fa
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

رفتن به کانال در Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

کانال ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 19 949 مشترک است و جایگاه 1 157 را در دسته پزشکی و رتبه 1 681 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 19 949 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 27 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -557 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -23 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 26.07% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 6.79% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 5 203 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 354 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 10 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 28 ژوئن, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته پزشکی تبدیل کرده‌اند.

19 949
مشترکین
-2324 ساعت
-1257 روز
-55730 روز
آرشیو پست ها
የወሊድ መከላከያ እንክብሎች ከመውሰዶ በፊት ጥቅሙን እና ጉዳቱን ያውቃሉ? የወሊድ መከላከያ እንክብሎች ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል ከሚጠቅሙን አማራጮች ውስጥ አንዱ በአፍ የሚወሰድ ወይም ኪኒን ተብሎ የሚጠራው የመከላከያ አይነት ነው፡፡ የተወሰኑ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች ኢስትሮጂንና ፕሮጀስትሮን /Estrogen and progesterone/ የተባሉ ሁለት ዓይነት ሆርሞኖችን ይይዛሉ፡፡ እነዚህ እንክብሎች ቅልቅል /Combination/ እንክብሎች ሲባሉ ሌሎች ደግሞ ከፕሮጀስትሮን (Progesterone) ብቻ የተሰሩ እንክብሎች ተብለው ይጠራሉ፡፡ አብዛኛዎቹ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል ወሳጅ ሴቶች ቅልቅል እንክብሎችን ይወስዳሉ፡፡ ጥቅሙ - ወቅቱን የጠበቀ የወር አበባ መታየት - ለመውሰድ ቀላል ነው - ዘጠና በመቶ (90%) ያህል አስተማማኝና ተስማሚ ነው፡፡ - የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ችግር አለመፍጠር - እርግዝናን አለማዘግየት - ከሌሎቹ የእርግዝና መከላከያ አይነቶች ጋር ሲነፃፀር በአንፃራዊ መልኩ ትንሽ የሚባል የደም መፍሰስ መኖር - ቅልቅል እንክብሎች (Combination)ተጨማሪ ጥቅሞች ይሰጣሉ ብጉርን፣ የአጥንት መሳሳትን፣ ካንሰር ያልሆነ የጡት ማደግ፣ ከማህፀን ውጭ እርግዝናን፣ የማህፀን ካንሰርንና ሌሎች ኢንፌክሽኖችን እንዲሁም ከብረት ማዕድን ማነስ የሚመጣ የደም ማነስን በመከላከል በኩል ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡ ጉዳት - በየቀኑ ግንኙነት ባይደረግ እንኳን እንክብሉን መውሰድ - ማቅለሽለሽና ማስታወክ ፣ የጡት ህመም - ሆድ መንፋት፣ የባህሪ መለዋወጥ በ2-3 ወራት ዉስጥ ሊሻሻል ይችላል - ከ2-3 ወር የሚቆይ የወር አበባ መዛባትና መጠን መቀነስ (አንዳንዴ ጠብታ ብቻ መታየት) ፡፡ የወሊድ መከላከያ እንክብልዎን መርሳትም ይህን ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡  እነዚህ የወሊድ መከላከያ እንክብሎች መወሰድ የሚኖርባቸው የወር አበባ መፍሰስ ከጀመረበት ከአምስተኛው ቀን ጀምሮ በየእለቱ ያለማቋረጥ ለሀያ አንድ ቀን ነው፡፡ የወሊድ መከላከያ እንክብሎችን መውሰድ ሲጀምሩ ሰውነትዎ እስኪለማመድ ድረስ መድሀኒቶቹ ለመስራት 7ቀናት ይፈልጋል/ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለመጀመሪያዎቹ 7ቀናት ተጨማሪ /ሌላ የወሊድ መከላከያ ዘዴ መጠቀም ያስፈልጋል (ለምሳሌ ኮንዶም)፡፡ በመድሀኒቶቹ ምክንያት የሚከሰትን የጎንዮሽ ጉዳት ለመቀነስና እርግዝናን ለመከላከል እንክብሎቹ መወሰድ ያለባቸው 24 ሰዓታት ባልበለጠ ልዩነት መሆን አለበት፡፡

ከመጠን በላይ ስኳር መጠቀም በሰውነታችን ላይ ምን ያስከትላል??? //////////////////////////////////////////////// በ 1ቀን ውስጥ መጠቀም ያለብን የስኳር መጠን ስንት እነደሆነ ብዙዎቻችን አንረዳም ነገር ግን ለወንዶች በቀን ውስጥ እስከ 9 የሻይ ማንኪያ ሲሆን ለሴቶች ደግሞ 6 የሻይ ማንኪያ ድረስ መጠቀም እንችላለን ነገር ግን ዚም መድረስ የሌለበት ሲሆን ከዚህ በላይ የሚጠቀሙ ከሆነ ከመጠን በላይ እንለዋለን እሱም የሚያስከትለው፡- 📌 ያልተፈለገ ውፍረት ፡- በሰውነታችን ውስጥ ሌኘቲን የሚባል ንጥረ ነገር መጥገባችንን የሚነግረን እና የረሃብ ስሜትን የሚቆጣጠር ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የስኳር መጠን በምንጠቀምበት ወቅት ስርውን እንዳይሰራ በማድረግ ረሃብ እንዲባባስ እና መብላት ከሚገባን በላይ እንድንመገብ ያደርጋል። 📌 የበሽታ መከላከል አቅምን ይቀንሳል 📌 ቡጉር ያመጣል ፡- ስኳር ሰውነታችን ወዝ እንዲያመርት ያደርጋል። 📌 የልብ ህመም ፡- ከፍተኛ የሆነ የስኳር መጠን በምንጠቀምበት ወቅት ላልተፈለገ ውፍረት እና ለደም ግፊት ስለሚያጋልጠን ወደልብ ህመም ይመራናል። 📌 በአይነት 2 ለሆነው የስኳር ህመም ያጋልጣል ፡- ኢንሱሊን በአግባቡ እንዳይስራ ስለሚያደርግ ይከሰታል። 📌 ለካንሰር ያጋልጠናል 📌 ድብርት ፡- ስኳር አብዝተን በምንጠቀምበት ጊዜ ስሜታችን እንዳይነቃቃ እና ድብርት ውስጥ እንድንገባ ያደርገናል። 📌 ቆዳችን ቶሎ ያረጃል ፡- ቆዳችን ቶሎ እንዲሸበሸብ እና ያረጀን እንድንመስል ያደርጋል ምክንያቱም ኮላጅን እና ኢላስቲን የሚባሉ ቆዳ እንዲለጠጥ የሚያደርጉ ሲሆኑ ስኳር በምናበዛበት ወቅት ግን ስራቸውን ያስተጓጉለዋል። 📌 በስብ ለተከማቸ ጉበት ያጋልጠናል ፡- በደማችን ውስጥ ያለውን ቅባት ስለሚጨምረው እንዲከሰት ያድርጋል። 📌 የኩላሊት ህመም ፡- ከፍተኛ የሆነ የስኳር መጠን በምንጠቀምበት ወቅት ኩላሊት አካባቢ ያሉት የደም ስሮች እንዲጎዱ ያደርጋል። 📌 የደም ግፊት ፡- ከፍተኛ የሆነ የስኳር መጠን በምንጠቀምበት ወቅት ደማችን ውስጥ ያለውን የግሉኮስ መጠን እንዲጨምር ያደርገዋል ስለዚህ የደም ቧንቧዎች ላይ ጫና እንዲፈጠር በማድረግ ወይም ለመለጠጥ የሚያስችላቸውን አቅም በማሳጣት የደም ግፊት እንዲጨምር ያደርጋል። 👉 ይህን ተረድታችሁ ስኳር በሚጠቀሙበት ጊዜ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ዶክተር ቤዛ አያሌው መልእክታቸውን ያስተላልፋል። ሰላም እና ጤና ከእናተ ጋር ይሁን !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! ዶ/ር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ በዉስጥ ልታወሩኝ ምትፈልጉ ቴሌግራም ላይ ከስር ሊንኩን ነካ በማረግ ታገኙኛላቹ https://t.me/DrSofonias

የፀጉር መበጣጠስን ለማስቀረት በሚል ውድ የውበት መጠበቂያና የፀጉር መንከባከቢያ ውጤቶችን ከመሸመት ይልቅ በቀላሉ የምናገኛቸውን ነገሮች እና ተፈጥሯዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ለፀጉራችን እንክብካቤ ማድረጉ የሚመረጥ ሲሆን፥ የውበት ባለሙያዎችም ይህንኑ እንድናደርግ ነው የሚመክሩን። በመሆኑም እነዚህን አምስት አማራጮች እንድንተገብራቸው ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ያወጣው መረጃ ይመክራል። 1.ዘይት መጠቀም፣ የወይራ ዘይት፣ የኮኮናት ዘይት አልያም ሌላ ማንኛውንም አይነት ዘይት ወስደን እናፈላዋለን፤ ከዚያም ለብ ሲል በጥንቃቄ የፀጉራችንን ስር በደንብ እያዳረስን እንቀባዋለን፤ ለአንድ ሰዓት ያህልም በሻሽ ወይም ፎጣ ጠቅልለን ካቆየን በኋላ በሻምፖ እንለቃለቀዋለን። 2. ተፈጥሯዊ ጭማቂዎች (ጂውሶችን) መጠቀም፣ አመሻሽ ላይ የነጭ፣ ቀይ ሽንኩርት አልያም የዝንጅብል ጭማቂን ወስደን በተመሳሳይ የፀጉራችን ስሩን በደንብ መቀባት፤ ከዚያም በማግስቱ ልንለቃለቀው እንችላለን። 3. የጭንቅላት ማሳጅ (መታሸት) የፀጉራችን ስር አካባቢ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በየቀኑ የምናደርገው የማሸት (ማሳጅ) የማድረግ ተግባር የደም ዝውውርን የሚያቀላጥፍ ሲሆን፥ የደም ዝውውር መቀላጠፍም በአንፃሩ የፀጉር ሴሎችን እድገት ያነቃቃል። 4.አረንጓዴ ሻይ መጠቀም፣ ሁለት የአረንጓዴ ሻይ ከረጢት በአንድ ኩባያ የፈላ ውሃ ላይ በመጠቀም የፀጉራችንን የስረኛው ክፍል መቀባት፣ ለአንድ ሰዓት ያህል ካቆየነው በኋላም እንደምንፈልገው ልንለቃለቀው እንችላለን። በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ የምናገኘው አንቲኦክሲዳንትስ የፀጉር መነቃቀልን ይከላከላል። በተጨማሪም የፀጉር ዕድገትን ያፋጥናል። 5. ጭንቀትን ማስወገድ፣ ለፀጉር መሳሳት እና መነቃቀል አብይ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው ጭንቀት ነው። በመሆኑም ከአላስፈላጊ ጭንቀት ራስን መከላከል እና የተመስጦ (ሜዲቴሽን) ተግባርን በማከናወን የፀጉር መነቃቀልንም ሆነ መሳሳትን መከላከል ይቻላል። ተመስጦ በተጨማሪም የሆርሞን መመጣጠን እንዲኖር በማገዝ የፀጉር እድገት ፍጥነትን እንደሚጨምርም ነው የሚነገረው።

በተለምዶ በሀገራችን ሰይጣን ፣እርኩስ መንፈስ የሰው አይን እየተባለ ስለሚጠራው ፣በአለም ላይ ከ50 ሚልየን ህዝብ በላይ የሚያጠቃውን በተለምዶ "የሚጥል በሽታ" (Eplilepsy ) ትንሽ ነገር ልበላቹ። የሚጥል በሽታ (Epilepsy) -የምንለው አንጎልን ከሚያጠቃ የአእምሮ በሽታዎች ፣ተላላፊ ያልሆነ በአለም ላይ ተንሰራፍተው ከሚገኙ በሽታዎች አንዱ እና ዋነኛው ነው።አእምሯችን የነርቭ ሴል ውህድ ሲሆን ከ 100 ቢሊየን በላይ የነርቭ ሴሎች አሉት።እነዚህ የነርቭ ሴሎች አንዱ ከሌላው ጋር እየተናበበ የሚሰራበት የራሱ የሆነ መንገድ (neural network) አለው።እነዚህ የነርቭ ክፍሎች በተለያየ ምክንያት እክል ይገጥማቸዋል።ይህ ሲሆነ የነርቭ ስርአቱ ይዛባል።በዚህ ሰአት በአንጎል ውስጥ በሚገኙ ሴሎች ውስጥ ከመጠን በላይ በሆነ ኤሌክትሪካዊ ንዝረት(electrical discharge) ጊዚያዊ መረበሽ ምክንያት የአእምሮ ትግበራ በድንገት መታወክ ሲኖር ምልክት ለተወሰኑ ደቂቃዎች በሚያሳይ ጊዜ አንድ ሰው ሲዝ አደረገ፣ (seizure)ተከሰተ እንላለን። -Epliepsy ምክንያቱ ባልታወቀ ቢያንስ በ24 ሰአት ልዩነት ሁለት ወይ ከዚያ በላይ ጊዜ ሲዝ ሲያደርግ እና በአብዛኛው ጊዜ ለአጭር ደቂቃዎች የሚቆይ ነው። አንድ ሰው ሲዝ ሲያደረግ የሚያሳየው ምልክቶችሰ? -አንድ ሰው ሲዝ አደረገ የምንለው ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች እንዳሉ ሆነው፣ የእጅ እና እግር መንዘርዘር፣መነቀጥቀጥ ለምሳሌ የፊት ብቻ መነቀጥቀጥ፣ወይም የእጅ ብቻ በአንድ በኩል ስሜት ማጣት፣የእይታ በአንድ በኩል ብልጭለጭታ ወይም ሽፍን ማለት፣አንዳንድ ጊዜ እራስን መሳት፣የአይነ መገለባበጥ፣ምራቅ በአፍ መፍሰስ ሊኖር ይችላል ማንን ያጠቃል? -Epilepsy ማንኛውንም የእድሜ ክልል የሚያጠቃ በሽታ ነው። አጋላጭ ምክንያቶችስ? -ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሰዎች ምክንያታቸው አይታወቅም -አንጎል ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች፣ቁስለቶች፣ኢንፌክሽን፣የጭንቅላት ወባ፣በዘር ሀረግ፣ወደ አንጎል የሚሄደው ደም ሰር ሲዘጋ ወይም ደም ሲፈስ፣ጭንቀት፣አልኮል መጠጥ ከመጠን በላይ የሚጠጡ ሰዎች፣የጭንቅላት እጢ፣መድሀኒቶችን በድንገት ማቆም፣አደንዛዥ እፅ ተጠቃሚዎች፣በእርግዝና ግዜ የሚፈጠር የየፅንስ አፈጣጠር ችግር እና በውልደት ጊዜ የፀንስ መታፈን፣የምጥ መርዘም፣በተለያየ ምክንያት ህፃናት ላይ ከመጠን በላይ ሙቀት መጨመር ለምሳሌ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን፣የሳንባ ምች ሲኖር፣እንቅልፍ ማጣት፣ እንዴት መከላከል እንችላለን? -የጭንቅላት ጉዳት እንዳይከሰት መከላከል በተለይ ሞተር አሽከርካሪዎች ሄልሜት እንዲያደርጉ ይመከራል -በእርግዝና ጊዜ በቂ የሆነ ፅንስ ክትትል ማድረግ -ህፃናት ላይ የሰውነት ሙቀት መጨመር ሲኖር ወዲያውኑ ህክምና ማድረግ -የደም ግፊት እና የደም ስኳር መጠን እንዳይጨምር መቆጣጠር -ከመጠን በላይ አልኮል መጠጥ እና አደንዛዥ እፆችን አለመጠቀም -የወባ በሽታ ምልክቶች ካሉ በቶሎ መታከም የሚያመጣውሰ ችግር? -መሬት ላይ በመውደቅ ግዜ መሰበር ወይም አካላዊ ጉዳት ሊኖር ይችላል፣ከዚህ በተጨማሪ ድባቴ(depression)፣መገለል፣የማህበራዊ ሂወት መስተጓጎል፣የኢኮኖሚ ጥገኝነት፣ከትምህርት ቤት እና ከስራ መሰተጓጎል፣የአንጎል ስራ ማቆም፣እስከሞት ሊዳርግ ይችላል። አንድን ሰው ሲዝ ሲያደርግ ብናገኝ ምን ማድረግ እንችላለን? -የሚጥል በሽታ በአብዛኛው መቆጣጠር ስለሚቻል በተቻለ መጠን አለመደናገጥ -በተለምዶ ክብሪት በተለምዶ መለኮስ ምንም ጥቅም የለውም -አንድ ሰው ሲወድቅ ቦታ ስለማይመርጥ ሊመታው የሚችለውን ነገር ማራቅ -ከወደቁ በዃላ አንገታቸው ጋር ትራስ ወይም ጨረቅ አድርጎ መደገፍ -በጎናቸው በኩል ጉልበታቸውን አጠፍ አድርጎ አንገታቸውን ቀና ፣አፋቸውን ዝቅ አድርገው ምላሳቸው ታጥፎ ወደ አየር ቧንቧ እንዳይገባ እና መታፈን እንዳይኖር መከታተል ከዛም መንቀጥቀጡ ሲያበቃ ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ህክምና ተቋም ከደረሱስ በዃላስ? -የህክምና ባለሙያው አተነፋፈሱ፣የደም ግፊቱ፣ የደም ስኳር መጠን እና አካላዊ ምርመራ አድርጎ ደህና መሆኑን አረጋግጦ ተጨማሪ እና አስፈላጊውን ምርመራ ሊያዝ ይችላል። -ምክንያቱ የታወቀ ከሆነ ማከም -ከዛም እንደ አስፈላጊነቱ ረዘም ለወራት እና ለአመታት ረዘም ላለ ጊዜ መድሀኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ። -መድሀኒቶች ከታዘዙ በዃላ የሀኪም ክትትል ማድረግ እጅግ በጣም ወሳኙ የህክምናው አካል ነው። መድሀኒቶችን እና የህክምና ክትትል ማቋረጥ ላልተፈለገ እና ለባሰ አደጋ ያጋልጣል። ዶ/ር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ ጤና ይብዛሎ!

✅ ወሲብ ለጤና የሚሰጣቸው 11 ጥቅሞች 1) የጉንፋን ተጋላጭነትን ይቀንሳል። የሰውነት በሽታ መከላከል አቅምን ይጨምራል!!! ወሲብ ማዘውተር የምንታመምበትን ግዜ ይቀንሳል። ግንኙነት የሚያዘወትሩ ሰዎችን ግንኙነት ከማያደርጉ ሰዎች ጋር ያነጻጸረ ጥናት ይህንኑ ይናገራል። ግንኙነት ሰውነትን ባክቴሪያ፣ ቫይረሶች እና ሌሎች ጀርሞችን የሚከላከልበትን አቅም እንዲያዳብር ያስችለዋል። በግንኙነት ብቻ እራሳችንን ከበሽታ መጠበቅ ባንችልም ጤነኛ የሆነ የወሲብ ህይወት አለን ማለት የተሻለ የበሽታ መከላከል አቅም አለን ማለት ነው። ከጤነኛ ግንኙነትም በተጨማሪ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተር፣ በቂ እንቅልፍ ማግኘት እንዲሁም ተገቢውን ክትባቶች መውሰድ ጤንነታችን በዘላቂ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችሉ መንገዶች ናቸው። … 2) የግንኙነት ፍላጎት መዳከምን ለማስተካከል!!! የግንኙነት ፍላጎት መዳከምን ለመቅረፍ ግንኙነት ማድረግ ይመከራል። ግንኙነት ማድረግ ስሜት እንዲጨምር ያደርጋል። በሴቶች ላይ በግንኙነት ግዜ የሚፈጠር የህመም ስሜት እና የብልት መድረቅን ለመቀነስ ግንኙነት ማዘውተር ይመከራል። ግንኙነት የሴት ብልት እንዳይደርቅ ያደርቃል። ወደ ብልት አካሎች ደም ዝውውር እንዲፈጠር በማድረግ ተለጣጭነትን ይጨምራል። እነዚህ ነገሮች ለግንኙነት ስሜት መዳከም መፍትሄ ይሆናሉ። … 3) የሴቶችን ሽንት መቆጣጠር ችሎታ ይጨምራል!!! 30 ፐርሰንት የሚሆኑ ሴቶች በህወት ዘመናቸው የሽንት መቆጣጠር ችግር ያጋጥማቸዋል። በግንኙነት ግዜ የስሜት ጣሪያ መድረስ የሴትን የዳሌ ጡንቻዎች ያጠነክራል። የነዚህ ጡንቻዎች መጠንከር የሽንት መቆጣጠር ብቃትን ይጨምራል። … 4) የደም ግፊት ለመቀነስ!!! የደም ግፊት ህመም ካለባቸው በሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች አንዱ ነዎት? ግንኙነት የደም ግፊት መጠንዎን ለመቀነስ ይረዳል። ብዙ ጥናቶች በወሲብ እና በወረደ ሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን መሃከል ግንኙነት እንዳለ ይናገራሉ። ሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን ማለት በደም ግፊት ንባብ ላይ የመጀመሪያው ቁጥር ነው። ግንኙነት ከአመጋገብ ለውጥ፣ አካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ጭንቀት መቀነሻ መንገዶች በተጨማሪ ለደግ ግፊት የሚረዳ መፍትሄ ነው። ነገር ግን ግንኙነት የደም ግፊት መቆጣጠሪያ መድሃኒቶች ተተኪ ሊሆን አይችልም። … 5) እንደ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ይቆጠራል!!! እንደ የተኛውም አካል ብቃት እንቅስቃሴ ወሲብ ካሎሪ ያቃጥላል። ተቀምጦ ቲቪ ማየት በደቂቃ 1 ካሎሪ ብቻ እንዲቃጠል ያደርጋል። ወሲብ የልብ ትርታን በመጨመር እንዲሁም የተለያዩ ጡንቻዎችን በማሰራት በደቂቃ 5 ደቂቃ እንዲቃጠል ያደርጋል። ግንኙነትን ማዘውተር ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተተኪ አይሆንም። ነገር ግን እንደ ጭማሪ እንቅስቃሴ ጥሩ ነው። … 6) የልብ ድካም ተጋላጭነትን ይቀንሳል!!! ጤነኛ ልብ ከፈለጉ ግንኙነትን ማዘውተር ጥሩ ነው። ወሲብ እንደ ኤስትሮጅን እና ቴስቶስተሮን ያሉ ሆርሞኖች መጠናቸው እንዲስተካከል ይረዳል። የነዚህ ሆርሞኖች በሰውነት ውስጥ መዛባት ለልብ ህመም እንዲሁም ለአጥንት በሽታ ተጋላጭ ያደርጋል። የልብ ጤናን ለመጠበቅ ግንኙነት ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። አንድ ጥናት እንደሚናገረው በሳምንት ሁለት ግዜ ግንኙነት የሚያደርጉ ወንዶች በልብ ህመም የመሞት እድላቸው በግማሽ የቀነሰ ነው። … 7) ህመም ለመቀነስ!!! ግንኙነት የህመም ስሜትን ለመቀነስ ይረዳል። ከጓደኛ የሚደረግ ግንኙነትም ሆነ ግላዊ ወሲብ የህመም ማስተናገድ ችሎታችንን ይጨምራል። የስሜት ጣሪያ መድረስ የህመም ስሜት የሚያዳፍኑ ሆርሞኖች እንዲለቀቁ ያደርጋል። አንዳንድ ሴቶች ግላዊ ወሲብ የወር አበባ ህመም እና ራስምታት ለመቀነስ እንደሚረዳ ይናገራሉ። … 8) የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል!!! አንድ ጥናት እንደሚናገረው ዘወትር የዘር ፈሳሽ የሚፈሳቸው ወንዶች የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነታቸው ዝቅ ያለ ነው። የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሌሎች መንስኤዎች ቢኖሩም ይህ መንስኤ ተጋላጭነትን የሚቀንሱበት አንዱ ቀላል መንገድ ነው። … 9) እንቅልፍ ለማሻሻል!!! ግንኙነት የተሻለ እንቅልፍ እንዲተኙ ያግዛል። ስሜት ጣሪያ መድረስ ፕሮላክቲን የተባለ እንቅልፍ የሚያግዝ ሆርሞን እንዲለቀቅ ያደርጋል። ፕሮላክቲን የመረጋጋት እና የእንቅልፍ ስሜትን ይጨምራል። ከግንኙነት በኋላ ለእንቅልፍ ቅርብ የምንሆንበት ምክንያት ይህ ነው። … 10) ጭንቀትን ለመቀነስ!!! ግንኙነት የጭንቀት መጠን ለመቀነስ ይረዳል። ንክኪ፣ መተቃቀፍ፣ መቀራረብ እንዲሁም ግንኙነት የደስታ ሆርሞኖች በሰውነታችን እንዲለቀቁ ያደርጋሉ። የቅርርብ ስሜት የጭንቀት ስሜትን የሚቀንስ ለጤና ተስማሚ የሆነ ድርጊት ነው። … 11) ካሎሪ ለማቃጠል!!! ግንኙነትን ካሎሪ ከሚቀንሱባቸው መንገዶች አንዱ ያድርጉ። አንድ ጥናት እንደሚናገረው ግንኙነት በወጣቶች ላይ በግማሽ ሰአት ውስጥ 108 ካሎሪ እንዲያቃጥሉ ይረዳል።

(ለሴቶች እህቶቼ ጠቃሚ መረጃ) ስለ የወር-አበባ መዛባት ሊታወቁ የሚገባቸው ነገሮች ፡- በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ የወር አበባ ሊዛባ ይችላል፡፡ ለመፍትሄው ግንዛቤ እንዲኖር መነሻዎችን መረዳት ያሻል፡፡ ቀን እያዛባ የሚመጣ የወር አበባ የተለያዩ ሁኔታዎችን ተከትሎ ሊከሰት ይችላል፡፡ ያለፈ ጊዜ የጤና ችግር፣ አንዳንድ መድኃኒቶች፣ የአኗኗር ዘይቤ እንዲሁም አሁን ያለዎት አጠቃላዩ የጤና ሁኔታ የወር አበባ ኡደትን ሊያዛቡ ይችላሉ፡፡ ከአንድ የወር አበባ ኡደት (እንደሚታወቀው) ከአንድ ፔሬድ መጀመርያ ቀን እስከሚቀጥለው ፔሬድ የመጀርያ ቀን ይቆያል፡፡ ይሄ የጊዜ ርዝመት ለሁሉም ሴቶች እኩል ወይም አንድ አይነት አይደለም፡፡ አብዛኛዎቹ በየ21 እስከ 35 ቀን፣ በአማካይ በየ28 ቀን የወር አበባ ያያሉ፡፡ የወር አበባ ከ2 እስከ 7 ቀን ሊቆይ ይችላል፡፡ የአንዳንድ ሴቶች የወር አበባ ቀን የማያሳልፍ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ በየጊዜው በየ24 ቀኑ የሚመጣ ለ4 ቀናትም የሚቆይ የሆነ፣ አለበለዚያ ደግሞ በተወሰነ መልኩ የተዛባ፣ የሚፈሰው የደም መጠን የበዛ ወይም በጣም አነስተኛ፣ የወር አበባ በመጣ ቁጥር በህመም የታጀበ፣ ምንም ህመም የሌለበት፣ ለረዥም ወይም ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ ለወራት ያህል ምንም ሳያዩ ከቆዩ ግን ምርመራ ማድረግ ወይም ባለሙያ ማማከር ተገቢ ይሆናል፡፡ በመጀመርያ መታሰብ የሚኖርበት ጉዳይ እርግዝና ነው፡፡ በ 28 ዓመት እድሜ የወር አበባን ለአንድ ጊዜ አለማየት እርግዝናን ለማሰብ በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ ማረጋገጥ ግን ያስፈልጋል፡፡ የወር አበባ ቢዛባ እንኳን ለማርገዝ የሚያስችለው ወቅት እንደተጠበቀ ነው፡፡ እርግዝና አለመኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ ከባለሙያ ጋር መመካከር መልካም ነው፡፡ ከዚህ በፊት የተዛባ የወር አበባ ከነበረ በአሁኑ ወቅት የተዛባው በተመሳሳይ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ችግርም ላያስከትል ይችላል፡፡ ቀደም ሲል ቀኑን ጠብቆ ይመጣ ከነበረ እና ምናልባትም የአልትራሳውንድ ምርመራ ተደርጎልዎት ውሃ የቋጠረ የመራቢያ አካል(ovary)እጢ ወይም መሰል ችግር ከነበረበት አሁን የገጠመዎት ችግር ከእሱ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል፡፡ ባለሙያ በሚያማክሩበት ጊዜ የሚወስዱትን ማንኛውም መድሃኒት ዝርዝር ይናገሩ፡፡ ለውጥረትም ይሁን ለጭንቀት የሚሰጡ መድሃኒቶች የወር አበባን ሊያዛቡ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከፍተኛ ውጥረት የወር አበባን ሊያዛባ ይችላል፡፡ ከልክ ያለፈ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግም ጨርሶውኑ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ያጠፋዋል፡፡ የክብደት መቀነስና የአመጋገብ ችግርም በቂ መነሻዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንግዲህ ለሃኪምዎ የገለጧቸው ሁኔታዎች ምንጭ ካልሰጡ ቀጣዩ ሃላፊነት የባለሙያው ይሆናል ማለት ነው፡፡ የታሮይድ እጢ ችግር የወር አበባ መዛባት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ሌሎች የተለያዩ ችግሮች የወር አበባ መዛባት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል የደም ማነስ፣ አባላዘር በሽታ ወዘተ፡፡ የወር አበባ መቆሚያ ወቅት(ማረጥ) ሲቃረብ እንዲህ አይነት ችግር ሊከሰት ይችላል፡፡ የወር አበባ መዛባት ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ ምልክቶችም ይኖሩታል፡፡ ላብና ሰውነትን የመወበቅ ስሜት እንደ ምሳሌ ይጠቀሳሉ፡፡ በ20ዎቹና በ30ዎቹ የእድሜ ክልል የማረጥ መቃረብን የሚያሳዩ ምልክቶች አይኖሩም፡፡ ለማንኛውም የወር አበባ ለምን እንደተዛባ፣ ከዚያም አልፎ ለምን እንደቀረ ለመረዳት ባለሙያ መጎብኘት መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ የወር አበባ መዛባት ተዘውትሮ የሚከሰትበት የእድሜ ክልል በአስራዎቹ ባሉ ወጣት ሴቶች ላይ ነው፡፡ ቀኑን በትክክል ተከትሎ ለመምጣት አንድ አመት አካባቢ ይፈጃል፡፡ የኮረዳነት ወቅት የሆርሞን ፍሰቶች ሚዛን ሊያዛባ ይችላል፡፡ ይህም የወር አበባ መዛባትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ባስ ሲል ወር እያሰለሰ ወይም በአጫጭር ጊዜ ስንዝር ሊመጣ ይችላል፡፡ አንዲት ወጣት ወር አበባ ማየት ካየችበት ጊዜ አንስቶ ከአመት በኋላ መዛባቱ ከቀጠለ ከተፈጥሮ ፍሰት ውጭ ሊሆን ስለሚችል ባለሙያ ማማከር ተገቢ ነው፡፡ በአጠቃላይ ጤና ብቻ ሳይሆን ሰውነትን በሌላ መልኩ ስለሚጎዱ የወር አበባ መዛባትን አስከትለው ሊሆን ይችላል፡፡ ከባድ እንቅስቃሴ የወር አበባን ከማዛባት እስከ ማስቀረት ሊያርሰው ይችላል፡፡ መጠነኛ እንቅስቃሴ ግን ውጥረትንም በመቀነስ የተዛባ የወር አበባን ያስከትላል፡፡ ለምሳሌ ያህል በቀን ለ20 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡ የወር አበባ ማየት (ቢዛባም እንኳ) ለቻለ ሁሉ ለመቅረቱ መነሻ ምክንያት እርግዝና ሊሆን ይችላል፡፡ እስከሚያረጋግጡ ድረስ እርጉዝ ነኝ ብሎ ማሰቡ ክፋት የለውም፡፡ እርጉዝ ካልሆኑ የሚከተሉት የወር አበባ እንዲቀር ወይም እንዲዛባ መነሻ ይሆናሉ፡፡ *.ከልክ ያለፈ ክብደት መቀነስ ወይም መጨመር፡፡ ምንም እንኳን የክብደት መጠን ዝቅተኝነት የተለመደ ቢሆንም ከልክ ያለፈ ውፍረትም የወር አበባን ሊያዛባ ይችላል፡፡ *.የአመጋገብ ችግር (ከልክ በላይ መብላት ወይም ከበቂ በታች መብላት) *.ከባድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፤ የወር አበባን አለማየት ከባድ ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ለረዥም ጊዜ በሚያካሂዱ ስፖርተኞች ላይ ይከሰታል፡፡ *.ውጥረት *.ህመም *.ጉዞ(የረዥም ርቀት ጉዞ) *.መድሃኒቶች፣ ለምሳሌ ያልተፈለገ እርግዝና ለመከላከል የሚወሰዱ ታብሌቶች፣ ቀለል ያለ አልፎ የሚመጣ፣ ቶሎ ቶሎ የሚመጣ ወይም የወር አበባው ጭርሱኑ እንዲቀር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ *.የሆርሞኖች መዛባት፣ የሆርሞኖች ሚዛን መጠበቅ *.ህገወጥ እፆችን መጠቀም *.በማህፀንና በማህፀን ዙርያ ካሉ የሰውነት ክፍሎች አካባቢ በሚከሰቱ ችግሮች *.ጡት ማትባት፣ ብዙ የሚያጠቡ እናቶች አጥብተው እስከሚያጠናቅቁ ድረስ የወር አበባ ቀኑን ጠብቆ አይመጣም፡፡ ምንም እንኳን የወር አበባ ቢያዩም እርግዝና ሊከሰት ስለሚችል ያስቡበት፡፡ እርጉዝ መሆን ካላሰቡ የወሊድ መከላከያ ይጠቀሙ፡፡ ቀድመው ለረዥም ጊዜ በማሰብ የድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብሎችን ደጋግሞ ላለመጠቀም ያስቡበት፡፡ የወር አበባን ሊዛባ ስለሚችል፡፡ የመራቢያ አካል ድክመት ሲያጋጥም የወር አበባ ሙሉ በሙሉ ያቆማል፡፡ ያለወቅቱ ተከሰተ የሚባለው ከ40 አመት በፊት ሲያጋጥም ነው፡፡ በሆድ እቃና በዳሌ አካባቢ የሚደረጉ የቀዶ ጥገና፣ የኬሞቴራፒ እና የጨረር ህክምና ችግሩን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ የቲቢ፣ የጉበት፣ የስኳርና ሌሎች ተቀራረቢ ህመሞች የወር አበባ እንዲቀር ወይም እንዲዛባ መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከነዚህ ህመሞች አንዱ ካለ በወር አበባ መዛባት ብቻ ሳይሆን ከመሰረታዊ ምልክቶቹ ጋር ይከሰታል፡፡ የወር አበባዬ አልመጣም ብለው አይጨነቁ፡፡ ለስሜታዊም ይሁን ለአካላዊ ሚዛን መጠበቅ ሲባል ዘና ይበሉ፡፡ በተለይ በዚህ ዘመን ብዙ ሴቶች በተደጋጋሚ የወር አበባቸው ይዛባባቸዋል፡፡ እርስዎም ከተዛባብዎት እርጉዝ ካልሆኑ በቀር የወር አበባዎን በሚቀጥለው ወር ይጠብቁት፡፡

(ግላውኮማ (Glaucoma የአይን ህመም) ግላውኮማ የምንለው የአይን ህመም በአይናችን ነርቭ ላይ ችግር የሚያስከትል ሲሆን በአይናችን ውስጥ የሚገኘው ግፊት መጨመር ምክንያት የሚከሰት ነው። የዚህ ግፊት መጨመር በአይናችን የምናያቸውን ምስሎች ወደ አንጎል የሚውስደውን የአይናችንን ነርቭ ይጎዳል ይህም በቀጣይነት ቋሚ ለሆነ የአይን ብርሃንን እጦት ይዳርጋል። ግላውኮማ በሚጀምርበት ጊዜ የሚያሳየው ቀዳሚ ምልክት ወይንም የህመም ስሜት ስለሌለ ማንኛውም ሰው መደበኛ የሆነ የአይን ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው ይህም አይናችን ለከፋ ጉዳት ከመጋለጡ በፊት ህክምና እንድናደርግለት ይረዳናል። ከ 40 አመት እድሜ በላይ ያሉ ሰዎች በአመት አንድ ጊዜ ወደ ሃኪም በመሄድ ምርመራን ማድረግ አለባቸው። የአይናችን ውስጥ ግፊት ለምን ይጨምራል? ግላውኮማ የሚከሰተው በአይናችን ውስጥ የሚገኘው ግፊት ሲጨምር ነው ያልን ሲሆን ይህ ደግሞ በዘር ፣ በኢንፌክሽን፣በአይን በቀዶ ጥገና ምክንያት በፊተኛው የአይናችን ውስጥ የሚገኘው ፈሳሽ በጤናማ ሁኔታ መንሸራሸር ሲያዳግተው ነው። ግላውኮማ በአብዛኛው ሁለቱንም አይነቶች የሚያጠቃ ሲሁን የህመሙ ክብደት ግን ሊለያይ ይችላል። በግላውኮማ የሚጠቁ እነማን ናቸው? * ከአርባ አመት እድሜ በላይ የሆኑ *በግላውኮማ የተጠቃ ቤተሰብ ያላቸው *የስኳር ህመምተኞች *የአይን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች የግላውኮማ ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው? በአብዛኛው ግላውኮማ በቅድሚያ የህመም ምልክት ላያሳይ ቢችልም ከጊዜ በሗላ ግን የመጀመሪያ ምልክት የሚሆነው በጥግ በኩል የሚጀምር የአይን ብርሃን ችግር ነው። ከምልክቶቹ ውስጥ:- *ድንገተኛ የሆነ የአይን ህመም *ከፍተኛ የራስ ምታት *የአይን ብዥታ *ጥርት ያለ እይታ አለመኖር *የአይን መቅላት *የአይን ብርሃን ማጣት *የአይን እይታ ጥበት ናቸው እነዚህ ሁኔታዎች ሲያጋጥምዎ በአፋጣኝ ወደ አይን ሀኪም መሄድ ይጠበቅቦታል። ግላውኮማን መከላከል ይቻላል? ግላውኮማ እንዳይከሰት መከላከል የማንችል ሲሆን ነገር ግን በቶሎ የህመሙ መኖር ከታወቀ ለመቆጣጠርና እንዳይባባስ ለማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። በግላውኮማ ምክንያት የተከሰተ የአይን ብርሃን ጉዳት ተመልሶ ሊስተካከል የማይችል ሲሆን የነበረው ጉዳት እየተባባሰ እንዳይሄድ ግን የአይን ግፊት መጠኑን መቀነስ ይቻላል። ህክምናቸውን በሚገባ የሚከታተሉ ታካሚዎች የአይን ብርሃናቸውን ማዳን ይችላሉ።

ሴክስ ላይ ቶሎ የመጨረስ ህክምና ======================= አንድ ሰው "በሴክስ ምክኒያት ከሚስቴ ጋር ልንፋታ ነው።" አለኝ። "በሴክስ ምክኒያት ስትል?" ብዬ እንዲያብራራ ጠየቅሁት። አፈር ብሎ "ቶሎ ስለምጨርስ ማለቴ ነው። ቢቸግረኝ ጂን አሪፍ ነው ሲሉ ሰምቼ ሞከርኩት። ግን ምንም ለውጥ የለውም።" አለኝ። "ከሚስትህ ጋር ተነጋግራችሁበታል?" አልኩት። "አልተነጋገርንበትም ግን ደስተኛ እንዳልሆነች እርግጠኛ ነኝ።" አለ። "እንዴት አወቅህ?" አልኩት። "ዘይት የሌለው ሽሮ ነው የምትወረውርልኝ።"... ቶሎ መጨረስ ከአራት ወንዶች አንዱ ላይ ያጋጥማል። ነገር ግን ብዙ ሰው ችግሩ እንዳለበት ለመናገር ስለሚፈራ ቁጥሩ ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል ይገመታል። ቶሎ መጨረስ የሚባለው ከ1ደቂቃ በታች ከጨረሰ ነው። ነገር ግን በሴክስ ጊዜ ያለው የሰአት ግንዛቤ የተዛባ ነው። አንዳንዶች ብ...ዙ ደቂቃ የቆዩ ይመስላቸውና በእውነታው ግን ጥቂት ነው የሚቆዩት። አንዳንዶች ደግሞ "ወዲያው ነው የምጨርሰው" ቢሉም ደቂቃዎች ይቆያሉ። ሌላው ሰዎች ቶሎ እንደሚጨርሱ (እንዲሁም የብልት መጠን ትንሽ እንደሆነ) እንዲሰማቸው የሚያደርገው ፖርኖግራፊ ነው። የፖርኖግራፊ ፊልም ላይ የሚቆዩት ደቂቃም ሆነ የብልታቸው መጠን መደበኛ አይደለም። በተጨማሪም "ወደ ገደለው" ስለሚገቡ ሮማንስ፣ "ወርማፕ" ...መተሳሰብ...መነጋገር....የመሳሰሉት ነገሮች የሉትም። ስለዚህ ፖርኖግራፊ ገሀዳዊውን እውነታ የማያሳይ ነገር ግን ያልተገባ ፍርሀት የሚፈጥር ነገር ነው። ቶሎ ለመጨረስም ሆነ ለሌሎች ከሴክስ ጋር ለተያያዙ ችግሮች ምርጡ ህክምና Sex therapy ነው። ጥንዶቹ በጋራ ሆነው ስለራሳቸው አካል፣ ስለአጋራቸው አካል፣ ስለ ሴክስ፣ ስለ ስጋታቸው፣ ስለመሻታቸው ...ወዘተ በግልፅ ይነጋገራሉ። Sex therapy እነዚህን ነገሮች በባለሞያ እገዛ የሚማሩበት ሲሆን ዘና ባለ ስሜት እርስበእር ሳይተፋፈሩ ተከባብረው ፈጣሪ የሰጣቸውን ደስታ እንዲደሰቱ መርዳት ነው። ከላይ ያለው ህክምና ችግሩን ከመሰረቱ የሚያስተካከል ሲሆን ስንጥቁን ወለል በጋዜጣ እንደመሸፈን አይነት የሆኑ ሌሎች ህክምናዎችም አሉ። የወንድ ብልትን የሚያደነዝዙ ክሬሞች። ብልት ከደነዘዘ ብዙ የደስታ ንክኪ ስለማይኖሮ ቶሎ መጨረስ አይኖርም። የአእምሮ መድሀኒቶች፦ አንዳንድ የአእምሮ መድኒቶች ቶሎ መጨረስን ያስተካክላሉ። በተለይ ተጓዳኝ የጭንቀትና የድብርት ህመም ካለ። ነገር ግን ተጎዳኝ የአእምሮ ህመም ሳይኖር ማዘዙ አይመከርም። ሌሎቹን ዘዴዎች በቀጣይ አቀርባለሁ።

ከስጋት ነፃ የሚሆኑባቸው መንገዶች የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ከእርግዝና ስጋት ነፃ የሆኑ ቀናቶች የትኞቹ ናቸው? =========== እርግዝናን ለመከላከል የወሊድ መቆጣጠሪያ መጠቀም የማይፈልጉ ብዙ ጥንዶች ተፈጥሮአዊ የእርግዝና መከላከያ ዘዴን ይመርጣሉ፡፡ ይህ ስሌትን የሚጠይቅ ዘዴ በወር አበባ ጊዜ የሚካሄዱ ለውጦችን ማወቅ ይጠይቃል፡፡ ይህ የስሌት እርግዝናን መከላከያ ዘዴ የተሳካ እንዲሆን ሴቶች የወር አበባን ሶስት ደረጃዎች ማወቅ ግድ ይላል፡፡ የወር አበባ ሶስት ደረጃዎች! የወር አበባ ሶስት ደረጃዎችን ማወቅ በቀላሉ እርግዝናን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡ 1. የመጀመሪያ ደረጃ፦ ይህ ደረጃ በህክምና አጠራር ፎሊውክላር ፌዝ ይባላል የወር አበባ ካየሽበት ከሁለተኛው (2) ቀን እስከ 14ኛው ቀን ያለውን ያካትታል፡፡ በዚህ ወቅት ሰውነታችን ዕንቁላልን የሚሰሩ ሆርሞኖች ይለቃል፡፡ 2. ሁለተኛ ደረጃ፦ ይህ የወር አበባሽ የመካከለኛ ጊዜ ሲሆን ለጽንስ ዝግጁ የሆኑ የደረሱ/የበሰሉ ዕንቁላሎች ከእንቁልጢ የሚለቀቁበት ደረጃ ነው፡፡ በዚህ ወቅት የሴት ዕንቁላል የሚፈለፈልበት ወቅት ስለሆነ ከፍተኛ የማርገዝ ዕድል ይኖርሻል፡፡ 3. ሶስተኛ ደረጃ፦ ሉቲያል ፌዝ የሚባል ሲሆን ይህ ደረጃ ዕንቁላል ከዕንቁልጢ(እንቁላል ዕጢ) ከተለቀቀበት ጊዜ ጀምሮ ይጀምራል፡፡ ይህ ደረጃ ከቀን 16 እስከ 28 ባለው ማንኛውም ጊዜ ሊከሰት ይችላል፡፡ የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ከስጋት ነፃ የሆነው የወር አበባ ጊዜ የትኛው ነው? 1. ከስጋት ነፃ የሆነው የወር አበባ ጊዜ ምን ማለት ነው? የወንድ የዘር ፈሳሽ (ስፐርም) በሴት የመራቢያ አካል ውስጥ ከ 3 - 5 ቀናቶች በህይወት መቆየት ይችላል፤ የሴት ዕንቁላል በህይወት የሚቆየው ደግሞ 24 ሠዓት ብቻ ነው፡፡ የሴት ዕንቁላል ከሚፈለፈልበት ጊዜ በአማካይ ከአንድ ሳምንት በፊት እና ከአንድ ሳምንት በኋላ ያሉት ጊዜዎች እርግዝና በከፍተኛ ሁኔታ የሚከሰትባቸው ጊዜዎች ናቸው፡፡ ሁሉም ሴቴች የተለያየ የዕንቁላል መፈልፈያ ጊዜ ሲኖራቸው ከቀን 12 እሰከ 19 ባለው የወር አበባ ኡደት ጊዜ ውስጥ ይከሰታል፡፡ ከነዚህ ቀኖች ውጪ ያሉት ጊዜዎች ከስጋት ነፃ የሆኑና እርግዝና የማይከሰትባቸው ቀናቶች ናቸው፡፡ 2. ከስጋት ነፃ የሆነው የወር አበባ ጊዜን እንዴት ማስላት ይቻላል? ከስጋት ነፃ የሆነው የወር አበባ ጊዜን ማስላት በጣም ቀላል ሲሆን እንዴት ማስላት እንደምንችል እንመልከት፦ • የመጨረሻው የወር አበባሽ መጀመሪያ ቀንን እወቂ፡፡ • ለተከታታይ 6 ወር የወር አበባሽን በመመልከት እረጂም እና አጭር የወር አበባ ኡደት ቀኖችሽን እወቂ፡፡ • በአማካይ ከ 26 – 32 ቀናቶች የሚቆይ የወር አበባ ኡደት የመጀመሪያው ሳምንት ከስጋት ነፃ የሆነ ጊዜ ነው። የወንድ የዘር ፈሳሽን በሴት የመራቢያ አካል ውስጥ ከ 3-5 ቀናቶችን እንደሚቆይ በማሰብ፡፡ ይህ ዘዴ የቀን አቆጣጠርን መሠረት ያደረገ ስለሆነ ውጤቱ ከሴት ወደ ሴትይለያያል፡፡ 3. ይህን ዘዴ መጠቀም የሚችሉት እነማን ናቸው? ይህን ዘዴ በመጠም የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ከስጋት ነፃ የሆኑ ቀናቶችን በማወቅ መጠቀም ያለመሳካት ዕድሉ በአመት ውስጥ ከ 3-4% ነው ስለዚህ ይህን ዘዴ መጠቀም ያለውን አደጋ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ ባለፉት 6 ወራቶች አማካይ የወር አበባሽ የሚመጣበት ጊዜ ከ 26 – 32 ቀናቶች ከሆነ ይህ ዘዴ በትክክል ይሰራል፡፡ 4. ይህን ዘዴ መጠቀም የማይችሉት እነማን ናቸው? ላለፉት ስድስት ወራቶች የወር አበባሽ የሚመጣበት ጊዜ ከ 26 – 32 ቀናቶች ወጪ ከሆነ አንቺ ይህን ዘዴ በፍጹም መጠቀም የለብሽም፡፡ በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ (በቅርቡ) ህፃን ልጅ ያላት ሴት ከወለደች በኋላ በአማካይ ለ 6 ወራቶች የወር አበባ መጠበቅ ይኖርባታል፡፡ ሌሎች እርግዝናን ለመከላከል የሚረዱ ዘዴዎች 1. ለወንዶች፦ • ኮንደም • ማምከን ወይም መኮለስ (Male Sterilization) 2. ለሴቶች፦ • በአፍ የሚወሰድ እንክብል (Oral Contaceptives) • ዲያፍራም (Diaphragm) • ኢምፕላንትስ (Implants) ናቸው። መልካም ጤንነት!!

✍️ #የአፍንጫ #መደፈን 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥ #በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #የአፍንጫ መደፈን(መታፈን) የሚከሰተው በአፍንጫ እና በአጎራባች ሕብረ ሕዋሳት እና የደም ሥሮች ከመጠን በላይ በሆነ ፈሳሽ ሲያብጡ የታፈነ ስሜት ይፈጥራሉ። የአፍንጫ መታፈን የአፍንጫ ፈሳሽን ወይም “ንፍጥ” ን ሊያካትት ወይም ላያካትት ይችላል። ⏩ #የአፍንጫ መታፈን ብዙውን ጊዜ እንደ የሳይነስ ኢንፌክሽን ያለ ሌላ የጤና ችግር ምልክት ነው፤ እንዲሁም በተለመደው ጉንፋን ምክንያትም ሊሆን ይችላል። 👉#መንስኤዎቹ 🔺 ሳይነሳይትስ 🔺 የአፍንጫ አለርጂ 🔺 ጉንፋን 🔺 አልኮል 🔺 ወደ አፍንጫ የሚሄድ አየር መድረቅ 🔺 ወደ አፍንጫ ባዕድ ነገር ሲገባ 🔺 የሆርሞን ለውጠጥ 🔺 ለሌላ ህመም የሚታዘዙ መድሃኒቶች (ለግፊት፣ ለድብርት፣ለሚጥል በሽታና ሌሎችም..) 🔺 አፍንጫ ላይ የሚወጡ ስጋዎች 🔺 አስም 🔺 እርግዝና 🔺 ጭንቀት 🔺 የታይሮይድ ችግር 🔺 ሲጋራ ማጨስ 👉 #መከላከያዎቹ 🔺 አርጂ የሚስነሱ ነገሮችን መከላከል 🔺 እንደ ሲጋራ ያሉ የሚረብሹ ነገሮችነን መራቅ 🔺 በቂ ውሃ መጠጣት የአፍንጨጫ እስፕሬዎች መጠቀም 🔺 ሌሎች የተለዩ ምክንያቶች ካሉ ማከም 👉 #እንዚህን #ምልክቶች #ካዩ #ወደ #ጤና #ተቋም #ይሂዱ! 🔺 የአፍንጫ መደፈኑ ከ 10 ቀናት በላይ ከቆየ 🔺 የአፍንጫ መደፈኑ ከ 3 ቀናት በላይ ከቆየ እና ተያይዞ ከፍተኛ ትኩሳት ካለዉ 🔺 ከአፍንጫ አረንጓዴ ወይም ቢጫ ፈሳሽ ከሳይነስ ህመም እና ትኩሳት ጋር ካለ 🔺 የበሽታ የመከላከል አቅማቸዉ ዝቅተኛ የሆነ እና አስም ያላቸዉ 👉👉 #ይህን መሰል እና ማንኛዉም ተያያዥ የጤና ጥያቄ ካሎት ወደ ጥሪ ማዕከላችን በመደወል ከጤና ባለሙያ ጋር ይማከሩ! ለመማከር 8809 ላይ ይደውሉ! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!! (#በጤና #ባለሙያ #ስጦታ)

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ቆዳ ሳይከፈት የዳሌ እና የታችኛው አከርካሪ ስብራት ቀዶ ሕክምና ለሦሥት ታካሚዎች ሰጥቷል። ይህም በሪፈራል ሆስፒታሉ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጸመ ነው ተብሏል
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ቆዳ ሳይከፈት የዳሌ እና የታችኛው አከርካሪ ስብራት ቀዶ ሕክምና ለሦሥት ታካሚዎች ሰጥቷል። ይህም በሪፈራል ሆስፒታሉ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጸመ ነው ተብሏል። እድሚያቸው 17፣ 43 እና 88 ለሆኑ ሦሥት ታካሚዎች አገልግሎቱ መሰጠቱን የአጥንትና የመገጣጠሚያ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ቃለአብ ተስፋዬ ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመኪና አደጋ ምክንያት የዳሌ እና የታችኛው አከርካሪ ስብራት ሕክምና የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመዋል። የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ሕክምናውን መጀመሩ አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ አዲስ አበባ የሚደረግ ጉዞን ያስቀራል ብለዋል። #ጎንደርዩኒቨርሲቲ

✍️ #ዝቅተኛ #የወንድ #የዘር #ህዋስ(#oligospermia) 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #የወንድ የዘር ፈሳሽ ህዋስ ማነስ የሚባለው የሚለቀቀው ህዋስ ቁጥሩ /መጠኑ ከመደበኛ ያነሰ ሲሆን ነው ፡፡ ትክክለኛ የስፐርም መጠን 15 ሚሊየን በ 1 ሚ.ሊ ፈሳሽ ውስጥ ነው፡፡ በህክምና አጠራሩ የዘር ፈሳሽ ህዋስ ማነስ (oligospermia) ሲባል የዘር ፈሳሽ ህዋስ ሙሉ በሙሉ አለመኖር ደግሞ (azoospermia) ይባላል። በአንድ የወንድ የዘር ፈሳሽ ከ 15 ሚሊዮን ያነሰ የወንድ የዘር ፈሳሽ ህዋስ ካለዎት የወንዱ የዘር ፈሳሽ ህዋስ መጠን ከወትሮው ዝቅተኛ ነው ተብሎ ይገመታል ። ዝቅተኛ የወንድ የዘር ፈሳሽ ዋናው ምልክት ልጅን ለመፀነስ አለመቻል ነው ፡፡ ሌላ ምንም ግልጽ ምልክቶች ላይኖሩ ይችላሉ ። ⏩ #ምልክቶቹ 🔹የዘር ፍሬ ከረጢት ላይ ህመም ወይም እብጠት መኖር 🔹 ዝቅተኛ የወሲብ ፍላጎት መኖር 🔹የፊት ወይም የሰውነት ፀጉር መቀነስ /የሆርሞን መዛባት ⏩ #መንስኤዎቹ 🔹 ያልተለመዱ የወንዱ የዘር ቅርፅ መኖር (morphology) 🔹 እንቅስቃሴት(motility) ችግሮች 🔹 ኢንፊክሽን 🔹 የሆርሞን አለመመጣጠን 🔹 መድሃኒቶችን ለረጅም ጊዜ መጠቀም 🔹 የደም መልስ ትቦዎች አብጦ መታየት 🔹 ጭንቀት ( የስራ ውጥረት) 🔹 ለጨረር የመጋለጥ እድል መኖር 🔹 ማጨስ ፣ መጠጣት 🔹 የሰውነት ክብደት መጨመር ⏩ #ምርመራው 🔹 የዘር ፈሳሽ ምርመራ(sperm analysis) 🔹 አልትራሳውንድ 🔹 የሆርሞን ምርመራ ⏩ #ህክምናው 🔹 በኢንፊክሽን ምክንያት የመጣ ከሆነ ኢንፊክሽኑን ማከም 🔹 የሆርሞን ህክምና 🔹 ቀዶ ህክምና ⏩ #መከላከያ #መንገዶች 🔹 ጭንቀትን ማስወገድ 🔹 የአመጋገብ ዘይቤን ማስተካከል 🔹 የሰውነት ክብደትን ማመጣጠን 🔹 አለማጨስ 🔹 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ 👉👉 #ያለመውለድ ችግር አጋጥሞ ችግሩ ከወንዱ ሊሆንባቸው ከሚችሉባቸው አጋጣሚዎች ዋነኛ መንስኤው በመሆን ይጠቀሳል ስለሆነም ስለችግሩ በቂ ግንዛቤ ለማግኘት 8809 ላይ ይደውሉ ባለሙያ ይምከሩ ! ከዚህና ተያያዥ በሆኑ የጤና ጉዳዮች ላይ ጥያቄ ካሎት በቤቶ ሆነው ወደ 8809 ላይ በመደወል ከባለሞያዎችን በቀጥታ በመገናኘት ይመካከሩ፡፡ ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ! (#በጤና #ባለሙያ #ከድጃ)