cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የጥበብ ቃል ✒️

#የጥበብ_ቃል ይህ የመድብሎች ውቅያኖስ ነው ✍️ ግጥም አለኝ በዚህ ቻናል እንዲጋራልኝ እፈልጋለሁ ለእምትሉ :- @selamnen ከላይ ባስቀመጥንሎት Account ያድርሱን እኛም ወደ ወድ ተከታዮቻችን ስራዎን እናደርሳለን።

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
547
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-57 روز
-1730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Repost from Creative G hub
እማ ወዲያ ዳሩን እየሳቅሽ ያለፍሽው ፣ ለ ህይወት አይበቃም ( ትንሽ ያ'ደይሽታ ) ትንሽ የቡና ጣዕም ካላጎናጸፉት አውቆ የተኛ እድሜ ፣ በ እግዜር ጥሪ አይነቃም። እማ ወዲያ ዳሩን "አንድ" ያልሽውን ህመም ፣ አልፏል አትቁጠሪው ይልቅ ከ ደጃፍሽ ሲጣራ የከረመ ፣ እግዜርሽን ጥሪው አሁን ናርዶስ ናርዶስ አሁን አደስ አደስ ፣ ይላል ያንገት ሽታሽ ያለሱ ለሳቅሽው ፣ ለዚያ መከራ ቀን... በይ እግዚአብሔር ይፍታሽ እኔን ለ ትላንትሽ
نمایش همه...
ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ ( በእውቀቱ ስዩም) የድሜ ነፋስ በገላየ : ተረማምዶ ኮበለለ ልቤን ክንዴን እያዛለ ያቀፍኩትን እየቀማ : የያዝኩትን እያስጣለ:: እድል በኔ ጨከነ ስል-በምረት እጅ ደባበሰኝ አንቺ ነጥቆ ከቅፌ ላይ-በትውስታ ደሞ ካሰኝ:: አሰታወሰኝ አስታወሰኝ:: ወድያው ታይቶ :ጠፊ ኩርፍያሽ ገራም ሳቅሽ : ልዝብ ልፍያሽ ያለም ዘፋኝ የማያውቀው የግልሽ ዳንስ ውዝዋዜ ትውስ ትውስ ባለኝ ጊዜ ከግር ጥፍሬ እስከ ጠጉሬ ደስታ ነው የሚያቀልመኝ ያንቺ ነገር ባሰብሁ ቁጥር :ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ:: በሰጠሽኝ ፀጋ መጠን: የሰራሽኝ ጉድ አያልቅም:: እኔ ባንች ትዝታ እንጂ: በተራቢ ቀልድ አልስቅም:: ማፍቀር ማለት ለካ ፍቺው : መጃጃል ነው አውቆ ፈቅዶ ከገደል ላይ መወርወር ነው ተጨፍኖ በራስ ፈርዶ:: አፈቀርኩሽ በየቀኑ :ተጃጃልሁኝ ደጋግሜ ከገደል ላይ ተከስክሼ: ሞተ ሲሉኝ አገግሜ ያጥንቶቼን ርጋፊ: እንደዛጎል ለቃቅሜ እንደ ቆሎ : ጥርሴን ቅሜ ያደረኩሽ ሲደንቀኝ: ያደረግሺኝ ሲገርመኝ እፍረት ፀፀት አይደለም: ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ ! አውቃለሁኝ ጊዜ ሂዷል :ታሪካችን ተጠቅልሏል:: በሄድንበት ጎዳና ላይ: የመለየት ዝናብ ጥሏል በርምጃችን ምልክት ላይ: ረጃጅም ሰርዶ በቅሏል ብቻ ምሾ ቢደረደር: የሆነውን ላይለውጠው ለንባየማ ፊት አልሰጠው:: ያሳሳምሽ ለዛ ቀርቶ :እንደ እንጎቻ እሚጥመኝ የነከሽኝ የቧጨርሽኝ: አገርሽቶ ቁስሉ ሲያመኝ ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ!! @bewketuseyoum19 @learneachother
نمایش همه...
ከግጥሞቼ ከፍ ማለት አለ ደግሞም እታች መዉረድ ሕይወት እንደዚ ናት ተቃራኒ መንገድ። ተፃፈ በሰላም @learneachother @selambishaw #የጥበብ ቃል ቻናላችንን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ🙏
نمایش همه...
✍እኔ የከሳውት እኔ የከሳውት አንተን በማብሰልሰል ሩቅ እየተጓዝኩ በማሰብ መተው ውስጥ ከራሴ ጋር ሁሌ ትግል እየገጠምኩ በማይጨበጥ ህልም አለም ስረማመድ በአይሆኑ ቅዠት መሀል ስንጎራደድ፤                እህል ውሀ ትቼ                         ኑሮ አሰልችቶኝ                 በደመነፍስ ሆኜ                            ናፍቆት አኮራምቶኝ            ያለቀው አካሌ ሞራሌ የራደው            ባለመኖርህ ውስጥ መኖር ጀምሬ ነው። አወይ ደምግባቴ ወዜ ደበዘዘ ብርቱ ፈገግታዬን ደርሶ ያቀዘቀዘ፡ ሀሳብ ሀሳብ ሀሳብ ሀሳብ ጉድአረገኝ ነፍስና ስጋዬን እንዳላዝ አገደኝ፤ በአለቀለት ተስፋ ፡ ተስፋ እየሰጠኝ ኮቴዬን አሳዶ ትዝታህ አከሳኝ። ✍Ab @learneachother
نمایش همه...
አለማዊው ተድላ አለማዊው ፌሽታ ሲገዛሽ ባይ እቱ ስም አወጣሁልሽ ብዬ አለሚቱ ለ አለማዊው ቅንጦት ለ አለማዊው ፌሽታ ለተራ ነገሮች ትምህርት አቁመሽ ስመለከት እቴ እውነቴን ነው ምልሽ ትዝ ትዝ ሁላ አለኝ አለማየሁ እሸቴ ( ተማሪ ልጄ ) የምር የምር የምር እውነቱን ስሰማ የምር ሆዴን ባሰኝ ደብዳቤው ወረቀት ላይ የሰው ፅሁፍ ነው እንጂ ያንቺ መች ደረሰኝ አለመማር ጎዳሽ 😑 በ_Semeon Join us 👉 @learneachother
نمایش همه...
ከግጥሞቼ ማንም ==== ሁሉም ነበር ሆኗል እስከ እንደዚ ድረስ ብቸኛ ኖሪ ነዉ ዘላለም ኢየሱስ!! እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በሰላም አደረሰን!! ተፃፈ በሰላም @learneachother @selambishaw #የጥበብ ቃል ቻናላችንን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ!!
نمایش همه...
ከግጥሞቼ ብል.... ==== ያለኝ ይበቃኛል ብሎ መኖር ነበር የሰዉ መሆን ልኩ አጉል ብልፅግና አዉሬነት ነዉ መልኩ። ተፃፈ በሰላም @learneachothet #የጥበብ ቃል ቻናልን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ🙏
نمایش همه...
ከግጥሞቼ ያሳስባል ===== ማን ያልመራን አለ ከጅብ እስካንበሳ ቀጥሎስ ምን ይሆን በኛ ላይ ሚነሳ?? ተፃፈ በሰላም ቢሻዉ @learneachother @selambishaw #የጥበብ ቃል ቻናላችንን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ🙏
نمایش همه...