cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Kombolcha online market

#የተለያዩ ኤክትሮኒክስ እቃዎችን ሽያጭና ግዥ ያገለገሉ ስልኮችን ኮምፒተሮችን ሀርድ ድስኮችን የምናቀርብበት ቻናል https://t.me/komolcha/onlinemarkete

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
288
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

LT tab, new storeg 64 ram 4 praic 7000
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
☑️ የእቃው አይነት | Monitor ☑️ የምርት አይነት | Dell ☑️ ስክሪን ስፋት | 19" Inch ☑️ ጥራት | 1366x768 (WxH) HD ☑️ የሚቀበለው ኬብል | VGA | DP | Power ☑️ ይዞታ | ትንሽ የሰራ 💰 ዋጋ | 5000 ብር 📞 Call +251920489895 📎 https://t.me/komolcha/onlinemarkete
نمایش همه...
20 ምርጥ መልዕክቶችን ላካፍላችሁ 1. ነገሮች ሲጠኑባችሁ ወደ ሱጁድና ዱዓእ ፍጠኑ እንጂ ብሶትና ለቅሶ አታብዙ፡፡ 2. ሁሉም ነገር ይሄዳል፤ ሲሄድ ግን አይመለስም፡፡ ዱዓእ ሲቀር፡፡ ዱዓእ ተስፋን፣ በረከትን፣ ሲሳይን፣ ድልን፣ ስጦታን ይዞ ይመለሳል፡፡ 3. በምድር ላይ አንድም ስኬታማ ሰው የለም፡፡ ለወላጆቹ መልካም የመዋል ታሪክ ያለው ቢሆን እንጂ፡፡ 4. የሰው ልጅ ሆኖ ከሀሳብ ነፃ የሆነ የለም፡፡ ሆኖም ግን ያለበት ሀገር ዱንያ መሆኗን እያስታወሰ ፈገግ የሚል ብዙ ሰው አለ፡፡ 5. ምርጦቹ ጓደኞችህ ዱንያ የሳቀችልህ ቀን አይደናገጡም፡፡ በዞረችብህ ጊዜም አይደሰቱብህም፡፡ 6. ግርማ ሞገስን ከሚያጎናጽፉ ነገሮች መካከል ብዙ አለማውራት፤ የፊትን ዉበት ከሚጨምሩ ነገሮች መካከል ፈገግታን ማብዛት ይገኙበታል፡፡ 7. የሰው ልጅ ባያምንበትም እንኳ የሚናገርን ሰው ሀሳብ ቢያዳምጥ የሚማረው ነገር ይኖራል፡፡ 8. ልጅህን ቁርኣንን አስተምረው፤ ቁርኣን ሁሉንም ነገር ያስተምረዋል፡፡ 9. ትላልቅ ሰዎችን አክብሩ፤ ዘመናቸው ባልሆነ ዘመን ውስጥ እየኖሩ ነውና፡፡ 10. ሁሉንም ሰው ለማስወደድና ለማርካት አትፍጨርጨር፡፡ በዚህ ጉዳይ ነቢያትም እንኳን አልተሳካላቸውምና፡፡ 11. ዉስጥህን ህመም እየተሰማህ ፈገግ የምትል ከሆነ የጥንካሬህ ማሳያ ነው፡፡ 12. የሰው ልጅ የሚመዘነው ባለው ነገር ሳይሆን በሚሰጠው ነው፡፡ ፀሐይ እሳት ጭምር አላት ነገርግን ብርሃን ትሠጣለች፤ ፍጥረተ ዓለሙን በብርሃን ትሞላለች፡፡ 13. በእናቱ እግር ሥር አገልጋይ ሆኖ የኖረ በሰዎች አናት ላይ ንጉስ ሆኖ ይኖራል፡፡ 14. ብዙ በመናገር የማይታወቅ ሰው መናገር ሲጀምር ትኩረት ይስባል፡፡ 15. ባመለጠችህ አንዲት ኮከብ አትከፋ፡፡ ሰማይ በከዋክብት የተሞላች ናት፡፡ እሷን ከረሳህ ምናልባት ጨረቃ ትወጣልህ ይሆናል ማን ያውቃል፡፡ 16. ከአላህ (ሱብሀነ ወተዓላ) መልካም ነገር እንጂ አላየንም፣ አልሰማንም፡፡ ወደ ቀናው መንገድ መራን፣ ጤና ሰጠን፣ ዕድሜ ሰጠን፣ ቤተሰብ ሰጠን፣ ብዙ ብዙ ነገር ሰጠን፡፡ 17. ልንረሳቸው ብንፈልግ እንኳን ዉስጣችን የማይረሳቸው ብዙ ኃጢአቶችን ይዘን እየዞርን ነው፡፡ 18. የሐዘን ባቡር ፉርጎው ቢበዛም ቢረዝምም የመጨረሻ ፌርማታው ደስታ ስለመሆኑ  አንጠራጠር፡፡ ዕድል 19. ዕድሜ ዕድል ነው፡፡ አንዳንድ ደግሞ ዕድሜ ነው፡፡ ዕድሜህ ሊሆን የሚችልን ዕድል በቀላሉ አታሳልፍ፡፡ 20. የተጃጃለ ሰው ሁኔታው እንደ በራሪ አዕዋፍ ነው፡፡ ከፍ ባለ ቁጥር ሰውን አሳንሶ ይመለከታል፡፡ https://telegram.me/Esmailseididris
نمایش همه...
ኢስማኢል

《 ተውሂድን አስመልክቶና ሌሎችም ጠቃሚ ትምህርቶች የሚለቀቁበት 》 !! በተጨማሪም ለሀይቅ ሙስሊሞች መልእክትን ማስተላለፊያ ቻናል ነው !!

የዱንያ ስንቅ በአላቂዋ ህይወት ውስጥ ወደምትፈልጋቸው ነገሮች ያደርስሃል‥ ⇘የአኺራው ስንቅ ደግሞ በዘውታሪዋ ህይወት ውስጥ ወደምትመኛቸው ፀጋዎች ያደርስሃል ። (وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ) " ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ (አላህን መፍራት) ነው ፡፡"
نمایش همه...
🌷የአረብ ሀገር ሴት ግን ታስደምመኛለች !! 🌷አብሶ እሄን ችግር ብትቀርፈው !! 🌻 እራሷ እንደ ሻማ ቀልጣ ለሌሎች ብርሃን የምትሆን ፣ እራሷን ዝቅ አርጋ ቤተሰቦቻን ከፍ የምታደርግ ፣ ባልተደላደለ ህይወት ለሌሎች መደላለደል የምተለፋ ፣ ለራስ መኖር ትርጉሙን ማታቀው ለሌሎች መኖርን የምትኖር ፣ ለምን ተለየች የአረብ ሀገር ሴት !! በሌላ አህጉር የሚኖሩ በአውሮፖ በአሜሪካ በሌሎችም ሀገራት ያሉ እህቶች ስራቸው በአንፃራዊ አረብ ሀገር ካሉት የተሻለ ስራ ነው ፣ እራሳቸውን ስለመለወጥ ብዙውን የሚያስቡት ለቤተሰብ አያስቡም እያልኩ አደለም በደንብ ያስባሉ ግን ከአርብ ሀገር ሴት ጋር ስታነፃፅራቸው ልዩነቱ ይሰፋል ስራቸውም ያልተመቻቸ ዳገት አሳር የበዛበት ነው ፣ ሰርተውም መላክ እንጂ መለወጥን የሚያስቡት ከስንት አንድ ናቸው !! እንዴት እንዴት ሆነው እንደሚያመጡት አላህ ነው የሚያቀው ያም ሆኖ ከብዙ አመታት ቆይታ በሃላ ወደ ሀገር ሲገቡ ብሩ ተኖ አልቋል ባዶ እጃቸውን ነው የሚገቡት ምን ያክል ቅስም ይሰበራል ከዛም ትዳር በመያዣ በማረፊያ ሰዓታቸው መልሰው ወደ መጡበት ሀገር ትንሽ ቂሪት ልሰብስብ ብለው ይመለሳሉ ለዚ ተጠያቂዋች በጥቂቱ እነዚ አካላት ናቸው ብዬ አስባለው 1⃣ ኛው ቤተሰብ ራሱ የሚል እምነት አለኝ ቤተሰብ እዛ ያለውን ችግር እና ስቃይ አይረዳም ብር ሲቸግረው እየጨቀጨቀ ማስላክ በዚ መልኩ በጣም ተጠያቂነት እናት አባት ሳይሆን ወንድሞች ናቸው እንዲ ሆናል እንዲያ ሆናል ብሎ ከአቅም በላይ ብርን ማስላክ ምንም እንዳትለወጥ ያደርጋል አንዳንድ በቃ አረብ ሀገር እህት አለኝ ፈታ ነው የምለው እያሉ የሷን ብር መጫወቻ የሚያደርጉ ብዙ ናቸው። አንዳንድ ለራስሽ አስቢ አብሽር እያለ የሚያበረታታ ቢኖርም አብዛኛው ግን ወዲያ ነው። እና እህቴ ለቤተሰብ አትለግሺ አይባልም በተለይ ለእናት እና ለአባት መርዳት ያስፈልጋል ግን ነገ መጠሽ የነሱ ሸክም ብቶኚ እሱም ሌላ ጣጣ ነውና ለራስሽም እያሰብሽ ሰርቶ መርዳት ሚችል ወንድም ከሆነ ደሞ እንዲሰራ ማበረታታት እንጂ እሱን እንደ ደሞዝ ብር እየላኩ እሱንም ማንሰፍ እራስሽንም ማዳከም የለብሽም እና አላህ እንዳለው በመለገስ ሰዓት በጣም መዘርጋት ማባከንም በጣም ማጠፍም መሰሰት መሃል ሆነሽ እነሱንም አንቺንም እየረዳሽ ሊሆን ይገባል። 2⃣ ኛው ሃለፍትና እና ሃላፊነት ማይሰማቸው ስግብግብ ወንዶች ናቸው !! በትዳር ስም ተቸግሪያለው በሚል ስም ብር ለመፍለጥ አንሰፍስፈው የሚጠብቁ ወንዶች ናቸው እወድሻለው በሚል ሆን ብለው በቻት እያዋራ በቃ ሀገር ቤት ስንገባ እንጋባለን በሚል ስትመጪ ማረፊያ ለአንዳንድ ነገሮች በሚል ብር እያስላከ እሱ ወይ ጫት ነው ሚቅበት ወይ ሌላ ትዳር ነው ሚመሰርትበት ስንቱን አየን ሰማን እነዛ ተቸገርኩ ወደድኩ ለሚል ሁላ ብር አትላኪ ሆን ብለው ለማጭበርበር የተሰለፉ ስግብግብ ወንዶች ናቸው ከነዚ ተኩላዋች እራስሽን ከቆጠብሽ ለራስሽ መሆን ትችያለሽ ለውጥም ይኖርሻል ከመፀፀትም ትድኛለሽ 3⃣ ኛው የዋህነትሽ ችግር ሆኖብሻል ሲበዛ የዋህ አቱኚ ሲበዛም ተጠራጣሪ አቱኚ መጠራጠር ግን በአንድዚ አይነት ነገር በጣም እርግጠኛ ለመሆን ይዳርጋል። የዋህነትሽን የተረዱ ናቸው በአንቺ ለመጫወት የሚመጡት እና አብዝቶ የዋህነት ችግር ነውና ቀንሺ ስንት ሰዋች ሸውዱሽ ስንት ሰዋች አታለሉሽ ሁሉም የሉም አደል ተነዋል ብርሽም ተናል አንዳንዱ ክብርሽንም ይዞ የሄደ ስንት አለ !! በጣም በዝቶ የዋህነትሽ ስልክ ሲቸግራቸው እንኳን አንድ የአረብ ሀገር ሴት በውስጥ ልጀናጀን እና ስልክ ላስልክ የሚሉ በቀቀን ወንዶች እንዳሉ አታቂም አላገጠመሽም አንቺስ አላክሽም ታዲያ በዚ በትንሹ የዋህ ከሆንሽ እንደው ወደድኩሽ ተቸገርኩልሽ ለሚልሽ አጭበርባሪማ ምን ያክል ነው ሚዘርፍሽ እና የዋህነትን ቀንሺ ለዚ መዳኛው ወደ ዲንሽ ተመለሽ ከአላህ ጋር በደንብ ተዋወቂ የዛኔ ነገሮች ሁላ ይስተካከላሉ ከአላህ በራቅሽ ቁጥር ነገሮች ሁላ ይበላሻሉ ስለዚ አማራጭ የሌለው ምርጫ ወደ አላህ መቅረብ ኢስላምን መኖር ነው ። 🌼 ቀጣይ ሌሎች ችግሮችን ለማየት ሞክራለው ለዛሬ እሄን ተግብረሽ ጠብቂኝ ኢንሻአላህ እንደምተገብሪው ተስፋ አለኝ ማ አሰላም። https://telegram.me/Esmailseididris
نمایش همه...
ኢስማኢል

《 ተውሂድን አስመልክቶና ሌሎችም ጠቃሚ ትምህርቶች የሚለቀቁበት 》 !! በተጨማሪም ለሀይቅ ሙስሊሞች መልእክትን ማስተላለፊያ ቻናል ነው !!

وَمَا قَدَرُوا اللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِ إِذْ قَالُوا مَا أَنزَلَ اللَّهُ عَلَىٰ بَشَرٍ مِّن شَيْءٍ ۗ قُلْ مَنْ أَنزَلَ الْكِتَابَ الَّذِي جَاءَ بِهِ مُوسَىٰ نُورًا وَهُدًى لِّلنَّاسِ ۖ تَجْعَلُونَهُ قَرَاطِيسَ تُبْدُونَهَا وَتُخْفُونَ كَثِيرًا ۖ وَعُلِّمْتُم مَّا لَمْ تَعْلَمُوا أَنتُمْ وَلَا آبَاؤُكُمْ ۖ قُلِ اللَّهُ ۖ ثُمَّ ذَرْهُمْ فِي خَوْضِهِمْ يَلْعَبُونَ «አላህ በሰው ላይ ምንም አላወረደም» ባሉም ጊዜ አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም፡፡ (እንዲህ) በላቸው፡- «ያንን ብርሃንና ለሰዎች መሪ ኾኖ ሙሳ ያመጣውን መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትኾኑ ማን አወረደው (የወደዳችኋትን) ትገልጿታላችሁ ብዙውንም ትደብቃላችሁ፡፡ እናንተም አባቶቻችሁም ያላወቃችሁትን ተስተማራችሁ፤» 🍂አንአም 91✍️
نمایش همه...
« ለምትጎነጨው ውሃ እንኳን ቢሆን ከሰዎች ፈላጊ ሆነህ በቀረብካቸው ቁጥር፤ እነርሱ ዘንድ የሚኖርህም ክብር በዚያው ልክ ይወርዳል። » ሸይኩል ኢስላም ኢብን ተይሚያ ረሂመሁላህ ” ﻭَﻣَﺘَﻰ ﺍﺣْﺘَﺠْﺖَ ﺇﻟَﻴْﻬِﻢْ - ﻭَﻟَﻮْ ﻓِﻲ ﺷَﺮْﺑَﺔِ ﻣَﺎﺀٍ - ﻧَﻘَﺺَ ﻗَﺪْﺭُﻙَ ﻋِﻨْﺪَﻫُﻢْ ﺑِﻘَﺪْﺭِ ﺣَﺎﺟَﺘِﻚَ ﺇﻟَﻴْﻬِﻢْ “ ﺷﻴﺦ ﺍﻹﺳﻼﻡ ﺇﺑﻦ ﺗﻴﻤﻴﺔ : ‏( ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ )
نمایش همه...
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال ሰሀባዎች የኢድ ደስታን በመካከላቸው እንዲህ ሲሉ ይገልፁ ነበር "ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሀል አእማል" እኔም ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሀል አእማል። Teqbelellahu mina weminkum salihal aimal
نمایش همه...
Ibnu Muhammedzeyn: ለማመላከት ያክል ፣ * ከሽርክ ራቅ አላህ ከእሳት ያርቃሃል * ተውሒድህን አጥብቀህ ያዝ ወንጀልህ ይማርላሃል * ረሱልን (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በአግባቡ ተከተል አሏህ ይወዳሃል * አሏህን የትም ቦታ ሁነህ ፍራው ያላሰብከውን ሲሳይ ይለግሳሃል * ሰዎችን አትማ መልካም ስራህን ታጣለህ አልያም ያልሰራሃውን ወንጀል ትሸከማለህ * የወንድምህን ነውር ደብቅ አላህ የአንተን ነውር ይደብቅለሃል * ዛሬ መስራት ያለብህን ስራ ለነገ አታዘግይ ነገ ይመጣል አንተ ግን ላትኖር ትችላለህ * ለራስህ የምትወደውን ለወንድምህ ውደድ * በራስህ ላይ ቢሆንም እንኳ ሐቅን ተናገር * ከመጥፎ ጓደኛ ይልቅ ብቸኝነትን ምረጥ * የሌሎቹን ነውር ከማስተካከልህ በስተፊት የራስህን ነውር አስተካክል * ሳታስተውል አትናገር ሳታስብ አትስራ * ሳታረጋግጥ አታውራ ሳያረጋግጡ ያወሩት መጨረሻው ፀፀት ነው * ረጋ በል በመረጋጋት ሰላም ትሆናለህ * አትቸኩል መቸኮል የፀፀት አባት የትእግስት ጠላት ነው * በግዜ ተኛ በጧት ለመነሳት ይረዳሃል * ሚስጥርህን ደብቅ ሚስጥሩን የደበቀ መልካም ነገር ሁሉ በእጁ ነው የሚሆነው * ያመነህን አትክዳ ያመነን መክዳት የሙናፊቅ ባህሪ ነው * ምላስህን ከሰዎች ላይ ያዝ ወዳጆችህ ይበዛሉ * ሌሎችን አክብር ሌሎች አንተን ያከብሩሃል ፣ https://t.me/IbnuMuhammedzeyn ፣ ✍ ወንድማችሁ ኢብኑ ሙሐመድዘይን https://telegram.me/Esmailseididris
نمایش همه...
ኢስማኢል

《 ተውሂድን አስመልክቶና ሌሎችም ጠቃሚ ትምህርቶች የሚለቀቁበት 》 !! በተጨማሪም ለሀይቅ ሙስሊሞች መልእክትን ማስተላለፊያ ቻናል ነው !!

የባህር ዳር ሙስሊም ወንድማማቾች ገፅ: አምልኮ (ዒባዳ) ዒባዳ አላህ ለሚወዳቸው ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ ንግግሮች እና ተግባሮች ሁሉ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ የአምልኮ ዓይነቶች ብዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ሰላት፣ ሩኩዕ፣ ሱጁድ ፣ እርድ(ዘብህ) ፣ ኹሹእ(መተናነስ)፣ መመካት፣ዱዓእ፣ፍራቻ(ኸዉፍ)፣ተስፋ ማድረግ (ረጃዕ)፣ ጠዋፍ እና መሐላ እንዲሁም ሌሎች አላህ የደነገጋቸው የአምልኮ ዘርፎች ሁሉ ዒባዳ ይባላሉ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ)) الأنعام: ١٦٢ (ስግደቴ አምልኮቴም ህይወቴም ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው በል)አል-አንዓም162 የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ)በሀዲሰል ቁድስ አላህ እንዲህ እንዳለ ይገልፃሉ ((ባሪያዬ እኔ ግዴታ ያደረግኩበትን ነገሮች ከመፈፀሙ በተሻለ ወደ እኔ የቀረበ የሚያደርገዉ ስራ የለም፡፡)) ቡኻሪ ዘግበዉታል አላህ መልዕክተኞችን የላከው ወደ እርሱ አምልኮት እንዲጣሩና በእርሱ አምልኮ ላይ የሚፈፀም ሽርክን (ማጋራትን) እንዲያወግዙ ነው፡፡አላህ እንዲህ ይላል፡- ((وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ)) النحل: ٣٦ (በየህዝቡም ሁሉ ዉስጥ አላህን አምልኩ ጣዖትንም ራቁ በማለት መልዕክተኞችን በእርግጥ ልከናል) አል ነህል 36 የአምልኮ የሚገነባባቸው መሰረቶች ሶስት ናቸው፡- አንደኛ፡- ለተመላኪው በሙሉ ልብ መውደድ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- ((وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ)) البقرة: ١٦٥ ‹‹እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡›(አል በቀራህ 165) ሁለተኛ፡- በሙሉ ልብ መከጀል:: አላህ አንዲህ ይላል፡- ((وَيَرْجُونَ رَحْمَتَهُ )) الإسراء: ٥٧ ‹‹እዝነቱንም ይከጅላሉ፡፡›› (አል ኢስራህ 57) ሶስተኛ፡- በሙሉ ልብ መፍራት:: አላህ እንዲህ ይላል፡- ((وَيَخَافُونَ عَذَابَهُ )) الإسراء: ٥٧ ‹‹ቅጣቱንም ይፈራሉ፡፡››(አል ኢስራህ 57 አላህ እነዚህን ሶስት ታላላቅ መሰረቶች በፋቲሃ ምዕራፍ እንዲህ በማለት አካቷቻዋል፡፡ ((الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ * الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ * مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ )) الفاتحة: ١ - ٤ ‹‹ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤ እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ፡፡ የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡››(አል ፋቲሃ 1-3) በመጀመሪያው አንቀጽ ውዴታ ተጠቅሷል፡፡ ምክንያቱም አላህ ባለ ውለታ ነው፡፡ ባለውለታ ደግሞ በዋለው ልክ ይወደዋል፡፡ በሁለተኛው አንቀጽ ክጀላ ተጠቁሟል፡፡ ሶስተኛው አንቀጽ ላይ ደግሞ ፍራቻ ተጠቅሷል፡፡ ምክንያቱም የምንዳና የመተሳሰብ ቀን ንጉስ ከቅጣቱ ይፈራል፡፡ ስለዚህም ነው አላህ በማስከተል እንዲህ ያለው (إِيَّاكَ نَعْبُدُ) ማለትም የነዚህ ሶስቱ ባለቤት ጌታ ሆይ ይህ አንቀጽ (الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ ) በሚጠቁመው ውዴታህ፣ ይህ አንቀጽ ( الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ ) በጠቆመው ክጀላህና ይህ አንቀጽ (مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ ) በጠቆመው ፍራቻህ አመልክሃለው ማለት ነው፡፡ አምልኮ በሁለት መሰፈርቶች እንጂ ተቀባይነት የለውም፦ 1ኛ፡- አምልኮን ለተመላኪው ብቻ ለይቶ መስጠት፡፡ አላህ ለእርሱ ፊት ብቻ ጥርት የተደረገን ስራ እንጂ አይቀበልም፡፡ አላሀ እንዲህ ይላል፡- ((وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ )) البينة: ٥ ‹‹የአላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት... እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)፡፡›› (አል በይነህ 5) ((أَلَا لِلَّهِ الدِّينُ الْخَالِصُ)) الزمر: ٣ ‹‹ንቁ! ፍጹም ጥሩ የኾነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው፡፡›› (ዙመር 3) ((قُلِ اللَّهَ أَعْبُدُ مُخْلِصًا لَّهُ دِينِي )) الزمر: ١٤ አላህን «ሃይማኖቴን ለእርሱ ያጠራሁ ኾኜ እግገዛዋለሁ» በል፡፡ (ዙመር 14) 2ኛ፡- መልዕክተኛውን (ﷺ) ተከታይ መሆን፡፡ አላህ ማንኛውም ስራ የመልዕክተኛውን (ﷺ) መመሪያ ያልተስማማ ከሆነ አይቀበልም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- ((وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا )) الحشر: ٧ ‹‹መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡›› (አል ሀሽር7) ((فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا فِي أَنفُسِهِمْ حَرَجًا مِّمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا )) النساء: ٦٥ ‹‹በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም፤ (ምእመን አይኾኑም)፡፡››(አል ኒሳህ 65) ነብዩም (ﷺ) እንዲህ ብለዋል من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فـهو رد} ‹‹በዚህ ዲናችን ውሰጥ ከሱ ያልሆነን አዲስ ነገር የፈጠረ ስራው ተመላሽ ነው፡፡›› ለአላህ ብቻ በመለየት ያልተሰራና ትክክለኛ ያልሆነ ስራ ትርጉም የለውም፡፡ እነዚህን ሁለት መስፈርቶች አካተው ከያዙ አንቀፆች ውሰጥ የሚከተለው በአል ከህፍ ምዕራፍ መጨረሻ ላይ የተወሳው የአላህ ቃል አንዱ ነው፡፡ ((قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُو لِقَاءَ رَبِّهِ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًا صَالِحًا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا )) الكهف: ١١٠ «እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደኔ የሚወረድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ (አል ከህፍ 11ዐ) የቴሌግራም ፔጃችንን ይቀላቀሉ join👇👇 https://t.me/muslimbrothersbahirdar የዋትሳፕ ግሩፓችን join 👇👇 https://chat.whatsapp.com/KWe3GYXXWcFLirrycsg32w
نمایش همه...
የባህር ዳር ሙስሊሞች መማማሪያ መድረክ

የቻናሉ ትኩረት! ✔ ተዉሒድ እና ሽርክን በማብራራት የነብያትን ተልዕኮ ማስገንዘብ ✔ ትክክለኛ የአህለሱናን መንሀጅ ግንዛቤ ማስጨበጥ ✔ ከትክክልኛው የኢስላም አስተምህሮ ያፈነገጡ አንጃዎችን በመረጃ ማጋለጥ እና ጥናታዊ ምላሾችን ማሰራጨት! ✔ ኢስላማዊ ወንድማማችነትን ማጠናከር

یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.