cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ኢትዮጵያ ታበጽዕ እደዊሃ ሐበ እግዚአብሔር

✝️✝️ ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ÷ይህ ስለ ኦርቶዶክሳዊት ሀይማኖትና አስተምህሮ ሀሳብ የምንለዋወጥበት ቤት ነው። ✍️በዚህ ቻናል👉 ወረብ፣ሀይማኖታዊ መፃሀፍቶች÷ ዜማ÷ ቅዳሴ ÷ መዝሙሮች ÷ መንፈሳዊ ፎቶግራፍና ሌሎችም የተለያዩ የምትፈልጉትን መረጃ በጠየቁበት ፍጥነት እናደርሳለን። ሀሳብ፣አስተያየት እንዲሁም ጥያቄዎች ካሉበት ያናግሩን 👉👉👉 @Ethiopia_Orthodox_tewahdo_bot

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
946
مشترکین
+224 ساعت
+37 روز
-330 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ትገለጣላችሁ።" (ቆላ. ፫፡፩-፬) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዕርገቱ የተስፋ ቃል ኪዳን ሰጥቶ ነበር። ለምሳሌ “እኔ ብሄድ ይሻላችኋል፤ እኔ ካልሄድሁ ጰራቅሊጦስ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ከሄድሁ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ፡፡” (ዮሐ. ፲፮፡፲) ብሏል፡፡ እርሱ በአካል ስለሚለያቸው የሐዘን ሰሜት እንዳይሰማቸው የሚያጽናና መንፈስ እንደሚልክላቸው ከሞቱ አስቀድሞ አብ በስሜየሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል”(ዮሐ ፲፬፥፮) ብሎ ነግሯቸዋል። ከምድራዊ አስተሳሰብና ከስጋ መንፈስ እንዲላቀቁ እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ እናንተ ግን ኃይልን ከላይ እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ" ሉቃ ፳፬፥፵፱ ብሏቸዋል፡፡ ይህንን ተስፋ በማመን ጌታችን ሲያርግ ወደ ሰማይ ትኩር ብለዉ ይመለከቱ የነበሩት ደቀ መዛሙርት በሃምሳኛዉ ቀን መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸዋል። እኛም ዕርገቱን እያሰብን ዓይናችንን ወደ ሰማይ እናነሳለን። የራሳችንንም ዕርገት ተስፋ እያደረግን ልባችንን ወደ ሰማያዊዉ ህይወት ከፍ ከፍ እናደርጋለን። በክብር ያረገ አምላክ ከትንሣኤ ሙታን በኋላ ያለውን ዕርገታችንን የክብር ያድርግልን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር። የእግዚአብሔር አብ ጸጋ የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት የቅድስተ ቅዱሳን የንጽሕተ ንጹሐን እመቤታችን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ዕጸ መስቀሉ የቅዱስ በዓሉ የታላላቆቹ ቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት የቅዱሳኑ ሁሉ በረከት ረድኤት ጸሎት ምልጃ አይለየን፤ ስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!! 👇👇👇 👇👇👇 @ethiopia_orthodox_tewahdo @ethiopia_orthodox_tewahdo @ethiopia_orthodox_tewahdo 👆👆👆ይቀላቀሉ እና ያጋሩ👆👆👆
نمایش همه...
የጌታችን የአምላካችን የፈጣርያችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ_ክርስቶስ_ዕርገት ዕርገተ_እግዚእነ ዕርገት ከጌታችና ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ነው። “ዕርገት" የሚለው ቃል ዐርገ ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ከታች ወደ ላይ መውጣት፣ ክፍ ከፍ ማለት፣ ማረግ ማለት ነው። ዕርገት (Ascension) ሲባልም ማረግን፣ ከፍ ከፍ ማለትን፣ ወደ ላይ መውጣትን ያመለክታል። በዓለ ዕርገትም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም የነበረውን የማዳኑን ሥራ ጨርሶ ወደ ላይ መውጣቱና በቀደመ ክብሩ በአብ ቀኝ መቀመጡ የሚከበርበት በዓል ነው፡፡ ለዚህም መሰረት እንዲሆን አርዮስን ለማውገዝ በኒቅያ የተሰበሰቡት ቅዱሳን አበው “ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ... በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ…” ብለው ዕርገቱን በቅዱሳት መጻሕፍት ዋቢነት አስረግጠው ደንግገዋል። ዕርገቱ የትሕትና ሥራው የመፈጸሙ ምልክት ነው አምላካችን ምሉዕ በኩለሄ (ሁሉን የሞላ እና በሁሉም ቦታ የሚኖር) ነዉ። ስለዚህ ጌታችን በባሕርይው መውጣት መውረድ የለበትም:: 'ወረደ፣ ተወለደ ሲባል ፍጽም ሰው መሆኑን የትህትና ሥራ መፈጸሙን ከመናገር ውጪ ከዙፋኑ ተለየ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ዐረገ ወጣ ሲባልም ከሰማያዊዉ ዙፋኑ ተለይቶ ነበር ማለት አይደለም:: በምድር ላይ ሊሰራ ያለውን ሁሉ መፈጸሙን ያመለክታል እንጂ:: እንዲሁም ጌታችን በዕርገቱ ምክንያት ከቤተክርስቲያን የተለየበት ጊዜ የለም። ነገር ግን ዕርገቱ በሥጋዉ የተደረገዉን ዕርገቱን ያመለክታል። ይህም ዕርገት ቅዱስ ሥጋዉ በምድር የስበት ቁጥጥር (Gravitational force) የማይዘው ለመሆኑ አስረጅ ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ አምላካዊ ስልጣኑን ያሳያል። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገቱ በምድር ላይ የሚሠራውን የትሕትና ሥራ የመፈጸሙ ምልክት ነው። ዕርገቱም ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት “ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ/ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ (መዝ ፵፮፥፭፡፮) እንዳለው በታላቅ ክብር እልልታና ምስጋና ነው፡፡ ጌታችን የድል ዕርገትን ያረገው ወደ ባሕርይ አባቱ ቀኝ ነው፡፡ በእርሱ ዕርገት የጸጋ መንፈስ ቅዱስና የዳግም ምጽአት ተስፋዎች ተሰጥተውናል፡፡ የእርሱ ዕርገትም ለነፍሣችን ዕርገት / ለዕርገተ መንግሥተ ሰማያት/ አርአያ ሆኖናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ክርስቲያኖች በጻፈው ክታቡ ይህንን ሲያስረዳ “ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ጌታችንን በአየር እንቀበለው ዘንድ ከእርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን” (፩ተሰ. ፬፡፲፯) ብሏል። ቅዱስ ያሬድም ዝማሬ በተባለው መጽሐፍ የጌታችንን ማዳን ከፅንሰቱ ጀምሮ እስከ ዕርገቱ ብሎም እስከ ዳግም ምጽአቱ ከብሉያትና ከሐዲሳት እያጣቀሰ አምልቶና አስፍቶ በተናገረበት የምስጋና ክፍል “ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና፤ ለድንግል ዘፈትሐ ማኅፀና፤ ለደቂቀ እስራኤል ዘአውረደ መና፤ ውእቱኬ ዘአድኃና ለሶስና እም እደ ረበናት፤ ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና / በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ፤ የድንግልን ማኅፀን የፈታ፣ ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረደ፣ ሶስናን ከረበናት እጅ ያዳነ፣ በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ' ብሏል። 'ዐረገ' መባሉ የሌለበት ቦታ ኑሮ ካለበት ቦታ ወደ ሌለበት ቦታ ሔደ ማለት አይደለም፡፡ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ወደ ባሕርይ አባቱ መመለሱን፣ የማዳን ሥራውን መፈጸሙን፣ በሥጋ በክብር ማረጉን ለመግለጽ ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደመና ዐረገ ሲል በክብር ማረጉን፣ ልዕልናውን መግለጹ ነው፡፡ ደመና ክብሩ ልዕልናው ነውና። በደመና ዐረገ መባሉ በእመቤታችን ጀርባ መታዘሉን ለመግለጥ ነው። ደመና ተብላ የተገለጠችው እመቤታችን ድንግል ማርያም ናትና። ከማርያም በነሣው ሥጋ ዐረገ ማለት ነው። ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ “እነሆ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል። (ኢሳ.፲፱፥፩) ብሎ አስቀድሞ በትንቢቱ የተናገረላት ደመና እመቤታችን ናት። ሊቁ ቅዱስ ያሬድም “ደመናሰ ዘይቤ ይእቲኬ ማርያም እንተ ጾረቶ ዲበ ዘባና፤ ደመናስ የሚላት አምላክን በጀርባዋ የተሸከመችው ማርያም ናት” በማለት ያስረዳል። ስለዚህ በደመና ዓምድ ዐረገ ሲል ከድንግል ማርያም በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማይ ዐረገ ማለት ነው። እስከ ቢታንያም አወጣቸው። በዓለ ዕርገት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ከሚከበሩት በዓላት አንዱ ነው። በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን (ከበዓለ ትንሣኤ አርባኛው ቀን) አይለቅም። የጌታችን ዕርገት ከትንሣኤ በኋላ በአርባኛው ቀን (በስድስተኛው ሐሙስ) የሚከበረው ቅዱስ ሉቃስ በሐዋርያት ሥራ ላይ ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው" (ሐዋ. ፩፡፫) በማለት የጻፈውን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ቤተክርስቲያንም ይህንን ትምህርት ኪዳን ብላ ትጠራዋለች። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ለሐዋርያት የነገራቸው መጽሐፈ ኪዳን ይባላል፡፡ ዕርገቱም የተፈጸመው ስለ ምጽኣቱ ባስተማረበትና ዳግም ይመጣል ተብሎ በሚጠበቅበት በደብረ ዘይት ተራራ ነበር። ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ይህንን “እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ” (ሉቃ ፳፬፡፶) ብሎ በወንጌሉ እንዲሁም “በዚያን ጊዜ ደብረ ዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ እርሱም ከኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል የራቀ ነው" ብሎ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፩፡፩፥ አስፍሮታል፡፡ በልደቱና በትንሣኤው የተገኙትና ለሰው ልጆች መልካሙን ዜና ያበሰሩት ቅዱሳን መላእክት በዕርገቱም ተገኝተው ለአሥራ አንዱ ሐዋርያት የዳግም ምጽአቱን ነገር አሳስበዋቸዋል። ቅዱስ ሉቃሰ ይህንን ሲገልጽ “እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤ ደግሞም። የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው * (ሐዋ ፩፥፲-፲፩) ብሏል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም እንደተናገረው እርሱ ዳግም ሲመጣ ሐዋርያቱ ብቻ ያይደለ የወጉት ጭምር ያዩታል (ራዕ ፩፡፯)፡፡ ሐዋርያቱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ የጌታችን ዕርገት በመርቀቅ /በርቀት/ ሳይሆን ቀስ በቀስ ሐዋርያት እያዩት በመራቅ /በርኅቀት ነው። ቅዱስ ሉቃስ ይህንን ሲያስረዳ "ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው " (ሐዋ ፩፥፱) በማለት ገልፆታል። ይህም የሚያመለክተው የሚታይ የሚዳሰስ ሥጋን ይዞት እንዳረገ ነው። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ በቅዳሴው "በአካል ወደ ሰማይ ባረግህበት ዕርገትህ ላይ˚ እንዳለው በአካል ነው ወደ ሰማይ ያረገው። ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም በቅዳሴው "በዚያች ሥጋ በመለኮት ኃይል ወደ ሰማይ ወደ ቀድሞ አኗኗሩ ዐረገ ያለው ይህንን ለማመልከት ነው፡፡ ይህንን ሲያብራራ “ሕማም የሚስማማው ግዙፍ ሥጋን ተዋሕዶ ሳለ ከስቅለቱ አስቀድሞ በባሕር ላይ ከሔደ፣ ዛሬ ነፋስን ከፍሎ ሲያርግ ቢታይ ማንም ማን አይጠራጠር። ሥጋው
نمایش همه...
አልተለወጠምና“ በማለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞቱና ከትንሣኤው አስቀድሞ በውኃ ላይ እንደተራመደ ሁሉ፣ በለበሰው ሥጋ ወደ ሰማይ ማረግም እንደሚቻለው አስረድቷል ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈወርቅ፣ ክፍል ፲፫ ምዕ ፥፹፯፡፲፪-፲፫/። ቅዱስ ሉቃስም “እያዩት ከፍ ከፍ አለ” ማለቱ በእርግጥ ዕርገቱ በአካል እንደነበር ያስረግጥልናል፤ ምክንያቱም ሰው መለኮትን መመልከት አይችልምና ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ስለ ጌታችን ዕርገት “በደብረ ዘይት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሲመገብ እጁን በደቀ መዛሙርቱ ላይ አኖረ፤ እያንዳንዳቸውንም ባረካቸው ከዚያም የእሳት ደመና ተቀበለው፤ ከእነርሱም ሰወረው፤ በጨርቅ የጠቀለሉት ይህ ሥጋ በኪሩቤል ክንፎች ተጋረደ፤ በጒልበት ያቀፉት ይህ ሥጋ በእሳት ሠረገላ ተቀመጠ፤ በዚህ ዓለም የተራበና የተጠማ ይህ ሥጋ እህል መብላት፤ ወይን መጠጥን ውሃም መጠጣት ወደ ማይሻበት ወደ አርያም ከፍታ ወጣ፤ በሊቀ ካህናቱ አገልጋዮችና በጲላጦስ አደባባይ ራቁቱን የቆመ ይህ ሥጋ በምስጋና መብረቅ ተሸፈነ፤ በእሳት ደመናም ተጋረደ፤ ጉንጮቹን በጥፊ የተመታ ይህ ሥጋ ከፍ ከፍ አለ" ብሏል። ቅዱስ ማርቆስ የጌታችንን ዕርገት በገለጸበት አንቀጽ “ጌታችን ኢየሱስም ከተነጋገራቸዉ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፥ በአባቱም በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፡፡” (ማር. ፲፮፡፲፱) ብሏል፡፡ “ወደ ሰማይ” የሚለው ቃል ወደ ሰማየ ሰማያት ማለት ነው :: ይህም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በሚሠራበት ወቅት በጸለየው ጸሎት ውስጥ እግዚአብሔርን “በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ!” (፩ኛ ነገ. ፰፡፪፯) ብሎ በጸለየው ይታወቃል። “ዐረገ” የሚለውም ( መላእክት አሳረጉት አላለም በራሱ ኃይል ሥልጣንና ማረጉን ያሳያል፡፡ ከጌታችን በቀር በራሱ ኃይል ያረገ የለም፡፡ ሌሎች ቅዱሳን፡ ለምሳሌ ኤልያስ እና ሄኖክም ቢሆኑ እግዚአብሔር ዐሳረጋቸው እንጂ በራሳቸው ስልጣን ዐላረጉም ። ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ይህንን "የእግዚአብሔር ልጅ ግን ያለ መሰላል በሚንቦገቦግ የደመና ተን (ጉም) ዐረገ፤ መለኮቱ ይተጋለታልና ወደ አየራትም ነጥቆታልና፤ ነገደ መናብርት ሊያሳርጉት አልመጡም ርሱ ራሱ በመለኮቱ ኀይል አብን ተካክሎ በቀኝ በኩል ተቀመጠባቸው” ሲል ገልጾታል። ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም ስለ ዕርገት በተናገረበት አንቀጽ ''በራሱ ሥልጣን ተነሣ፤ ርሱን ያስነሣው ማንም አይደለም፤ በሚያርግም ጊዜ ማንም ርሱን ያሳረገ አይደለም፤ ኤልያስን አስመልክቶ ዕርገቱ በጌታ አማካይነት የኾነ ነውና እንዲያርግ ያደረገው ጌታ ነው፤ ከዚኽም የተነሣ በሠረገላ እና በእሳት ፈረስ የከበረ ሥነ ሥርዐት ተደረገለት (፪ኛ ነገ ፳፥፲፩)፤ ምክንያቱም ወደ ዐረገበት ቦታ በራሱ ማረግ አይቻለውምና፤ የጌታችን ግን እንደተጻፈው ተለየ፤ ወደ ላይ ለመነሣት ምንም ዐይነት መንኲራኲር አላስፈለገውም፤ በአንድ ቦታ በተወሰነ ጊዜ የሚቀመጡት ሰው በአጋዥ መውጣት ያስፈልገዋል፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ ብቻ ነውና፤ የእግዚአብሔር ልጅ ግን ራሱ እግዚአብሔር ነውና መንኰራኵር አያስፈልገውም” በማለት የእርሱ ዕርገት በራሱ ስልጣን መሆኑን አብራርቶታል። በአብ ቀኝ ተቀመጠ። ጌታችን በዕርገቱ በአብ ቀኝ ተቀመጠ” መባሉ ለእግዚኣብሔር ግራና ቀኝ ታችና ላይ ኖሮት ሳይሆን ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን በስልጣን እኩል መሆናቸዉን የሚያስረዳ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ ፪፡፯ "ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰዉም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ዝቅ አደረገ። እንደ ሰዉም ሆኖ ራሱን አዋረደ” የሚለዉ ቃል ጌታችን በሥጋዌው ራሱን በፈቃዱ ዝቅ አደረገ እንጅ በክብር ከአብ ከመንፈስቅዱስ እንደማይለይ ያስረዳናል፡፡ በቤተክርስቲያን ኣስተምህሮ መሰረት በአብ ቀኝ ተቀመጠ ማለት በሥልጣን አንድ መሆንን ያሳያል፡፡ ስለዚህም ነቢዩ ዳንኤል በትንቢቱ በሌሊትም ራእይ አየሁ፤ እነሆም የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ፤ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘለዓለም ግዛት ነው፣ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።” (ዳን. ፯፡፲፫-፲፬) ሲል ተናግሯል። ስለዚህ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ስንል በክብር በልዕልና ከአብ ጋር እኩል ነው ማለታችን ነው። ይህም ከተዋሕዶ በፊት ደካማ፣ በደለኛ እና ውርደት ይስማማው የነበረው የእኛ ሥጋ ከተዋሕዶ በኋላ ጸጋን የሚያድል፣ እውነተኛ ፍርድን የሚያደርግ፣ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ሥልጣን ያለው እውነተኛ ፈራጅ አምላክ እንደሆነ ለመግለጽ ነው እንጂ በመለኮቱስ ከአብ ሥልጣን ዝቅ ያለበት የዐይን ጥቅሻ ያህል ጊዜ እንኳ የለም። “ቀኝ” የሚለው ቃል ኃይልን ቅድስናን ወይም ክብርን የሚያመለክት ነው ። ኃይልን ከመግለፅ አኳያ ነቢየ እግዚኣብሔር ክቡር ዳዊት "የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች” (መዝ. ፩፲፯፡፲፭) ሲል ተናግሯል፡፡ ክብርም ከመግለጽ አኳያ "ጻድቃንን በቀኙ ያቆማቸዋል" (ማቴ. ፳፭፡፴) እንላለን። ስለዚህም "የእግዚአብሔር ቀኝ ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ፣ ጽድቅ ፣ ክብር ማለት ነው። ይህም በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ያህልም ያህልም የሚከተሉትን ማየት ይቻላል፡፡ ጌታ ጌታዬን፡ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው። (መዝ. ፻፱፡፻) ከእንግዲህ ወዲህ የሰውን ልጅ በኀይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይ ደመናም ሲመጣ ታዩታላችሁ አለው። (ማቴ ፳፮፥፳፬) እነሆ፥ ሰማይ ተከፍቶ የሰው ልጅም በእግዚኣብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ። (ሐዋ ፯፡ ፶፮) ኀጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፣ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፡፡ (ዕብ ፩፡፫) በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ (ዕብ ፰፡፩) እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና፡፡ (ዕብ ፲፪፡፱) የጻድቃንን ዕርገት ያስገነዝብ ዘንድ ዐረገ። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤው በተስፋ ለምንጠብቀው ትንሣኤያችን አርአያ እንደሆነው ዕርገቱም ለዕርገተ ነፍሳችን፣ መንግሥተ ሰማያትን ለመውረሳችን አርአያ ምሣሌ ነው። እግዚአብሔር ወልድ የጻድቃንን ዕርገት ያስገነዝብ ዘንድ ዐረገ። ከእኛ የተዋሐደዉን ሥጋ በዕርገቱ ከአባቱ ቀኝ በእግዚአብሔርነቱ አስቀመጠው። እንግዲህ በዕርገቱ የእኛን ሥጋ ከመላዕክት ሁሉ በላይ አክብሮ በሰማያት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስተካክሎ ካስቀመጠውማ እንደምን እኛን መንግሥተ ሰማያትን አያወርሰንም ሊባል ይችላል? (፩ተሰ. ፳፡፲፯) ክርስቲያኖች በሰማያት ስፍራ ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረን እንደምንቀመጥ የጌታችን ዕርገት ያረጋግጥልናል። የጌታችን ዕርገት ዓይነ ልቡናችንን እሱ ወደ አለባት መንግስተ ሰማያት ይመራል። ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ሲያስረዳ እንዲህ ሲል ይላል፡፡ "ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ በአለበት በላይ ያለውን ሹ፡፡ የላይኛውን አስቡ ፤ በምድር ያለውንም አይደለም። እናንተ ፈጽማችሁ ሞታችኋልና፤ ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋራ በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰወረች ናትና። ሕይወታችሁ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ ያንጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በፍጹም ክብር
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
🌼🌹🌹🌼🌹🌹🌹🌹🌼🌹🌹🌹🌼 እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለፈጣርያችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ዕርገቱ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የቅዱስ በዓሉ በረከት አይለየን አሜን።🌹🌼🌼🌻🌻🌻🌹🌻🌹🌻🌼🌼🌹🌹🌹 መልካም በዓል 👇👇👇 👇👇👇 @ethiopia_orthodox_tewahdo @ethiopia_orthodox_tewahdo @ethiopia_orthodox_tewahdo 👆👆👆 ይቀላቀሉ እና ያጋሩ 👆👆👆
نمایش همه...
☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘ ሥርዓተ ማኅሌት ዘበዓለ ዕርገት ☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️ የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ" ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCmahlet @EOTCmahlet መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለመታክፍቲክሙ መሠረተ ዓለም እለ ፆሩ: ኖትያተ ኖኅ ሥላሴ ወዕፀወ ዐባይ ሐመሩ: ዲበ መንበርክሙ ሰብአ ሶበ አምላከ ነፀሩ: ኪሩቤል ወሱራፌል ታሕተ እገሪሁ ገረሩ: እስመ ለሊሁ አዘዘ ወእሉ ተፈጥሩ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዚቅ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለአብ ንሴብሕ: ሃሌ ሉያ ለወልድ: ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ: ዓቢይ ዜማ ተሰምዓ በሰማይ ዘመላዕክት ግናይ: እንዘ የዓርግ ወልድ ዲበ መንበሩ: ኲሎሙ መላዕክት ትንሣኤሁ ዘመሩ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ወረብ ዓቢይ ዜማ ተሰምዓ በሰማይ ዲበ መንበሩ እንዘ የዓርግ ወልድ/፪/ ኲሎሙ መላዕክት ትንሣኤሁ ዘመሩ መላዕክት ሱራፌል ወኪሩቤል/፪/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዘጣዕሙ:- ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ: ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ: እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዚቅ ኦ ምዕራግ እምድር እስከ ሰማይ: ወብኪ ተሐደሰ ቀዳሜ ኲሉ ፍጥረት። @EOTCmahlet ወረብ ኦ ምዕራግ ደብረ ኃይል እምድር እስከ ሰማይ/፪/ ወብኪ ተሐደሰ ቀዳሜ ኲሉ ፍጥረት #እገሌ/፪/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዓዲ (ወይም) ዚቅ ዓርገ ሰማያተ በዓምደ ደመና: ለድንግል ዘፈትሐ ማኅጸና: ለደቂቀ ፳ኤል ዘአውረደ መና: ዓርገ ሰማያተ በዓምደ ደመና። @EOTCmahlet @EOTCmahlet መልክዐ ኢየሱስ ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሃላ ዘኢይሔሱ: ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ: ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሱ: አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቌጸል በርእሱ: አሕጉረ ፀር ወረሰ ኢያሱ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዚቅ አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት: ወይትረኃዋ ኆኃት እለ እምፍጥረት: ወይባዕ ንጉሠ ስብሐት: ፍኖተ ግበሩ ለዘዓርገ እንተ ዓረብ እግዚአብሔር ስሙ: ወተፈሥሑ በከመ ዳዊት ተፈሥሐ ሶበ ተአቱ ታቦተ አምላከ ፳ኤል ካህናት አተወት ጽዮን ውስተ መካና። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ወረብ አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት ወይትረኃዋ ኆኃት እለ እምፍጥረት/፪/ ይባዕ ንጉሠ ስብሐት/፬/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዓዲ (ወይም) ነገሥተ ምድር ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር: ወዘምሩ ለአምላክነ: ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዓርገ ውስተ ሰማይ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet መልክዐ ኢየሱስ ሰላም ለአጻብኢከ አጻብዓ አዳም ዘተኬነዋ: ወነቀለ ዐፅመ በእንተ ሕይወታ ለሔዋ: ኢየሱስ ክርስቶስ አመ ተለዓልከ እምድረ ጼዋ: ለገነተ ጽድቅ ዘእደ ሱራፊ ሐጸዋ: ቤዛ ኃጥአን ኲሎሙ ደምከ አርኃዋ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዚቅ ዓርገ ውስተ አርያም ጼዊወከ ጼዋ: ወወሃብከ ጸጋከ ለዕጓለ እመሕያው። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ወረብ ዓርገ "ውስተ አርያም"/፪/ ጼዋ ጼዊወከ/፪/ ወወሃብከ "ጸጋከ"/፪/ ለዕጓለ እመሕያው/፪/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዓዲ (ወይም) ተለዓልከ እግዚኦ በኃይልከ: ንሴብሕ ወንዜምር በጽንዕከ: እግዚኦ መኑ ከማከ: ወዓርገ ሰማያተ ኀበ አቡሁ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet መልክዐ ኢየሱስ ሰላም ለዕርገትከ ዘኢይትረከብ መጠኑ: ወለንብረትከ ሰላም ለአቡከ ውስተ የማኑ: ኢየሱስ ክርስቶስ እለ ኪያከ ተአምኑ: ቅዱሳነ ዘእምኃቤከ ወንጹሐነ ይኩኑ: ጰራቅሊጦስሃ መንፈሰከ ፈኑ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዚቅ ዓርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት: ወነበረ በየማነ አቡሁ: ዳግመ ይመጽእ በስብሐት: ይኮንን ሕያዋነ ወሙታነ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ወረብ "ዓርገ በስብሐት"/፪/ ውስተ ሰማያት/፪/ ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት/፪/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዓዲ (ወይም) ለዘዓርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት: ተኮነኑ ሎቱ መላዕክት ወኲሉ ፍጥረት። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ምልጣን ዮም ፍሥሃ ኮነ በእንተ ዕርገቱ ለክርስቶስ: እምድኅረ ተንሥአ እሙታን በአርብዓ ዕለት: በይባቤ ወበቃለ ቀርን: አማን መንክር ስብሐተ ዕርገቱ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet አመላለስ አማን በአማን/፬/ መንክር ስብሐተ ዕርገቱ/፬/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet እስመ ለዓለም ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ: አዓርግ ሰማየ ኀበ አቡየ ወአቡክሙ: ኀበ አምላኪየ ወአምላክክሙ: ዘንተ እንከ ይቤሎሙ ዓርገ ውስተ ሰማያት: ካዕበ ይመጽእ በዘዚአሁ ስብሐት: ሠርጎሙ ለሐዋርያት ብርሃኖሙ ለእለ ውስተ ጽልመት: መድኃኔ ነገሥት ክብሮሙ ለመላዕክት: ኖላዊሆሙ ለአሕዛብ ለከ ስብሐት። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዓዲ አውጽኦሙ አፍአ እስከ ቢታንያ: አንሥአ እዴሁ ወባረኮሙ: ወይቤሎሙ አንትሙ ሰማዕትየ: አነ እፌኑ ተስፋሁ ለአቡየ ላዕሌክሙ: አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እስከ ትለብሱ ኃይለ እምአርያም። @EOTCmahlet አመላለስ: አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም : እስከ ትለብሱ ኃይለ እምአርያም። 🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCmahlet👈 👉@EOTCmahlet👈 👉@EOTCmahlet👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCmahlet # Join & share # መዝሙረ ዳዊት 8/9/2016 ከምሽቱ 2:00-3:00 ➡️ለመማር ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ 💠💠💠💠💠 https://t.me/mezmu85 ለበለጠ መረጃ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ https://t.me/p09Geez
نمایش همه...
ዋዜማ ሃሌ ሉያ አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት: ወይባዕ ንጉሠ ስብሐት: ወረዳ ህየ አምላክ ምስለ ኃይል: ወሠበረ ኆኃተ ብርት: ወቀጥቀጠ መናሥግተ ዘሐፂን: ነአምን ሕማሞ ለዘኢየሐምም: ተገምረ ዘኢይትገመር: ኃጢአተነ ነሥአ ዘአልቦ ኃጢአት: ዓርገ ወልድ በስብሐት ውስተ ሰማያት። በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ ወዕርገቱ ዮም ሰማያት በስብሐት ምስለ መላእክት ወዕርገቱ ዮም ሰማያት። @Memhir_sirak
نمایش همه...
ዋይዜማ ዘዕርገት ዎበ፩ -1623053161497.mp37.10 MB