fa
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

رفتن به کانال در Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

کانال ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 19 949 مشترک است و جایگاه 1 157 را در دسته پزشکی و رتبه 1 681 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 19 949 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 27 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -557 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -23 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 26.07% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 6.79% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 5 203 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 354 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 10 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 28 ژوئن, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته پزشکی تبدیل کرده‌اند.

19 949
مشترکین
-2324 ساعت
-1257 روز
-55730 روز
آرشیو پست ها
በድጋሚ የተፖሰተ ዶክተር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ ነኝ ቪማክስ የስንፈተ ወሲብ መዳኒት ብዙዎቻቹ በ inbox የምትጠይቁኝ ነገር ነው vimax ስለሚባለው የስንፈተ ወሲብ መዳኒት ትንሽ ነገር ልበል እንደምታውቁት በማህበራዊ ሚድያ ብስፋት የሚያስተዋዉቁት ነገር ነው። ከማህበራዊ ሚድያ ደሞ እውነተኛ ነገር ማግኘት አዳጋች ነገር ነው እናም ዝም ብላቹ ከፊስቡክ ወይም ከቴሌግራም የሚለቀቁትን ማስታወቅያዎች አምናቹ ምንም አይነት መዳኒት ባትገዙ ጥሩ ነው በጣም አደገኛ ሊሆንባቹ ይችላል በተለይ የዉስጥ ደዌ ችግሮች ያሉባቹ በጣም መጠንቀቅ ይኖርባቹሃል የህክምና ባለሞያዎን ማመከር አለባቹ የወንድ ብልት ያለመቆም ችግር ምልክቶች የብልት አልቆም ማለት የብልት ቆሞ ያለመቆየት/ ቶሎ መልፈስፈስ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ የቁመት ማጠር እና/ የመቀጠን ችግር ቶሎ የመጨረስ ችግር በአጠቃላይ ከለይ የጠቀስኳቸው የስንፍፈተ ወሲብ ችግሮች እንዳለባቹ ካረጋገጣቹ ችግሩን በህክምና ሞክራቹ ለዉጥ ከሌለዉ ደግሞ ሌሎች ስንፈተ ወሲብን ሊያክሙ የሚችሉ መድሃኒቶች አሉ ግን ኬት ማግኘት እንዳለባቹና የትኞቹ ናቸው ትክክለኛና ፈዋሽ የሆኑትን ማወቅ ይኖርባቹኃል ቢያንስ ቢያንስ ስለ መዳኒቶቹ Google ላይ ማጣራት እና Original ምን አይነት እንደሆነ መለየት ትችላላቹ የጎንዮሽ ጉዳቱቹ ምንምን እንደሆኑ Google ይነግራቹኃል በህክምና ሞክራቹ ወይም ሀኪም ማማከር ፈርታቹ መዳኒት ለመጠቀም የምትፈልጉ በጥያቅያቹ መሰረት ስለ Vimax የተወሰነ ነገር ልበላቹ እና ኬት እንደምታገኙ አድራሻ ለምትጠይቁኝ ሰጣቹኃለው Vimax Originally የካናዳ ምርት ሲሆን ጥቅሞቹ 1 የብልት አልቆም ማለት ቆሞ ያለመቆየት ቶሎ መልፈስፈስ ችር ላለበት 2 የቁመት እና የዉፍርት ችግር 3 ቶሎ የመጨርስ ችገር/የዘር ፈሳሽ የማምለጥ vimax አወሳሰድ/አጠቃቀም እንዷ ብልቃጥ 60capsule/60እንክብል ነው ምቲዘው ባለ 30capsule የምቲዝም አለች ግን እኔ የማወራው ስለ original ነው አወሳሰዱ በቀን አንድ አንድ ቢሆን ይመከራል በቀን ሁለት ሁለትም መውስድ ይቻላል። Side Effect/የጎንዮሽ ጉዳት እነሱ እንደሚሉት ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት አያመጣም ይበሉ እንጅ እኔ ከማቃቸው ተጠቃሚዎች እንደተረዳሁት የጨጓራ በሽታ ያለባቸው ላይ ለመጠቀም አስቸጋሪ ነው ነግር ግን ጎን ለጎን የጨጓራ መዳኒት እየወሰዱ የሚጨርሱም አሉ ከዚ ዉጪ ሌላ ምንም አይነት ጎዳት የለዉም አንድ አንዶች ላይ አላርጂክ ከሞሆን በስተቀር። የሚከለክላቸው ነገሮች መዳኒቱን መጠቀም ከጀመራቹ መዉሰድ/መጠቀም የሌለባቹህ ነገሮች .አልኮል/አረቄ ነገሮች ናቸው። መዳኒቶቹን መግዛት የምትፈልጉ እኔ ትክክለኛው Original Vimax አስመጪዎችን ስልካቸውን ልሰጣቹህ እችላለው መዳኒቱ ሀገር ዉስጥ እንዲሸጥ ገና ፍቃድ ስላላገኘ በዚም ምክንያት ዋጋው በጣም የተጋነነ ነው በዛ ላይ አስመጪዎቹ እየሸጡ ከተያዙ ወይም እጃቸው ላይ ከተገኘ የሚቀጡ ነው የሚሆኑት እናም ብዙ ጊዜ እራሳቸውን ደብቀው ነው የሚሸጡት ነገር ግን እኔ በትክክል ስለማዉቃቸው ችግር አይኖርም መዳኒቱም ፍቃድ ሊያገኝ በሂደት ላይም ስለሆን ብዙም አያሳስብም። በተጨማሪም የኔ ምክር ነው ጫት እየቃማቹ መዳኒቱን ባትወስዱ/ባትጠቀሙ ጥሩ ነው ቢያንስ መዳኒቱን እስክጨርሱ ጫቱን ብተዉት እላለው ስለ ጫት የጎንዮሽ ጉዳቶች በቅርቡ ፅፍላቹኃለው የአስመጪዎችን ስልክ እና አድራሻ በብዛት inbox ላይ ስትጠይቁኝ የነበራቹ ስልካቸው 0992484672 በ inbox ለማግኘት https://t.me/Sellerman12 አመሰግናለው እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

ራስ ማዞር መምን ምክንያት እንደሚመጣ፣ ምልክቶቹ፣ ማን ተጋላጭ እንደሆነ እና ምን ማድረግ እንዳለብን እናያለን፡፡ አብራችሁን ቆዩ!! ራስ ማዞር ምንድነው? አዞረኝ በምንልበት ጊዜ ከብዙ ምልክቶች እና ስሜቶች ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ራስን መሳት፣ የድካም ስሜት፣ ሚዛን ለመጠበቅ መቸገር እና ሌሎችንም ያጠቃልላል፡፡ አካባቢዎ ወይም እርሶ እየዞሩ ወይም እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ የሚሰማ አይነት ራስ ማዞር በሳንሳዊ አጠራሩ ቨርታይጎ ይባላል፡፡ በምን ምክንያት ይመጣል? ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ፤ እንደ የውስጠኛው የጆሮ ክፍል ችግር፣ በመኪና ሲጓዙ መታመም እና የመድሐኒቶች የጎንዮሽ ችግር ይጠቀሳሉ፡፡ አንዳንዴም ተጓዳን የጤና እክሎች እንደ ኢንፌክሺን፣ አደጋ፣ የልብ ችግር፣ የደም ዝውውር ችግር ጋር ሊያያዝ ይቻላል፡፡ በሌላ መልኩም ከማይግሪን፣ የነርቭ በሽታዎች፣ የደም ውስጥ ስኳር መጠን መቀነስ፣ ደም ማነስ፣ አንዳንድ መድሐኒቶች፣ ጭንቀት እና ውሃ አለመጠጣትም ምክንቶች ሊሆኑ ይችላለሉ፡፡ ምልክቶች ራስ ማዞር በተለያዩ እንቅስቃሴዎች እንደ መራመድ፣ ድንገት መቆም ወይም ከራስ ቅል እንቅስቃሴ ጋር ሊባባስ ይችላል፡፡ ብዙዎች ላይ የሚታዩ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፤ · በዙሪያ ያሉ ነገሮች የሚንቀሳቀሱ የሚመስል ስሜት · ራስን መሳት · ሚዛን ለመጠበቅ መቸገር · ጭንቅላት ላይ የሚከብድ ስሜት ተጋላጭነት - በእድሜ የገፉ ሰዎች - ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ችግር ከነበረ ሃኪሞት ጋር መቼ መሄድ አለቦት? · ተደጋጋሚ፣ ድንገት የመጣ፣ በጣም ከባድ ወይም ረዘም ላለ ጊዜ የማዞር ስሜት ከተሰማዎት · ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ስሜቶች ካሎት - ሀይለኛ ራስ ምታት - ደረት ላይ የህመም ስሜት - ለመተንፈስ መቸገር - ለመተንፈስ መቸገር - እጅ እና እግር ላይ መደንዘዝ እና አለመታዘዝ - ራን መሳት - የአይን ብዥታ - የልብ ምት መዛባት - የልብ ምት መዛባት - ለመራመድ መቸገር - ማስመለስ - ማንቀጥቀጥ - የመስማት አቅም መቀነስ ምን ማድረግ ይቻላል? · ሚዛኖትን በማንኛውም ጊዜ ሊስቱ እንደሚችሉ ከግምት ውስጥ ያስፈቡ · በድንገት ከመቀመጫ መነሳትም ሆነ መራመድን ያስወግዱ፤ ካልሆነም ከዘራ ይጠቀሙ · የማዞር ስሜት ከተሰማዎት ቁጭ ይበሉ ወይም ይረፉ · የማዞር ስሜት ከተሰማዎት ቁጭ ይበሉ ወይም ይረፉ · የማዞር ስሜት ካት መኪና አይንዱ ከባድ ማሽኖችንመ አያንቀሳቅሱ · ቡና፣ አልኮል፣ ጨው እና ሲጃራ አይጠቀሙ · በቂ ፈሳሽ ይውሰዱ · ጤናማ አመጋገብ ይኑሮት · በቂ እንቅልፍ ያግኙ · በቂ እንቅልፍ ያግኙ · ከሚያስጨንቆት ነገር ይራቁ እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

ዛሬ በስራ ገበታ ላይ ሳለን አንዲት እናት የሁለት አመት ልጇን ፊቱን ቀይ የጥፍር ቀለም ቀብታዉ ብንጠይቃት ለኪንታሮት መድሃኒት ነው ሲሉኝ ነዉ አለችን። ነገር ግን ከመጥፋት ይልቅ እየተስፋፋ ሲመጣ እና ኢንፌክሽን ሲፈጥር ፈርቼ ወደ ህክምና አመጣሁት አለችኝ። እኔም ለምን ካነበብኩት ስለቆዳ ኪንታሮት ጀባ አልላችሁም ብዬ ይህን ጀባ አልኳችሁ። . የቆዳ ኪንታሮት በሽታ ምንድን ነው ? መንስኤውና እና መፍትሔውስ ? . የኪንታሮት በሽታ (Molluscum contagiosum ) ፓክስ ቫይረስ በሚባል የሚመጣ የቆዳ ኢንፌክሽን ነው። ብዙውን ጊዜ በማንኛውም የሰውነት ቆዳ ላይ በፊት ፤ አንገት፤ ሆድ፤ እጅ እግር ላይ ሊወጣ ይችላል። ሲወጣም ትንንሽ ነጭ (2 to 5 millimeters) የሚሆኑ መሃላቸዉ የሰረጎደ የቆዳ ቁስሎች ሲሆን በነጠላ ወይም በብዛት ሊወጡ ይችላሉ። ብዙዉን ጊዜ ያለ ህክምና በራሳቸው ከ 6 እስከ 12 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚጠፋ ቀላል የቆዳ በሽታ ሲሆን በጥቂቶች ላይ እስከ 4 ዓመት ሊቆዮ ይችላሉ፡፡ . መተላለፍያ መንገዶች ምንድናቸው? . Molluscum የሚያመጣ ቫይረስ በቀጥታ ከሰው ወደ ሰው አካላዊ ግንኙነት እና በተበከለ ግዑዝ ነገሮች ይተላለፋል። በአልባሳት እና ፎጣዎች ፣ ገላ መታጠቢያዎች ፣ ገንዳ እና መጫወቻዎች ሊያካትት ይችላል፡፡ . ይህ ቁስል ያለበት ሰው ቁስልን በመንካት ወይም በመቧጨር ካንድ የሰውነት ክፍል ወደ ሌላ የሰዉነት ክፍል በመንካት ሊያስተላልፍ ይችላል። . ለበሽታው ተጋላጭ ማነው ? . በማንኛዉም ሰዉ ላይ ሊወጣ ቢችልም በብዛት እድሜያቸው ከፍ 1 በታች እና ከ1 እስከ 10 ዓመት ዕድሜ ልጆች ላይ አብዛኛውን ጊዜ ይከሰታል ፡፡ . ለበሽታው የመጋለጥ እድሉ ያላቸው ሰዎች እነማን ናቸዉ ?? . የተዳከመ የበሽታ መቋቋም አቅም ያላቸው ሰዎች (ለምሳሌ ፣ በኤች አይ ቪ የተያዙ ሰዎች ወይም በካንሰር የተያዙ ወዘተ )፡፡ በነዚህ ግለሰቦች ላይ እድገታቸው ትልቅ የበዛ እና ለማከም በጣም ከባድ ሆኖ ሊወጣ ይችላል። . የቆዳ አለርጂ ያላቸው ። የኑሮ ሁኔታ በተጨናነቀበት ሞቃታማ እና እርጥበት አዘል አየር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ፡፡ . የሕክምና አማራጮች ምንድናቸው? . ምክንያቱም molluscum contagiosum በጤናማ ግለሰቦች ላይ ያለህክምና በራሱ የሚጠፋ ስለሆነ ብዙዎች ላይ ያለ ህክምና ይጠፋል፡፡ ነገር ግን ቁስሎቹ በጾታ ብልት ውስጥ (በብልት ፣ በብልት ወይም በፊንጢጣ አከባቢ) ላይ ወይም አከባቢ ከወጣ ሕክምና ሊያስፈልገው ይችላል። በወሲብ ግንኙነት የሚተላለፍ ሌላ በሽታ ሊኖርብዎ ስለሚችል በዚህ አካባቢ ቁስሎች ከተገኙ ወደ ጤና ተቋም ሄዶ መታየቱ ጥሩ ነው ፡፡ . የሕክምና አማራጮች ?? . 1. አካላዊ መወገድ . ቁስሎች አካላዊ መወገድ ክራዮቴራፒ (ቁስሉ በፈሳሽ ናይትሮጅን) በመጠቀም ፤ ኪዉርቴጅ በመፋቅ እና የጨረር ሕክምናን ሊያካትት ይችላል፡፡ እነዚህ ህክምናዎች በሰለጠኑ የጤና ባለሞያ የሚሰጡ ናቸው። . ቁስሎች ወይም ቁስሎች ውስጥ ያለውን ፈሳሽ በእራስዎ ላማስወገድ መሞከር እና ማስወገድ ጥሩ ሀሳብ አይደለም፡፡ የቁስሎችን ፈሳሽ ሳያውቁ ወደ ሌላ የሰውነት ክፍሎች ሊያሰራጩ ይችላሉ። ቆዳውን በመቧጨር የባክቴሪያ ኢንፌክሽን ሊያስከትሉ ይችላሉ ። . 2. የቅባት-ሕክምና . የፖዶፊልሎቶክሲን ክሬም (0.5%)፡፡ ሌሎች አማራጮች አዮዲን እና ሳሊሊክሊክ አሲድ ፣ ፖታስየም ሃይድሮክሳይድ ፣ ትራይቲኒቲን ፣ ካንታሪንዲን እና ኢሚኢይሞድ ናቸው ፡፡ እነዚህ ሕክምናዎች በጤና ባለሙያ የታዘዙ መሆን አለባቸው ፡፡ . እንዴት መከላከል ይቻላል? . 1. ቁስሎችን አለመነካካት የራስዎን ቆዳ ብቻ ሳይሆን የሌላውን ሰው ጨምሮ የቆዳ ቁስሎችን የያዘውን ቆዳ አለመንካት አስፈላጊ ነው። መነካካት እና መቧጨር ቫይረሱን ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊያሰራጭ እና በሽታውን ወደ ሌሎች ሰዎች በቀላሉ ለማሰራጨት ቀላል ያደርገዋል፡፡ . 2. ቁስሎችን መሸፈን . ሌሎች ቁስሉ እንዳይነካውና በበሽታው እንዳይጠቃ ለመከላከል አካባቢውን ንፁህ በሆኖ ልብስ ወይም በፋሻ መሸፈን እና ማድረቅ አስፈላጊ ነው ፡፡ የተጠቁ ቆዳን ለማፅዳትና ለማድረቅ ያስታውሱ ፡፡ . 3. እጅዎን መታጠብ . በጣም ጥሩው መንገድ ጥሩ ንፅህናን (ንፅህና) ልምዶችን መከተል ነው፡፡ እጆችዎን በንጽህና መጠበቅ የሞለስከም ኢንፌክሽንን እና እንዲሁም ሌሎች ብዙ ኢንፌክሽኖችን ለማስወገድ በጣም የተሻለው መንገድ ነው ፡፡ እጅን መታጠብ ከሌሎች ሰዎች የተነሱትን ወይም በእነሱ ላይ ሊኖሩ የሚችሉ ጀርሞችን ያስወግዳል ፡፡ . 4. ልብሶችን ፊጣዎችን ወይም ማንኛውም የግል እቃዎችን እያጋሩ ።

የደም ማነስ ''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''' የደም ማነስ ምንድነው? ''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''' አንድ ሰው የደም ማነስ ህመም አለበት የሚባለው በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ምክንያቶች በደም ውስጥ የቀይ ደም ህዋሳት ቁጥር ሲመናመን ነው። ለመሆኑ እኒህ ስሜቶች ምን ምን ናቸው? ''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''' ከፍተኛ የድካም ስሜት ማዞር ጆሮ ውስጥ ጭውው የሚል ድምጽ መሰማት ብዥ ማለትና አንድ ነገር ሁለት መስሎ መታየት የልብ ምት መሰማት እና የመሳሰሉት ሲሆኑ የደም ማነሱ የከፋ ሲሆን ደግሞ ትንፋሽ ማጠርና ቶሎ ቶሎ መተንፈስ፣ የደረት ውጋትና የእግር ማበጥ ሊከሰት ይችላል። ይህም ልብ የደም እጥረቱን ለማካካስ በምታደርገው ከፍተኛ ትግል ከጊዜ በኋላ እየደከመች በምትሄድበት ወቅት የሚከሰት ሁኔታ ነው። ሃኪሞች በሚመረምሩበት ወቅት ደግሞ የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያስተውሉ ይችላሉ። የፊትና የአይን ቆብ ውስጠኛው ክፍል መገርጣት/መንጣት የምላስ ልሙጥ መሆን ወይም ስጋ መምሰል የአፍ ጠርዝና የከንፈር ቁስለት የመዳፍና የውስጥ እግር መንጣት/መገርጣት እና ወዘተ ሲሆኑ በተጨማሪም ለደም ማነ መንስኤ የሆኑ ሌሎች የውስጥ ደዌ ምልክቶችም ሊታዩ ይችላሉ። ስለምን እኒህ የቀይ ደም ህዋሳት ቁጥራቸው ይመናመናል? ''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''' በአጠቃላይ የደም ማነስ ምክንያቶችን በሁለት ታላላቅ ክፍሎች ማየት ይቻላል 1. ከሰውነት ደም መፍሰስ፣ በአደጋ፣ በወሊድ ጊዜ፣ የወር አበባ ከተለመደው ሲበዛ፣ በቀዶ ህክምና ወቅት ከጨጓራና ከተለያዩ የውስጥ ኣንጀት ቁስሎችና እባጮች መድማትና ወዘተ 2. የቀይ ደም ህዋሳት ቁጥር ማነስ -በበቂ ቁጥር ያለመመረት (የመቅኒ መስተጓጎል፣የብረት iron ቫይታሚን ቢ 12 እና ፎሊክ ኣሲድ እጥረት) -የተፋጠነ የቀይ ደም ህዋሳት መሞት፣ በተለይም በሃገራችን ዋነኛው የደም ማነስ መንስኤ ከብረት (iron) እጥረት የሚመጣ ሲሆን ይህም የተመጣጠነ ምግብ ኣቅርቦት በቂ ባለመሆኑና በሆድ ውስጥ ደምን የሚመጡ ትላትሎች በብዙ የሃገራችን ማህበረሰብ ውስጥ በመኖራቸው ነው። በብረትና(iron) በቫይታሚን (vitamin) እጥረት የሚከሰተው ደም ማነስ የትኛው የማህበረሰብ ክፍል ይበልጡን ተጋላጭ ነው? ''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''' -ነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶች -ህጻናትና ታዳጊዎች፣ -ቲቢንና ኤች አይ ቪን ጨምሮ የተለያዩ ህመም ያለባቸው ወገኖች፣ -ስጋን ጨምሮ የተለያዩ የእንስሳት ተዋጽኦዎች በበቂ ሁኔታ ማግኘት የማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ እጥረት ወዘተ እንዴት ይታወቃል? ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ከላይ ያሉት ስሜቶችና ምልክቶች በብዙ ህመሞች ላይ የሚስተዋል በመሆኑ ታማሚው በኣቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ሊያደርግ ይገባል። የጤና ባለሞያዎችም የሚከተሉትን ምርመራዎች በላቦራቶሪ እንደየአስፈላጊነታቸው ሊያዙ ይችላሉ።እነዚህም ምርመራዎች የደም ማነስ መኖሩንና መንስኤውን ለማውቅ ይረዳሉ። -ሙሉ የደም ቆጠራ፣ የቀይ ደም ህዋሳትን ብዛት ለማወቅ -በማይክሮስኮፕ በመታገዝ የቀይ ደም ህዋሳት መልክና ቅርጽ ምርመራ፣ -የብረትና የተለያዩ ንጥረ ነገሮች ፣ቫይታሚኖችን ጨምሮ መጠናቸውን ከደም ውስጥ መለካት፣ -በተመረጡ ሁኔታዎች ከአጥንት መቅኒ ናሙናም ሊወሰድ ይችላል። እንዴት ይታከማል? ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ህክምናው እንደየምክንያቶቹ የተለያየ ቢሆንም የከፋ የደም ማነስ ያለ እንደሆነ ግን ከህመምተኛው የደም አይነት ጋር ተስማሚ የሆነ በህክምና ተቋም ውስጥ ደም በመስጠት የታካሚውን ህይወት መታደግ ይችላል።ለመጠነኛና መካከለኛ የደም ማነስ ግን ለደም ማነሱ ምክንያት የሆነውን ነገር በመለየት ይታከማል። በንጥረ ነገሮች እጥረት ለተከሰተ የደም ማነስ እጥረት ያለበትን ንጥረ ነገር በመስጠት ይታከማል። -የብረት(iron) እጥረት ፣ በብረት የበለጸጉ እንክብሎችን በመስጠት (ferrous sulphate, ferrous fumarate, ferrous gluconate) እንዲሁም በፍጥነት ብረቱን መተካት ሲያስፈልግ በመርፌ የሚሰጥ የብረት ቅንብር( dextran) መስጠት ይቻላል። -ለቫይታሚን ቢ 12 vitamin B 12 እጥረት ፣በመርፌ cobalamin የተሰኘ መድሃኒት ይሰጣል። -ለፎሊክ ኣሲድ እጥረት የ folic acid እንክብል በመስጠት ይታከማል። በሌሎች ምክንያቶች የሚመጡት እንደየምክንያቱ የሚታከሙ ይሆናል። መከላከል ይቻል ይሆን? ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ከላይ እንደጠቀስነው በሃገራችን ዋነኛው የደም ማነስ ምክንያት የንጥረ ነገሮች፣ በተለይም የብረት እጥረት እንደመሆኑ በብረትና በቫይታሚች የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ በነዚህ ንጥረ ነገሮች እጥረት የሚከሰተው የደም ማነስ መከላከል ይቻላል።ይህንንም የተመጣጠኑ ምግቦችን በመመገብ መከላከል እንችላለን። በብረት የበለፀጉ ምግቦች በጥቂቱ ጉበት ቀይ ስጋ ዓሣ ባቄላ፣አተር ጥቁር ቸኮሌት እና ሌሎች በቫይታሚን ቢ 12 (vitaminB12) የበለፀጉ ምግቦች በጥቂቱ ቀይስጋ እና ዓሣ ዶሮ ፣ እንቁላል ወተትና ሌሎችም በፎሊክ አሲድ (folic acid) የበለፀጉ ምግቦች በጥቂቱ አረንጓዴ ኣትክልት አትክል( ጎመን፣ ሰላጣ) ጥራጥሬዎች (ባቄላ፣ አተር፣ምስር) ለውዝ ፍራፍሬዎች( ብርቱካን፣ሙዝ፣ወይን፣አቮካዶ፣ፓፓያ፣ እንጆሪ ) ቀይ ሽንኩርት እና ሌሎች በተጨማሪም የሆድ ትላትሎችን የግልና የአካባቢ ንፅናችንን በመጠበቅ መከላከል እንችለላለን። ከላይ እንደተጠቀሰው እነዚህን ስሜቶችና ምልክቶች ስናስተውል በአፋጣኝ ወደ ወደጤና ተቋም ማምራት ተገቢ ይሆናል።ነገር ግን የመከላከያ ማስታዎሻውን ዘወትር መከተል ለሁላችንም አስፈላጊ እንደሚሆን መገንዘብ ያሻል እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias @DrSofonias

1. በመነጽር ሊስተካከል የሚችል የእይታ ችግር ( Refractive error) 2. የዓይን ሞራ (cataract) 3. በተለያየ ምክንያት የሚከሰት የዓይነ መስታወት ጠባሳ ( በተለይም የቪታሚን ኤ እጥረት፤ ኩፍኝ፤ የዓይነ መስታውት ቁጣ/ምርቀዛ…ወዘተ) 4. የዓይን ግፊት ህመም (Glaucoma) 5. የእይታ ነርቭ ችግር (Optic atrophy) 6. የእይታ አንጎል ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች (Cerebral visual impairment) 7. ያለ ጊዜው ቀድመው በሚወለዱ ጨቅላ ህጻናት ላይ ረቲና ውስጥ የሚፈጠር ችግር [Retinopathy of Prematurity (ROP)] 8. ከውልደት ጀምሮ የሚፈጠሩ የዓይን በሽታዎች (congenital. malformations) በህጻናት ላይ የዓይን ችግሮችን እንዴት መለየት እንችላለን? • በኢትዮጵያ ከ80 በመቶ በላይ ዓይነ ስውርነትን የሚያስከትሉ በሽታዎችን መከላከል ወይም በህክምና ማስወገድ የምንችላቸው ናቸው፡፡ • ይኸውም አስቀድሞ በጊዜው ( በተለይም ህጻናት የዓይንና አንጎል እድገት ላይ ባለበት ከ8 ዓመት በፊት) ችግሩን በመለየትና አስፈላጊውን ህክምና በማድረግ ነው፡፡ • ነገር ግን የአብዛኛዎቹ ህጻናት ዓይን ችግር የሚታወቀው ትምህርት ሲጀምሩ በትምህርት ቤት ውስጥ በሚያሳዩት የዕይታ ችግር በመምህራኖቻቸው ሲሆን ይህም ዉጤታማ ህክምና ለማድረግ በጣም የዘገየ ሊሆን ይችላል፡፡ • ስለሆነም ወላጆች/አሳዳጊዎች አስቀድመው፤ 1. የህጻናትን ዓይን በማየትና 2. በሚያሳዩት ባህርይ የዓይን ችግር መኖሩን መለየት ይችላሉ፡፡ በህጻናት ዓይን ላይ ችግር ስለመኖሩ ጠቋሚ ምልክቶች፡- 1. በዓይን ዉሰጥ መሃል ላይ ነጭ ነገር/ነጥብ መታየት 2. መጫወቻ አሻንጉሊት/ብርሃን ወይም የሰውን ፊት አተኩሮ አለማየት እና የሚንቀሳቀሱ ነገሮችን በዐይናቸው አለመከተል ( በጨቅላ ህጻናት ላይ የእይታ መቀነስ ምልክት ነው) 3. አንዱ ወይም ሁለቱም ዓይኖች መጠን ከመደበኛ በታች ትንሽ ወይም ትልቅ መሆን 4. ሸውራራ ዓይን 5. የዓይን ቅላት 6. የዓይን ውስጥ እብጠት /ቁጣ/ምርቀዛ 7. አብዝቶ በተደጋጋሚ እንባ መፍሰስ 8. ዓይነ መጎልጎል (Proptosis) ህጻናት የሚያሳዩትን የባህርይ ለዉጥ በማጥናት የዓይን ችግር መኖሩን መለየት:- 1. ጨቅላ ህጻናት 3 ወር እድሜ ሲሞላቸው የሰው ፊት ላይ ካላተኮሩና ፈገግታ ካላሳዩ 2. ህጻናት አተኩረው ሲያዩ አንድ ዓይናቸውን የሚሸፍኑ ከሆነ 3. ሲያነቡ ወይም የሚያዩትን ነገሮች ወደ ፊታቸው የሚያቀርቡ ከሆነ ወይም ወደ ቴሌቪዥን፤ ኮምፒዩተር፤ ሰሌዳ በጣም ቀርበው ብቻ የሚያዩ ከሆነ 4. አተኩረው ሲመለከቱ ፊታቸውን ወደ አንድ አቅጣጫ የሚያዞሩ ወይም ጭንቅላታቸውን የሚያገድሉ ከሆነ 5. እድሜያቸው ከፍ ያሉ ህጻናት ደግሞ የሚያዩት ነገር ደብዛዛ ነው ወይም ለማየት ተቸግሬለሁ ብለው ከተናገሩ 6. በትኩረት ሲመለከቱ ወይም ከሩቅ በሚያዩበት ጊዜ የዓይን ቆብ አጥብበው የሚያዩ ከሆነ 7. የሚያዩት ነገር ደርቦ / ሁለት ሁለት ሆኖ መታየት 8. ዓይነ ዥዋዥዌ (ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የዓይን እንቅስቃሴ) 9. በተደጋጋሚ ዓይናቸውን ማሸት/ማሳከክ ሲኖር ወላጆች/አሳዳጊዎች የህጻናትን ዓይን ጤና ለመጠበቅ ምን ማድረግ አለበቸው? • የህጻናትን የእጅና የፊት ንጽህና መጠበቅ • ክትባት በወቅቱ ማስከተብ (በተለይም የኩፍኝ ክትባት) • የተመጣጠነ ምግብ መመገብ (በተለይም አትክልትና ፍራፍሬ በቪታሚን ኤ የበለጸጉ ምግቦችን እንደ ካሮት፤ ማንጎ፤ አቮካዶ፤ አረንጓዴና ሰፋፊ ቅጠላ ቅጠል ያላቸውን) 🥕 🥑 🥦 • የህጻናት ዓይን ላይ ችግር መኖሩን ከጠረጠሩና ጠቋሚ ምልክቶችን ካዩ ሳይዘገዩ ወዲየውኑ ወደ ዓይን ሕክምና ተቋም በመውሰድ ማስመርመር ያስፈልጋል፡፡ በህክምና ተቋም የሚደረጉ ምርመራዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ - የእይታ ልኬት ይደረጋል - የመነጽር ልኬት (ህጻናት ሲሆኑ የዓይን ጠብታ በመጨመር የሚደረግ ምርመራ) - የዓይን ዉጪና ውስጥ ምርመራ - እንደችግሩ ዓይነት ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ ምርመራዎች (ለምሳሌ፡ አልትራሳውንድ፤ CT scan/MRI) ማድረግ ሊያስፈልግ ይቻላል፡፡ - ሙሉ ምርመራ ለማድረግ የማይተባበሩ ህጻናት ከሆኑ ደግሞ የሰመመን (ማደንዘዣ) መድኃኒት በመስጠት የሚደረግ ምርመራ • የህጻናትን ሕክምና መዘገየትን ማስወገድ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ • የሐኪም ምክር በተገቢው መፈጸም ወሳኝ ነው፡፡ • መደበኛ ክትትል ሳያቋርጡ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሕክምናው እንደ ችግሩ ዓይነትና ደረጃ የተለያየ ሲሆን፡- • የመድኃኒት ሕክምና • የመነጽር ሕክምና • አንድ ዓይን ለተወሰነ ጊዜ በመሸፈን ስንፈተ ዕይታን ማስተካከልና • የቀዶ ጥገና ሕክምና ሊሆን ይችላል። ጤነኛ ህጻናትን መቼ መቼ የዓይን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል? • በወቅቱና በጊዜው መታከም ያለባቸው አስቀድመው ያልታወቁ የዓይን ችግሮች/በሽታዎች የህጻናት ዓይነ ስውርነትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ • በመሆኑም አስቀድሞ በወቅቱ ችግሮችን በማወቅና በመለየት መቅረፍና ዓይነ ስውርነትን መከላክል ይቻላል፡፡ • ይኸውም መደበኛ የዓይን ምርመራ በማድረግ ነው፡፡ የመጀመሪያ የዓይን ምርመራ መቼ መደረግ አለበት? • አንድ አመት እድሜ ላይ ፤ ከዚያ መዋለ ህጻናት(KG) ከመግባታችው በፊት። በአጠቃላይ፡- • ከልደት - 2 ዓመት ዕደሜ ፤መጀመሪያ ምርመራ በ 6 - 12 ወር ዕድሜ ላይ • ከ 3 - 5 ዓመት ዕድሜ ፤ ቢያንስ አንድ ጊዜ ማስመርመር • ከ6 – 17 ዓመት ዕደሜ፤ አስቀድሞ 1ኛ ክፍል ከመግባታቸው በፊት፤ ከዚያ በዓመቱ ማስመርመር ያስፈልጋል፡፡

" ቶሎ የመርጨት ችግር/early ejaculation(EE) //////////////////////////////////////////////////////////// ➥ ቶሎ የመርጨት ችግር ማለት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከመፈጸምዎ በፊት ወይም ከጀመሩ ከአንድ ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ የወንድ የዘር ፍሬ(ስፐርም) መፍሰስ ነው። ➥ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት አንድ ወንድ የዘር ፈሳሹ የሚወጣበት የተወሰነ ጊዜ የለም ፣ ነገር ግን በፍጥነት የመርጨት ችግር ሲገጥም አንተና ባለቤትህ ለመደሰት በቂ ጊዜ እንደሌለ ሊሰማቹ ይችላል። ሊያበሳጭ አልፎ ተርፎም ሊያሳፍር ይችላል ፣ ግን ለወንዶች የተለመደ ጉዳይ ነው። ➥ ቶሎ የመርጨት ችግር አልፎ አልፎ ብቻ ቢከሰት የሚያስጨንቅ ነገር አይደለም። ➥ ያለጊዜው የወንድ የዘር ፈሳሽ መንስኤዎች እና የአደጋ ምክንያቶች መንስኤው በትክክል አይታወቅም። ግን የአንጎል ኬሚስትሪዎ ቢያንስ በከፊል ምክንያቱ ሊሆን ይችላል። በአእምሮአቸው ውስጥ ዝቅተኛ የኬሚካል ሴሮቶኒን ያላቸው ወንዶች ለመራባት አጭር ጊዜ ይወስዳሉ። ➥ ስሜታዊ ምክንያቶች ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ እነዚህም፦ 📌📌 ውጥረት 📌📌የመንፈስ ጭንቀት 📌📌 የጥፋተኝነት ስሜት 📌📌 የግንኙነት ችግሮች 📌📌 በራስ የመተማመን ስሜት አለመኖር 📌📌 ደካማ የሰውነት ገጽታ 📌📌 ስለ ወሲባዊ አፈፃፀምዎ መጨነቅ 📌📌 ስለ ወሲብ ሀሳብ አሉታዊ ስሜቶች (ወሲባዊ ጭቆና) 📌📌 አንዳንድ አካላዊ ሁኔታዎች 📌📌 ያልተለመዱ የሆርሞን ደረጃዎች 📌📌 መደበኛ ያልሆነ የነርቭ አስተላላፊዎች (መልእክቶች ወይም ግፊቶች ወደ ቀሪው የሰውነትዎ የሚያስተላልፉ ኬሚካሎች አለመመጣጠን) 📌📌 በፕሮስቴት ወይም በሽንት ቧንቧዎ ውስጥ እብጠት ወይም ኢንፌክሽን 📌📌 ከሆድዎ የሚወጣ ቱቦ ከሰውነት ውስጥ የሚወጣ ቱቦ እና 📌📌 ከወላጆችዎ የሚወርሷቸው የጄኔቲክ ባህሪዎች ቶሎ የማሰስ ችግርን ያስከትላሉ። ➥ አንዳንድ ጊዜ PE(premature ejaculation) የብልት መቆም ችግር(ED) ላለባቸው ወንዶች ችግር ሊሆን ይችላል። ያ ብልት ለወሲብ በቂ ሆኖ በማይቆይበት ጊዜ ነው። የብልት መቆሚያቸውን ሊያጡ ይችላሉ ብለው የሚጨነቁ ወንዶች ወደ ፈሳሽ ለመውጣት የሚጣደፉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። ለመላቀቅ ከባድ ልማድ ሊሆን ይችላል። ➥ የብልት መቆራረጥን ማከም ያለጊዜው መውጣትን ሊያጠፋ ይችላል። ➥ ብዙ የመድኃኒት አማራጮች አሉ። ➥ ያለጊዜው የወንድ የዘር ፈሳሽ መውጣት በሁለት መንገድ ይከሰታል እነዚህም፦ 1, ስነ ልቦናዊ ቀውስ እና 2 በአካላዊ ችግሮች አማካይነት ይከሰታል። ➥ ስነ ልቦናዊ ችግር ከሆነ የአእምሮ ጤና ባለሙያ ማግኘት ጠቃሚ ነው። በአካላዊ ችግር የተፈጠረ ከሆነ ፣ የሽንት ሥርዓትን በሚነኩ ሁኔታዎች ላይ የሚያተኩር ዩሮሎጂስት የተባለ ሐኪም እንዲያዮት ይመከራል። ✍️ ቶሎ የማፍሰስ ችግርን ለመቆጣጠር ምን ማድረግ አለብኝ? ➥ የ Kegel መልመጃዎች ወይም እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ። ➥ ሊያፈሱ በተዘጋጁበት ወቅት የብልትዎን ጫፍ ይጭመቁ። ➥ በወሲብ ወቅት ሀሳብዎን ሌላ ቦታ ያድርጉ። ➥ በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ለማፍሰስ ሲዘጋጁ ብልቶን ለሰከንዶች ከሴቷ ብልት ያውጡ። ➥ ኮንዶም ይጠቀሙ ➥ ግለ ወሲብ ወይም Masturbation አስቀድመው ይጠቀሙ ➥ የ ስንፈተ ወሲብ ወይም erectyle dysfuction መድሀኒት የሆነውን sindenafil ወይም ቫይግራን ይጠቀሙ በቀን የሚጠቀሙት መጠን ከ 100 ሚ.ግ መብለጥ የለበትም! ➥ ጭንቀትዎን ያስወግዱ! ጭንቀት ቶሎ የመርጨት ችግርን ያፋጥናል! ➥ ትራማዶል - ይህ የወንድ የዘር ፈሳሽ እንዲዘገይ የሚያደርግ የህመም ማስታገሻ ነው። ፀረ -ጭንቀቶች ካልረዱ ሊታዘዝ ይችላል። ይህ መድሃኒት ሱስ የሚያስይዝ ነው ፣ ስለሆነም ለእርስዎ አማራጭ ላይሆን ይችላል። ➥ ማደንዘዣ ክሬም ወይም የሚረጭ - ስሜትን ለመቀነስ ስሜታዊነትዎን በወንድ ብልትዎ ራስ ላይ ያደርጉታል። ለ 30 ደቂቃዎች ያህል ይተውት። የጾታ ግንኙነትዎን እንዳያጡ ወይም ለባልደረባዎ የስሜት መቀነስ እንዳይኖር ከወሲብ በፊት መታጠብ አለበት። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

➥ የታዘዘውን አመጋገብ እና ፈሳሽ ገደቦችን ይከተሉ። ➥ሁሉንም መድሃኒቶች በትክክል ይውሰዱ እና ማንኛውንም የጎንዮሽ ጉዳቶች ለሐኪሙ ይንገሩ። የጡንቻ ቃና እና ጥንካሬ ለማገዝ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ። ➥ ክብደትዎን(ውፍረትዎን) ይቀንሱ። ➥ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ይምሩ። ➥ ከመጠን በላይ መጠጣት የመሳሰሉትን በጾታዊ ግንኙነትዎ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ ሌሎች ነገሮችን ያቁሙ ➥ ማጨስን ያቁሙ። ✍️ ልጆች መውለድስ እችላለሁ? ➥ የወንድ የዘር ፍሬ በኩላሊት በሽታ የማይጎዳ ቢሆንም በማህፀን ውስጥ ያሉ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ። አዲስ ሕፃን ለማንኛውም ቤተሰብ ደስታ ነው። ነገር ግን እርግዝና በሰውነትዎ ላይ ከፍተኛ ጫና ሊፈጥር ይችላል። የኩላሊት በሽታ ወይም የኩላሊት ውድቀት ካለብዎ እርስዎ እና ያልተወለደውን ልጅ ጤናዎን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል። በተጨማሪም የኩላሊት በሽታዎን ሊያባብሰው ይችላል። ➥ ለማርገዝ ካሰቡ ከሐኪም ጋር በጥንቃቄ መወያየት አለብዎት።

✍️ " የኩላሊት በሽታ ያለበት ሰው ወሲብ ቢፈፅም ምን ይሆናል?" //////////////////////////////////////////////// ➥ ብዙ ሰዎች ወሲባዊነት የሚያመለክተው የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ብቻ ነው ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ወሲባዊነት እንደ መንካት ፣ ማቀፍ ወይም መሳም ያሉ ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል። ስለራስዎ ምን እንደሚሰማዎት ፣ ምን ያህል በጥሩ ሁኔታ እንደሚነጋገሩ እና ወደ ሌላ ሰው ለመቅረብ ምን ያህል ፈቃደኛ እንደሆኑ ያጠቃልላል። ➥ የኩላሊት በሽታ ወይም የኩላሊት ውድቀት ካለብዎ ወሲባዊነትዎን ሊነኩ የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ እነዚህም 📌 ሆርሞኖች 📌 ነርቮች 📌 የኃይል ደረጃዎች እና 📌 መድሃኒቶች ናቸው። ➥ ነገር ግን እርስዎ እና ዶክተሮች እነዚህን ለውጦች ለመቋቋም ማድረግ የሚችሏቸው ነገሮችም አሉ። ➥ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ወይም ከጤና እንክብካቤ ባለሙያ እርዳታ ለማግኘት አይፍሩ። ✍️ ለወሲብ ፍላጎት ካጣሁስ? ➥ የኩላሊት በሽታ ወይም የኩላሊት ውድቀት ሲኖርዎት ለወሲብ ያለዎት ፍላጎት ሊለወጥ ይችላል። መጀመሪያ ላይ ለወሲብ ያነሰ ፍላጎት ሊኖርዎት ይችላል። ይህ ሊከሰት ይችላል ምክንያቱም በበሽታዎ ምክንያት የሚመጣውን አካላዊ እና ስሜታዊ ለውጦች ለመቋቋም ብዙ ኃይል ያስፈልግዎታል። ከጊዜ በኋላ ግን ፍላጎትዎ ወደ መደበኛው ሊመለስ ይችላል። አንዳንድ ሕመምተኞች መቆም ወይም ማቆየት የበለጠ ከባድ ሊሆንባቸው ይችላል። ይህ ከኩላሊት ውድቀት ጋር በጣም የተለመደ ነው። ➥ በዲያሊሲስ ወይም በሌሎች ህክምናዎች ሙሉ በሙሉ ሊወገዱ የማይችሉ መርዛማ ቆሻሻዎች በደም ውስጥ በመከማቸት ከመድኃኒት የጎንዮሽ ውጤቶች ሊመጣ ይችላል። ከእነዚህ ችግሮች ውስጥ ብዙዎቹ ሊታከሙ ይችላሉ። ➥ ስሜቶች እንዲሁ በወሲባዊ ተግባር ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። ይህ ውጥረትን ፣ የመንፈስ ጭንቀትን ፣ ነርቮችን ፣ የአካል ጉዳተኝነትን ወይም የሞትን ፍርሃት ፣ የጋብቻ ችግሮችን እና ሌሎችንም ይጨምራል። ➥ ለአንዳንድ ሰዎች የኩላሊት በሽታ መያዛቸው አነስተኛ የመሳብ ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርጉ አካላዊ ለውጦችን ሊያስከትል ይችላል። ይህ ደግሞ የወሲብ ፍላጎትን ሊጎዳ ይችላል። 👉 የጾታ ሕይወታቸው እየተለወጠ መሆኑን ያወቁ ባለትዳሮች ከሐኪማቸው ጋር መነጋገር አለባቸው። ከእነዚህ ችግሮች ውስጥ ብዙዎቹ ሊታከሙ ይችላሉ። ✍️ ለኩላሊት ህመምተኞች የግብረ ሥጋ ግንኙነት ደህንነቱ የተጠበቀ ነውን? ➥ አንዳንድ ሕመምተኞች እና አጋሮቻቸው ወሲባዊ እንቅስቃሴ የታካሚውን ሞት ሊያስከትል ወይም የዲያሊሲስ መዳረሻን ወይም የተተከለውን ኩላሊት ሊጎዳ ይችላል ብለው ይጨነቃሉ። በኩላሊት ህመምተኞች ላይ በወሲባዊ ግንኙነት ላይ ምንም ገደቦች መደረግ የለባቸውም። የወሲብ እንቅስቃሴ በመድረሻ ጣቢያው ላይ ጫና ወይም ውጥረት ካላደረገ ጉዳት አያስከትልም። ፍርሃት ሰዎች የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ያለአግባብ እንዲያስወግዱ ሊያደርግ ይችላል። ➥ ንቅለ ተከላ ከተደረገ በኋላ ጠባሳው መፈወስ እስኪጀምር ድረስ ወሲብ ለማድረግ መጠበቅ አስፈላጊ ነው። አንዴ ዶክተርዎ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን እንደገና መቀጠል ይቻላል ብሎ ከነገሮት ቡሀላ የሚያስጨንቅ ምንም ምክንያት የለም። ➥ ለአንዳንድ ባለትዳሮች የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ አይቻልም። አንዳንዶች ወሲብ እንደበፊቱ አስፈላጊ እንዳልሆነ ይሰማቸዋል። እንደ መንካት ፣ ማቀፍ እና መሳሳም ያሉ እንቅስቃሴዎች የግብረ ሥጋ ግንኙነት ባይኖርም እንኳን የሙቀትነት እና የጠበቀ ስሜት ይሰጣሉ። ➥ የወሲብ ህክምና ባለሙያዎች አማራጭ ዘዴዎችን ሊመክሩ ይችላሉ። ✍️ የወሲብ ችግሮች በአካላዊ ወይም በስሜታዊ ምክንያቶች መሆን አለመሆኑን እንዴት አውቃለሁ? ➥ ይህ ከእርስዎ እና ከባልደረባዎ የተሟላ የህክምና ፣ የስነ -ልቦና እና የወሲብ ታሪክ ይጠይቃል። መድሃኒቶች ለወሲባዊ የጎንዮሽ ጉዳቶች ካላቸው መገምገም እናም ከተቻለ መለወጥ አለባቸው። የደም ምርመራዎች የስኳር በሽታን ለመመርመር የሆርሞን ደረጃዎችን እና የደም ስኳር መጠንን ማካተት አለባቸው። ለወንድ ብልት የነርቭ እና የደም አቅርቦት ጥሩ ከሆነ እና እነሱ ካሉ ለማየት ታካሚዎች ሊመረመሩ ይችላሉ። የአካላዊ ችግር ካልተገኘ የስሜታዊ ምክንያት ግምት ውስጥ መግባት አለበት። ✍️ ችግሩ አካላዊ ከሆነ ምን ማድረግ ይቻላል? ➥ ብልታቸው ደካማ ወይም ለማይቆዩ ታማሚዎች ለማቆየት ብዙ አማራጮች አሉ። የወንድ ብልት ተከላ ቀዶ ጥገና ተጣጣፊ ወይም ከፊል ጠንካራ ዘንጎችን ወደ ብልት ውስጥ ያስገባል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ቀዶ ጥገና ወደ ብልት የደም ፍሰትን ያሻሽላል። ቀዶ ጥገና የማይፈልጉ ከሆነ ሆርሞኖች ሊሰጡ ይችላሉ። በአፍ እና በመርፌ የሚሰሩ መድኃኒቶች መነሳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። የውጭ መሳቢያ መሣሪያዎች ብልትን ለወሲብ ከባድ ሊያደርጉት ይችላሉ ፣ ግን ጊዜ እና የእጅ ጥንካሬ ይፈልጋሉ። ➥ የሴት ብልት በወሲባዊ እንቅስቃሴ ወቅት ህመም ሊኖረው ይችላል። ዝቅተኛ የሆርሞን መጠን የሴት ብልት ድርቀት ሊያስከትል ይችላል። በውሃ ውስጥ የሚሟሟ የሴት ብልት ቅባትን መጠቀም ከግብረ-ሥጋ ግንኙነት ጋር የተጎዳውን ህመም ሊቀንስ ወይም ሊያቆም ይችላል። የፔትሮሊየም ጄሊን አይጠቀሙ ምክንያቱም በበሽታ የመያዝ አደጋን ከፍ ሊያደርግ ይችላል። ➥ አንዳንድ ሕመምተኞች ጉልበት ላይኖራቸው ይችሉ ይሆናል ወይም ለኃይል ግፊት ፣ ለሆርሞን ለውጦች ወይም ለደም ግፊት መድኃኒቶች በመዳከም ምክንያት ተጨማሪ ጊዜ ሊፈልጉ ይችላሉ። የደም ግፊት መድሃኒት ወይም ተጨማሪ ሆርሞኖች ለውጥ ሊያስፈልግ ይችላል። ✍️ ችግሩ ሥነ ልቦናዊ ከሆነ ምን ማድረግ ይቻላል? ➥ እንደ የኩላሊት በሽታ እና የኩላሊት ውድቀት ያሉ ከባድ ኪሳራዎች ሲያጋጥሙዎት የመረበሽ ወይም የመንፈስ ጭንቀት የተለመደ ነው። እነዚህ ስሜቶች የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ጨምሮ በብዙ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የኃይል ማጣት እና ዝቅተኛ ፍላጎት ሊያስከትሉ ይችላሉ። የወሲብ ችግር ከተከሰተ ብዙውን ጊዜ ሀፍረት እና የጥፋተኝነት ስሜት ይከተላሉ። ችግሩ እንደገና ይከሰታል ብለው መፍራት ግለሰቡ ከወሲባዊ ሁኔታዎች እንዲርቅ ሊያደርግ ይችላል። የመዝናኛ ልምምዶች እነዚህን ፍራቻዎች ለመቆጣጠር ይረዳሉ። አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ አእምሮን በሥራ ላይ ለማቆየት ይረዳል እናም የአካል ሁኔታን እና የሰውነት ምስልን ያሻሽላል። የወሲብ ችግሮች ከቀጠሉ የወሲብ ሕክምና ሊረዳ ይችላል። ችግሩ ሥነ ልቦናዊ ቢሆንም እንኳ ለአካላዊ ችግሮች ከተጠቀሱት የሕክምና አማራጮች መካከል አንዳንዶቹ ጠቃሚ ናቸው። ✍️ የወሲብ ሕክምና ሊረዳ ይችላል? ➥ የወሲብ ሕክምና ጥንዶችን እና ግለሰቦችን ወሲባዊ ችግሮች ይመለከታል። በወሲባዊ ሕክምና ውስጥ የመጀመሪያው ደረጃ ለግለሰቡ ወይም ለባልና ሚስት ወሲባዊ ትምህርት ሊሆን ይችላል። ቴራፒስቱ በቤት ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ያሳውቃችኋል። እነዚህም፦ 📌 የመገናኛ ልምምዶችን ፣ 📌 የጭንቀት መቀነስ እንቅስቃሴዎችን እና አስደሳች ንክኪዎችን በመስጠት እና በመቀበል ክህሎቶችን የማሻሻል መንገዶችን ይለማመዳሉ። ✍️ የኩላሊት ህመምተኞች እራሳቸውን ለመርዳት ምን ማድረግ ይችላሉ?

የጡት ካንሰር ህመም የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር! የጡት ካንሰር ህመምን ለመከላከል የራስ መመርመሪያ ዘዴዎችን መጠቀም ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንዲሁም ምልክቶች ሲታዩ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን
የጡት ካንሰር ህመም የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር! የጡት ካንሰር ህመምን ለመከላከል የራስ መመርመሪያ ዘዴዎችን መጠቀም ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንዲሁም ምልክቶች ሲታዩ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራ ማድረግ ይመከራል። #BreastCancerAwarenessMonth

የጡት ካንሰር ህመም የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር! የጡት ካንሰር ህመምን ለመከላከል የራስ መመርመሪያ ዘዴዎችን መጠቀም ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንዲሁም ምልክቶች ሲታዩ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን
የጡት ካንሰር ህመም የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር! የጡት ካንሰር ህመምን ለመከላከል የራስ መመርመሪያ ዘዴዎችን መጠቀም ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንዲሁም ምልክቶች ሲታዩ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራ ማድረግ ይመከራል። #BreastCancerAwarenessMonth

የነስር መንስኤዎች /////////////////////////////////////// ነስር (epistaxis) ድንገተኛ የሆነ አስደንጋጭ ከአፍንጫ ደም መፍሰስ ሲሆን በአብዛኛው ለከፋ አደጋ የማይዳርግ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ነስርን ከሚነሳበት ክፍል በመነሳት በሁለት ይከፈላል፡፡ 1, ከፊተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Anterior Nosebleeds) ከአፍንጫ ቀደዳዎች መካከል አካባቢ የሚገኙ የደም ስሮች ሲጎዱ የሚከሰት ሲሆን ከ90 በመቶ በላይ ለሚከሰት የነስር ዓይነት ምክንያት ነው፡፡አብዛኛዉን ጊዜ ህፃናት ላይ ይከሰታል እንዲሁም በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል፡፡ 2, ከኋለኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Posterior Nosebleeds) በአብዛኘው በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ ይከሰታል፡፡ ወደ ዉስጥ ካሉ የደም ስሮች የሚመጣ መጠኑ በዛ ያለ ደም ይኖረዋል እናም የተለየ ሕክምና የሚያስፈልገው እና ውስብስብ ነው፡፡ ነስርን የሚያመጡ መንስኤዎች 📌 በአፍንጫ ላይ አደጋ/ አፍንጫ መጎርጎር 📌 የደም ግፊት መጨመር 📌 የደም መርጋት ችግር 📌 የደም ማቅጠኛ መድሐኒቶች 📌 የመተንፈሻ አካላት ህመም 📌 ቀዘቃዛ እና ደረቅ የአየር ንብረት 📌 ለኬሚካል ተጋላጭ መሆን 📌 አልኮል እና በአፍንጫ የሚወሰዱ አደንዛዥ እጽ 📌 እርግዝና ነስርን መከላከያ መንገዶች 📌 በአብዛኛው ነስር የሚከሰተው በቀዘቀዘ እና በደረቅ የአየር ንብረት ስለሆነ አፍንጫ እንዳይደርቅ ቫዝሊን (Petroleum jelly) መጠቀም 📌 አፍንጫዎን በጣትዎ አለመነካካት 📌 የነስር መንስኤ ከሌላ የጤና ችግር ጋር ተያያዥነት ካለው ሐኪም ማማከር 📌 ሲጋራ ከማጨስ መቆጠብ ነስር ከተከሰተ በኋላ ወደ ሐኪም መሄድ የሚያስፈልገው 📌 አፍንጫዎን ለ10 ደቂቃ ያህል ይዘው ቆይተው ነስሩ ካልቆመ 📌 ወዲያዉኑ ወዲዉኑ በተደጋጋሚ የሚነስር ከሆነ 📌 ለነስሩ ጋር ተያይዞ ደም ማስመለስ ካለ 📌 ራስ ማዞር ወይንም ራስ መሳት ካለዉ 📌 ከፍተኛ ትኩሳት ካለ 📌 የልብ ምት የሚጨምር ከሆነ እና ለመተንፈስ መቸገር ካለ 📌 ሰውነት ላይ ሽፍታ/መበለዝ ካለ 📌 ከአፍንጫ ሌላ ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች ደም መፍሰስ ካለ 📌 ደምን ለማቅጠን የሚጠቅሙ መድኃኒቶችን የሚወስዱ ከሆነ 📌 የደም መርጋትን የሚያስተጓጉሉ ማንኛውንም ዓይንት ሕመም ካለ 📌 የኬሞቴራፒ ሕክምና በቅርቡ ወስደው ከነበረ ነስር እንዴት ይቆማል 📌 ከጭንቅላትዎ ጎንበስ ማለት (ጭንቅላትን ወደ ላይ ቀና ማድረግ የሚፈሰውን ደም ወደ ጉሮሮ በማምጣት ጉዳት ያስከትላል) 📌 ቀጥ ብለው መቀመጥ 📌 ሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች በአውራ ጣት እና በጠቋሚ ጣት ግጥም አድርጎ ለአስር ደቂቃ ይዞ ማቆየት 📌 በአፍ የሚመጣን ደም መትፋት 📌 ነስሩ ካቆመ በኋላ አፍንጫዎን አለመነካካት 📌 ቢያንስ ለ24 ሰአታት ያህል ሞቅ ያሉ መጠጦችን አለመጠቀም የነስር ህክምና 📌 ደም በሚፈስበት ቦታ የአፍንጫ እስፖንጅ ማስገባት እና ከ 24-48 ሰአት ማቆየት(የሚገባዉም ሆነ የሚዎጣዉም በጤና ባለሙያ እርዳታ ነዉ፡፡) 📌 ለደም መርጋት የሚሆኑ መድሀኒቶች 📌 የተቀደዱ የደም ስሮችን ካሉ በኬሚካል(ሲሊቨር ናይትሬት በመጠቀም) እና በቀዶ ህክምና ማስተካከል ይገኙበታል። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

ጤና አዳም (Arugula) ውልደቱ አውሮፓ ባልካን አካባቢ ነው፡፡ ሳይንሳዊ ስያሜው አሩጉላ (Arugula) ይሰኛል፡፡ፀረ- ባክቴሪያ፣ፀረ-ፈንገስ፣ፀረ- መርዝማ እና ፀረ- ውክሳጅ ተግባራትን ያከናውናል፡፡ በአውሮፓ የባህል ሕክምና ውስጥ ገናና ስም አለው፡፡ ዛሬም ቢሆን በአውሮፓ ባህላዊ ሕክምና ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ በአገራችንም ቢሆን ለሰው ልጅ ጤና የሚሰጠውን ፈውስ በመመልከት ጤና- አዳም የሚል ስያሜን አትርፎለታል፡፡ በሻይ፣ በቡና፣ በወተት፣ ተወቅጦ በውሃ ተብጥብጦ ይጠጣል፡፡ጤና አዳም ለውጥ ማጣፈጫ በመሆን በሽሮና በበርበሬ ውስጥ ሳይቀር በመግባት ይታወቃል፡፡ምግብ ጣዕሙን ጠብቆ እንዲቆይም የማድረግ ብቃት አለው፡፡ ለአብነት አይብን ማንሳት እንችላለን፡፡ ዛሬ ስለዚህ ታአምረኛ ተክል ሳይንስ ያረጋገጣቸውን የጤና በረከቶች እናጋራችሁአለን፡፡ 1. የተመገባችሁት ምግብ አልስማማ ካላችሁ፣ በጋዝ(አየር) ምክንያት ሆዳችሁን የሚነፋ፣ቁርጠት ካጋጠማችሁ ምናልባትም ትውከትና ተቅማት በምግብ መመረዝ ምክንያት ካጋጠማችሁ ጤና አዳም እርጥቡን በውሃ ጨምቃችሁ ጠጡ፡፡ ከቻላችሁ የተወሰነ ቅንጣቢ አኝካችሁ በውሃ አወራርዱት ውጤቱን በፍጥነት ታዩታላችሁ፡፡ ምክንያቱም ጤና አዳም ባክቴሪያዎችን በመግደል አኩሪ ገድል አለውና፡፡ 2. የቆዳና የእግር ፈንገስ ያስቸግራችኋል፡፡ ዘመናዊ መድኃኒት በመፈለግ ጊዜና ገንዘብዎን አያባክኑ፡፡በቀላሉ ጤና አዳሙን ይውቀጡና እግሮን ቀብተው ያሳድሩት መፍትሔውን ያገኙታል፡፡ 3. የጡንቻና የአጥንት መገጣጠሚያ ሕመም ካለብዎት በየዕለቱ ለተወሰኑ ወራት ጠዋት ጠዋት ጤና አዳም ጨምቀው በውሃ ይጠጡ ለችግሮ መፍትሔ በቅፅበት ያገኛሉ፡፡ 4. ሴቶች በተለይ ከወር አበባ መምጣት ጋር በተያያዘ ለሚከሰት የጠለመደ የሆድ ቁርጠት ለብ ያለ ውሃ ከጤና አዳም ጭማቂ ጋር ብትጠጡ ቁርጠት ደና ሰንብት ይሉታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አእምሮችሁንና በአጠቃላይ የነርቭ ስርዓታችሁን ዘና የማድረግ ብቃት አለው፡፡ 5. ጤና አዳም ጎጂ ነፍሳትን የማባረርና የመግደል ልዩ ብቃት አለው፡፡ ስለሆነም ቢንቢን፣በረሮ፣የወባ ትንኝና፣ዝምብ የመሳሰሉትን ከቤትዎ የማባረር ችሎታ ስላለው ጤና አዳሙን ወቅጦ በውሃ በጥብጦ በመርጨት በሽታ አምጪ ነፍሳትን በቀላሉ መከላከል ይችላሉ፡፡ 6. ጤና አዳም በውስጡ በያዘው ፀረ- መርዛማ ንጥረነገርና ፀረ-ባክቴሪያ በፊቶ ቆዳ ላይ የሚገኙ የሞቱ ሕዋሳትን በማስወገድ የፊት መጨማደድና የለጊዜ ማርጀትን ይከላከላል፡፡ ወቅጠው ፊትዎን ማታ ተቀብተው ጠዋት ለብ ባለ ውሃ ቢታጠቡት ልዩነቱን ያገኙታል፡፡ 7. ከፍተኛ የቫይታሚን ሲ ንጥነገር የየያዘ በመሆኑ የተፈጥሮ የበሸታ አቅማችንን በማጎልበት በበሽታ በቀላሉ እንዳንጠቃ ይረዳናል፡፡ ስለሆነም ጠዋት በባዶ ሆድዎ በውሃ ውስጥ የተወሰነ ጭማቂ ጤና አዳም የመጠጣት ልምድ ያዳብሩ፡፡ 8. ጤና አዳምን በሻይ ፣በቡና፣በውሃ ወይም እንዲሁ አኝከው የሚወጡ ሴቶች የወር አበባ ሑደታቸው ጤናማ ይሆናል፡፡ የተዛባም ከሆነ እንዲስተካከል ያደርጋል፡፡ 9. በእንቅልፍ እጦት ለምትቸገሩ መልካም ዜና አለው ጤና አዳም፤ ብቻ እንናተ አዝውትራችሁ ተመገቡት ሰላማዊ እንቅልፍ እሱ ይቸራችኋል፡፡ 10. ለደም ግፊት ጤና አዳም ወሳኝ መድኃኒት ነው፡፡ የደም ፍሰትን ያሻሽላል፣ደም ቧንቧ ጥበት ያሰፋል፡፡ በአጠቃላይ የልብ ጤናን ይጠብቃል፡፡ 11. ጤና አዳም በአስም፣በሽንት ፊኛ ኢንፊክሽን ለሚሰቃዩ ሰዎችም ትልቅ መፍትሔ እንደሆነ በሳይንስ ተረጋግጧል፡፡ እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን! እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

✍ #በእርግዝና #ጊዜ #የሚከሰት #የደም #ማነስ 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #አንዲት ነፍሰጡር ሴት የደም ማነስ ከያዛት በደምዋ ውስጥ በቂ እና ጤናማ የሆነ ቀይ የደም ሴል አንሷታል ማለት ነው። ነፍሰ ጡሯ ሴት የደም ማነስ ካለባት ቀይ የደም ሴል ለሰውነትና ለተረገዘው ጽንስ ንጹህ አየር (Oxygen) ማድረስ ያቅተዋል። ⏩ #አንዲት ሴት በምታረግዝበት ወቅት ሰውነትዋ የተረገዘውን ጽንስ እድገት ለመደገፍ ሲል ቀድሞ ከነበራት ደም የበለጠ ያመርታል፡፡ ነገር ግን ነፍሰ ጡሯ ሴት በቂ አይረን ወይም ተመሳሳይ የሆኑ ሌሎች ንጥረ ነገሮችን የምታገኝ ካልሆነ የሚያስፈልገውን ያህል ደም ማምረት ስለማትችል በእርግዝና ጊዜ ሰውነትዋ ሊያመርት የሚገባውን ያህል ተጨማሪ ደም ሊኖራት አይችልም፡፡ ⏩ #በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ማነስ ዓይነት በሶስት ይከፈላል፡- 👉 #በአይረን #እጥረት #የሚከሰት #የደም #ማነስ 🔺 የአይረን እጥረት የደም ማነስ የሚከሰተው ሰውነት በቂ አይረን ካላገኘ እና በቂ የሆነ ሄሞግሎቢን ማምረት ሲያቅተው ነው፡፡ ይህ ማለትም በቀይ የደም ሴል ውስጥ ፕሮቲን አለመኖር ሲሆን ይህም ኦክስጂንን ከሳንባዎች ወደ ተቀረው የሰውነት ክፍል የሚያዳርስ ነዉ፡፡ 👉 #በፎሌት #እጥረት #የሚከሰት #የደም #ማነስ 🔺 ፎሌት ማለት በተፈጥሮ በተለያዩ ምግቦች ውስጥ ማለትም አረንጓዴ ቅጠል ውስጥ የሚገኝ ቫይታሚን A እና B ሲሆን ይህም ሰውነት ጤናማ ቀይ የደም ሴሎችን ጨምሮ አዳዲስ ሴሎች እንዲፈጠሩ የሚያስችል ነው፡፡ 👉 #በቫይታሚን #ቢ12 #እጥረት #የሚከሰት #የደም #ማነስ 🔺 ጤናማ ቀይ የደም ሴሎችን ለመፍጠር ሰውነት ቫይታሚን ቢ 12 የተሰኘውን ንጥረ ነገር ይፈልጋል። ነፍሰጡር የሆነችው ሴት ይህንን ቫይታሚን የያዙ ምግቦችን በበቂ ሁኔታ ካልተመገበች ጤናማ የሆኑ ቀይ የደም ሴሎችን ለማምረት አትችልም፡፡ 👉 #በእርግዝና #ጊዜ #የሚከሰት #የደም #ማነስን #የሚያባብሱ #ሁኔታዎች 🔺 እርግዝናው መንትያ ከሆነ 🔺 ከመጀመሪያው እርግዝና በቅርበት በድጋሚ እርግዝና ከተከሰተ 🔺 የጠዋት ጠዋት ማስመለሱ (morning sickness) ብዙና የማያቋርጥ ከሆነ 🔺 እርግዝናው በታዳጊነት እድሜ ከሆነ 🔺 በአይረን የበለጸገ ምግብ የማይመገቡ ከሆነ 🔺 ከእርግዝናው በፊት የደም ማነስ ታማሚ ከሆነ 👉 #ምልክቶቹ 🔺 የገረጣ እና የለሰለሰ ቆዳ ፣ ጥፍር ፣ ከንፈር 🔺 ድካምና አቅም ማጣት 🔺 የትንፋሽ መቆራረጥ፣ የፈጠነ የልብ ምት ፣ አንድ ነገር ላይ ትኩረት የማድረግ ችግር…… 👉 #መፍትሄዎቹ 🔺 በአይረን የበለጸጉ ምግቦችን ማዘውተር 🔺 ፎሊክ አሲድን እርግዝና በሚያስቡ ወቅት ቀድሞ መውሰድ እርግዝና ላይም ሆነው በአግባቡ መጠቀም 🔺 ምልክቶቹ ከታዩ ወደ ህክምና መሄድ እንዲሁም የእርግዝና ክትትልን ማድረግ።

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias - آمار و تحلیل کانال تلگرام @drsofonias