cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ኢማሙ አቡ ሀኒፋ(ኢማሙል አዕዞም)

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላህ ወበረካቱ የዚህ channel ቀዳሚ እና ዋነኛ አላማው ስለሃነፍይ መዝሀብ ፊቂሆች፣የተለያዩ ሃዲሶች.. እና ትምህርት አዘል የሆኑ ኢስላማዊ ታሪኮችን የምናስተላልፍበት ቻናል ነው ያላችሁን ማንኛውም አስተያየት ሆነ ቅሬታ 👉👉 @AmuAmii በዚህ መልኩ ልታደርሱን ትችላላቹ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
365
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ኢማሙ አቡ ሀኒፋ(ኢማሙል አዕዞም) አሰላም አሊኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ በትዊተር ስለ አንድ ሰው ታሪክ አያየሁ ነበር እና እሄን ታሪክ ሁሉም ሰው እንዲሰማው በእውነት እፈልጋለሁ ፣እና ልብ ቡሎ ሚያዳምጥ ጆሯችሁን ስጡኝ በአረብኛ ነው ግን "ኢንሻአላህ" የምችለውን ሁሉ እሞክራለሁ ከመጀመራችን በፊት አንድ ነገር ማለት የምፈልገው ነገር አለ። ሁለት ዓይነት ሕልሞች አሉ- ከአላህ (ሱ.ወ) የሆነ ህልም እና ከሸይጣን የሆነ ህልም ከአላህ ዘንድ ያሉ ሕልሞች ምናልባት ከመጥፎ ነገር ያስጠነቅቁዎታል ወይም አስደሳች ዜና ይሰጡዎታል እናም አንዳንድ ጊዜ ሙስሊም ሲሞት እና ዕዳ ሲኖርባቸው በህልም መልክ ለ ቤተሰብ አልፎም ለ ጌደኛ ምልክት በሚሆን መልኩ በህልም ይመጣል ወደ ታሪኩ እንግባ ባለታሪኩ ሲናገር እንዱህ በማለት ይጀምራል "እኔ  የ21 አመቴ ወጣት ስሆን ጓደኛዬ ከጥቂት ወራት በፊት በመኪና አደጋ ህይወቱ አለፈ" አላህ ያራሃመው - " መልካም ‎ ስነምግባር ነበረው የማይወደውም የለም ወላጆቹ ጭምር እና ለሁሉም ያለውን ክብር፣ ደግነት እና መልካም ስነምግባር ሁሉም ይመሰክራል።" "በሞቱ ሁሉም ሰው ተደናግጧል፣ ማለት ምንችለስ  አልሀምዱሊላህ ብቻ ነው። እሱ ከሞተ በኋላ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ እንደተሰቃየ እና በጀሃነም እንደተቃጠለ ህልሜ አየሁ። በአላህ እምላለሁ ሁል ጊዜ  ባየሁት ነገር በጣም እየፈራው ነው ከእንቅልፌ የምነቃው። "እና ለምን እንዲህ እንደሆነ አላመንኩም "እውን ግን ይህ ነገር እሱ ላይ እየሆነ ነው?" እራሴን እጠይቃለው በአላህ እምላለሁ። ሁሉም የሚያቀው ሰው ስለበጎነቱ ይመስክር ማንም ሰው ስለሱ መጥፎ ነገር የማውራት አቅም አየኖረውም , ቅዠቶቹ በተደጋጋሚ መጡብኝ እርዳታ ፈልጎ ይመስላል.. የሰማያትንና የምድርን ፈጣሪ በሆነው አላህ እምላለሁ ጩኸቱ ትክክል እንዳልነበረ፣ ጩኸቱ በጣም አስፈሪ ነበር ከአእምሮዬ ሊጠፋ አልቻለም ለሱ ይሆን ዘንድ ሶደቃህ ጃሪያህን ስጠሁ ዱዐም አረኩለት ምንም አይነት ወንጀል ቢሰራ ምናልባት አላህ እሱን ይቅር ይለዋል። በማለት ነገር ግን ምንም ነገር ባረግ ምንም ለውጥ አልመጣም ምንም አልተፈጠረም። ቅዠቶቹ ሊለዩኝ አልቻሉም። "የተሰቃየበት አሳፋሪ ምስል በአእምሮዬ ተቀርቅሯል  አንድ ሰይድ ከጆሮውና ከአፉ እንዲሁም ከጥፍሩ ስር ወጣ። ሰይድ ሚባለው ፈሳሽ ነገር ሲሆን ከ ደም ጋር የተቀላቀለ ነገር  ነው." እሱ ነገር ከአእምሮዬ  ሊጠፋ አልቻለም "መተኛትን ጠላው እሱን ሲያሰቃይ ላለማየት እንቅልፌን አልተኛም ነበር ዱዓ እና ሶደቃ በስተቀር ምንም  ነገር ማረግ አልቻልኩም ወደ ሼክ መሄድ ፈልጌ ነበር እነዚህ ሁሉ ምን እንደሆኑ ንገረኝ ህልሞች ያብራራሉ? ብዬ ለመጠየቅ ግን ሁሉም ከሸይጣን ብቻ እንደሆነ እና እሱ እንዳልሆነ ተስፋ አድርጌ በመቃብሩ ውስጥ እየተሰቃዩ አይደለም በማለት ሼኽ ጋር መሄዱን ተውኩት ። ከዚያ ከሁለት ቀን በኋላ እሱ እየተሰቃየ  ቅዠት አየው ወደኔም መጣ" ሁለት ግዙፍ ፍጡሮች አፅም ወዳለበት እና ሰዎች ወደሚቀጠበት ቦታ ይጎትቱታል። እዛም ያሰቃዩታል የቀለጠ ብረት በጆርሮው ይጨምሩበታል በሰቀቀን ይጮሀል በድምፁ ውስጥ አስከፊ ህመም ይታያል እጆቹ ተቃጥለዋል እንዴት ብዬ ፈራሁ አሰቃቂ ነበር" በመጨረሻም በህልም አናገርኩት፡ "ስሙን ጠርቼ ለምን እንዲህ ያደርጉብሃል? ወላጆችህን ስታከብር እና ሰላትህን ስትጠብቅ ለምን እንዲህ ያደርጋሉ? ምን አይነት ኃጢአት ብሠራ?" ነው አነጋገረኝ እና እንዲህ አለኝ፡ "ሙዚቃ ያ"* ሙዚቃ! ከሞትኩ በኋላ  መቃብር ውስጥ ከገባሁ በኋላ ቀብሬ ውስጥ እየተሰቃሁ ያለሁት ዘውታሪ በሆነ ወንጀል ነው ሁሌ እንደተሰቃየሁ አንድም ቀን እረፍት አላየሁም እሄ ሁላ በ ሙዚቃ የተነሳ ነው አለኝ "ይህን ብቻ ነው የማስታውሰው ከዚያም እንደገና ጎተቱት። የእሱ እይታ ልቤን ሰበረው ። የስቃይ  ጩኸት ነበር ሚጮሀው በየምሽቱ ባንኜ እንድነቃ የደርገኝ ነበር፣ ኃጢአቱ ሙዚቃ መሆኑን አወኩኝ ። ነገር ግን ዘውታሪ የሆነ ወንጀል ሲል አልገባኝም ምን ማለቱ ነው? ለቀናት ስለሱ እያሰብኩ እራሴን አጨናነኩኝ " ከዚያም አልሀምዱሊላህ አንድ የ Instagram አካውንት እንበረው አስታወስኩ በዛ ላይም ዘፈኖች፣ ሙዚቃ፣ ይለቅ ነበር ምን ያህል ተከታይ እና ላይክ እንደለው ሳይ ልቤ ተሰበረ ማንም ግን መሞቱን አያውቁም!! ዘውታሪ የሆነ ወንጀል ሲለኝ እሄን ማለቱ ነው ሰደቀቱል ጃሪያ ወይም ዘውታሪ የሆነ ሰደቃ እንዳለ ሁሉ ዘውታሪ የሆነ ወንጀል አለ ሚለቃቸውን ዘፈኖች ሰው ባዳመጠው ልክ ነበር እሱ ወንጀል ሚያገኘው በዛም ሚቀጣው በጣም ያሳዝናል ነገር ግን "ስለ እሱ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም ስለ ይለፍ ቃሉ(Password) ፣ ኢሜሉ ምንም ማቀው ነገር አልነበረም ነገር ግን እሱ አሁንም እየተሰቃየ እነደሆነ ሳስበ መፍትሄ  ፍለጋ ሄድኩ። ነገር ግን ወላሂ ምንም መፍትሄ ማግኘት አልቻልኩም በእነዚህ ቀናት ውስጥ እፎይታ አግኝቼ አላውቅም ነበር መተኛት እሰኪያቅተኝ ድረስ እጨነቅ ነበር የኔ ጥፋት  እንደሆነ ተሰማኝ እንደዛ እያረገ መሆኑን እያወኩ ምንም አላልኩትም ነበር ተው ይቅርብህ አላልኩትም ነበር በቻ አላህ ረድቶኝ ወደ አካውንቱ ገብቶ ሁሉንም መደለት ሚችል ሰው አገኘው በመጨረሻም ስለ ሁኔታው አስረድቼው ሁሉንም ነገር ደለተው ከረጅም ጊዜ በኋላ ጊዜ አካውንቱን ካዘጋሁ በኋላ የእንቅልፍ እፎይታ አገኘሁ ምንም ቢሆን ግን ያየሁትን ምስል እነዴት ሲሰቃይ እንደነበር መቼም አልረሳውም። ያ ነገር ለኔ ዘፈን እነድጠላ ከበቂ በላይ ነበር ከዛን ቀን ቡሀላ ሰምቼም አላቅም የተረደሰሁት ነገር ይህ ዓለም ፈተና ብቻ መሆኑን ነው። ይህ ነገር አብዛኞቻችን ላይ አለ ጓደኛችን ምንም ውንጀል ቢሰራ መምከር ቡሎ ነገር አልፈጠረብንም ለምን? የነብዩ ኡመት ሚለየው በበጎ ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል አልነበር እሱን የት ጣልነው መች ነው እርስ በእረስ ምንደራረሰው አላህን ልንፈራ ይገባላ አብሶ በ ዘፈን ሰው ሁሉ ሀላል በሚመስል መልኩ ሁሉም ጋር አለ ምን ያህል ልባችንን እንደሚያደርቀው ወላሂ.. ማለት ሚቻለው አላህ ሰምተው ከሚጠቀሙት ከሚሰሩበትም ያድርገን አሚን🤲 #share & #join 👇👇👇👇👇👇 @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune       #መካከለኛ ሁን# For any Comment 👇👇👇👇 @AmuAmii
نمایش همه...
ኢማሙ አቡ ሀኒፋ(ኢማሙል አዕዞም) ሀዲስ ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል:- «የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ንግግር ግልጽ ነበር። የሰማው ሁሉ በቀላሉ ይገነዘበዋል።» (አቡ-ዳውድ ዘግበውታል) #share & #join 👇👇👇👇👇👇 @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune       #መካከለኛ ሁን# For any Comment 👇👇👇👇 @AmuAmii
نمایش همه...
ኢማሙ አቡ ሀኒፋ(ኢማሙል አዕዞም) ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም ወቢሂ ነስተዒኑ ዐውነከ ያከሪም አልሀምዱ ሊላሂ ረቢል ዐለሚን ወሶላቱ ወሠላሙ ዐላ ሠይዲና ሙሀመድ ወአሊሂ ወሷህቢሂ አጅመዒን የሶላት ፈርዶች የሶላት ፈርዶች 6 ናቸው። እነሡም፦ 1-የመካፈቻ ተክቢራ ማድረግ አሏሁ አክበር ማለት 2-መቆም ለሚችል ሠው 3-ቁርአን መቅራት ገር የሆነለትን 4-ሩኩዕ ማድረግ 5-ሡጁድ ማድረግ 6-የመጨረሻው ረከዐ ተሸሁድን ሚያስቀራ ቀድር መቀመጥ ከላይ የጠቀስናቸውን ከ6ቱ አንዱን ካጎደለ እያወቀም ቢሆን ቢረሣም ሶላቱ ይበላሻል። ኢንሻአሏህ በቀጣይ የሶላት ዋጂቦችን እናያለን አሏህ ያቆየን🙏🙏🙏 #share & #join 👇👇👇👇👇👇 @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune       #መካከለኛ ሁን# For any Comment 👇👇👇👇 @AmuAmii
نمایش همه...
ኢማሙ አቡ ሀኒፋ(ኢማሙል አዕዞም) ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም ወቢሂ ነስተዒኑ ዐውነከ ያከሪም አልሀምዱ ሊላሂ ረቢል ዐለሚን ወሶላቱ ወሠላሙ ዐላ ሠይዲና ሙሀመድ ወአሊሂ ወሷህቢሂ አጅመዒን የትጥበት ሡናዎች የትጥበት ሡናዎች 5 ናቸው። እነሡም፦ 1-ሁለት እጆቹን ማጠብ ነው መጀመሪያ ውሀ ወዳጠራቀመበት እቃ ከማስገባቱ በፊት 2-በመፈግፈግ ጉያውን ማጠብ 3-ከሠውነቱ ላይ ነጃሳ ካለ መጀመሪያ ነጃሣውን ማጥራት 4-ውዱእ ሊያደርግ ነው ለሶላት እንደሚያደርገው እግሩ ሲቀር 5-በላይ ውሀ እያፈሠሠ ራሡንና ሌሎች የሠውነት ክፍሎችን 3 ጊዜ ማጠብ ከዚህ በኋላ ለምሣሌ በሻወር ገላውን ሚታጠብ ከሆነ ከሻወሩ ወጥቶ እግሮቹን ይጠብ ሴት ልጅ ፈርድ የሆነባትን ትጥበት በምትታጠብበት ጊዜ ፀጉሯን መፍታት የለባትም ወንድ ልጅ ፀጉሩን ተሠርቶ ከሆነ መፍታት አለበት። ኢንሻአሏህ በቀጣይ የሶላት ፈርዶችን እናያለን አላህ ያቆየን 🙏🙏🙏 #share & #join 👇👇👇👇👇👇 @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune       #መካከለኛ ሁን# For any Comment 👇👇👇👇 @AmuAmii
نمایش همه...
ሀዲስ ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል:-«የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ድዳቸው እስኪታይ ድረስ በጣም ሲስቁ አይቻቸው አላውቅም። ፈገግ ብቻ ነበር የሚሉት።» (ቡኻሪና ሙስሊም) #share & #join 👇👇👇👇👇👇 @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune       #መካከለኛ ሁን# For any Comment 👇👇👇👇 @AmuAmii
نمایش همه...
ኢማሙ አቡ ሀኒፋ(ኢማሙል አዕዞም) ሀዲስ አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የ አላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:- «ጥፍጥና ቆራጩን (ሞትን) በብዛት አስታውሱ» (ቲርሚዚይ ዘግበውታል) #share & #join 👇👇👇👇👇👇 @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune       #መካከለኛ ሁን# For any Comment 👇👇👇👇 @AmuAmii
نمایش همه...
ኢማሙ አቡ ሀኒፋ(ኢማሙል አዕዞም) ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም ወቢሂ ነስተዒኑ ዐውነከ ያከሪም አልሀምዱ ሊላሂ ረቢል ዐለሚን ወሶላቱ ወሠላሙ ዐላ ሠይዲና ሙሀመድ ወአሊሂ ወሷህቢሂ አጅመዒን የትጥበት ግዴታዎች የትጥበት ግዴታዎች 3 ናቸው። እነሡም፦ 1-መጉመጥመጥ 2-በአፍንጫው ውሀን መሣብ 3-ሙሉ አካላቱን በውሀ ማዳረስ(ማስነካት) ኢንሻአላህ በቀጣይ የትጥበት ሡናዎችን እናያለን አሏህ ያቆየን።🙏🙏🙏 #share & #join 👇👇👇👇👇👇 @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune       #መካከለኛ ሁን# For any Comment 👇👇👇👇 @AmuAmii
نمایش همه...
ኢማሙ አቡ ሀኒፋ(ኢማሙል አዕዞም) ሀዲስ አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የ አላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:- ❝ሸኮና ብጋበዝ እንኳን በግብዣው እገኛለሁ። የሸኮና ስጦታ ቢበረከትልኝም እቀበላለው።❞ (ቡኻሪ ዘግበውታል) #share & #join 👇👇👇👇👇👇 @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune       #መካከለኛ ሁን# For any Comment 👇👇👇👇 @AmuAmii
نمایش همه...
ኢማሙ አቡ ሀኒፋ(ኢማሙል አዕዞም) ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም ወቢሂ ነስተዒኑ ዐውነከ ያከሪም አልሀምዱ ሊላሂ ረቢል ዐለሚን ወሶላቱ ወሠላሙ ዐላ ሠይዲና ሙሀመድ ወአሊሂ ወሷህቢሂ አጅመዒን አሊይ ረዲየሏሁ አንሁ ከነብያችን ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሠለም ሰምተው እንዲህ አሉ ከቁርአን አንድ አያህ የቀራ ሠው አሏህ በእያንዳንዱ ሀርፍ 10 አጅር ይሠጠዋል ከሶላት ውስጥ ሁኖ ከቀራ ደግሞ በእያንዳንዱ ሀርፍ 100 አጅር ይሠጠዋል በውዱእ ላይ ሁኖ ነገር ግን ሶላት ላይ ሣይሆን ከቀራ ደግሞ በእያንዳንዱ ሀርፍ 10 አጅር ይሠጠዋል ያለ ውዱእ ከቀራም እንደዚሁ በእያንዳንዱ ሀርፍ 10 አጅር ይሠጠዋል ነገር ግን ያለ ውዱእ ቁርአን መንካት አይችልም። ጀናብተኛ ሁኖ ቁርአን መቅራት አይችልም ጀናብተኛ ሁኖ ግን ቁርአን ከቀራ ወንጀል ላይ ይወድቃል። #share & #join 👇👇👇👇👇👇 @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune       #መካከለኛ ሁን# For any Comment 👇👇👇👇 @AmuAmii
نمایش همه...
ኢማሙ አቡ ሀኒፋ(ኢማሙል አዕዞም) ሀዲስ አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦❝እኔን የታዘዘ አላህን ታዟል። በኔ ላይ ያመፀ በአላህ ላይ አምጿል። መሪን የታዘዘ እኔን ታዟል። በመሪ ላይ ያመፀ በኔ ላይ አምጿል።❞ (ቡኻሪና ሙስሊም) #share & #join 👇👇👇👇👇👇 @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune @mekakelegna_hune       #መካከለኛ ሁን# For any Comment 👇👇👇👇 @AmuAmii
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.