cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የተዋህዶ ልጆች

ይህ channel ኦርቶዶክሳዊ ዝማሪዎችን፤መልዕክቶችን በvideo and በaudio የምታገኙበት መሆኑን ላሳስብ እውዳለው Channel: @mezmurortodox Group: @tewahedoo12 ⚓️ አዳዲስ ስብከቶች ባጭር ባጭሩ ⚓️ አዳዲስ መዝሙሮች ከነግጥሙ ⚓️ ሁሉም ኦርቶዶክስ ሊኖርበት የሚገባ 👇አስተያየት👇ለመስጠት 👉 @satmary 👈 @yelozye 👆👆👆👆👆👆 ✨✨✨✨✨✨

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
201
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#መስቀሉ_አበራ እዮሐ አበባዬ መስከረም ጠባዬ(፪) መስከረም ሲጠባ ተተክሎ ደመራ ህዝበ ኢትዮጵያን እዩት ችቦውን ሲያበራ በታላቁ ብርሃን በመስቀል ደመራ(፪) በኃጢአት ጨለማ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ተውጠን ሳለን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የክርስቶስ መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ብርሃን ሆነልን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ትምህርተ መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ሆኖን ላመንነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ በቃሉ ለምንድን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የእግዚአብሔር ኃይል ነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ✞ መስቀል ባንዲራችን የነጻነት አርማችን(፪) በኢየሩሳሌም አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ አይሁድ አብረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ያዳናቸውን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ አናውቅም ብለው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የድሉን መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ከመሬት ቀብረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ መስሏቸው ነበር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ውጦ የሚያስቀረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ በቀራንዮ ጎልጎታ ጠላታችን ድል ተመታ(፪) ንግሥቲቷ እሌኒ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ በጣም የታደለች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ደመራን አቁማ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ፍለጋ ጀመረች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ መስቀለ ክርስቶስ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ወዴት ነው እያለች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ በጣን ጢስ ተመርታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ መስቀሉን አገኘች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ በመስቀል መከታ ቆስጠንጢኖስ ድል ተመታ(፪) ነገር ግን መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ተቀብሮ አልቀረም አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ተራራ አፍርሶ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ጠላት አሳፈረ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ መስቀል ሲወጣ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ታላቅ ሁካታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ድውይ ሲፈወስ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ አንካሳው ዳነ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ሙታን ተነሱ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ይመስገን ጌታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ብርሃን ወጣ ከመስቀሉ ክርስቲያኖች እልል በሉ (፪) መስቀል መከታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ይሁን ጋሻችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ እንዳይደፈር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ዳር ድንበራችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ኢትዮጵያ ኑሪ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ በእምነት ፀንተሽ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ጌታ በመስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የባረከሽ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ መስቀሉ አበራ እንደ ፀሀይ ጮራ (፪) መስቀሉን አምነን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ተሳልመነዋል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ከክብሩ ዙፋን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ በእርሱ ባርኮናል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ እንሰግድለታለን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የፀጋ ስግደት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ በእርሱ ላይ ስላለ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ኃይለ መለኮት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ መስቀል የእኛ ጋሻ የዲያብሎስ ድል መንሻ (፪) የኢትዮጵያን መኩሪያ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ኑ ተመልከቱልን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የመስቀሉን ብርሃን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ነፀብራቁን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ እፀ መስቀሉ ነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የእኛ መከታችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የተሰጠን ለእኛ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ምልክታችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ በመስቀል እንመካለን እንድንበታለን(፪) የዳዊት ልጅ ያዕቆብ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የሀገራችን ኩራት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የኢትዮጵያ ንጉሥ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ጌታን የሚፈራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ መስቀል ተሸክሞ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ሀገሪቱን ሲዞር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ድካሙን ሳይፈራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ መስቀል ተሸክሞ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ብርሐን እያበራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የመስቀሉ ፍቅር በእኛ ላይ ይደር(፪) መናገሻ እንጦጦ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የረር አምባ አመራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ሲፈለግ ሰንብቶ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የመስቀል ተራራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ጊሸን ላይ አገኘ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የአምባሰል ተራራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ግማደ መስቀሉ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ አርፏል ከዚያ ስፍራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ መስቀል መስቀላችን የክርስቲያን ኃይላችን(፪) የመስቀል ለታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የደመራው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ኢትዮጵያውያን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ተደስተው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ በሀገር ልብሳቸው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ አምረው ደምቀው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ በአደባባዩ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ተሰብስበው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ ይዘምራሉ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ መስቀል ብለው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ የመስቀሉ ደመራ በኢትዮጵያ ሲያበራ(፪) መዝሙር በማኅበረ ፊሊጶስ @ortodoxmezmur @Eftah_bemaleda
نمایش همه...
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሰን! በፍቅር ተስቦ የወረደው ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የፍቅሩን ፍፃሜ በመስቀል ላይ ገልፆልን ሀያል ጌታ በመሆኑ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል እኛም ልክ እንደ ሐዋርያቱ በተዘጋ ቤት ሆነን ትንሳኤውን ሰምተናል ረድኤት በረከቱ በእያለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን! @Eftah_bemaleda
نمایش همه...
@bisrate_gebrel Des yemil mezmur new smiew
نمایش همه...
نمایش همه...
🎉መልካም_ፋሲካ 🎉 "ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ" የትንሣኤ መዝሙር 💚 @Eftah_bemaleda 💚
نمایش همه...
#ተነስቷል ሞት ሊይዘው አልቻለምና የተገነዘበትን ልብስ ትቶ ልብሰ መንግስቱን ለብሶ ተነሳ... በተወለደ ጊዜ የእናቱን መሀተመ ድንግልና እንዳለወጠ ሁሉ በትንሳኤውም መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል በመላእክት ታጅቦ በክብር ተነሳ። እንኳን አደረሳችሁ መልካም በዓለ ፋሲ
نمایش همه...
#ተነስቷል ሞት ሊይዘው አልቻለምና የተገነዘበትን ልብስ ትቶ ልብሰ መንግስቱን ለብሶ ተነሳ... በተወለደ ጊዜ የእናቱን መሀተመ ድንግልና እንዳለወጠ ሁሉ በትንሳኤውም መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል በመላእክት ታጅቦ በክብር ተነሳ። እንኳን አደረሳችሁ መልካም በዓለ ፋሲካ ይሁንልን! @mezmurortodox
نمایش همه...
ስለምንስ ከሙታን መካከልስ ትፈልጉታላችሁ እንሆ ጌታ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል እኛንም ከሀጥያት ግዛት ነፃ አውጥቶናል !በሞቱ የትሳኤን ብርሃን አሳየ ዳግም ህይወትንም ሰጠን!!!!! 😍😍😍😍እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤ አደረሳችሁ
نمایش همه...
ማቴዎስ 27 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ሲነጋም የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤ ² አስረውም ወሰዱት፥ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት። ³ በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ፦ ⁴ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ። እነርሱ ግን፦ እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ። ⁵ ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ። ⁶ የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው፦ የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ። ⁷ ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት። ⁸ ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ። ⁹ በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው፦ ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፥ ¹⁰ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት የሚል ተፈጸመ። ¹¹ ኢየሱስም በገዢው ፊት ቆመ፤ ገዢውም፦ የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን? ብሎ ጠየቀው፤ ኢየሱስም፦ አንተ አልህ አለው። ¹² የካህናት አለቆችም ሽማግሎችም ሲከሱት ምንም አልመለሰም። ¹³ በዚያን ጊዜ ጲላጦስ፦ ስንት ያህል እንዲመሰክሩብህ አትሰማምን? አለው። ¹⁴ ገዢውም እጅግ እስኪደነቅ ድረስ አንዲት ቃል ስንኳ አልመለሰለትም። ¹⁵ በዚያም በዓል ሕዝቡ የወደዱትን አንድ እስረኛ ሊፈታላቸው ለገዢው ልማድ ነበረው። ¹⁶ በዚያን ጊዜም በርባን የሚባል በጣም የታወቀ እስረኛ ነበራቸው። ¹⁷ እንግዲህ እነርሱ ተሰብስበው ሳሉ ጲላጦስ፦ በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው፤ ¹⁸ በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። ¹⁹ እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፦ ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ ብላ ላከችበት። ²⁰ የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ግን በርባንን እንዲለምኑ ኢየሱስን ግን እንዲያጠፉ ሕዝቡን አባበሉ። ²¹ ገዢውም መልሶ፦ ከሁለቱ ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው፤ እነርሱም፦ በርባንን አሉ። ²² ጲላጦስ፦ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው? አላቸው፤ ሁሉም፦ ይሰቀል አሉ። ²³ ገዢውም፦ ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው? አለ፤ እነርሱ ግን፦ ይሰቀል እያሉ ጩኸት አበዙ። ²⁴ ጲላጦስም ሁከት እንዲጀመር እንጂ አንዳች እንዳይረባ ባየ ጊዜ፥ ውኃ አንሥቶ፦ እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተጠንቀቁ ሲል በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ። ²⁵ ሕዝቡም ሁሉ መልሰው፦ ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን አሉ። ²⁶ በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ። ²⁷ በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ አከማቹ። ²⁸ ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት፥ ²⁹ ከእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፥ በፊቱም ተንበርክከው፦ የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ ዘበቱበት፤ ³⁰ ተፉበትም መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት። ³¹ ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት ሊሰቅሉትም ወሰዱት። ³² ሲወጡም ስምዖን የተባለው የቀሬናን ሰው አገኙ፤ እርሱንም መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት። ³³ ትርጓሜው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደሚባለው ስፍራ በደረሱ ጊዜም፥ ³⁴ በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም። ³⁵ ከሰቀሉትም በኋላ ልብሱን ዕጣ ጥለው ተካፈሉ፥ ³⁶ በዚያም ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር። ³⁷ ይህ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው የሚል የክሱን ጽሕፈት ከራሱ በላይ አኖሩ። ³⁸ በዚያን ጊዜ ሁለት ወንበዶች አንዱ በቀኝ አንዱም በግራ ከእርሱ ጋር ተሰቀሉ። ³⁹ የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና፤- ⁴⁰ ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራው፥ ራስህን አድን፤ የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ከመስቀል ውረድ አሉት። ⁴¹ እንዲሁም ደግሞ የካህናት አለቆች ከጻፎችና ከሽማግሎች ጋር እየዘበቱበት እንዲህ አሉ። ⁴² ሌሎችን አዳነ፥ ራሱን ሊያድን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ፥ አሁን ከመስቀል ይውረድ እኛም እናምንበታለን። ⁴³ በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ብሎአልና ከወደደውስ አሁን ያድነው። ⁴⁴ ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዶች ደግሞ ያንኑ እያሉ ይነቅፉት ነበር። ⁴⁵ ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ። ⁴⁶ በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም፦ አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው። ⁴⁷ በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተው፦ ይህስ ኤልያስን ይጠራል አሉ። ⁴⁸ ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጠ፤ ሰፍነግም ይዞ ሆምጣጤ ሞላበት፥ በመቃም አድርጎ አጠጣው። ⁴⁹ ሌሎቹ ግን፦ ተው፥ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደ ሆነ እንይ አሉ። ⁵⁰ ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ። ⁵¹ እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤ ⁵² መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤ … ⁵⁶ ከእነርሱም መግደላዊት ማርያምና የያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም የዘብዴዎስም የልጆቹ እናት ነበሩ።
نمایش همه...