cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

پست‌های تبلیغاتی
11 214
مشترکین
+424 ساؚت
+327 عوز
+7530 عوز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ክስ ወይም የክስ መልስ ማሻሻያ ማስፈቀጃ ሲቀርብ መረሣት የሌለባቸው ጉዳዮች ------------------------ የክስ ማሻሻያው የክሱን ወይም የመከላከያውን አቤቱታ በማብራራት ክርክሩን በተሻሻለ ሁኔታ የሚገልፅ እና ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት የሚረዳ ሆኖ ከተገኘ በተከራካሪውቹ ጥያቄ ወይም በፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ማንኛዉም አቤቱታ ሊሻሻል ይችላል(ቁ 91)። ማሻሻያው መከናወን ያለበት ከፍርድ በፊት ነው። አቤቱታው ሲሻሻል ፍ/ቤቱ ስለ ሚኪሳራው አስፈላጊውን ትዕዛዝ መስጠት አለበት። የክሱ መሻሻል ነገሩን በመጀመሪያ ከቀረበለት ፍ/ቤት ስልጣን በላይ ያደረገው ከሆነ የመጀመሪያ ፍ/ቤት ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ያስተላልፋል። ጉዳዩ የተላለፈለት ፍ/ቤትም የነገሩን መስማት ይቀጥላል። በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 91 መሠረት አቤቱታውን ለማሻሻል የሚቀርቡ አቤቱታዎች በተገቢው ሁኔታ መቅረብ አለባቸው፡፡ የአቤቱታ ማሻሻያ የሚፈቀደው የቀረበው አቤቱታ ፍ/ቤትን የሚያሳምን እንደሆነ ነው፡፡ የሚሻሻለው ነጥብ ምን እንደሆነ ባልታወቀበት የሚፈቀድ ከሆነ የክርክር ሂደትንም የሚያበላሽ ከመሆኑም በላይ ፍ/ቤትም ግራ-ቀኝንም ለበለጠ ወጪና እንግልት የሚዳርግ ነው፡፡ አቤቱታ ማሻሸል መብት ብቻ ሳይሆን ፍ/ቤትን የማሳመን ግዴታም አለበት፡፡ ሚስጥር አድርገው ይዘው ነጥቦቹ ባልተጠቀሱበት አቤቱታዬን ለማሻሻል እንድፈቀድልን በሚል የሚቀርበው ማመልከቻ አቤቱታውን የሚያበራራ ወይም ለትክክለኛ ፍትህ አሳጣጥ አስፈላጊ መሆን አለመሆኑን በምንም መልኩ ማወቅም አይቻልም፤ የሚፈቀድበትም አሳማኝ ምክንያት የለም፡፡ አንድ ተከራካሪ ክሱን ለማሻሻል ወይም ክርክሩን ለመለወጥ ፍ/ቤትን ለመጠየቅ መብት ያለው ሲሆን ፍ/ቤቱ ግን ጥያቄውን የሚቀበለው የክሱ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ ክስ የቀረበበትን ጉዳይ በይበልጥ ግልጽ የሚያደርገው ወይም ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት አስፈላጊ መሆኑን ሲያምን ነው፡፡ ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት በማናቸውም ጊዜ ፍርድ ቤት ተገቢ ሆኖ ሲያገኘው የክሱ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ ነገሩን ይበልጥ የሚያብራራ ወይም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የሚረዳ ከሆነ ክሱ እንዲሻሻልና ክርክሩ እንዲለወጥ ሊፈቀድ የሚችል እንደሆነ የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 6 በመ/ቁ. 20416 በሰጠው ውሳኔ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ እንዲሁም ደግሞ የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 21 በመ/ቁ. 104621 በሰጠው ውሳኔ የክስ ማሻሻያ ነጥብ ተለይቶ መታወቅ ያለበት መሆኑንና ክሱ የሚሻሻልባቸው ነጥቦች ተገቢነት መመርመር ያለበት የማሻሻያ ትዕዛዙ ከመሰጠቱ በፊት እንደሆነ የሰበር ችሎቱ በሰጠው ውሳኔ አስፍሯል፡፡ ፍርድ ቤቱ የዚህ ዓይነቱን ፈቃድ የሚሰጠውም የክሱን መሻሻል ተገቢ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ስለመሆኑም ከዚሁ ውሳኔ እና ከፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 91 አጠቃላይ ይዘትና መንፈስ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚህ ውጪ የሚሻሻልበትን ነጥብ ሚስጢር አድርገው ይዘው በደፈነው አቤቱታዬን አሻሽዬ እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ በሚል የሚቀርበው አቤቱታ በፍርድ ቤቶች የተለመደ ተከራካሪ ወገኖችን ለወጪና እንግልት የሚዳርግ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ደግሞ በሚቀርቡት የመከላካያ መልሶች ክፍተቶች ስገለጹ ክሴን ላሻሽል በሚል አቤቱታ ያቀርባሉ፤ ይህ ደግሞ ተገቢ አይደለም፡፡
نمایش همه...
👍 15
የፍትሐብሔር ክስን ስለማሻሻል የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 91 በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 91 ላይ እንደተቀመጠው የክሱ መሻሻል ይበልጥ ጉዳዩን የሚያብራራ እና ለትክክለኛ ፍትህ የሚረዳ ከሆነ ፍ/ቤቱ የከሳሽም ክስ ሆነ የተከሳሽ መልስ እንዲሻሻል መፍቀድ ያለበት መሆኑን ይደነግጋል ሆኖም ግን ክሱ እንዲሻሻል በሚፈቅድበት ጊዜ የማሻሻያው ማመልከቻ የክሱን ሁኔታ የሚያብራራና ምክንያታዊ መሆኑን በሚገባ መመርመር ያስፈልጋል፡፡ሆኖም ግን አንድ አንድ ጊዜ ‹‹ለትክክለኛ ፍትህ ›› ምትለዋን ሀረግ ለጥጦ በመተርጎም በክስ ማሻሻል ሰበብ በመጀመሪያ ክስ ያልቀረበን አዲስ ነገር የሚጨመርበት እና ቀድሞ ያልተነሳ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ በተሻሻለው ክስ ተካተው ሲቀርቡ ይስተዋላል፡፡ ይህ ደግሞ ከድንጋጌው ይዘት እና አላማ ጋር የሚጋጭ እና የፍ/ቤቱን ጊዜ እና ወጪ ከማራዘም በተጨማሪ ጉዳይን በማጓተት በተከራካሪዎች መብትም ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡ በፍ/ህጉ አንቀጽ 1856፤ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 244 (2)((ረ) እና 245(1) ጣምራ ንባብ መረዳት እንደሚቻለው ተከሰሽ የይርጋ መቃወሚያ በመጀመሪያ መልስ ላይ ያላቀረበ ከሆነ ሆነ ብሎ እንደተዋቸው ያቆጠራል የሚል ይዘት ያለው ሲሆን የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 6 በሰበር መ/ቁ 20416 እና በቅጽ 21 በሰበር መ/ቁ 104621 ላይ በክስ ማሻሻል ሰበብ የተረሳን የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ በተሻሻለ ክስ ውስጥ አካቶ ማቅረብ እንደማይቻል እና ፍ/ቤቱም ይህንን መቀበል እንደሌለበት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ JOIN 👇⚖️ https://t.me/ethiolawtips
نمایش همه...
ስለ አቤቱታ ማሻሻል 5 የሰበር ውሳኔዎች 1- ከሳሽ በመጀመሪያ ቀጠሮ ያላቀረበው ማስረጃ በሂደት እንዲያቀርብ ከተፈቀደ ተከሳሽም የቀረበውን ማስረጃ አግባብነት እና ተአማኒነት ለመቃወም እንዲችል የመከላከያ መልሱ እንዲያሻሽል ሊፈቀድለተ ይገባል፡፡ ተከሳሽ በማስረጃው ላይ አስተያየት ብቻ እንዲሰጥ መገደብ የመከላከል መብቱን ያጣብባል፡፡ /ሰ/መ/ቁ. 160314 ቅጽ 24/ ጥያቄ--ዓላማው አዲስ የቀረበውን ማስረጃ አግባብነት እና ተአማኒነት ለመቃወም ከሆነ ይህንኑ በሚሰጠው አስተያየት በሚገባ ለመቃወም የሚችል እንደመሆኑ የመከላከያ መልስ ማሻሻል ለምን አስፈለገ? 2- ክስ እንዲሻሻል ሲፈቀድ ከሳሽ ቀድሞ ያቀረበውን የክስ ምክንያት መቀየር አይችልም፡፡ ስለሆነም ብድር ለማስመለስ የቀረበ ክስ እንዲሻሻል ከተፈቀደ በኋላ የክሱን ምክንያት ወደ ያላአግባብ መበልፀግ በመቀየር የተሻሻለ ክስ ከቀረበ ፍርድ ቤቱ ሊቀበለው አይገባም፡፡ ያለመቀበሉ ውጤት ክርክሩን በቀድሞው የክስ ምክንያት እንዲቀጥል ያደርገዋል፡፡ ሆኖም ከሳሽ በቀድሞው የክስ ምክንያት መቀጠል ካልፈለገ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ይዘጋዋል፡፡ /ሰ/መ/ቁ. 161736 3 ለ 2 በሆነ በአብላጫ ድምጽ የተሰጠ/ ጥያቄ--መዝገቡ ከተዘጋ በኋላ ከሳሽ ዳኝነት ከፍሎ በቀድሞው ወይም በተሻሻለው የክስ ምክንያት አዲስ ክስ ማቅረብ ይችላል? 3- የመከላከያ መልስ እንዲሻሻል ሲፈቀድ ተከሳሽ በመጀመሪያ መልሱ ላይ ያላቀረበውን አዲስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማንሳት አይችልም፡፡ /ሰ/መ/ቁ. 55973 ቅጽ 12/ ጥያቄ-- የክስ አቤቱታው ከተሻሻለ ተከሳሽ በመጀመሪያው መልሱ ላይ ያላካተተውን አዲስ መቃወሚያ ማንሳት ይችላል? 4- አቤቱታ ሊሻሻል የሚችለው በጉዳዩ ላይ ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት በማንኛውም ጊዜ ነው፡፡ ስለሆነም በጉዳዩ ላይ ፍርድ ተሰጥቶ መዘገብ ከተዘጋ በኋላ አቤቱታ ለማሻሻል የሚቀርብ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፡፡ /ሰ/መ/ቁ. 89641 ቅጽ 15/ 5- ከሳሽ ክሱን እንዲያሻሽል ተፈቅዶለት ካሻሻለ ምንም እንኳን በተሻሻለው ክስ ላይ የተጨመረው ነገር መሰረታዊ የይዘት ለውጥ የማያመጣ መስሎ ቢታይም ፍርድ ቤት ተከሳሹ ለተሻሻለው ክስ አዲስ የመከላከያ መልስ እንዲያቀርብ ዕድል ሊሰጠው ይገባል፡፡ በመሆኑም “በተሻሻለው ክስ መልስ እንዲሰጥበት ማድረጉ የሚያመጣ ለውጥ አይኖረውም” በሚል ምክንያት ተከሳሽ ለተሻሻለው ክስ የመከላከያ መልሱን ሳያቀርብ ፍርድ ሊሰጥ አይችልም፡፡ /ሰ/መ/ቁ. 95620 ቅጽ 16/ By Abraham Yohannes #ሼር
نمایش همه...
👍 11❤ 1
نمایش همه...
ከሥራ የተሰናበቱ ዳኞችን ለሁለት ዓመታት ጥብቅና እንዳይቆሙ የከለከለ የአዋጅ ድንጋጌ እንዲሻር ጥያቄ ቀረበ - ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best And Reliable News Source In Ethiopia

ከሥራው የተሰናተ ዳኛ ሥራውን ካቆመበት የመጨረሻ ቀን ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ይሠራበት በነበረው የፌዴራል ፍርድ ቤት ደረጃ በማናቸውም ችሎት በጥብቅና እንዳይቆም የሚከለክለው የፌዴራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/2013 አንቀጽ 32(1)

የቤት ሽያጭ ውሎችን በሚመለከት በሰበር ችሎት የተሰጡ ውሳኔዎች.pdf
نمایش همه...
የቤት_ሽያጭ_ውሎችን_በሚመለከት_በሰበር_ችሎት_የተሰጡ_ውሳኔዎች.pdf6.92 KB
👍 11
የቤት ሽያጭ የመንደር ዉል በሕግ ተቀባይነት  አለው? የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፣ ማለትም ቤትና መሬት በርካታ ሰዎች በመንደር ውል የሚሻሻጡ ቢሆንም በርካታ ሰዎች ተግባሩን ስላደረጉት ግን ሕጋዊ አያሰኘውም። ይህ የመንደር ውል በሕግ ተቀባይነት የማይኖረው የሰነድ ማረጋገጥ ዋና ዓላማን የሚጥስ መሆኑ ነው ። ሰነድ ለምን ይረጋገጣል? ባይረጋገጥስ ምን ችግር አለው ? አንደኛ በተዋዋዮቹ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግዛት ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሦስተኛ ወገን ለሚያነሳው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። ሦስተኛ ወገን የሚባሉት እነማን ናቸው ያልን እንደሁ፣ ከገዥና ሻጭ ውጪ ያሉ የትኛውንም ወገኖችን ያካትታል። ለምሳሌ የመንግሥት አካል፣ የክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር፣ ባንክ፣ ለምሳሌ ሽያጩ ይፍረስልኝ የምትል/የሚል ሚስት/ባል . . . ወዘተ እነዚህ ሁሉ 3ኛ ወገን ይባላሉ። ከእነዚህ አካላት አንዱ፣ እንበልና በመንደር ውል በተፈጸመ ንብረት ላይ ጥያቄ ቢያነሱ ሙግቱን ያለምንም እሰጥ አገባ አሸነፉ ማለት ነው። በመንደር ውል ቤት የገዛ ሰው ቀለጠ ማለት ነው። በአጭሩ ውል የሚረጋገጥበት ዋንኛ ዓላማ ሦስተኛ ወገኖች ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። "የመንደር ውል ችግሩም ይሄ ነው" ። እርግጥ ውል በሰነዶች ሲረጋገጥ መንግሥት ቴምብር ያሳርፍበታል። ገቢ ያገኛል። ገዥና ሻጭ ሰነዱን ይዘው ክፍለ ከተማ ሲሄዱ የመንግሥት አካል ቀረጥ ይጥላል። ከዚያም ገቢ ይገኛል። ተዋዋዮች ሕጋዊ ሰነድ ይዘው ስለቀረቡ፣ ሕጋዊ አገልግሎት አግኝተው የስም ማዞርያ አሹራ ይከፍላሉ። ይህም ሌላ ገቢ ነው። ለዚህም ነው ውሉ በሕጉ ላይ የተቀመጠውን ፎርም ስላሟላ እንደ ሕጋዊ ውል ተቆጥሮ ተፈጻሚነት የሚኖረው። ተፈጻሚነት ይኖረዋል ማለት ግን ምን ማለት ነው? በአጭሩ ለምሳሌ ሻጭ ለገዢ ስም አላዞርልህም ቢል ፍርድ ቤት ከሶ በግዴታ ስም እንዲያዞር፣ ገዥ ላይ ለደረሰው ኪሳራም ካሳ እንዲያገኝ ይሆናል ማለት ነው። ይህን ዕድል ግን በመንደር ውሎች ላይ ለማሳካት አስቸጋሪ ይሆናል። በመንደር ውል የተሸጠ ንብረት እጣ ፈንታው ምንድነው? በፍርድ ቤት ቀርቦ ያልተመዘገበ ውል፣ ወይም በውል አዋዋዮች ፊት ያልተረጋገጠ የመንደር ውል እንደ ሕጋዊ ተቆጥሮ አፈጻጸም ሊቀርብበት አይችልም። በዚህ ላይ ምንም ብዥታ መኖር የለበትም። የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በጽሑፍ መሆን አለበት፣ በሁለት ምስክሮች ፊት መሆን አለበት። በአዋዋይ ፊት መሆን አለበት። ወደ ጥያቄው "ውሉ በመንደር ቢደረግ እጣ ፈንታው ምንድነው የሚሆነው? እውነት ለመናገር በዚህ ረገድ ሕጉ የተረጋጋ አይደለም :: የአገሪቱ የመጨረሻ ፍርድ ቤት የሆነው ሰበርም ቢሆን ከውል አዋዋይ (ውልና ማስረጃ) ውጪ የተደረጉ የመንደር ውሎች ይፀናሉ ወይስ አይፀኑም በሚለው ላይ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ውሳኔ ሰጥቷል። በአንድ በኩል፣ ሰዎች በመንደር ከተዋዋሉና ነገር ግን ፊርማቸውን ካልተካካዱ ውሉ በተዋዋዮቹ መካከል ብቻ ይጸናል ብሎ የወሰነበት ፍርድ አለ። (ሰበር መዝገብ ቍ 21448) በሌላ በኩል ደግሞ የመንደር ውል በውል አዋዋይ ፊት እስካልተመዘገበ ድረስ ሕግ ተቀባይነት አይኖረውም የሚል ፍርድ አለ። (ሰበር መዝገብ ቁ 83674) ይህ ማለት ውሉ የሚጸናው በእነሱ ላይ ብቻ ነው። ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብ ግን አይችልም። ምን ማለት ነው፣ አንድ ሰው ቤቱን በመንደር ውል ቢሸጥና ውል ለማፍረስ ፍርድ ቤት ቢሄድ ገዥ ገንዘቡን ለመክፈል ይገደዳል። ሻጭም ቤቱን ለመስጠት ይገደዳል። ሆኖም ግን፣ ለምሳሌ ባንክ በቤቱ ላይ ጥያቄ ቢኖረው የመንደር ውሉ አይጸናበትም። ወይም ደግሞ ሻጭ ላይ ባለ ዕዳ የሆነ ሰው ዕዳዬ ቤቱ ተሸጦ ይከፈለኝ ቢል ቤቱ ተሸጧልና አይከፈልህም ሊባል አይችልም። ምክንያቱም በመንደር ውል ስለተሸጠ። አደጋውም እዚህ ላይ ነው። ገዢው የመንደር ውሉን ይዞ "እኔ እኮ ይሄን ቤት ገዝቼዋለሁ" ብሎ ጥያቄ ያነሱ ሦስተኛ ወገኖችን ዝም ሊያሰኛቸው አይችልም። ስለዚህ ገዢ በመንደር ውል መፈራረሙ ወዶና ፈቅዶ በራሱ ላይ አደገኛ አደጋን ጋብዟል:: https://t.me/ethiolawtips
نمایش همه...
👍 19
ከዳግም ዳኝነት /review of judgement/ ጋር በተያያዘ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጣቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች ቅጽ 6 የሰ/መ/ቁ 08751 በፍብ/ሾ/ሾ/ህግ ቁጥር 6 መሠረት ፍርድ ከተሰጠ በኋላ የተሰጠውን ፍርድ ሊያስለውጥ የሚችል አዲስ ማስረጃ መገኘቱ ብቻውን ዳግም ዳኝነት እንዲታይ የማያስችል ሲሆን ፍርዱን እንደገና ለማየት የተገኘው ማስረጃ ሀሰተኛ ሰነድ፣ በሀሰት የተሰጠ የምስክር ቃል፣ መደለያ ወይም ወንጀል ጠቀስ ተግባር ሆኖ ይህ አዲስ የተገኘው ማስረጃ የውሳኔውን መሠታዊ ይዘት የሚነካ መሆን አለበት። አዲስ የተገኘው ማስረጃ ፍርድ ቤቱ በጭብጥነት ይዞ ውሳኔ ከሰጠበት ጉዳይ ውጭ ከሆነ ጉዳዩ በዳግም ዳኝነት ሊታይ አይችልም። ቅጽ 9 የሰ/መ/ቁ 42871 የዳግም ዳኝነት አቤቱታ በፍብ/ሾ/ሾ/ህግ ቁጥር 6 መሰረት የቀረበለት ፍርድ ቤት ዳኝነቱ ድጋሜ ሊታይ ይገባል ወይም አይገባም በማለት በሚሰጠው ውሳኔ ላይ አመልካች የሰበር አቤቱታ ከሚያቀርብ በስተቀር ይግባኝ የማቅረብ መብት የለውም። ቅጽ 9 የሰ/መ/ቁጥር 43821 በዚህ መዝገብ ቁጥር የሰበር ችሎት በመ/ቁጥር 16624 የያዘውን አቋም ማለትም በፍ/ብ/ሼ/ሼ/ሕ/ቁጥር 6 መሰረት የዳግም ዳኝነት ጥያቄ መቅረብ ያለበት ይግባኝ ከመቅረቡ በፊት እንጂ በይግባኝ ቀርቦ ውሳኔ ባገኘ ጉዳይ አይደለም በማለት የሠጠው የሕግ ትርጉም በመለወጥ የዳግም ዳኝነት ጥያቄ ጉዳዩ በይግባኝ ታይቶ ውሳኔ ከተገኘ በሁዋላም ቢሆን በቁጥር 6 ሾር የተመለከቱት መመዘኛዎች ተሟልተው እስከተገኙ ድረስ መቅረብ እንደሚችል ገልጾ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ቅጽ 15 የሰ/መ/ቁ 93137 በሀሰተኛ ማስረጃ ወይም በመደለያ ምክንያ ባለጉዳዩን የሚጎዳ ውሳኔ የተሰጠው በሰበር ችሎት ከሆነ የዳግም ዳኝነት ጥያቄ በመርህ ደረጃ የሚስተናገደው ውሳኔውን ለሰጠው ፍርድ ቤት ቢሆንም አንድ ጉዳይ በዳግም ዳኝነት በሚታይበት ግዜ ፍሬነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ሒደት ስለሚያካትት ፍሬነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን  ስልጣን ደግሞ ለሰበር ችሎት ያልተሰጠው በመሆኑ የደግም ዳኝነት ጥያቄ በሰበር ችሎት ሊስተናገድ አይችልም። ስለዚህ የዳግም ዳኝነት አቤቱታው ሊስተናገድ የሚገባው ፍሬነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን በተሰጣቸው ፍርድ ቤቶች መሆን አለበት። ቅጽ 19 የሰ/መ/ቁ 104028 በፍብ/ሾ/ሰ/ህ/ አንቀፅ 6 ሾር የተመለከቱት አስፈላጊ መስፈርቶች በተሟሉበት ሁኔታ አንድ ክስ በይርጋ መዘጋቱ ዳግም ዳኝነት ጥያቄውን ላለማስተናገድ እንደበቂ ምክንያት የማይወሰድበ
نمایش همه...
👍 10
ውል በተናጠል መሰረዝ /አንደኛው ተዋዋይ ወገን በተናጠል ውሉን መሰረዝ/ Unilateral Cancelation of Contact ==================== አንደኛው ተዋዋይ ወገን የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌን መሠረት በማድረግ ውልን በተናጠል ለመሠረዝ የሚችለው ከሚከተለት ሶስት ሁኔታዎች አንደኛው የተሟላ መሆኑን ለማስረዳት ሲችል ነው፡፡ • የመጀመሪያው ባለዕዳው በውሉ ላይ በተመለከተው መሠረት የውሉን ግዴታ የሚፈፅምበት ቁርጠኛ ጊዜ በውሉ ላይ በግልፅ ተመልክቶ እንደሆነና በውሉ ላይ የተገለፀው ቁርጥ የሆነ የውል መፈፀሚያ ጊዜ ያለፈ እንደሆነ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ አንደኛው ተዋዋይ ወገን በተናጠል ውሉን ለመሰረዝ የሚችል መሆኑን የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 እና የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1775(ለ) ድንጋጌዎች በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡ • ሁለተኛው ምክንያት ባለዕዳው ውሉን ያልፈፀመበትን ምክንያትና ሌሎች የአካባቢ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ዳኞች ባለዕዳው ውሉን የሚፈፅምበት የችሮታ ጊዜ ከሰጡት በኋላ ባለእዳው በዳኛ ውሣኔ በተሰጠው የችሮታ ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ሳይፈጽም የቀረ እንደሆነ መሆኑን ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1770 ድንጋጌዎች ለመረዳት ይቻላል፡፡ • ሶስተኛው ባለገንዘቡ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 በተደነገገው መሠረት ሌላኛው ተዋዋይ (ባለዕዳው) በውል የገባውን ግዴታ የሚፈፅምበትን ጊዜ በመግለፅ ማስጠንቀቂያ የሰጠ ሲሆንና በማስጠንቀቂያው በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሳይፈፅም ሲቀር መሆኑን ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል፡፡ አንደኛው ተዋዋይ ወገን ሌላኛው ተዋዋይ ወገን በውሉ መሠረት እንዲፈፅም ለመጠየቅና ማስጠንቀቂያ ለመስጠት የሚችለው በመጀመሪያ እሱ የበኩሉን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም የተዘጋጀ ሲሆን እንደሆነ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1857 በግልፅ ይደነግጋል፡፡ ስለሆነም ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ መሠረታዊ ዓላማና ግብ እንደዚሁም የድንጋጌውን የተፈፃሚነት ወሰን ለመረዳት የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771 ንዑስ አንቀጽ 1 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1757 ድንጋጌዎች ጋር በማጣመር መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አንፃር ስንመዝነው አንደኛው ተዋዋይ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771 ንዑስ አንቀጽ 1 ሌላኛው ተዋዋይ ውሉን እንዲፈፅምለት ለመጠየቅ፤ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 ድንጋጌዎች መሠረት የውል መፈፀሚያ ጊዜ ግልፅ ማስጠንቀቂያ በመስጠትና በፍትሐብሔር ቁጥር 1787 በተደነገገው መሠረት ውሉን በተናጠል ለመሠረዝ በመጀመሪያ በእሱ በኩል በውል የተጣለበትን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑ በማስረጃ ለማረጋገጥ የቻለ መሆን እንዳለበት የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1757 እና የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌዎችን ይዘትና መሠረታዊ ግብ በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡ ሕግ አውጭው በውል ለገባው ግዴታ ተገዥ በመሆን በእሱ በኩል ያለውን ግዴታ ያልፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ለማረጋገጥ ያልቻለ አንድ ተዋዋይ ወገን ሌላኛውን ተዋዋይ ወገን ቀድሞ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን በተናጠል እንዲሰርዝ በማሰብ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌን አውጇል ተብሎ አይገመትም፡፡ አንድ ተዋዋይ የውሉን መፈፀሚያ የጊዜ ገደብ በመግለጽ ለሌላኛው ወገን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውል በተናጠል ለመሰረዝ የሚችለው በመጀመሪያ እሱ በውሉ የገባውን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡ ሰ/መ/ቁ. 57280 ቅጽ 13፣ ፍ/ህ/ቁ. 1770፣ 1771፣ 1774፣ 1757፣ 1787
نمایش همه...
👍 10
Share 73514.pdf
نمایش همه...
73514 (1).pdf1.38 KB
Share 204199.pdf
نمایش همه...
204199.pdf1.06 MB
👍 2❤ 1