይ ክብረ በአላት የሚያደርገዉን ድጋፍ የከተማዉ አስተዳደር እያደረገ ይገኛል ብለዋል ።