fa
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

رفتن به کانال در Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

کانال ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 19 967 مشترک است و جایگاه 1 154 را در دسته پزشکی و رتبه 1 678 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 19 967 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 26 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -547 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -20 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 24.05% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 7.27% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 4 805 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 453 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 9 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 27 ژوئن, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته پزشکی تبدیل کرده‌اند.

19 967
مشترکین
-2024 ساعت
-1217 روز
-54730 روز
آرشیو پست ها
ጤና ይስጥልኝ ውድ የቴሌግራም ቻናል ተከታታዮቻችን ለዛሬ ስለ ደም ዓይነቶች ምን ያህል ያውቃሉ? አብረን እንከታተል ABO blood Group System share @DrSofonias የደም ዓይነት በቀይ የደም ሴሎች ሽፋን(ገጽ) ላይ የሚገኝ በውርስ የወሰድነውን አንቲጅን(Antigen) መሠረት ያደረገ የደም ክፍፍል ነው፡፡ አራት ዋና ዋና የደም ዓይነቶች አሉ እነሱም ኤ፣ ቢ፣ ኤቢ እና ኦ ናቸው፡፡ የደም ዓይነት ከእናትና አባት በወረስነው ዘረመል(ጂን) ይወሰናል፡፡ ሰውነታችን በአማካይ ከአራት እስከ ስድስት ሊትር ደም ይይዛል፡፡ ደም ከቀይ የደም ሴል፣ ነጭ የደም ሴል እና ፕሌትሌትስ (በፈሳሽ መሰል ፕላዝማ) የተሰራ ወይም የተገነባ ነው፡፡ የፕላዝማ(Plasma) 90% ውሃ ሲሆን በተጨማሪ ፕሮቲን፣ ሆርሞንና ውጋጅ ቆሻሻዎችን ይዟል፡፡ የደማችን 60% የሚሆነው ፕላዝማ ሲሆን 40% የሚሆነው ደግሞ የደም ሴሎች ናቸው፡፡ የደም ሴሎቻችን እያንዳንዳቸው የራሳቸው ተግባር አላቸው ቀይ የደም ሴሎች ኦክስጂን ወደተለያየ የሰውነት ክፍል ያደርሳሉ ካርበን ዳይኦክሳይድ እና ቆሻሻዎችን ከሰውነታችን ያስወግዳሉ፤ ደም ቀይ ቀለም እንዲኖረው አድርገውታል፡፡ ነጭ የደም ሴሎች ሰውነታችን በሽታ የመከላከል ሥርዓት አንዱ ክፍል ሲሆን ኢንፌክሽንን በመዋጋት ይረዳናል፡፡ ፕሌትሌትስ ደም እንዲረጋ በማድረግ የደም መፍሰስን ይከላከላሉ፡፡ የደም ዓይነታችን የሚለየው/የሚታወቀው በደም ውስጥ በሚገኙ አንቲጅን(Antigen) እና አንቲበዲ(Antibody) አማካይነት ነው፡፡ አንቲበዲ(Antibody) ሰውነታችን ከውጪ ለሚገቡ ጀርሞችን ለመከላከል የሚጠቀምበት የበሽታ መከላከያ ሥርዓት ክፍል ነው፡፡ አንቲጅን በቀይ የደም ሴሎች ገጽ ላይ የሚገኙ ፕሮቲኖች ናቸው አንቲበዲዎች በፕላዝማ ውስጥ የሚገኝ ፕሮቲን ሲሆን ከውጭ ወደሰውነታችን የገቡ ማንኛውንም ነገሮች በመለየት እንዲወገዱ ለበሽታ የመከላከል ስርዓት ጥቆማ ያደርጋል፡፡ የኤ.ቢ.ኦ የደም ሥርዓት ክፍፍል ምን ይመስላል? አራት ዋና ዋና የደም ዓይነቶች አሉ፡፡ • ኤ(A)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ኤ አንቲጅን ብቻ ይገኛል (በፕላዝማ ውስጥ ደግሞ ቢ አንቲበዲ ይገኛል)፡፡ • ቢ(B)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ቢ አንቲጅን ብቻ ይገኛል (በፕላዝማ ውስጥ ደግሞ ኤ አንቲበዲ ይገኛል)፡፡ • ኤቢ(AB)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ኤ እና ቢ አንቲጅን ይገኛሉ (በፕላዝማ ውስጥ ደግሞ ምንም ዓይነት አንቲበዲ አይገኝም) • ኦ(O)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ምንም ዓይነት አንቲጅን አይገኝም (በፕላዝማ ውስጥ ሁለቱም ኤ እና ቢ አንቲበዲ ይገኛሉ)፡፡ የትኛው የደም ዓይነት ለየትኛው የደም ዓይነት መስጠት ይችላል? ✓ ኦ(O) የደም ዓይነት ለማንኛውም ሰው ደም መለገስ ይችላል፡፡ ✓ ኤ(A) የደም ዓይነት ያለው ሰው ኤ እና ኤቢ የደም ዓይነት ላለቸው ደም መለገስ ይችላል፡፡ ✓ ቢ(B) የደም ዓይነት ያለው ሰው ቢ እና ኤቢ የደም ዓይነት ላለቸው ደም መለገስ ይችላል፡፡ ✓ ኤቢ(AB) የደም ዓይነት ያለው ሰው ኤቢ የደም ዓይነት ላለው ሰው ብቻ ደም መለገስ ይችላል፡፡ ከየትኛው የደም ዓይነት መቀበል ይችላሉ? ✓ ኦ(O) የደም ዓይነት ካለዎት ከ ኦ(O) ብቻ ይቀበላሉ፡፡ ✓ ኤ(A) የደም ዓይነት ካለዎት ከ ኤ(A) እና ከ ኦ(O) ብቻ ይቀበላሉ፡፡ ✓ ቢ(B) የደም ዓይነት ካለዎት ከ ቢ(B) እና ከ ኦ(O) ብቻ ይቀበላሉ፡፡ ✓ ኤቢ(AB) የደም ዓይነት ከማንኛውም የደም ዓይነት መቀበል ይችላሉ፡፡ ከኤ(A) እና ቢ(B) አንቲጅን በተጨማሪ ሌላ ሶስተኛ አንቲጅን አለ እሱም አር.ኤች ፋክተር(Rh factor) ይባላል፡፡ በደም ውስጥ ሊኖርም ላይኖርም ይችላል በደም ውስጥ ሲገኝ ፖዘቲቭ (+) ይባላል በደም ውስጥ ሳይገኝ ሲቀር ደግሞ ነጌቲቭ(-) ይባላል፡፡ • ሌሎች መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንድደርስዎ ፔችንን ላይክ ሼር ያድርጉ ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ተጭነው የኛ ቤተሰብ ይሁኑ ስለምትከታተሉን ከልብ አመሰግናለሁ መልካም ጤንነት

ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንደምን አላችሁ በእውነቱ ከሆነ የሁላችሁንም ጥያቄ መመለስ እንደማልችል እንድትረዱኝ እና እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ። ሶሻል ሚድያ የከፈትኩበት ዋነኛ ሀሳብ ያለኝን እውቀት ሼር ላ
ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንደምን አላችሁ በእውነቱ ከሆነ የሁላችሁንም ጥያቄ መመለስ እንደማልችል እንድትረዱኝ እና እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ። ሶሻል ሚድያ የከፈትኩበት ዋነኛ ሀሳብ ያለኝን እውቀት ሼር ላደርግ እንጂ የሁላችሁንም ጥያቄማ ማስተናገድ ለኔ ከባድ ነው! እንደምታውቁት ጤና ከፍተኛ ጊዜን ይፈልጋል። ከዚህ በፊት ስልኬ ግልፅ ነበር እናም ቀኑን ሙሉ ይደወልልኝ ነበር እኔም ሲመቸኝ በሰዓቱ ስራ ከሌለብኝ አወራቸው ነበር እናም ከአንድ ሰው ገር በቀላሉ 20 ደቂቃ አወራ ነበር። በጣም ከባድ እየሆነብኝ ሲመጣ ስልኬንም አነሳሁት! እናም እንድትረዱኝ የምፈልገው በርካታ ሰዎች የምትጠይቁኝ ጥያቄ ቀንግግር ህክምና ሳይሆን በአካል ህክምና የሚፈታ ነው። እንዲሁም እኔ የቴሌግራም እና የ Youtube ቻናሌን የከፈትኩበት ዋነኛ ምክንያት የጤና መረጃዎችን ምልክቶቹን እና ህመሙን ተረድታችሁ እና ተገንዝባችሁ 1, እራሳችሁን ከበሽታ እንድትጠብቁ ምን አይነት ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባችሁ እንድታውቁ 2, የበሽታዎችን ሁኔታ ተረድታችሁ እና ተገንዝባችሁ ወደ ህክምና ተቋም በግዜ ሄዳችሁ እንድትታከሙ ነው። ስለዚህ ውድ የተከበራችሁ ተከታዮቼ ይህንን አውቃችሁ በስራ ምክንያት በጣም እረፍት የለኝም በአካል የህክምና ምክር እሰጣለሁ እንዲሁም ታካሚዎችን እመለከታለሁ በተጨማሪም ያለኝን ግዜ አጣብቤ በሶሻል ሚድያ የጤና መረጃዎችን አደርሳቹሀለው ስለዚህ ሲመቸኝ ጊዜ ካለኝ ጥያቄዎችን እመልሳለሁ ከዛ ውጪ ግን የሁላችሁንም ጥያቄ ማስተናገድ እንደማልችል እንድትረዱኝ ስል በአክብሮት እጠይቃቹሀለው🙏 አመሠግናለሁ ሰላም ሁኑልኝ!

☑️ ታዲያ ችግሩ ምንድን ነው? 1. መቀራርብ አለመቻል በርካታ ጥንዶችን ግንኙነታቸው ውስጥ ወሲብ አለመኖሩ አልያም ለወሲብ የመነቃቃት ፍላጎት አለማሳየት ያበሳጫቸዋል፡፡ ለምሳሌ:- በአንድ ወቅት በአሜሪካ ውስጥ በተደገ ጥናት ከ15% - 20% የሚደርሱ ግንኙነቶች ወሲብ አልባ ሲሆኑ ከአገቡት መካከል እድሜአቸው ከ50 ዓመት በታች የሆኑ ባለትዳሮች ላለፉት ጥቂት አመታት የወሲብ ግንኙነት አልፈፀሙም፡፡ ከ40 ዓመት በታች የሚሆኑት ቁጥራቸው 20% የሚደርሱት ደግሞ በአመት ጥቂት ጊዜዎች ወይም በወር አንድ ጊዜ ብቻ የወሲብ ግንኙነት ያደርጋሉ፡፡ ነገር ግን እዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባን ጉዳይ በእያንዳንዱ የትዳራችን እርከን ውስጥ ወሲብ አስፈላጊነቱ ባያጠያይቅም ከጊዜ በኋላ ግን ትዳሮች ከአካላዊ ንክኪ ይልቅ ወደ መንፈሳዊ ቅርርቦች ይሸጋገራሉ፡፡ በዚህም በወሲብ ጊዚ የነበረን ጥብቅ ቅርርብ ያክል ባይሆን አብሮ ለመዝለቅ ያክል የሚሆኑ ቅርርብ መፍጠሪያ መንገዶችን መጠቀም እንችላለን፡፡ 🔹 መሳሳም 🔹 ተጓዳኝን አሁንም እንደተወደዱ ለማሳየት አልፎ አልፎ ስልክ በመደወል የፍቅር ቃላቶችን መጠቀም 🔹 አረፍ ሲሉ ቆንጆ ነገር እየሰሙ አልያም እየተመለከቱ ወይንም ጎንጨት እያሉ ቢሆን የተጓዳኝን እግር፣ ጀርባ ማሸት 🔹 በየጊዜው በተጓዳኝ ላይ ያለንን እምነት ክብር ማሳየት 2. ክህደት ክህደት ዋነኛው የጋብቻ ቆራጭ መጋዝ ነው፡፡ ክህደት ሲፈፀምብዎ በተጓዳኝዎ ላይ ያልዎት እምነት ስለሚጠፋ ተነጋገግሮ ችግሩን ለመፍታት ያልወት ተነሳሽነት ይቀንሳል፡፡ ነገር ግን ጋብቻ ሁሌም ቢሆን የሚበልጠውን በማሰብ መታደስ ይችላልና ተቀምጦ በመነጋገር ችግሩን ለመፍታት መሞከር የተሻለ ነው፡፡ ጥናቱ እንደሚያሳየው ከሆነ 22% የሚሆኑ ወንዶች ቢያንስ አንድ ጊዜ ከሌላ ሴት ጋር ሲማግጡ ከአገቡ ሴቶች መካከል 14% የሚሆኑት ቢያንስ አንድ ጊዜ በትዳራቸው ላይ ይማግጣሉ፡፡ 36% የሚሆኑት ሴቶችና ወንዶች ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር የወሲብ ግንኙነት አላቸው ተብሎ ይታመናል፡፡ በሚገርም ሁኔታ ግን 70% ያገቡ ሴቶች እንዲሁም 54% ያገቡ ወንዶች በፍቅር አጋራቸው የሚፈፀምባቸውን ክህደት አያውቁም፡፡ 3. ጭቆና አንዳንድ ጊዜ ጭቆና ሲባል በአካል ላይ የሚፈፀም ብቻ የሚመስለን እንኖራለን፡፡ ነገር ግን በስሜትም በገንዘብም ደረጃ ጭቆና ይፈፀማል፡፡ ጭቆና ብዙ ጊዜ በትዳር አጋር ላይ ብቻ የሚፈፀም ቢሆንም አንዳንዴ ግን ልጆችንም ይጨምራል፡፡ አንዳንድ ትዳሮች ጭቆናው ጫፍ የወጣ እስካልሆነ ድረስ ልጅ ያለአባት/ያለእናት እንዳያድግ እና ከዛሬ ነገ ለውጥ ሊመጣ ይችላል ብሎ በማሰብ ወደ ፍቺ ላያመራ ይችላል፡፡ 4. ሱስ አንዳንዴ እንደቁማር፣ አደንዛዥ እፅ፣ መጠጥ የመሳሰሉ ሱሶች ከትዳራችን በላይ ሆነው ሊታዩን ይችላሉ፡፡ ትዳሩ ውስጥ የሚገኘው ይህ አካል ከሱስ ማገገሚያ ህክምናዎችን ለመውሰድ ፍቃደኛ ሳይሆንና መላቀቅ ሳይችል ከቀረ ጋብቻው አደጋ ውስጥ ይወድቃል፡፡ ውሎ አድሮም ፍቺ ሊከተል ይችላል፡፡ 5. የተጋነኑ እሳቤዎች በርግጥ አንድ ሰው ተሰርቶ ነው ወደ ጋብቻ መግባት ያለበት ወይንስ ጋብቻ ውስጥ ይሰራል የሚለው ጥያቄ መልስ እንደየግለሰቦች ይወሰናል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ለፍቺ የሚዳረጉ ትዳሮች ሌላኛው ምክንያታቸው ከትዳር በኋላ ይቀየራል፣ ከተጋባን በኋላ ይህን ባህርይውን ይተዋል አልያም ከተጋባን በኋላ ይህን ያደርግልኛል፣ ይህን ያሳካልኛል የሚሉ የተጋነኑ እሳቤዎችንና አመለከታከቶችን ይዘው ወደ ትዳር ይገባል፡፡ የማታ የማታ ግን እነዚህ የተጋነኑ እሳቤዎች የትዳሩ መፍረስ ምክንያት ሆነው ይመጣሉ፡፡ 6. በዘመዶች መከካል ያል ግጭት የእናቷን ጥቅም ከቤተሰባችን ጥቅም ታስበልጣለች፡፡ ከትዳራችን ይልቅ ለአባቱ የተሻለ ትኩረት ይሰጣል፡፡ የሚሉ ምክንያቶች ወደኋላ በተደጋጋሚ ለሚደረጉ ጭቅጭቆች በር በመክፈት ትዳሩን ወደፍቺ ያንደረድሩታል፡፡ 7. በወሲብ አለመጣጣም ብዙ ጊዜ ከትዳር በኋላ በፍቅረኝነት ዘመን የሚደረጉ ወሲቦች ፍፁም ተቃራኒ ሆነው ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ከትዳ በፊት ለወሲብ ያለን ፍላጎት እጅግ ከፍ ያለ በመሆኑ በሳምንት ለበርካታ ቀና በቀን ውስጥ በድግግሞሽ ልንፈፅም እንችላን፡፡ ነገር ግን ከትዳር በኋላ በሚፈጠሩ ጫናዎች እንደልጅ ማሳደግ ብዙ ጊዜን ስራ ላይ ማሳለፍ የመሳሰሉ ጫናዎች ለወሲብ ያለንን ፍላጎት ሊገሉት አልያም የምናደርገውም ወሲብ እንደቀድሞው በፍቅር የተሞላ ላይሆን ስለሚችል በወሲብ አለመጣጣም ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህን ችግር አስተውለው መፍትሄ ማስቀመጥ የማይችሉ ጥንዶች ሊፋቱ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው፡፡ 8. የውፍረት መጨመር ይህ ምክንያት በቀጥታ ሳቢ ከመሆን አልያም ካለመሆን ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ ምናልባት ልናገኝ የሚገባንን ክብርም ሊያሳጣን ይችላል፡፡ ብዙ ጊዜ ውፈረት በሚከሰት ጊዜ ለመቀነስ ምንም አይነት ፍላጎትም ከተከተለ መሰላቸት ሳቢ አለመሆን ይከተሉና ትዳሩ የመፍረስ አደጋ ሊገጥመው ይችላል፡፡ 9. ማንነትን ማጣት ከሁለት አንዳቸው ስኬታማ ሆነው የቤት ውስጥ ጉዳዮችን መሸፈን በሚችሉበት ወቅት አልያም ልጅን ለማሳደግ በማሰብ ስራ ማቆም ሲከሰት ቀስበቀስ ማንነትን ማጣትና ጭቅጭቅ ብቅ ማለት ይጀምራሉ፡፡ ይህ ደግሞ ውሎአድሮ ወደተካረረ ፀብ ተለውጦ ትዳርንም ሊበትን ይችላል፡፡ 10. የአዕምሮ መቃወስ አልያም የአካል ጉዳት መከሰት ከሁለት አንዳቸው ላይ የአዕምሮ መቃወስ አልያም የአካል ጉዳት ሲደርስ አንዳቸው አስታማሚ መሆናቸው ግልፅ ነው፡፡ ነገርየው በጋብቻ ቀን እንደገቡት ቃል ቀላል ላይሆን ይችላልና አስታማሚነት ሁሉም የሚቀበለው ጉዳይ ላይሆን ይችላል፡፡ በርግጥ አንዳንዶች ይህን ከባድ ጊዜ ተቋቁመውና የትዳር አጋራቸውን እየተንከባከቡ እስከህይወት ዘመናቸው ድረስ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ ይህን ማድረግ ያልቻሉት ግን ወደ ፍቺ ሊያመሩ ይችላሉ።

ጥንዶች ለፍቺ ምን ያነሳሳቸዋል? የሞላቸው ብቻ አይደሉም እጅግ የተትርፍርፋቸው ናቸው፡፡ በትዳር በቆዩባቸው 27 ዓመታት ሶስት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ የማይክሮሶፍት ኩባንያ መስራችና የአለማችን አራተኛው ከበርቴ ሰው ቢሊጌትስና ሚሊንዳ ጌትስ፡፡ አሁን ግን ሁሉም ነገር ታሪክ ወደ መሆኑ ይመስላል፤ የ27 ዓመታት ትዳራችንን አፍርሰናል ብለዋል፡፡ ☑️ ለመሆኑ ጥንዶችን ለፍቺ ምን ያነሳሳቸዋል? ብዙ የፍቺ ወረቀቶችን ብታገላብጡ በዋናነት የገንዘብ አጥረት ወደ ፍቺ እንደሚመራ ትገነዘባላችሁ፡፡ አነስተኛ ገቢ ካለው ሰው ጋር ህይወትን ለመመስረት መሞከር በአብዛኛው ግንኙነቱን እስከወዲያኛው ሲያበላሸውም ታዝባችሁ ይሆናል! ሆኖም ግን ሀብታም መሆን ፍቺን ሙሉ በሙሉ ያስወግዳል ማለት አይደለም፡፡ ሚሊየነሮችን እና ቢሊየነሮችን ያካበቱ ብዙ ስኬታማ ሰዎች አሁንም ትዳራቸውን በፍቺ እየቋጩት ይገኛሉ፡፡ ይህ ደግሞ የሚያሳየው ለፍቺ ምክንያቱ የገንዘብ እጥረት ብቻ እንዳልሆነ ነው፡፡

☑️ ታዲያ ችግሩ ምንድን ነው? 1. መቀራርብ አለመቻል በርካታ ጥንዶችን ግንኙነታቸው ውስጥ ወሲብ አለመኖሩ አልያም ለወሲብ የመነቃቃት ፍላጎት አለማሳየት ያበሳጫቸዋል፡፡ ለምሳሌ:- በአንድ ወቅት በአሜሪካ ውስጥ በተደገ ጥናት ከ15% - 20% የሚደርሱ ግንኙነቶች ወሲብ አልባ ሲሆኑ ከአገቡት መካከል እድሜአቸው ከ50 ዓመት በታች የሆኑ ባለትዳሮች ላለፉት ጥቂት አመታት የወሲብ ግንኙነት አልፈፀሙም፡፡ ከ40 ዓመት በታች የሚሆኑት ቁጥራቸው 20% የሚደርሱት ደግሞ በአመት ጥቂት ጊዜዎች ወይም በወር አንድ ጊዜ ብቻ የወሲብ ግንኙነት ያደርጋሉ፡፡ ነገር ግን እዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባን ጉዳይ በእያንዳንዱ የትዳራችን እርከን ውስጥ ወሲብ አስፈላጊነቱ ባያጠያይቅም ከጊዜ በኋላ ግን ትዳሮች ከአካላዊ ንክኪ ይልቅ ወደ መንፈሳዊ ቅርርቦች ይሸጋገራሉ፡፡ በዚህም በወሲብ ጊዚ የነበረን ጥብቅ ቅርርብ ያክል ባይሆን አብሮ ለመዝለቅ ያክል የሚሆኑ ቅርርብ መፍጠሪያ መንገዶችን መጠቀም እንችላለን፡፡ 🔹 መሳሳም 🔹 ተጓዳኝን አሁንም እንደተወደዱ ለማሳየት አልፎ አልፎ ስልክ በመደወል የፍቅር ቃላቶችን መጠቀም 🔹 አረፍ ሲሉ ቆንጆ ነገር እየሰሙ አልያም እየተመለከቱ ወይንም ጎንጨት እያሉ ቢሆን የተጓዳኝን እግር፣ ጀርባ ማሸት 🔹 በየጊዜው በተጓዳኝ ላይ ያለንን እምነት ክብር ማሳየት 2. ክህደት ክህደት ዋነኛው የጋብቻ ቆራጭ መጋዝ ነው፡፡ ክህደት ሲፈፀምብዎ በተጓዳኝዎ ላይ ያልዎት እምነት ስለሚጠፋ ተነጋገግሮ ችግሩን ለመፍታት ያልወት ተነሳሽነት ይቀንሳል፡፡ ነገር ግን ጋብቻ ሁሌም ቢሆን የሚበልጠውን በማሰብ መታደስ ይችላልና ተቀምጦ በመነጋገር ችግሩን ለመፍታት መሞከር የተሻለ ነው፡፡ ጥናቱ እንደሚያሳየው ከሆነ 22% የሚሆኑ ወንዶች ቢያንስ አንድ ጊዜ ከሌላ ሴት ጋር ሲማግጡ ከአገቡ ሴቶች መካከል 14% የሚሆኑት ቢያንስ አንድ ጊዜ በትዳራቸው ላይ ይማግጣሉ፡፡ 36% የሚሆኑት ሴቶችና ወንዶች ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር የወሲብ ግንኙነት አላቸው ተብሎ ይታመናል፡፡ በሚገርም ሁኔታ ግን 70% ያገቡ ሴቶች እንዲሁም 54% ያገቡ ወንዶች በፍቅር አጋራቸው የሚፈፀምባቸውን ክህደት አያውቁም፡፡ 3. ጭቆና አንዳንድ ጊዜ ጭቆና ሲባል በአካል ላይ የሚፈፀም ብቻ የሚመስለን እንኖራለን፡፡ ነገር ግን በስሜትም በገንዘብም ደረጃ ጭቆና ይፈፀማል፡፡ ጭቆና ብዙ ጊዜ በትዳር አጋር ላይ ብቻ የሚፈፀም ቢሆንም አንዳንዴ ግን ልጆችንም ይጨምራል፡፡ አንዳንድ ትዳሮች ጭቆናው ጫፍ የወጣ እስካልሆነ ድረስ ልጅ ያለአባት/ያለእናት እንዳያድግ እና ከዛሬ ነገ ለውጥ ሊመጣ ይችላል ብሎ በማሰብ ወደ ፍቺ ላያመራ ይችላል፡፡ 4. ሱስ አንዳንዴ እንደቁማር፣ አደንዛዥ እፅ፣ መጠጥ የመሳሰሉ ሱሶች ከትዳራችን በላይ ሆነው ሊታዩን ይችላሉ፡፡ ትዳሩ ውስጥ የሚገኘው ይህ አካል ከሱስ ማገገሚያ ህክምናዎችን ለመውሰድ ፍቃደኛ ሳይሆንና መላቀቅ ሳይችል ከቀረ ጋብቻው አደጋ ውስጥ ይወድቃል፡፡ ውሎ አድሮም ፍቺ ሊከተል ይችላል፡፡ 5. የተጋነኑ እሳቤዎች በርግጥ አንድ ሰው ተሰርቶ ነው ወደ ጋብቻ መግባት ያለበት ወይንስ ጋብቻ ውስጥ ይሰራል የሚለው ጥያቄ መልስ እንደየግለሰቦች ይወሰናል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ለፍቺ የሚዳረጉ ትዳሮች ሌላኛው ምክንያታቸው ከትዳር በኋላ ይቀየራል፣ ከተጋባን በኋላ ይህን ባህርይውን ይተዋል አልያም ከተጋባን በኋላ ይህን ያደርግልኛል፣ ይህን ያሳካልኛል የሚሉ የተጋነኑ እሳቤዎችንና አመለከታከቶችን ይዘው ወደ ትዳር ይገባል፡፡ የማታ የማታ ግን እነዚህ የተጋነኑ እሳቤዎች የትዳሩ መፍረስ ምክንያት ሆነው ይመጣሉ፡፡ 6. በዘመዶች መከካል ያል ግጭት የእናቷን ጥቅም ከቤተሰባችን ጥቅም ታስበልጣለች፡፡ ከትዳራችን ይልቅ ለአባቱ የተሻለ ትኩረት ይሰጣል፡፡ የሚሉ ምክንያቶች ወደኋላ በተደጋጋሚ ለሚደረጉ ጭቅጭቆች በር በመክፈት ትዳሩን ወደፍቺ ያንደረድሩታል፡፡ 7. በወሲብ አለመጣጣም ብዙ ጊዜ ከትዳር በኋላ በፍቅረኝነት ዘመን የሚደረጉ ወሲቦች ፍፁም ተቃራኒ ሆነው ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ከትዳ በፊት ለወሲብ ያለን ፍላጎት እጅግ ከፍ ያለ በመሆኑ በሳምንት ለበርካታ ቀና በቀን ውስጥ በድግግሞሽ ልንፈፅም እንችላን፡፡ ነገር ግን ከትዳር በኋላ በሚፈጠሩ ጫናዎች እንደልጅ ማሳደግ ብዙ ጊዜን ስራ ላይ ማሳለፍ የመሳሰሉ ጫናዎች ለወሲብ ያለንን ፍላጎት ሊገሉት አልያም የምናደርገውም ወሲብ እንደቀድሞው በፍቅር የተሞላ ላይሆን ስለሚችል በወሲብ አለመጣጣም ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህን ችግር አስተውለው መፍትሄ ማስቀመጥ የማይችሉ ጥንዶች ሊፋቱ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው፡፡ 8. የውፍረት መጨመር ይህ ምክንያት በቀጥታ ሳቢ ከመሆን አልያም ካለመሆን ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ ምናልባት ልናገኝ የሚገባንን ክብርም ሊያሳጣን ይችላል፡፡ ብዙ ጊዜ ውፈረት በሚከሰት ጊዜ ለመቀነስ ምንም አይነት ፍላጎትም ከተከተለ መሰላቸት ሳቢ አለመሆን ይከተሉና ትዳሩ የመፍረስ አደጋ ሊገጥመው ይችላል፡፡ 9. ማንነትን ማጣት ከሁለት አንዳቸው ስኬታማ ሆነው የቤት ውስጥ ጉዳዮችን መሸፈን በሚችሉበት ወቅት አልያም ልጅን ለማሳደግ በማሰብ ስራ ማቆም ሲከሰት ቀስበቀስ ማንነትን ማጣትና ጭቅጭቅ ብቅ ማለት ይጀምራሉ፡፡ ይህ ደግሞ ውሎአድሮ ወደተካረረ ፀብ ተለውጦ ትዳርንም ሊበትን ይችላል፡፡ 10. የአዕምሮ መቃወስ አልያም የአካል ጉዳት መከሰት ከሁለት አንዳቸው ላይ የአዕምሮ መቃወስ አልያም የአካል ጉዳት ሲደርስ አንዳቸው አስታማሚ መሆናቸው ግልፅ ነው፡፡ ነገርየው በጋብቻ ቀን እንደገቡት ቃል ቀላል ላይሆን ይችላልና አስታማሚነት ሁሉም የሚቀበለው ጉዳይ ላይሆን ይችላል፡፡ በርግጥ አንዳንዶች ይህን ከባድ ጊዜ ተቋቁመውና የትዳር አጋራቸውን እየተንከባከቡ እስከህይወት ዘመናቸው ድረስ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ ይህን ማድረግ ያልቻሉት ግን ወደ ፍቺ ሊያመሩ ይችላሉ።

ጥንዶች ለፍቺ ምን ያነሳሳቸዋል? የሞላቸው ብቻ አይደሉም እጅግ የተትርፍርፋቸው ናቸው፡፡ በትዳር በቆዩባቸው 27 ዓመታት ሶስት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ የማይክሮሶፍት ኩባንያ መስራችና የአለማችን አራተኛው ከበርቴ ሰው ቢሊጌትስና ሚሊንዳ ጌትስ፡፡ አሁን ግን ሁሉም ነገር ታሪክ ወደ መሆኑ ይመስላል፤ የ27 ዓመታት ትዳራችንን አፍርሰናል ብለዋል፡፡ ☑️ ለመሆኑ ጥንዶችን ለፍቺ ምን ያነሳሳቸዋል? ብዙ የፍቺ ወረቀቶችን ብታገላብጡ በዋናነት የገንዘብ አጥረት ወደ ፍቺ እንደሚመራ ትገነዘባላችሁ፡፡ አነስተኛ ገቢ ካለው ሰው ጋር ህይወትን ለመመስረት መሞከር በአብዛኛው ግንኙነቱን እስከወዲያኛው ሲያበላሸውም ታዝባችሁ ይሆናል! ሆኖም ግን ሀብታም መሆን ፍቺን ሙሉ በሙሉ ያስወግዳል ማለት አይደለም፡፡ ሚሊየነሮችን እና ቢሊየነሮችን ያካበቱ ብዙ ስኬታማ ሰዎች አሁንም ትዳራቸውን በፍቺ እየቋጩት ይገኛሉ፡፡ ይህ ደግሞ የሚያሳየው ለፍቺ ምክንያቱ የገንዘብ እጥረት ብቻ እንዳልሆነ ነው፡፡

ኩላሊት በሽታ አለቦትን? ውድ ወንድምና እህቶቼ የሚከተለውን የኩላሊት መድሀኒት አዘገጃጀት ይከታተሉ ፦ የዌራ ዘይት 3 የሾርባ ማንከያ 2 ትልቁ ሲኒ የተፈጨ ቦግዶኒስ ይላወሳል 3 የሾርባ ማንከያ ቦግዶኒስ በ1 ሌትር ውሃ ማታ ማታ ሲተኛ በውሃው በጥብጦ መዋጥ ሲተኙ በሚያመው ኩላሊት በኩል መተኛት አከታትሎ ሳምንት ሳይረሳ ከተደረገ የኩላሊት ጠጠር አለ ተብሎ ኦፖራሲዮን ይሆናሉ ተብሎ ዶክተር የፃፈለት እንኳን ቢኖር በበጉዶኒሱ ሰበብ ጠጠሩ ይወጣል ። መውጣቱ ሊታወቅም ይችላል የተለቀ ከሆነ ትንሽ ከሆነ ሳያቁት ይወጣል በተለይ አንድ ሌትር በቀን ከጠጡ ይጨመርና ቋቅ እስኪል ጥግብ ብለው መጠጣት አለቦት አደራ በሚያም ጎን መተኛቱ አይዘንጉ ከመዳኒቱ አላህ ያገናኛችሁ የሚባለው ይህን የመሰለ ሰበብ በተግባር የታየለት በግዶኒስ በመቀቀልም በረድ አድርጎ ውሃው ጠግቦ በመጠጣትም እንደ አትክልትም መብላት የተቀቀለውም መብላት ይመከራል። የኩላሊት ህመም ያለበት ሰው ለመቆም የሚከለክል ለመንገድ ጉዞ የሚከለክል ጎን የሚወጋ ጠጠር ያለበት ፊት እንኳን እንዲገረጣ መልክ ቢቀይርም ሰበቡን በማድረስ በአሏህ እርዳታ በጉዶኒስ ይታከሙ ። ለራሴም ሰበብ ሆኖኛል ውጪ የተፃፈለት የኩላሊት ጠጠር ያለበት ወጥቶለት በሶፍት ተይዞ ወደ ወጭ የፃፈው የነበረው ዶክተር ተይዞ ሲሄድ በአይኔ ያየሁት ከወንድ ልጅ ብልት ይወጣል ተብሎ የማይታሰበ በአይኔ በብሌኑ አይቻለሁ ወደ ዶክተሩ የተኬደው ቀሪ ካለ ተብሎ ቼክ ለመደረግና ዶክተሩ አዝኖ ሲመረምረው ወደ ሌላሃገር ሲፃፍለት የገንዘብ አቅም እንደሌለው ሲነግረው ሰውየው በጣም ያለ ውጪ እንደ ማይቻል በሃዘኔታ ስለሸኘው ለማበሰርም ጭምር ከአቶብስ ተራ ወደ ሾላ ሲሄድ በኩላሊት በሽታ ይሰቃያሉ ኩላሊት በሽታ ያለበት ካለ ይህን ጉድ ከኔ ነው የወጣው ስለዚ የተያዘ ካለ ብሎ አሰራሩ ነገረኝ። ሁለት ሆነን ኩላሊታችን የሚያመን ሰራነው ሁለታችን ሰበብ ሆነን ቦግዶኒሱ እኛም ሰበብ ሆነን እናተም ተጠቀሙበት የነገርኳቸው ሁሉ እንደተዋቸው እየነገሩኝ ነው ወሊላሂል ሃምድ አላህ የሁሉም ነገር መድሃኒት ፈጠረ ለኩላሊት ከፈጠረው መድሃኒት አንዱ ብየዋለሁ ። በግዶኒስ መልካም ተግባር ከሰሩ በትክክል ይድናሉ ሼር ሼር ሼር አድርጉት ለተሰቃየ ሰው ሰበብ ይሆናል እራሴም ተጠቅሜበት ድራሹ ጠፋ መቆምና ብዙ ጉዞ ማድረግ አልችልም ነበር ወሊላሂል ሃምድ ተሻለኝ ብዙ ሰው በዚ በሽታ የተጠቃ አለ አሰራጩት ለአንድ ሰው ሂወት ማዳን አጅሩ ከባድ ነው ምርጥ የኩላሊት ዶክተር ነው ተጠቀሙት ።

☑️ ሳንባ ምች እንዴት ይከሰታል? የሳንባ ምች በባክቴሪያ እና በቫይረስ አማካይነት የሚከሰት በሽታ ነው፡፡ በፈንገስ እና የኬሚካል ሽታ በሚበዛበት ቦታ የሚሰሩ ሰዎች ላይም በሽታው ሊከሰት ይችላል፡፡ በሽታን የመከላከል አቅማቸዉ የደከመ የስኳር ፣የኤች አይ ቪ እና የካንሰር በሽተኞችንም በብዛት ያጠቃል፡፡ የተበከለ አየር ወደሰዎች የመተንፈሻ አካል በሚገባበት ሰዓት በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ኢንፌክሽን በመፍጠር ለሳንባ ምች ያጋልጣል፡፡ የሳንባ ምች በሽታን በተመለከተ ጠቅላላ ሀኪም አደራው ካሳሁን ሙያዊ ትንታኔ ሰጥተውናል፡፡ ጉንፋን ቶሎ ቶሎ የሚያጠቃቸው ፣የአስም በሽተኞች ፣ሲጋራ የሚያጨሱ እና አልኮል አዘውትረው የሚጠጡ ሰዎች በበሽታው የመያዝ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ የሳንባ ምች በሽታ ዕድሜያቸዉ ከአምስት ዓመት በታች እና ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን በብዛት ያጠቃል፡፡ ☑️ የሳንባ ምች በሽታ ምልክቶች 🔹 ከሶስት እስከ አምስት ቀን አክታ የቀላቀለ ሳል መሳል፣ 🔹 የሰውነት ትኩሳት መጨመር ፣ 🔹 ትንፋሽ ማጠር፣ 🔹 የራስ ምታት ስሜት መኖር፣ 🔹 ብርድ ብርድ ማለት፣ 🔹 በሳል ወቅት የደረት ውጋት መባባስ፣ 🔹 ላብ ላብ ማለት፣ 🔹 የልብ ምት መጨመር፣ 🔹 የሰውነት ድካም መኖር፣ 🔹 የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ 🔹 ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ናቸው፡፡ ☑️ የሳንባ ምች በሽተኛ ማድረግ ያለበት ነገር በተገቢው መንገድ በባለሙያ የታዘዘውን መድሃኒት መውሰድ፡፡ በቂ እረፍት ማድረግ፣ አልኮል አለመጠጣት፣ አለማጨስ፣ ጉንፋን የሳንባ ምችን የመቀስቀስ ባህሪ ስላለው ተገቢውን ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ☑️ በሽታውን ለመከላከል መደረግ ያለበት ተገቢውን የአመጋገብ ስርአት በመከተል መመገብ፣ የሚሰጡ ክትባቶችን ተቆጣጥሮ ማስከተብ፣ የግል እና የአካባቢን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ፣ ሳል እንደተከሰተ በአስቸኳይ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ እና ተገቢውን ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ህፃናት በሽታው በተከሰተ ከሶስት እስከ አምስት ቀናት ውስጥ ካልታከሙ ህይወታቸው አደጋ ላይ ስለሚወድቅ ወላጆች ትኩረት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

የሳንባ ምች ውሃ መቋጠር እና መፍትሄው ምንድን ነው? ሳንባ በተለያዩ ምክንያቶች ለሕመም ሊጋለጥ ይችላል። በርግጥ የሳንባ ህመሞችን በአግባቡ ሕክምና በመከታተል መዳንም እንደሚቻል ሃኪሞች ይገልጻሉ።

ለጥርስ ጤና የሚጠቅሙ 6 የምግብ አይነቶች ********** በዛሬው የና አምድ ለጥስ ጤና መልካ የሆኑ ስድስ ምግቦችን እመለከታለን። ✔ወተት ወተ በካልሺየምና በሌሎች ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ስለሆነ ለጤናማ ጥርስ ጠቃሚ ነው፡፡ በተጨማሪም በአፍ ውስጥ ያለውን የአሲድ ደረጃ የሚቀንስ በመሆኑ የጥርስ መበላትን ይከላከላል፡፡ በመሆኑም ወተትን መጠቀም የጥርስ ጤናን ለመጠበቅ ወሳኝ በመሆኑ ወተትን ማዘውተር ይመከራል። ✔አሳ አሳ ቫይታሚንና ሌሎችን ማዕድናት በውስጡ የያዘ በመሆኑ ለጤና ጠቃሚ ነው፡፡ በአሳ ውስጥ ለጤና አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ስለሚገኙበት እንዲጠቀሙ ይበረታታል፡፡ የስጋ አይነቶች ለአፍ ጤና መልካም እንደሆኑ ይነገራል ፤ አሳ በተለየ የተሻለ ጠቀሜታ አለው፡፡ ✔ትኩስ ፍራፍሬ ትኩስ ፍራፍሬ አብዝቶ መመገብ ለጥርስ ጠቃሚ ነው፡፡ በሲትሪክ አሲድ የበለፀጉትን አለመመገብ ቢኖርብዎትም የብርቱካን የአሲዱ መጠን ዝቅተኛ በመሆኑ ከሌሎች በተሻለ መጠቀሙ መልካም ነው። ✔ጥርስን ለማንጣት የሚረዳ ስትሮቤሪ እና አፕል የመሳሰሉትን መመገብ ጠቃሚ ነው፡፡ ✔እርጎ እርጎ ፣ ከድድና መንጋጋ በሽታ የሚከላከሉ ካልሺየምና ፕሮባዮቲክስ ስላለው ለአፍ ጤና ጠቃሚ ነው፡፡ ስለዚህ በየቀኑ እርጎን ከገበታ አለመለየት ይመከራል። ✔ነጭ ሽንኩርት ነጭ ሽንኩርት ለአፍ ጤና ጠቃሚ ከሆኑ ምግቦች አንዱ ነው፡፡ ነጭ ሽንኩርት በውስጡ ባለው አሊሲን ንጥረ ነገር በአፍ ውስጥ ያለን ባክቴሪያ ይገድላል። እነዚህ ባክቴሪያዎች አብዛኛውን ጊዜ የጥርስ መበላትና የአፍ በሽታ የሚያስከትሉ ናቸው፡፡ ✔ሽንኩርት ሽንኩርትም በአፍ ውስጥ ያሉ በሽታ አምጪ ባክቴሪያዎችን ይከላከላል። ለዚህም ሽንኩርት ጥሬውን መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ ✔ መሰረታዊ ጉዳይ ለጥርስ ጤና የአፍ ንፅህና አጠባበቅ ልምምድ ማዳበር እና የተጠቀሱትን ምግቦች መመገብ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ካልሆነ የጥርስ እንደ ብሬስ፣ ጥርስ ተከላ እና ሌላም ከፍ ያለ ህክምና ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ✔ ማሳሳቢያ - ጨውና ስኳር ለጥርስ መቦርቦር ምክንያት በመሆናቸው ሰዎች እንዳያዘውትሯቸው በጥርስ ህክምና ባለሙያዎች ይመከራል።

የሺሻ ጉዳት #Like #Share ሺሻ ማጨስ የተጀመረው ቱርክ ወይም ህንድ ውስጥ ነው ተብሎ ይገመታል፡፡ አሁን ግን በመላው አለም በተለይም አሜሪካ፤ካናዳ እና እንግሊዝ በመሳሰሉት ያደጉ ሃገሮች ውስጥ ሳይቀር እየተስፋፋ መጥቷል፡፡ ሺሻ የሚጠቀሙ ሰዎች ብዙ ጊዜ "ሺሻ እኮ ምንም ጉዳት የለውም፡፡ ተፈጥሯዊ ነገር ነው፡፡ ይሄ እኮ ከፍራፍሬ ነው የሚሰራው" ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ግን እውነት ሺሻ ምንም ጉዳት የለውም? ሺሻ ምንድን ነው? ሺሻ ማለት የትንባሆ ቅጠልን ከሞላሰስ (የስኳር ተረፈ ምርት) ወይም የፍረፍሬ ጣእም ካለው ሲረፕ ጋር ቀላቅሎ ማጨስ ማለት ነው፡፡ ኢትዮጲያ ውስጥ ሺሻን ለማጨስ የምንጠቀመው ከሰል ነው፡፡ የትንባሆው ቅጠል በሞላሰሱ ወይም በፍራፍሬ ሲረፕ እርጥብ ይሆናል፡፡ ብዙ ጊዜ የእንጆሪ፤ የአፕል፤ ቸኮሌት፤ ኮኮናት እና የናና ጣእም ያላቸው የፍርፍሬ ሲሮፖች ለሺሻ ተመራጭ ናቸው፡፡ ያንን በከሰሉ አሙቆ የሚወጣውን ጭስ በውሃ ውስጥ እያለፈ ሲመጣ ጭሱን በቱቦ መማግ ነው ሺሻ ማጨስ የሚባለው፡፡ ሺሻ ውስጥ ምን አለ? የትንባሆውን ጭስ ለማጣፈጥ እና ጉሮሮ ላይ እንዳይከብድ ለማድረግ ቅጠሉ ከፍራፍሬ ሲረፕ ወይም ከሞላሰስ ጋር ይቀላቀላል እንጂ ልክ እንደ ሲጋራ ሺሻም የሚሰራው ከትንባሆ ቅጠል ነው፡፡ ስለዚህ በውስጡ ልክ እንደ ሲጋራ ኒኮቲን (ትንባሆ ውስጥ የሚገኝ አነቃቂ እና ሱስ አስያዥ ንጥረ ነገር) ፤ ካርቦን ሞኖኦክሳይድ፤ አርሰኒክ እና ሊድ የተባሉትን መርዛማ እና ጎጂ ንጥረ ነገሮች ይዟል ማለት ነው፡፡ ሲጋራ ከማጨስ ሺሻ ማጨስ አይሻልም? ብዙ ጊዜ ሰዎች ሺሻን የሚያጨሱት ለተወሰነ ሰአት ስለሆነ እና እንደ ሲጋራ በየቤቱ ስለማይገኝ ከሲጋራ ይሻላል ይላሉ፡፡ የሺሻ ጭስ የፍራፍሬ ጣእም ስላለው እና ጭሱ በውሃ ውስጥ ስለሚያልፍ ጎጂ የሆኑት ንጥረ ነገሮች በውሃው ይፀዳል ብለው ያምናሉ፡፡ ነገር ግን ♣ ልክ እንደ ሲጋራ ሁሉ ሺሻም ኒኮቲን ስላለው ሱሰኛ ያረጋል፡፡ እንደውም በሺሻ ውስጥ ያለው ኒኮቲን በሲጋራ ውስጥ ካለው ኒኮቲን በእጥፍ ይበልጣል፡፡ ♣ አንድ የሺሻ ፕሮግራም ቢያንስ ቢያንስ አንድ ሰአት እና ከዛ በላይ ይፈጃል፡፡በዚህ ጊዜ አንድ ሰው ከ 150 እስከ 200 ጊዜ ያህል ጭሱን ይምጋል፡፡ አንድ ሲጋራ አጭሶ ለመጨረስ ግን 20 ጊዜ ጭሱን መማግ ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡ ስለዚህ አንድ የሺሻ ፕሮግራም 8 ወይም ከዛ በላይ ሲጋራ አከታትሎ ማጨስ እንደ ማለት ነው፡፡ (ይሄ ጥናት የተሰራው በአለም የጤና ድርጅት ነው) ♣ ሲጋራም ሆነ ሺሻ የሚሰሩት ከትንባሆ ቅጠል ስለሆነ ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣሉ፡፡ ከነዚህ በሽታዎች ውስጥ የሳንባ ካንሰር እና የመተንፈሻ አካል ችግሮች፤ የጉሮሮ ካንሰር፤ አፍ ውስጥ የሚወጣ ካንሰር፤ ከጉሮሮ ወደ ጨጓራ ምግብን የሚወስደው የምግብ ቧንቧ ካንሰር እና የልብ ችግሮች ናቸው፡፡ በተጨማሪም ለአይን ህመም እና ለቆዳ መሸብሸብ ይዳርጋል፡፡ ♣ ከሲጋራ በተለየ ሁኔታም ሺሻውን ለማጨስ በከሰል ስለምንጠቀም ከከሰሉ የሚወጣውን መርዛማ ንጥረ ነገር ነገር ካርቦን ሞኖኦክሳይድን ጨምሮ ወደ ሳንባችን ይገባል፡፡ ♣ አሁን አሁን የትንባሆ ቅጠል የሌለባቸው ኸርባል በመባል የሚታወቁ ሺሻዎች ወደ ገበያው እየመጡ ነው፡፡ ከምን እንደሚሰሩ አምራቾቹ ግልፅ አድረገው መናገር አይፈልጉም፡፡ቢሆንም እሱም ቢሆን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ካርቦን ሞኖኦክሳይድን ጨምሮ ወደ ሳንባችን ማስገባቱ አይቀርም፡፡ ♣ ሺሻ ሲጨስ በቡድን ተቀምጦ እየተቀባባሉ ስለሆነ የሚጨሰው የተለያዩ በትንፋሽ እና በምራቅ የሚተላለፉ በሽታዎች ከአንዱ አጫሽ ወደ ሌላው አጫሽ በቀላሉ ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡ለምሳሌ እንደ ቲቢ እና ሄፒታይተስ የመሳሰሉት በሽታዎች ይገኙበታል፡፡ ♣ ሲጋራ ወይም ሺሻ የሚጨስበት ቦታ መገኘት ባናጨስ እንኳን በእጅ አዙር ለጭሱ እና ለጉዳቱ ያጋልጠናል፡፡ ስንተነፍስ ጭሱን መማጋችን አይቀርም፡፡ ይሄንን ፈረንጆቹ ሰከንድ ሃንድ ስሞክ ይሉታል፡፡ ♣ ስለዚህ ለጤንነታችን ሲባል በተቻለ አቅም ሺሻን ማጨስ ማቆም አለብን፡፡ https://t.me/DrSofonias/581

የስኳር በሽታ ምንድን ነው? ምልክቶቹና መፍትሄው!!! አንድ ሰው የስኳር በሽተኛ ነው የምንለው በሰውነቱ ውስጥ የሚገኘው የደም ግሉኮስ(ስኳር) በጣም ሲጨምር ሲሆን ይህም ሊከሰት የሚችለው አንደኛ የሰውነታችን የኢንሱልን የማምረት ብቃት በቂ ሳይሆን ሲቀር፣ ሁለተኛው ደግሞ ሰውነታችን የተመረተውን ኢንሱሊን በአግባቡ መቀበል ሳይችል ሲቀር ወይም ሁለቱም ባንድ ላይ ሲከሰት ነው። እዚህ ላይ ኢንሱሊን ምንድንነው ብላችሁ ካላችሁ፡ ምግብ ስንበላ ሰውነታችን ምግቡን ወደ ስኳር ይቀይረዋል፤ በዚህ ሰዓት የሰውነታችን ጣፊያ (pancreas) ኢንሱሊን የሚባለውን ነገር ያመነጫል፤ ይህ ኢንሱሊን የሰውነታችን ህዋሶች እንዲከፈቱ በመርዳት የተመረተው ግሉኮስ (ስኳር) ወደ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ለሀይል ምንጭ እንድንጠቀምበት ይረዳል። በዓለምአቀፍ ደረጃ በአሁኑ ሰዓት 380 ሚሊዮን ህዝቦች በስኳር በሽታ ተይዘው ይገኛሉ። የዓለም ጤና ድርጅት እንደገመተው ከሆነ በ 2030 ይህ ቁጥር በእጥፍ ይጨምራል። ባለንበት ጊዜ የስኳር በሽታ የሚያጠፋው ነፍስ በኤድስና በጡት ካንሰር ሕይወታቸው የሚያልፍ ሰው ተደምሮ ይበልጣል። ከሌሎች በሽታዎች በበለጠ የስኳር በሽታ ለአይነ ስውርነት, የኩላሊት ሥራ ማቆም እና ለልብ በሽታ ዋና መንስኤ ሆኖ ይገኛል። ሁለት አይነት የስኮር በሽታ አይነቶች አሉ፦ 1. አይነት አንድ (Type 1) የስኳር በሽታ በጣም ከባዱ የስኮር በሽታ አይነት ሲሆን ከኢንሱሊን አመራረት ጋር የተያያዘ ነው። አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው በሕጻንነትና በጉርምስና (teenager) ጊዜ ነው። ሆኖም ግን በሌላ የእድሜ ክልል ውስጥ አይከሰትም ማለት አይደለም። በዚህ አይነት የስኳር በሽታ ላይ የሰውነታችን አሰራር የራሱን ጣፊያ የሚያጠቃበት ሁኔታ አለ። ተመራማሪዎች ለምን እንደሆነ እስካሁን እርግጠኛ ባይሆኑም የሰውነታችን የመከላከሊያ ስርዓት (immune system) በስህተት በጣፊያ ውስጥ የሚገኙትን ኢንሱሊን የሚያመርቱ ህዋሶች እንደውጭ አካል በመመልከት ያጠፋቸዋል። ኢንሱሊን የለም ማለት ደግሞ የስኳር ክምችት ጨምሮ ወደ ግሉኮስ ሳይቀየር ይቀርና ሰውነታችን የሚያስፈልገውን ግሉኮስ ሳያገኝ ይቀራል። በህክምና ካልታዩት ይህ የበዛ የስኳር ክምችት አይንን፣ ኩላሊት፣ ነርቭን እና ልብን በመንካት ሞት ድረስ የሚደርስ አደጋ ሊያደርስብን ይችላል። 2. አይነት ሁለት (Type 2) የስኮር በሽታ ሁለተኛው አይነት የስኳር በሽታ ደግሞ ከኢንሱሊን ጋር ብዙም ያልተያያዘ ሲሆን ብዙውን ጊዜ የሚያጠቃው ከ35 ዓመት በላይ ያሉ ጎልማሶችን ነው። በዚህ በሽታ የተጠቁ ህመምተኞች ከፊሉን ለሰውነታቸውን የሚያስፈልገውን ኢንሱሊን ማምረት የሚችሉ ሲሆን ችግሩ ብዙውን ጊዜ የኢንሱሊኑ መጠን በቂ ሆኖ አለመገኘቱ ነው። ቅድም እንደተገለፀው ኢንሱሊኑ የሰውነታችንን ህዋሶች በመክፈት ግሉኮስ እንዲገባ ሙከራ ቢያደርግም አይሰራም። አብዛኛውን ጊዜ በዚህ የሚጠቁት ከሚፈለገው በላይ ክብደት ያላቸው ሰዎች ሲሆኑ ብዙውን ጊዜ እንደ ስፖርትና የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር መከላከል ሊቻል ይችላል። በዘር የሚተላለፈው የስኳር በሽታም እዚህ ውስጥ ይመደባል። የስኳር በሽታ ምልክቶች ቶሎ ቶሎ ሽንት መምጣት ከባድ የሆነ ጥማት ከባድ የሆነ ራብ ድንገተኛ የክብደት መጨመር ድንገተኛ የክብደት መቀነስ የተቆረጠ ወይም የተቀደደ የሰውነት ክፍል ቶሎ አለመዳን ስሜት አልባ መሆን የእይታ መጠን መቀነስ (ብዥ ማለት) የስኳር በሽታ መከላከያ መንገዶች ክብደታችንን መከታተል እንቅስቃሴ (ስፖርት) መስራት የተስተካከለ የአመጋገብ ስርዓት መኖር ከካፌ ወይም ሬስቶራንቶች የሚወጡ 'ቴክ አዌይ' አለማብዛት (ቤት ውስጥ አዲስ (fresh food) ነገሮችን መስራትና መጠቀም) መጠጥ ማቆም ማጨስ ማቆም የደም ግፊትን መከታተል በየጊዜው በዶክተር መታየት (check up) በአጠቃላይ የአኗኗር ዘይቤያችንን ጤነኛ ወደ ሆነ መንገድ መቀየር

#የስኳር #በሽታ (Diabetes Mellitus) • የስኳር በሽታ ማለት ሰውነታችን ግሉኰስ (ስኳር) የሚባለውን ንጥረነገር መጠቀም ባለመቻሉ የሚፈጠር ችግር ነው። በዚህ ጊዜ በደም ውስጥ ያለው የግሉኰስ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። • ይህ የሚሆነው ደግሞ ከሚከተሉት ባንዱ ነው። 1. ቆሽት ውስጥ የሚገኝ ህዋስ (ሴል) ኢንሱሊን የሚባለውን ሆርሞን ማምረት ባለመቻሉ የኢንሱሊን መጠን በመቀነሱ 2. ሰውነታችን ወይም ህዋሳት ኢንሱሊንን ተላምዶ ኢንሱሊኑ ጥቅም የማይሰጥ መሆኑ። 3. ቆሽት ውስጥ ኢንሱሊንን የሚያመርተው ቤታ ሴል በተለያየ ምክናየት በመጎዳቱ #በዚህ የተነሳ 1. ሰውነታችን ስኳርን በበቂ ሁኔታ አይጠቀምም 2. የስኳር ምርትና መጠን በደም ውስጥ ይጨምራል 3. ኢንሱሊን ችግሩን መቆጣጠር አይችልም። #ኢንሱሊን ማለት ቆሽት ውስጥ የሚመረት ሆርሞን ሲሆን በደም ውስክ ያለው የስኳር መጠን እንዳይጨምር የሚያደርግ ነው። #የኢንሱሊን ስኳር መጠን በደም ውስጥ እንዳይበዛ የሚያደርገው በሚከተሉት መንገዶች ነው። 1. ደም ውስጥ የነበረውን ስኳር ወደ ጉበት ለስዶ ማጠራቀም 2. በደም ውስጥ የነበረውን ስኳር ጡንቻ ውስጥ እንድጠራቀም ማድረግ 3. በደም ውስጥ የነበረውን ስኳር እያንዳንዱ ሴል እንድጠቀመው ማድረግ #በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ጨመረ የሚባለው በስኳር መጠን መለኪያ መሳሪያ (Gluco Meter) ተለክቶ ሲሆን ይህም 1. ለ8 ሰአት ያህል ሳይመገብ ይለካና ከ126 mg/dl በላይ ከሆነ 2. ምግብ በልቶ ሲለካ ከ200 mg/dl በላይ ከሆነና ሌሎችም ማረጋገጫዎች አሉ። #ያልታከመና ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የስኳር በሽታ የሚከተለውን ችግር ያመጣል። • የነርቭ መጎዳት • የአይን ጉዳት • የኩላሊት መጎዳት • የልብ ጉዳት • የደም ቱቦ ጉዳት • የእግርና እጅ ጫፍ መጎዳት #በዋናነት ሁለት አይነት የስኳር በሽታዎች አሉ። 1. የመጀመሪያው አይነት የስኳር በሽታ፡ በቤተሰብ ውስጥ ካለ የመጠቃት እድል አለ ተብሎ የሚታሰብ ሲሆን የራሳችን በሽታ ተከላካይ ሴል ኢንሱሊንን የሚያመርተውን ሴል በማጥቃቱና በአንዳንድ ቫይረስ ምክናየት የሚመጣ በሽታ ነው። • እስከ 45 አመት ባለ የእድሜ ክልል የሚመጣ ሲሆን ኢንሱሊን ባለመኖሩና ባለመመረቱ የሚከሰት ነው። • 10%ቱን ይይዛል። 2. ሁለተኛው አይነት የስኳር በሽታ፡ ጣፊያ ውስጥ ኢንሱሊን ቢመረትም የተመረተው ኢንሱሊን ጥቅም የማይሰጥና ሰውነታችን የተላመደው በመሆኑ የሚፈጠር ነው። • ከ45 አመት በኋላ የሚመጣና 90%ቱን የሚይዝ ነው። • እድሜ መግፋት፡ ውፍረት፡ ንደትና ብስጭት እንደ አነሳሽነት ይቆጠራሉ። 3. በእርግዝና ጊዜ የሚመጣ የስኳር በሽታ ቢኖርም ከወሊድ በኋላ ለብዙዎቹ እናቶች ይጠፋል። • ይህ የሚሆነው በእርግዝና ወቅት የሚመረት ሆርሞን የኢንሱሊንን መጠን ስለሚቀንስ ነው። • ከወሊድ በኋላ ሆርሞኑ ስለሚጠፋ ኢንሱሊን ይስተካከላል። #አጠቃላይ የስኳር በሽታ ምልክቶች • ቶሎ ቶሎ ውሀ መጠጣት • ቶሎ ቶሎ መሽናት • ቶሎ ቶሎ የሚመጣ የርሀብ ስሜት • ክብደት መቀነስ • የድካም ስሜት • እይታ ላይ ብጅታና በቀላሉ እጅና እግር መቁሰል። • በወንዶች ላይ የወሲብ ስሜት መቀነስ፡ የብልት መልፈስፈስና የጡንቻ መልፈስፈስ • በሴቶች ላይ ደግሞ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን፡ በቀላሉ በፈንገስ ኢንፊክሽን መጠቃትና የቆዳ መገርጣትና ማሳከክ #እነማን ተጋላጭ ናቸው? 1. በቤተሰብ ውስጥ የስኳር ተጠቂ ካለ 2. ውፍረት 3. እድሜ መጨመር 4. የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ 5. ከፍተኛ የደም ግፊት 6. ከፍተኛ ኮሌስትሮል 7. ከፍተኛ የስብ ጥርቅም ዋና ዋናዎቹ ናቸው። #የስኳር በሽታ የአኖኖር ዘይቤን በማስተካከልና በመድሀኒት ይታከማል። #አስቡ፡ የማይታከም የስኳር በሽታ በአንጎል፡ በልብ፡ በአይን፡ በኩላሊት፡ በደም ቱቦዎችና በእግር አካባቢ ከባድ ጉዳት ያስከትላል። # የነርቭ መጎዳት፡ የአይን መጥፋት፡ መስማትን መነጠቅ፡ ኩላሊት ከጥቅም ውጭ መሆን፡ እግር መቆረጥ ሁሉ ሊያደርስ ይችላል። # ነገር ግን የስኳር መጠኑን በየጊዜው እየተከታተለ የአኖኖር ዘይቤውን በሚያስተካክል ሰው ላይ ችግሩ እምብዛም አይደለም። # አመጋገብ፡ የአካል እንቅስቃሴ፡ ከንደትና ብስጭት መራቅ፡ የታዘዘ መድሀኒትን በአግባቡ መውሰድና በየጊዜው በጤና ባለሙያ እየታዩ መረጃና ትምህርት የሚያገኙ ከሆነ ችግሩ በቀላሉ ይስተካከላል፡፡ የሚያስከትለውን ጉዳት መከላከል ይቻላል። # የስኳር በሽታን ችላ ካልን ለከፍተኛ የስኳር በሽታ(ኬቶ አሲዶሲስ) ያጋልጠናል። ይህ ደግሞ ሰውነትን በቀላሉ ያጠቃል። ለሞትም ይዳርጋል!!! https://t.me/DrSofonias/578

ያለመድሀኒት የደም ግፊት ለመቀነስ የሚረዱ በሳይንስ የተደገፉ ዘዴዎች ምንም እንኳ መድኋኒት መውሰድ ግድ የሚሆንባቸው ሰዎች ቢኖሩም ለሁሉም ሰው ግን መድኃኒት መጀመር ላያስፈልግ ይችላል። ይህ ከሐኪሞ ጋር በመወያየት የሚወሰን ሲሆን ያለ መድሀኒት የደም ግፊት ለመቀነስ እንደሚረዱ በሳይንስ የተደገፉ ዘዴዎች እንዳሉ ማወቅና መተግበር ጠቃሚ ነው። በመሆኑም የሚከተሉትን ዘዴዎች ተጠቅመው የደም ግፊቶትን ይቀንሱ ስል እመክራለሁ ። ልብ ይበሉ ፦ በተለይ የኩላሊት ድክመት ፣ የልብ ድካምና ስኳር ካለቦት መድሀኒት ሊያስፈልጎት ስለሚችል እባክዎት ከሐኪሞ ጋር ይመካከሩ። 1ኛ፦ የአተነፋፈስ ዘዴ፡ በየቀኑ አየር ወደ ሳንባች በደንብ ሳብ አርገን ለ 4 ሰኮንድ ያህል በመያዝ ቀስ አርገን ወደ ውጭ መተንፈስ ። ይህን ለአስር ደቂቃ ያህል በየቀኑ መደጋገም ። ዮጋ ኒድራ/Yoga nidra ቪዲዮ ከዩቲዩብ በመመልከት አሰራሩን ማወቅ ይቻላል። ይህ መላ ሰውነታችንን ዘና/relax በማድረግ የደም ግፊት እንዲቀንስ ይረዳል ። 2ኛ፦የጨው መጠንን መቀነስ ፡ በአሁን ሰዓት ብዙ ነገሮች ጨው በብዛት ይይዛሉ፦ ዳቦ ጨው አለው፤ ካች ኣፕ ብዙ ጨው አለው....ወዘተ። ይህም ሳናውቀው የጨው አወሳሰዳችንን ከፍ ያደርገዋል ። ጨው የደም ግፊትን በብዛት ከፍ ከሚያደርጉ ነገሮች ዋንኛው ነው። በመሆኑም በቀን ከሚያስፈልገን 1.5 ግራም አብዝተን ባንጠቀም ይመከራል። ምግቦችን ስናዘጋጅም ሆነ ስንመገብ የጨው መጠናቸውን መመልከት ይኖርብናል ። 3ኛ፦ የደም ግፊትን ለመቀነስ የሚረዱ ምግቦችን ማዘውተር ፡ እንደ ነጭ ሽንኩርት ፣ ሙዝ፣ ቀይ ሽንኩርት ፣ ስትሮበሪ፣ ሰናፍጭ(spinach) የመሳሰሉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን መጠቀም የደም ግፊትን ለመቀነስ ይረዳል ። 4ኛ፦የአልኮል መጠጥ መተው /በጣም መቀነስ 5ኛ፦ የኣሳ ዘይትን መጠቀም፡ በብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች የተደገፈ ነው። ከ70 በላይ የሆኑ ጥናቶች የኣሳ ዘይት የደም ግፊትን ለመቀነስ እንደሚረዳ አሳይተዋል ። 6ኛ፦ጭንቀትን መቀነስ፦ ጭንቀት ኮርቲሶልና አድሬናሊን የተባሉ ንጥረ ነገሮችን በመጨመር የደም ግፊትን ከፍ ያደርጋል ።በመሆኑም የጭንቀት መጠንን የሚቀንሱ እንደ ፀሎት ፣ ዮጋ፣ ሜዲቴሽን የመሳሳሉ ዘዴዎችን በመጠቀም የደም ግፊት እንዳይጨምር ማድረግ ይቻላል ። በተለይ የረጅም ጊዜ ጭንቀት ካለቦት መነሻውን ለይተው መፍታት አለቦት። የስነ አእምሮ ወይም የስነ ልቦና ባለሙያ ማማከር ካስፈለጎ ሳያመነቱ ያድርጉት ። 7ኛ፦ ሰፖረት መስራና ውፍረትን መቀነስ፦ ይህን ማድረግ በርካታ የጤና ጥቅሞች ያሉት ሲሆን የደም ግፊትን መከላከልና መቀነስ ከዋነኞቹ ነው። 8ኛ፦ በቂ እንቅልፍ መውሰድ ፦ በቀን ከ7-8 ሰዓት መደበኛ እንቅልፍ መውሰድ የደም ግፊትን ለመቀነስ ሲረዳ የእንቅልፍ እጦት በተቃራኒው የደም ግፊት ከፍ እንዲል ያደርጋል ። በቂ እንቅልፍ በመውሰድ ፣ስፖርት በመስራትና ጨው በመቀነስ የደም ግፊትን እንከላከልም እንቀንስም። ጤናና ሰላም ከናንተ ጋር ይሁን ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👇👇👇 ከኛ ብዙ መልካም ነገሮችን ያገኛሉ !!

*ለኩላሊት በሽታ የመጋለጥ አጋጣሚን መቀነስ የሚቻልበት ፱ መንገዶች።* ኩላሊት የባቄላ መሰል ቅርጽ ሲኖረው የጀርባ አጥንት ባላቸው እንስሳት ውስጥ አስፈላጊ የሆነ የቁጥጥር ሚና ያለው የሰውነት ክፍል(አካል) ነው።ከመጠን ያለፈ ግልኮስ ሲኖር ማስወገድ፣በሰውነት ውስጥ በሚካሄዱ ሂደቶች ሁሉ የሚፈጠሩትን ተረፈ ምርት ማስወገድን (ከውሃ ሽንት ውስጥ ፺ በመቶ የሆነውን ውሃ በማምጠጥ ለዳግም ጥቅም እንዲውል የሚደረገው በዚሁ አካል ነው።) እንዲሁም ለሽንት ተረፈ ምርት መዘጋጀትና መወገድ፣የአሲድ ቤዝ መጠን በሰውነት ውስጥ ማመጣጠን፣የደም ግፊትን መቆጣጠር(ውሃ እና ጨውን ማመጣጠን) እና ኤሌክትሮላይትን የመቆጣጠር ሥራ ይሰራል። ኩላሊት እንደ ተፈጥሯዊ ማጣርያ ሊቆጠር ይችላል።ደምን በማጥራት በውሃ ውስጥ የሟሙ ተረፈ ምርቶችን ወደ ሽንት ከረጢት ይልካል።ኩላሊት በተጨማሪም የተለያዩ ሆርሞኖችን ያመርታል።ለምሳሌ ካልሲትሪኦል፣ኤራይቶሮፖኤቲ እና ሬኒንኢንሃምን። ኩላሊት የስረኛው የጎድን አጥንት አካባቢ ሲገኝ ከልብ ጥንድ በሆኑት የደም ላኪ ቧንቧዎች ደም ተቀብሎ በማጣራት ጥንድ ለሆኑት ደም መላሽ ይልካል።በዚህ ጊዜ ኩላሊት ያስቀረው አላስፈላጊ ተረፈ ምርት ወደ ሽንት ከረጢት(ፊኛ) ይላካል። የተለያዩ አይነት የኩላሊት በሽታዎች ኤሉ።የሽንት ቧንቧ ቁስለት(ኢንፌክሽን)፣የሽንት ቧንቧ እክል መግጠም ፣የተለያዩ የኩላሊት ካንሰር፣የኩላሊት ምች(renal cysts) እና የኩላሊት ጉዳትን ያጠቃልላል። የኩላሊት ካንሰርንና የኩላሊት ምች(renal cysts) ሊታከም የሚችለው የተጠቃውን ኩላሊት በማስወገድ ብቻ ነው። የተቀሩትን ደግሞ በኩላሊት ንቅለ ተከላና በዲያላሲስ ሊታከሙ የሚችሉበት አማራጮች ናቸው። በተጨማሪም አስጊ የሆነ የኩላሊት ጠጠር በአልትራ ሳውንድ ህክምና ጠጠሮቹን በመሰባበር ወደ ጥቃቅን ስብርባሪዎች በመቀየር በሽንት በኩል እንዲወጡ ይደረጋል።ምንም እንኳን ጠጠሩ በሽንት ቧንቧ ውስጥ ተጉዞ ሲወገድ የህመም ስሜት ቢፈጥርም። በመሆኑም በሚከተለው መንገድ ኩላሊትን በእነዚህ በሽታዎች የመጠቃት እድሉን መቀነስ ይቻለል። ፩) አትክልትና ፍራፍሬን በመመገብ ፪) ተከታታይነት ያለው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ፫) የደም ስኳር መጠን በመጠበቅና ዝቅ በማድረግ ፬) መደበኛ የሆነ የደም ስኳር መጠን ልኬት በማድረግ ፭)ወደ ሰውነት ውስጥ የሚገባውን የጨው መጠን ዝቅ በማድረግና ውሃ በብዛት በመጠጣት(ቢያንስ በቀን ፪ ሌትር) ፮) ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ በማቆም ፯) ከፋብሪካ መድሃኒቶች(ኪኒን) ይልቅ ተፈጥሯዊ የበሽታ መከላከያ ምግቦችን በመጠቀም ፰) በየጊዜው የኩላሊት ምርመራ ክትትል በማድረግ

‹‹የደም መርጋት በሽታ ሊድንም ላይድንም ይችላል ...›› ደም መርጋት (Deep vein thrombosis (DVT)) ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። የደም መርጋት ችግር በአብዛኛው ጊዜ የሚታየው ደምን ከሰውነት ወደ ልብ በሚመልሱ ደም መላሽ የደም ስሮች ውስጥ የተቋጠረ ደም መርጋት ሲፈጠር ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በታፋና በጭን ውስጥ ገባ ብለው በሚገኙ ተለቅ ባሉ ደም መላሽ የደም ስሮች ውስጥ ነው የሚከሰተው ፡፡  የደም መርጋት መነሻ ምክንያት የደም መርጋት የሚፈጠረው በደም መላሽ የደም ስሮች ውስጥ ደም መዘዋወርን የሚቀነስ ወይም የሚቀየር ሁኔታ ሲፈጠር ነው፡፡ - ለረዥም ግዜ የአልጋ ቁራኛ መሆን በተለይም እንቅስቃሴ የሌለበት - በዘር የሚተላለፍ በቤተሰብ አባላት ላይ የሚታይ ከሆነ - ከወሊድ በኋላ እስከ ስድስት ሳምንታት ባለው ጊዜ ውስጥ - ከመጠን በላይ ውፍረት - በቅርብ ጊዜ ቀዶ ጥገና ህክምና መደረግ - በተለያዩ ምክንያቶች ከመጠን በላይ የደም ሴሎች መፈጠር  በተጨማሪም ሊከሰትባቸው የሚችልባቸው ምክንያቶች - ካንሰር - በተፈጥሮ የገዛ ሰውነትን የሚፃረሩ በሽታዎች ለምሳሌ (ሉፖስ ) - ሲጋራ ማጨስ - የወሊድ መቆጣጠሪያ ኪኒኖች መውሰድ - ለረጅም ሰዓታት በመቀመጥ  የደም መርጋት ምልክቶች ደም መርጋት ከላይ እንደተጠቀሰው በታፋ እና በጭን በሚገኙ ተለቅ ባሉ ደም መላሽ የደም ስሮች የሚፈጠር ሲሆን በብዛት የሚታየው በአንድ በኩል ብቻ ነው፡፡ የተፈጠረው የደም መርጋት ደም ዝውውርን ስለሚዘጋ የሚከተሉት ስሜቶች ይታያሉ፡፡ የቆዳ ቀለም መቅላት የእግር ህመም ስሜት የታመመውን እግር በሚነኩበት ጊዜ የሙቀት ስሜት ይኖረዋል፡፡ የታመመው እግር በኩል እብጠት መታየት ለምርመራ በሚቀርቡበት ጊዜ ያበጠና የቀላ ሲነኩት የህመም ስሜት የሚፈጥር እግር ወይም ጭን ይታያል፡፡ ይህ ሁኔታ ሲፈጠር በአስቸኳይ ወደ ጤና ተቋም መሄድ አስፈላጊ ነው፡፡  ምርመራዎች በብዛት በመጀመሪያ ደረጃ የሚሰሩ ምርመራዎች ሁለት ናቸው የደም ምርመራ እግር ላይ የተቋጠረውን ደም ለማየት ዶፕለር አልትራሳውንድ የተባለ ምርመራ ይደረጋል፡፡ የደም መርጋት መኖሩ እንዳለ ከታወቀ የደም መርጋት ለመፈጠሩ ምክንያቶችን ለማወቅ ተጨማሪ የደም ምርመራዎች ይደረጋሉ፡፡  ህክምና - ደም ማቅጠኛ (Anticoagulant) መድሀኒቶች ይታዘዛሉ - ከመድሀኒት በተጨማሪ በእግር ውስጥ የደም ዝውውርን ለመጨመር ስቶኪንግ ሊታዘዝ ይችላል፡፡ - ለረዥም ሰዓታት የሚቀመጡ ከሆነ እግርዎን በየጊዜው ማንቀሳቀስ ተገቢ ነው - በተጨማሪም የረጋው ደም ወደ ላይ ወደ ሳንባ እንዳይሄድ ለመከላከል በደም ስር በኩል የማጣሪያ ወይም የማጥለያ ወንፊት ሊቀበር ይችላል፡፡አንዳንድ ጊዜም የረጋውን ደም ለማስወገድ ወይም ለመበተን የሚያስችሉ መድሀኒቶች በቀጥታ ደሙ ወደረጋበት ቦታ በመርፌ በኩል ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ @DrSofonias