cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

📋የሂዲ... ፅሁፎች📋

❤እንኳን ወደ💙 ሂዲ ፅሁፎች💙 በሰላም መጣችሁ❤ በዚህ ቻናል በፅሁፎቼ ልምድ እንደምታገኙባቸው ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ..🙏 ✔የፍቅር ገጠመኞችን ✔ አነቃቂ ፅሁፎችን ✔ልብ ሰራቂ ግጥሞችን እና መሳጭ✔ የፍቅር ተከታታይ ታሪኮችን ያገኛሉ... ታዲያ የምን መፋዘዝ ነው ገባ ገባ በሉ @hiditiለማንኛውም አስተያየት በዚህ ያገኙኛል..ቻናሉን ሼር ማድረግ አይርሱ

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
179
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

😘😘😘😘😘😘😘😗😗😗😗😘😘😘😗😙😙🤨😘😘😗😗😗😘😗😗😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😗😗😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘 @malslni😘 la hidiya
نمایش همه...
3.73 KB
ሂወቴ እዚህ ምድር ላይ መስማት የማንፈልጋቸው ብዙ ቃላቶች አሉ። ስንሰማቸው የሚያሙን እና የሚያስከፉን......ሂወቴ እኔ ደሞ ቻው የሚለውን ቃል አልወደውም...😔 መቼስ ለምን¿አትለኝም አይደል?.....ካልከኝ ግን ቻው ማለት እስከ ዘላለም ወይንም ደሞ እስከመጨረሻው ስለሚመስለኝ ነው። አ ል ወ ደ ው ም !! በጣም ነው የምጠላው እስከዛሬ ስፅፋልህም ቻው ብዬህ አላውቅም አይደል!? ካልኩህ ግን እረስቼው አልያም ደሞ ተሳስቼ ነው የሚሆነው 😯 ዛሬ ግን ሂወቴ ልልህ ነው መሠለኝ።ደስ የማይል ስሜት እየተሠማኝ ነው። አንዳንዴ ደና ሳንሆን ደና ነን እንላለን።ምክንያቱም የእኛ ደና መሆን ደና የሚያደርጋቸው ብዙ ሠዎች አሉ እና😒 ዋናው ደሞ ሂወቴ ደና መሆን ነው አይደል!!? ሁሌም ደና ሁንልኝ....ሂወቴ ሰው ዝም ስላለ የለም ማለት አይደለም። ዝም ብሎ እና ሳይኖር የሚኖር ብዙ ሠው አለ። በእርጋታ እና በዝምታ ምን እና ለምን ነገሮች ምን እንደሆኑ ሳያውቅ በዝምታ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች አሉ።ኧረረረሰ በጣም ብዙ ሠው በአለም ላይ ብዙ ሰዎች መጥፎ ሆነው ሳይሆን ሚሠጡትን ፈልገው ሲያጡ መድረስ ፈልገው ሳይችሉ ሌሎችን ለማስደሰት እነሱ ይከፉ እና ዝቅ ይላሉ። ከዚያም ያኔ መጥፎዎች ይባላሉ። ሂወቴ ...በአንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ እንደሚሆንም ደሞ አምናለሁ አንድ ቀን ትፈልገኛለህ በጣምም እናፍቅሀለሁ💛 እኔ ግን የዛኔ አልኖርም አ ብጠራኝም አልሰማም አ!!ሂጂ ባልከኝ መንገድ ሂጃለሁ። ጥፊ ባልከኝ መንገድ ጠፋቻለሁ። ግን ትፈልገኛለህ..ላንተ እንደ እኔ የሚሆንልህ ስታጣ ትፈልገኛለህ።የዛኔም ቆይቼም አርፍጄም ቢሆን መጣለሁ።።እየሮጥኩም ሄጄ በዝግታ መጣልሀለሁ። በጨለማም ሄጄ በብርሀንም እመለስልሀለሁ። ሂወቴ😔 ከሠው ጋር ሆነህ ሂጂ ብለኋኝ ብቻህን ስትሆን ግን መጣልሀለሁ😯 የዛኔም በጣም አስፈልግሀለሁ። እስከዚያው ግን ሂጂ ባልከኝ መንገድ ሄጃለሁ👣👣👣👣👣👣👣👣👣👣👣👣👣👣👣👣👣👣👣👣👣👣👣 በቃ ሂወቴ ብዙ አልጨቅጭቅህ✋ ✍ሂዲ @hidihebron @hiditiyehubiii
نمایش همه...
😱😱😱😱👏👏👏👏👏👏👏
نمایش همه...
🙏 ተመስገን አምላኬ🙏 ተመስገን አምላኬ እምባየ ወረደ፣ ስክበው የኖርኩት ልፋቴ ተናደ፣ በ'ጀ የነበረው ብርታቴ ነጎደ፣ አብሬው የኖርኩት ህልሜም ጥሎኝ ሄደ። 🙏 ተመስገን ፈጣሪ🙏 በስንት የሰራሁት ቤቴም ፈራረሰ፣ ህይወቴ ኑሮየ ይሄው ተቃወሰ፣ ይበልጥ የመሰለኝ ሀሳቤ 'ረከሰ፣ የመራመድ ተስፋ ዳቦው ተቆረሰ፤ 🙏ተመስገን ፈጣሪ🙏🙏 ይሄው አቅም አጥቼ.... አሁን ተኝቻለሁ፣ ጨለማው ደስ ብሎኝ..... ብርሀን ፈርቻለሁ፣ ከ ረዢም ጉዞየ.... ይሄው ቀርቻለሁ፣ መቀጠል ሲደክመኝ... ተስፋ ቆርጫለሁ፤ 🙏ግን አንተ ተመስገን🙏🙏🙏 ተመስገን ያልኩት ቃል... ከ አፌ ሳይወጣ፣ ይሄው ደግሞ በጧት... ሌላ መርዶ መጣ፣ አለፈልኝ ብየ ሳቀናው አንገቴን፣ እኔም ወጉ ደርሶኝ ስገፋ ጭንቀቴን፣ የመኖሬ ተስፋ ሲያሸንፍ ፍርሀቴን፣ ደግሞ ሌላ ህመም በ ልቤ ይነግሳል፣ አይኔም እንደ ዘበት ወንዝ ሆኖ ይፈሳል። 🙏ግን ተመስገን አንተ🙏 ከወሰድከው በላይ.... ብዙ አድለኸኛል፤ ልቤ ተስፋ ቆርጦም.... "አመስግን" ይለኛል።። (by....MuBa🖌)
نمایش همه...
ትላንት ነበር 😒 እህህህ ምኑ ይለኛል እንዴ....🥺 ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። በቃ ትላንት ነበር ዛሬ አይደለም☺️ እና ሰፈራችን ወደሚገኘው ዛፍ ስር ቁጭ ብያለሁ...ብቻዬን ነኝ..በእጄም ማስታወሻዬን ይዣለሁ....ብዙ ነገሮች ለብዙ አመታት ነው የፃፍኩበት...ለምን እና ለማን እንደፃፍኩት እማላውቀው ብዙ ደብዳቤዎች ውስጡ አሉ....ከፍቼም ማንበብ ጀመርኩ....📖 እኔ ግን ምን አይነት ሰው ነኝ?እኔንጃ....እኔም መልሱን እየፈለኩ ነው..ግን አልሀምዱሊላህ አሁን በጣም ደስተኛ ነኝ....ደና ሆኛለሁ በጨለማ ለሚኖሩትም አላህ ቀን አለው....ብርሀንን..ሚሰጣቸው ቀን ይመጣል.. የልባቸውንም መሻት ይፈፅምላቸዋል.. እህቴ .....የማይረዳን ማስረዳት ከባድ ነው አይደል ....ብትምይለትም..እና ደጋግመሽ ብትነግሪው እንኳን የማይረዳን....ሰው በቃ ተይውው ለቻልሽውን ሞክረሽ እርግፍ አድርገሽ ተይው ...... አትከተይው ከመንገድሽ አስወጭው.....👍👍 አንችን እኮ ብዙ ሊረዱሽ የሚፈልጉ እንዳሉ አትርሽ....እህቴ አስተውይ ፈልገሽ አይደለም የተውሽው ስለማይረዳሽ እንጅ ካንች ይልቅ ለራሱ ቦታ ስለሚሰጥ.... ያንች የነበር ቆይታሽን አጭር ስላደረገብሽ ሰው አትጨነቂ.......የማይረዳሽ ሰው ሊወድሽ አይችልም....ብቻ ደብተሬን ዘጋሁ...ወደ ቤቴም ገባሁ..ቀጥ ብዬም ወደ አልጋዬ ነው የሄድኩት....... አንዳንዴ መተኛት ብቻ ደስ ይል የለ....😌 የሚሆነውን ሁሉ ረስቶ ለጥ ማለት...... አላህን በምክንያት ብቻ አታመስግኑት ....ሁሌም ቢሆን ፈጣሪህን አትርሳ ወዳጄ.....ብዙ ጊዚ አላህን የምናስታውሰው ፈተና ውስጥ ስንሆን ብቻ መሆን የለበትም🙏 ✍ሂዲያ
نمایش همه...
.....🧕 እኔ ፀሀፊ ነኝ!!✍..... የምፅፈው የሆንኩትን፣መሆን ፈልጌ ያልሆንኩትን እና ወደ ፊት መሆን የምፈልገውን ነው። በፁሁፌ ውስጥም ሀዘን፣ደስታ፣እና የተደበላለቀ ስሜት ይነበባል....ብዕሬን አንስቼ ስፅፍ ከራሴ ጋር ሆኜ ወይም ከራሴ ጋር ተጣልቼ ሊሆን ይችላል.... በፅሁፌ ውስጥ የሆነ ልጅ አለ....ለብዙ ነገሮች ምሳሌ የሆነ ወንድ ....በሚቀያየር ስሜቴ ውስጥ አብሮኝ ያለ... የተሰማኝን ስሜት በእሱ ውስጥ የማስተላልፍበት .....እኔ ብዕር ስሆን እሱ ወረቀቴ የሆነ.... ፅሁፌ ስለ ብዙ ነገር ነው...ስለ እናት ፣ስለ ፍቅረኛ፣ስለ ጓደኛ ....አንዳንዴም ደሞ ስለ እራሴ ሊሆን ይችላል...ሁሉም ወሳኝ ነገሮች ናቸው....መኖርን ትርጉም ሊሰጡኝ ይችላሉ... ፀሀፊ መሆን መታደል ነው...የተሰማህን በወረቀት መስረዳት ትችላለህ....ታሪክህንም ማስቀመጥ ትችላለህ። ሂዲያ✍ @hidihebron
نمایش همه...
ታውቃለህ......ግን ያለምንም ምክንያት ነው የወደድኩህ ለምን ለሚለው ጥያቄ እንኳን መልስ ሳይኖረኝ።ለሌላውም ሰው ብቻ ሳይሆን እኮ ለእኔም የማይገባኝ ስሜት ነው ላንተ ያለኝ🥺 ግን ቀን አጎደለን አንተን ወዲያ እኔን ደሞ ወዲያ አደረገኝ። ምን አድርገን ነው ምንስ ነው ያጠፋነው እኔ እኮ አላውቅም!! የዛኔ ነው ሊቀጥል ያለው ያቋረጠው...ከዚያ በኃላ አልነጋም ከዚያ በሆላ ለእኛ አልነጋም በተለይ ደሞ ለእኔ 😔 ምናለ ግን አንዳንድ ሰዎች ጋር አብረን መኖር ባንችል እንኳን ያን ሰው አንዳንድ ቀን ብናገኘው እና ደስተኛ ብንሆን ምናለ....ለጥቂት ሰአት እንኳን አብረናቸው መሆን ብንችል..ግን ምን አለበት😞 ያው እኔ እንደሆንኩ መመኜት አያልቅብኝም። ደሞስ መች ይሠለቸኝና..ብቻ ችግር ከእኔ ችግር አለበት መሰለኝ...ስቃዬ በዛ ህመሜ ..እንባዬ ...ብቻ ህመም ብቻ ስቃይ ....ፈጣሪም አመረረ በእኔ ላይ አበዛው ቢሆንም ሁሉንም በልቤ ይዤ ....አፍኜዋለሁ...ግን መቼ እንደምተነፍሰው አላውቅም..ብቻግን ያመኛል ምኔን እንደሆነ አለማወቄ የብስ ያሳመኛል። በቃ ከአመታት በሆላ የጠፍው ህመሜ ዳግም ማገርሸቱን ብቻ ነው የማውቀው። እስካለሁ ይቀጥላል .........ግን ከሌለሁስ😭 ✍ሂዲ
نمایش همه...
አንተን መርሳት ከባድ ነው😔 ይገባኛል የኛን ኑሮ ያየነው እኛ ብቻ ነን...ያሳለፍነውን መከራ የምናውቀው እኛው ብቻ ነን...ተስፋ ቆርጠን ተስፋ አለን እያልን..አብረን ባልነበርንባቸው ቀናቶች አብረን እንዳለን አይደል እየኖርን ያለነው። እመጣለሁ ብለኸኝ ብዙ ጊዜ አልመጣህም ደርሻለሁ ብለኸኝ ብዙ ጊዜ አልደረስክም😔 እንድታወራ ፈልጌ ብዙ ጊዜ ዝም ብለሀል...ቢሆንም ግን... ቢሆንም ግን አንተን መተው ከባድ ነው...ተራራን እንደመግፋት ...በውሀ ላይ ከመራመድ የበለጠ ከባድ ሳቅህ ይሰማኛል..ጠረንህ ልቤ ውስጥ ሁሌም አለ።ሁሌም ያልመጣህባቸው ቀናቶች ከመጣህባቸው ቀናቶች ይበልጣሉ🥺ቢሆንም ግን አንተን መተው ከባድ ነው።ሁልጊዜም እኮ ሳልነግርህ ውዬ የምነግርህ ነገር ቢኖር እወድሀለሁ❤ ነው። አለም ላይ ብዙ አዲስ ነገሮች የሉም...የነበሩ ነገሮች ግን እንደቀጠሉ ናቸው። ብዙ ጥያቄዎችም መልስ የላቸውም...እና ለምን?ብዙ ሰዎች መጠየቅ ይወዳሉ? እኛ ደሞ ለአብዛሀኞቹ መልስ የለንም.....🥺 የውልህ ካልመጣህ እረዳሀለሁ አ.. ስትቀርብኝም እረዳሀለሁ አ...ዝም ብትለኝም እረደሀለሁ አ......😔 እኔም ግን .....😔......እኔም ግን......ከረሳውህ ተረዳኝ በርግጥ አንተን መርሳት ከባድ ነው። ካልተረሳሁም በቀር የምረሳህም አይመስለኝም🤕 ደሞ እኔ እልሀለሁ እብድ ብሆንም እውነታ አለኝ። ከነገርኩህ ያልነገርኩህ የለም🖤 ይቀጥላል......... ✍ሂዲያ 16/7/2014/
نمایش همه...
ለአንተ የፃፍኩት ደብዳቤ ። መችና እንዴት እንደፃፍኩት ግን እኔጃ...🙇‍♀ ከቀናቶች በኃላ ተመልሼ መጣሁ..እኔ አልሀምዱሊላህ በጣም ደና ነኝ። አንተስ ሂወት እንዴት ይዞሀል? ጥሩ ነው እንደምትለኝ ተስፋ አደርጋለሁ🙏 ትዝ ይልህ ከሆነ መጀመርያ የተጣላን ሰሞን...አንተን መርሳት ከባድ ነው ብዬህ አልነበር....😔አዬህ እውነቴን ነው።ከብዙ ቀናቶች በኃላም ዛሬም ልቤውስጥ አለህ. 🖤❤️🖤❤️🖤❤️🖤❤️🖤❤️🖤❤️🖤❤️🖤❤️🖤❤️🖤❤️🖤❤️🖤 ያ በሀጥያት ያደፈው ልቤ ውስጥ🖤ዛሬም አለህ። "ስለ ብርሃን ከነገረህ ይልቅ ብርሀንን ያሳየህን ሠው በህይወትህ አመስግን"🙏 ደሞ ሁል ጊዜ አንተ ሳታውቅና ስላንተ የሚያስብ እና የሚጨነቁ ብዙ ሰዎች አሉ🥺 እኔም ከእነሱ መሀል አንዷ ነኝ...... አንች ግን እንዴት ነሽማ በለኝ😢 አንች ጋርስ ምን አዲስ ነገር አለ ብለህ ጠይቀኝ¿¿ እኔ ጋራ ብዙ አዲስ ነገር አለ። በእርግጥ ብዙ ሰዎች በህይወቴ መተው ሂደዋል...🥺እኔም ብሆን ብዙዎች ጋር ሄጃለሁ..ያው አንተን ለመርሳት ብዬ ያላደረኩት የለም.....ግን አንተን መርሳት ከባድ ነው። ፍቅር ግን ምንድነው???? የፍቅርስ መለኪያው ምንድነው???? አንተስ ፍቅርን በምን ነው የለካኸው??? መስፈርትህስ ምንድን ነበር????? እኔጃልህ.....🤦‍♀ እናም በመጨረሻ ሁሌም አላህ ከምትፈራው ነገር ይጠብቅህ🙏ሠላምህንም ያብዛው....🙏 ✍ሂዲያ
نمایش همه...
ከጀርባ ፅሁፎቼ...∞∞∞ አንተ ስታስበው...............!!😒 ባለፈው ስታወራ ሰማሁ,,,,,,,ስሜን በመጥፎ ስታነሳው እሷኮ💁‍♂.. እንዲህ ናት ስትል ሰማሁ...በእርግጥ አልደነገጥኩም..ለምንስ አላልኩም!! ግን ገረመኝ የእውነት ገረመኝ....😔 @@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@ አንተ ስታስበው እኔ እንዲህ አይነት ሰው ነኝ እንዴ?!! ስልህ ስትለኝ የነበረው አይነት. አይን አይኔን እያየህ ንገረኝ🥺 በብዙ መከራ የገነባሁትን ስሜን ነበር!!በአንድ ንግግርህ ስትንደው የሰማሁት🤕አንተ ስታስበው ማን ከወደደው ጋር መኖርን አይመኝም..?ማንስ ከሚወደው መራቅን ይመርጣል..የምር እስኪ አስበው..?😔ማን አለ ክፉ ልሁን ብሎ የከፋ¿¿ማን አለ??እኔ ግን እብድ ባልሆን ይቆጨኝ ነበር!! "የምንወደውን ሰው ከፈተና እንጠብቀዋለን እንጅ እኛ አንፈትነውም" አበቃሁ🙏 ✍ሂዲያ
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.