cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Kesis Getnet Aytenew

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
2 506
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-127 روز
-4930 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
6👍 3
+++ ለእመ ኮነ እሑድ በጳጉሜን +++ #መዝሙር "ከመ እንተ መብረቅ" በል ❖ የዕለቱ መልእክታት፣ ምስባክና ወንጌል [የዓመቱ መጨረሻ ግጻዌ] መልእክታት:- ➊. ፩ኛ ቆሮንቶስ ፩ : ፩ - ፲ (1:1-10) ➋. ፪ኛ ጴጥሮስ ፫ : ፲ - ፍጻሜ (3:10-ፍጻሜ) ➌. የሐዋ/ሥራ ፱ : ፩ - ፲ (9:1-10) + ምስባክ ዘቅዳሴ እግዚአብሔርሰ ገሐደ ይመጽእ። ወአምላክነሂ እያረምም። እሳት ይነድድ ቅድሜሁ። ትርጉም:- እግዚአብሔር ግልጽ ሆኖ ይመጣል። ዝምም አይልም። እሳት በፊቱ ይነድዳል። (መዝ ፵፱ : ፪ /49 : 2) + ወንጌል ዘቅዳሴ የሉቃስ ወንጌል ፲፯ : ፲፩ - ፍጻሜ /17:11-ፍጻሜ ፲፩ ወደ ኢየሩሳሌምም ሲሔድ በገሊላና በሠማርያ መካከል አለፈ። ፲፪ ወደ አንዲት መንደርም ሲገባ በሩቅ የቆሙት አሥር ለምጻሞች ተገናኙት፤ ፲፫ እነርሱም እየጮኹ። ኢየሱስ ሆይ፥ አቤቱ፥ ማረን አሉ። ፲፬ አይቶም። ሒዱ፥ ራሳችሁን ለካህናት ዐሳዩ አላቸው። ፲፭ እነሆም፥ ሲሔዱ ነጹ። ከእነርሱም አንዱ እንደ ተፈወሰ ባየ ጊዜ በታላቅ ድምጽ እግዚአብሔርን እያከበረ ተመለሰ፥ ፲፮ እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም ሣምራዊ ነበረ። ፲፯ ኢየሱስም መልሶ። አሥሩ አልነጹምን? ዘጠኙስ ወዴት አሉ? ፲፰ ከዚህ ከልዩ ወገን በቀር እግዚአብሔርን ሊያከብሩ የተመለሱ አልተገኙም አለ። ፲፱ እርሱንም። ተነሣና ሒድ፤ እምነትህ አድኖሃል አለው። ፳ ፈሪሳውያንም። የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች ብለው ቢጠይቁት፥ መልሶ። የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም፤ ፳፩ ደግሞም። እነኋት በዚህ ወይም። እነኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው። ፳፪ ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ። ከሰው ልጅ ቀኖች አንዱን ልታዩ የምትመኙበት ወራት ይመጣል አታዩትምም። ፳፫ እነርሱም። እነሆ በዚህ፥ ወይም። እነሆ በዚያ ይሉአችኋል፤ አትሂዱ አትከተሉአቸውም። ፳፬ መብረቅ በርቆ ከሰማይ በታች ካለ ከአንድ አገር ከሰማይ በታች ወዳለው ወደ ሌላ አገር እንደሚያበራ፥ የሰው ልጅ በቀኑ እንዲህ ይሆናል። ፳፭ አስቀድሞ ግን ብዙ መከራ እንዲቀበል ከዚህም ትውልድ እንዲጣል ይገባዋል። ፳፮ በኖኅ ዘመንም እንደ ሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመን ደግሞ እንዲሁ ይሆናል። ፳፯ ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ይበሉና ይጠጡ ያገቡና ይጋቡም ነበር፥ የጥፋት ውኃም መጣ ሁሉንም አጠፋ። ፳፰ እንዲሁ በሎጥ ዘመን እንደ ሆነ፤ ይበሉ ይጠጡም ይገዙም ይሸጡም ይተክሉም ቤትም ይሠሩ ነበር፤ ፳፱ ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ግን ከሰማይ እሳትና ዲን ዘነበ ሁሉንም አጠፋ። ፴ የሰው ልጅ በሚገለጥበት ቀን እንዲሁ ይሆናል። ፴፩ በዚያም ቀን በሰገነት ያለ በቤቱ ያለውን ዕቃ ሊወስድ አይውረድ፥ እንዲሁም በእርሻ ያለ ወደ ኋላው አይመለስ። ፴፪ የሎጥን ሚስት አስቡአት። ፴፫ ነፍሱን ሊያድን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም የሚያጠፋ ሁሉ በሕይወት ይጠብቃታል። ፴፬ እላችኋለሁ፥ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሁለተኛውም ይቀራል። ፴፭ ሁለት ሴቶች በአንድ ወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች ሁለተኛይቱም ትቀራለች። ፴፮ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሁለተኛውም ይቀራል። ፴፯ መልሰውም። ጌታ ሆይ፥ ወዴት ነው? አሉት። እርሱም። ሥጋ ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ አላቸው። + ቅዳሴ ~ ያዕቆብ ዘሥሩግ (ተንሥኡ) - በግዕዝ ዜማ © Kesis Getnet Aytenew @ ጳጒሜን 2015 ዓ.ም _______ + ቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/kesisgetnetaytenew + ቴሌግራም መወያያ፦ https://t.me/gitsawie
نمایش همه...

3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዐውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ ዐውደ ዓመት ንዒ ማርያም ለምሕረት ወሣህል። እዛኝ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረድኤት አትለየን። ቸር ዐውደ ዓመት ታድርግልን። ሰላሙን ያድለን። አሜን።
نمایش همه...
13👍 1
የእግዚአብሔር ቤተ-ሰቦች እንዴት ሰነበታችሁልኝ? እንኳን ለዐዲስ ዓመት ዋዜማ በቸርነቱ አደረሳችሁ። መጭውን ዓመት የሰላም ያድርግልን። ከአንድ ወር በላይ ከዚህ ሰፈር ጠፍቼ ነበር። የጠፋሁት ኢንተርነት በመዘጋቱ ምክንያት መሆኑን እያሳወቅሁ አሁንም ሁኔታዎች እስከሚስተካከሉ ድረስ በትዕግሥት እንድትጠብቁኝ በፍቅር እጠይቃለሁ። ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር ሰላሙን ያብዛልን።
نمایش همه...
14👍 2
ማንም እየተነሣ የሚጐማምደው ቀኖና የለንም። ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል፣ ሰንሰለቷን ለመቊረጥ ስትነሣ እንዲህ ተቆርጠህ ትጣላለህ። ውግዘቱ ተገቢ ነው። ልብ ግዙና በይቅርታ ተመለሱ!
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ መልእክት የቅዱስነታቸው አይደለም፤ #ተረጋጉ!!! አጀንዳ ማስቀየሻ መሆኗ ነው። ተነቃቅተናል! ያ ደግ አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ (ከሣቴ ብርሃን) በዕለተ ቀኑ መፍትሔ ያመጣል!! እስከዚያው በዝግታ ሆነን ሲኖዶሳችን የሚያስተላልፈውን ጥብቅ መልእክት እንጠባበቅ! የሐሰት ዜና የሚረጩትን እየሰማን አንደናገጥ! ሐሰት ምንጊዜም ሐሰት ነው።
نمایش همه...
መጽሐፍ ጸሐፊውን ይመስላል። ጸሐፊው ረብ ከሌለው መጽሐፉም ረብ የሌለው ባዶ ወረቀት ይሆናል። በጸሐፊው መጽሐፉ ይታወቃል። "ይደልዎ ለዘያነብብ ቅድመ ይዝክር ለበዓለ መጽሐፍ" ይልብሃል ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ!
نمایش همه...
በሕገወጥ መንገድ ከተሾሙ የሕወሓት 'ጳጳሳት' መካከል አንዱ በከባድ የመኪና አደጋ ተጐድተው ተኝተዋል። ዛሬ ደግሞ ብዙ ቦታዎች በመሬት መንቀጥቀጥ እየተናጡ ነው። ከተረዳነው ይህ የእግዚአብሔር ቊጣ ነው!
نمایش همه...
እግዚአብሔር በሚያውቀው ይህን Video ስመለከት እያለቀስሁ ነበር። ከዚህች ሕፃን ጀርባ መዘመር እና ማመስገን የሚፈልጉ በጣም በርካታ ልዩ ፍላጐት ያላቸው ወገኖች እንዳሉ አንዱ ማሳያ ነው። እኔ በበኲሌ በአድናቆት ደጋግሜ ተመልክቸዋለሁ። ልጅቱም እየቊነጠነጠች ስታመሰግን ተመልክቼ እንባዬ አልቆመልኝም። አዘጋጁ ኮሚዲያን እሸቱ መለሰ ሊመሰገን ይገባል። ድንቅ ነገር ነው ያሳየን። የዲ/ን ቴዎድሮስ ዮሴፍን ጉልበት ዝቅ ብሎ ሲስም ደግሞ ትሕትናው ግዘፍ ነሥቶ ታይቷል። ዲ/ን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ጐንበስ ብሎ የሕፃኗን እጅ ሳመ፣ እሸቱ መለሰ ደግሞ የዲ/ን ቴዎድሮስ ዮሴፍን ጉልበት ዝቅ ብሎ ሳመ። ልዩነቱ ግልጽ ነው! በነገራችን ላይ ዘማሪው ጥሪውን አክብሮ መገኘቱ መልካም ነው ባይ ነኝ። ነገር ግን ጥያቄ አለኝ፦ ፩ኛ. መሥዋዕት ነው። "ለከ እሠውእ መሥዋዕተ ስብሐት" እንዲል ክቡር ዳዊት። በዚያም ላይ ሚልዬኖች የሚመለከቱት መርሐ ግብር እንደመሆኑ መጠን ነጠላ መልበስ ነበረበት። እርቃኑን ሲዘምር ማየት ያሳፍራል! ይኼ ለምን ሆነ? ፪ኛ. መዝሙሩ ኦርቶዶክሳዊ ለዛ አለው ወይ? ይኸው መዝሙር "በድንኳኔ ዝማሬዬ ብዙ ነው" የሚለው መዝሙር ከግጥም እና ከዜማ አንጻር ኦርቶዶክሳዊ ላሕይ አጥቼበታለሁ። ደግሞም ከእነዚያ "ፍኖተ ጽድቅ" ከሚባሉት የተሐድሶ ጨፋሪዎች ጋር አብሮ 'ሲዘምረው' የነበረ ዘፈ-መዝሙር ነው። እኔ በበኲሌ ቀጥ ያለ አካሔድ ስለምሻ የልቤን አውጥቼ ጽፌያለሁ። [የግል ምልከታዬ ነው!] © Kesis Getnet Aytenew
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.