cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አዲስ ነገር መረጃ

አዲስ ነገር መረጃዎች መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
76 188
مشترکین
-1924 ساعت
-1297 روز
-51430 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

በትግራይ ክልል የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የ17 ወር ውዝፍ ደሞዝ እስካሁን አልተከፈላቸውም ተባለ፡፡ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የጤና ባለሙያዎች የ17 ወር ደሞዝ ሳይከፈላቸው በመቆየቱ ከቤት ኪራይ ጀምሮ በተለያዮ ወጪዎች በእዳ ተይዘው እንደሚገኙ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡ የክልሉ ጤና ቢሮ የፈውስና ተሃድሶ ዋና የስራ ሂደት ተተኪ ዶክተር ስምኦን ገብረጻዲቅ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ባለሙያዎቹ ለመኖር ሲሉ ለሚያስፈልጋቸው ወጪ በብድር ሲጠቀሙ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህም የጤና ባለሙያዎቹ አገልግሎት ለመስጠት ችግር እንደሆነባቸው ጠቅሰዋል፡፡ ሌላው ከጣቢያችን ጋር ቆይታ የነበራቸው የአይደር አጠቃላይ ሪፈራል ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገ/እግዚአብሔር እንዳሉት ውዝፍ የ22 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያም እስካሁን እንዳልተከፋላቸው አንስተዋል፡፡ ችግሩን የክልሉም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ቢያቁም እስካሁን ምላሽ አልተሰጠንም ብለዋል፡፡ @Addis_News
نمایش همه...
👍 1
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፈተና መቼ ይሰጣል ? እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ የ2016 ዓ/ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል። ፈተናው ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ ነው። ከ70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ይሰጣል ተብሏል። ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራበት ነው። ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ሚኒስቴሩ ለኢፕድ ከሰጠው መረጃ ተመልክተናል። በሌላ በኩል ፤ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ የሬሜዲያ ተማሪዎች ከታህሳስ ወር ጀምሮ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ቢሆንም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተመደቡ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገላቸውም። @Addis_News
نمایش همه...
በጃፓን ሰው የማይኖርባቸው ቤቶች ብዛት ዘጠኝ ሚሊዮን ደርሷል የጃፓን መንግሥት ያወጣው የቅርብ ጊዜ አኃዛዊ መረጃዎች፣ በሀገሪቱ ሰው የማይኖርባቸው የባዶ ቤቶች ብዛት ዘጠኝ ሚሊዮን መድረሱ አለምን ጉድ እያሰኘ ነው። በጃፓን ሰው የማይኖርባቸው ወና ቤቶች ብዛት በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት ቤቶች ውስጥ 13.8 ከመቶ ድርሻ እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል። በሀገሪቱ ለባዶ ቤቶች መብዛት ዋነኛ ምክንያት ተብለው ከተቀመጡት መካከል የወሊድ መጠን መቀነስና በገጠር የሚኖረው ህዝብ መመናመን ናቸው። ከሁሉም በላይ፣ ሰው ከማይኖርባቸው ዘጠኝ ሚሊዮን ቤቶች ውስጥ ከአንድ ሦስተኛ በላይ ወይም 3.85 ሚሊዮን የሚሆኑት ቤቶች በቀጥታ የተተዉ ናቸው ሲል የሀገር ውስጥ ጉዳይ እና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ያወጣው የዳሰሳ ጥናት ውጤት ያሳያል። የህዝብ ቁጥር እየቀነሰ የሚሄድባቸው የገጠር ቀበሌዎች ባዶ ወይም የተተዉ ቤቶችን ብዛትን መገኛ በመሆን ይመራሉ። ዋካያማ እና ቶኩሺማ አውራጃዎች በ21.2 በመቶ በላይ ባዶ ቤቶች የሚገኙባቸው ቦታዎች ናቸው። ሌላው ደግሞ የጃፓን የግብር ህግ ለባዶ ቤቶች መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል በማለት ወቀሳ እየቀረበበት ነው። ምክንያቱም በጃፓን ህንፃዎች ካረፉበት መሬት ይልቅ ቤት ያላረፈበት ባዶ መሬት የበለጠ ቀረጥ ይስባል ይባላል፣ ይህም ሰዎች ያረጁ ቤቶችን ከማፍረስ እንዲቆጠቡ አድርጓል በሚል ይጠቀሳል። Via:Infraethiopia @Addis_News
نمایش همه...
👍 9🔥 2
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የጸሎተ ሐሙስ ሥነ ስርዓት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል። @Addis_News
نمایش همه...
ደንበኞች ከትንሳኤ በዓል ዋዜማ ጀምሮ ኃይል ቆጣቢ አጠቃቀምን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አገልግሎቱ ጠየቀ በትንሳኤ በዓል ዋዜማና ዕለት የኃይል መዋዥቅና መቆራረጥ ለመቀነስ፤ ከተከሰተም አፋጣኝ ምላሽ ለመሰጠት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። እንዲያም ሆኖ ሊያጋጥም የሚችለውን የኃይል መዋዠቅና መቋረጥ ለመቀነስ በውጭ ንግድ ላይ ከተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች በስተቀር ሌሎች ሁሉም የከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች ከዋዜማው ከቀን 7 ሰዓት ጀምሮ እስከ በዓሉ ዕለት ድረስ ከዋናው ግሪድ የሚጠቀሙትን ኤሌክትሪክ እንዲያቋርጡ አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል። ደንበኞች በቤት ውስጥ የሚገለገሉባቸው የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች ኃይል ቆጣቢና ለአደጋ የማያጋልጡ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ እና የኤሌክትሪክ ኃይል ጭነት በማይበዛበት ሰዓት በተለይ ከምሽቱ 4፡00 እስከ ንጋቱ 11፡00 ባሉት ጊዜያት እንዲጠቀሙ ጠይቋል። የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ደግሞ በዓሉ ሲደርስ የሚኖረውን አላስፈላጊ ወረፋ ለማስቀረት እንዲችሉ ከወዲሁ የሚበቃቸውን ያህል የኤሌክትሪክ ኃይል አስቀድመው እንዲገዙ (ካርድ እንዲሞሉ) አገልግሎቱ መክሯል። @Addis_News
نمایش همه...
👍 2
በገበታ ለሀገር የተገነቡ ሎጆችን የማስተዳደር ኃላፊነቱ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሠጠ። በገበታ ለሀገር የተገነቡ ሎጆችን ስራ የማስኬድ ተግባርን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስካይ ላይት ሆቴል ተቋሙ በኩል እንዲወጣ ዛሬ የስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል። ስምምነቱ በቅርቡ የተመረቁትን ሃላላ ኬላ ሎጅ፣ ጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅ እና ወንጪ ኢኮ ሎጅ እና በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የጎርጎራ ፕሮጀክትንም ያካትታል። "ቀጣይ የስራ ማስኬድ እና ማስተዳደር ተግባሩ ለብሔራዊ ሰንደቅ ተሸካሚው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሃላፊነት መሰጠቱም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ከማስቻሉም ባለፈ ለአለምአቀፍ የቱሪዝም መዳረሻነት ትውውቅ ከፍ ያለ ዕድል ይፈጥራል።" ሲል የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስታውቋል። @Addis_News
نمایش همه...
በቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ ዳላስ ቢያንስ 20 የፍልስጥኤም ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ቢያንስ 20 የፍልስጤም ድምፅ በማሰማት የሚቃወሙ ሰዎች በቴክሳስ ዩኒቨርስቲ በዳላስ ካምፓስ የጋዛ ህብረት ካምፕ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአካባቢው ፖሊስ ገልጿል።  ረቡዕ ጠዋት ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ድንኳኖችን በመትከል እንኳን ወደ ጋዛ ነፃነት ስፍራ በሰላም መጡ ሲሉ መልዕክት አጋርተዋል። ረቡዕ ከሰአት በኋላ ፖሊስ ካምፑን ሲያፈርስና ተቃዋሚዎችን በቁጥጥር ስር ሲያውል ታይቷል። ከሰልፈኞቹ መካከል ምን ያህሉ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እንደሆኑ ግልጽ አይደለም። ፍልስጤምን የሚደግፉ ዋና ዋና ሰልፎች በአሜሪካ የኮሌጅ ካምፓሶች ተሰራጭተዋል፣ በኦስቲን የሚገኘው የቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች በተመሳሳይ በቁጥጥር ስር አውሏል።ፍልስጤማውያን በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኙ የዩንቨርስቲው ካምፓሶች ፀረ-ጦርነት ሰልፎችን ላደረጉ ተቃዋሚዎች ምስጋናቸውን ለመግለጽ በጋዛ ጎዳናዎች ላይ ወጥተዋል። በማዕከላዊ ጋዛ ዲየር ኤል ባላህ በስደተኛ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በአሜሪካ ኮሌጆች ተቃዋሚዎችን የሚያመሰግኑ ምልክቶችን ይዘው ወጥተዋል። ሰልፎቹ ጦርነቱ እንዲቆም በዩንቨርስቲው አስተዳደሮች፣በ አሜሪካ መንግስት እና በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ላይ ጫና እንደሚፈጥር ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል። በሌላ በኩል በዮርዳኖስ መንግስት ስር የሚተዳደረው ፔትራ የዜና ወኪል እንደዘገበው ሁለት የዮርዳኖስ የእርዳታ ልዑካን ምግብ፣ ዱቄት እና ሰብአዊ ርዳታዎችን የያዙ ምርቶችን ሲያጓጉዙ በእስራኤል ሰፋሪዎች ጥቃት እንደደረሰባቸው ዘግቧል። @Addis_News
نمایش همه...
👍 4
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ አየር መንገዱ ካለፈው ዓመት አንጻር በተያዘው ዓመት የመንገደኞቹ ብዛት በ30 በመቶ ይጨምራል ብለው እንደሚጠብቁ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ባለፈው ዓመት የአየር መንገዱ መንገደኞች ብዛት 13 ነጥብ 9 ሚሊዮን ነበር። የአየር መንገዱ መንገደኞች ብዛት ዘንድሮ የሚጨምረው፣ አየር መንገዱ መዳረሻዎቹን በማስፋቱና በዓለም ላይ የአየር ትራንስፖርት በማንሠራራቱ እንደኾነ ተገልጧል። ኾኖም አየር መንገዱ ያዘዛቸው አዳዲስ አውሮፕላኖች መዘግየታቸውና በሞተር እጥረት የቆሙ አውሮፕላኖች መኖራቸው ችግር እንደኾኑበት መስፍን መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። አየር መንገዱ በዓመቱ በ20 በመቶ ጭማሪ 7 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን መስፍን ገልጸዋል ተብሏል። @Addis_News
نمایش همه...
👍 3
መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ትናንት ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በአስቸጋሪ ኹኔታ ላይ የነበሩ 1 ሺህ 180 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን መልሷል። ትናንት ከተመለሱት ፍልሰተኞች መካከል፣ 1 ሺህ 98ቱ ወንዶች፣ 79ኙ ሴቶች እንዲኹም ሦስቱ ጨቅላ ሕጻናት እንደኾኑ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። 228ቱ ተመላሾች ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች ዕድሜ ያላቸው ናቸው ተብሏል። ኮሚቴው ከሚያዝያ 4 ጀምሮ እስከ ትናንት በጠቅላላው 13 ሺህ 900 ፍልሰተኞችን ከሳዑዲ ዓረቢያ መልሷል። @Addis_News
نمایش همه...
👍 3
ኬንያን በታንዛኒያ በኩል ከዛምቢያ ጋር የሚያገናኘውና 400 ኪሎ ቮልት የሚሸከመው የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በኅዳር 2025 እንደሚጠናቀቅ ቢዝነስ ደይሊ ዘግቧል። የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ዝርጋታ መጠናቀቅ፣ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ከደቡባዊ አፍሪካ አገራት ጋር ኃይል ለመሸጥና ለመግዛት ያስችላቸዋል። ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ታንዛኒያ የምሥራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር አባል ናቸው። ኢትዮጵያ ለታንዛኒያና ደቡባዊ አፍሪካ አገራት ኃይል የመሸጥ እቅድ አላት። ኬንያ፣ ከታንዛኒያ ጋር የሚያስተሳስራትን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የዘገየ ዝርጋታ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ ላይ እንደኾነችም ዘገባው አመልክቷል። @Addis_News
نمایش همه...
👍 6