cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

🇪🇹🇪🇹ከእኛው ለኛው🇪🇹🇪🇹

👉ኢትዮጵያን እናውቃታለን ወይስ አናውቃትም? ጥያቄው ለናንተ ይቀላቀሉን 🇪🇹አሰደሳችና አስተማሪ ወጎችን 🇪🇹ግጥሞችን 🇪🇹የኋላ ታሪካችንን እንመረምራለን፣ 🇪🇹አስደናቂ የሀገራችንን ታሪኮችና ንጉሦች 🇪🇹ጥንታዊነት የዘመኑ ስልጣኔ ነው። 👉እናንት ሼር ለማረግ ካልሰነፋቹ እኔም ለናንተ ለማድረስ አልሰነፍምና @eyuelgebremariam

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
262
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

አሪፍ ቻናል ነው። እንደምትጠቀሙበት ተስፋ አለኝ። 🙏🙏🙏🙏👍👍👍👏👏👏🙌🙌🙌👐👐👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
نمایش همه...
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ውድ ተከታታዮቼ እና ውድ አንባቢዎቼ ለቻናላችን እድገት ሲባል ሼር ማረግዎን አይዘንጉ አዲስ የገባቹህም ብትሆኑ ለሌሎች ሰዎች ሼር ማረጋችሁን እንዳትረሱ። 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 @yegitmmedbil @yegitmmedbil @yegitmmedbil
نمایش همه...
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 በራስ መተማመን ተላብሰን ድህነታችንን አሸንፈን በዓለም አደባባይ ላይ ቀና ብለን የሀገራችንን ቅርሶችን በአግባቡ ጠብቀን የውጭውን ዓለም አማልለን ወደ ሀገራችን መሳብ አልቻልንም።ብርቅዬዋን ቅርስ ሉሲን እንኳን አሜሪካ ድረስ የወሰድን፣ጎብኝ ወደ ቅርስ ይመጣል እንጅ ቅርስ ወደ ጎብኝ ሄዶ የማያውቀውን አዲስ ደካማ ልምድ ያስመዘገብን ሆነናል። ስለ ግል ኑሮአችን ብቻ የምንኳትን ምስኪኖች ነን።የእኔ የራሴ ሕይወት ምስክር ነው። "ቀዳዳ በርሜልን የመሙላት ጥድፊያ መሆኑን አውቃለውና።" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
نمایش همه...
".....ኢትዮጵያ ውስጥ ኑሮ በእሾህ የተከበበ ፅጌሬዳ ነው።የተወሰነ ጊዜ ቆይተህ በእርጋታ እሾሁን በጥንቃቄ አልፈህ ፅጌሬዳውን ስታገኝ በቂ ዘላቂ ፍቅርና ውበት ደስታና ሰላም ይሰጥሃል ።ደስታህንና ፍቅርህንም የሚጋራልህ ብዙ ሰው አለ።ሰው ነህና ብታገባ ይዘፈንልሀል።ብትታመም ይታዘንልሀል ።ብትሞት ይለቀስልሀል።እናም ሰው መሆንህ ያኮራሀል።በምዕራቡ አለም ፅጌሬዳው ቅርብህ ነው።እስከሰራህ ድረስ በእሾህም አልተከበበም።ችግሩ ግን ብቻህን ሩጠህ ፅጌሬዳውን እንዳገኘህ መዐዛውን ልትስብ ብቻህን ስትመቻች ውስጡ በእሾህ የተሞላ እንደሆነ ትረዳለህ።አንተ በምዕራቡ አለም ከቁጥሮች መካከል የምትኖር ቁጥር ነህ።ያኔ ኑሮህ ጎምዛዛ ወይም ጣእም አልባ ይሆንብሀል።እንደ ሰው መብቶችህ በእጅጉ የተከበሩ ቢሆኑም ለብቻህ ነህና ሰው መሆን ያስጠላሀል !"....... ከ ዝጎራ የተወሰደ ዶክተር አለማየሁ ዋሴ
نمایش همه...
•…ኢትዮጵያን የነካ… "…ጣልያን የሮማ ገና ልዕለ ኃይል ከሚባሉት የዓለም ኃያላን መንግሥታት መካከል አንዷ ነበረች። የካቶሊክ ሃይማኖት መንበረ ጵጵስና መቀመጫ፣ በሥነ ሥዕል፣ በሥነ ህንጻ፣ በሙዚቃው የተራቀቁ ጠቢባን መናሃሪያ ማዕከልም ነበረች። ሮማ በቅኝ ግዛት ያልገዛችው ሃገር በጣም ጥቂት እንደነበር፣ እነ ጀርመን ሁሉ በሮማውያኑ ሥር እንደነበሩ ይነገራል። እስራኤል ኢየሩሳሌምም በእነሱ ቁጥጥር ስር ነበር። ክርስቶስ ኢየሱስም ለሞት የበቃው በሮማውያኑ የፍርድ ሸንጎ ነበር። ገናናዋ ሮማ ከዘመን ብዛት እየወደቀች ብትመጣም እንኩትኩቷ ወጥቶ የአውሮጳ ደሃ ሃገር እንድትሆን ያደረጋት ግን የማይነካውን በመንካቷ " የእግዚአብሔር መቅደሱ ኢትዮጵያን" በመዳፈሯ ነው። ውቃቢ የራቃት፣ መቅኖዋ የፈሰሰው፣ ቆሌዋም የተገፈፈው ኢትዮጵያ ላይ ከተነሣሣች በኋላ ነው። (በዐፄ ሱስንዮስ ዘመን የሠሩትን ሴራ ለማለት ነው) …አሁን ደግሞ ከጣሊያን ትምህርት ያልወሰደች ከተፈጠረች 400 ዓመት እንኳ በቅጡ ያልሞላት፣ በአይሪሽ ስደተኞች የተፈጠረች፣ የዘመኑ ልዕለ ኃያል ሃገር ነኝ ባይ አማሪካ የሌለ አቅበጥብጧታል። 24/7 ኢትዮጵያን ለመናድ እንቅልፍ አጥታ የምታድረዋ አማሪካ መውደቂያዋ ብቻ ሰይሆን ለመታሰቢያ የሚተርፍ ነገር በዚህ ምድር ሊያሳጣት ነው መሰል የሌለ ተቅበዥብዣ ዘው ብላ ገብታለች። ታደርግ ትሠራውን አሳጥቷል። …ኢትዮጵያን ሲያዩዋት ጭርንቁስ፣ ደሀ፣ ምስኪን፣ የእኔ ቢጤ፣ አቀመ ቢስ እንኳን ገፍተዋት እፍ ቢሏት ተከስክሳ በአፍጢሟ ተደፍታ ብትንትኗ የሚወጣም ነው የምትመስላቸው። ብዙዎች ኢትዮጵያን የሚያዩት በዓለም መነፅር ነው። እሱ መነፅር ደግሞ የኢትዮጵያን ቁልጭ ያለ ማንነት ለማሳየት አይመችም። ያወዛግባቸዋል። እናም ይሸወዳሉ። ከዚያም ይገዳደሯታል።ሊገፏት፣ ሊጨብጧትም ይሞክራሉ። ሆኖም ግን አይሳካላቸውም። ባልተሳካላቸው ቁጥር ደግሞ የበለጠ ንዴት ቁጣቸው፣ እልሃቸውም ይጨምራል። ከዚያ በኋላ የመውጊያውን ብረት ይቃወማሉ። ይገፋሉ። ራሳቸው ተወግተው ይወድቃሉ። …ወያኔ የዓለም መንግሥታት ሁሉ የርኩሰታቸው ፈቃድ ማስፈጸሚያ ጓንታቸው ነበር። ቅድስት ኢትዮጵያ ላይ ነውር ኃጢያታቸውን የሚያራግፉበት ፈረሳቸው ነበር። የኢትዮጵያን ቅድስና የሚሸረሽርላቸው መሳሪያቸው ነበር። በኢትዮጵያ በኩል አፍሪካን መጠምዘዣ ሮቦታቸው ነበር። የኢትዮጵያን ቅድስና የሚያረክስ ሰይጣን የዲያብሎስ ግልገላቸው ነበር። በመቅደስ ኢትዮጵያ ውስጥ በርኩሰት እንዲመላለሱ የሚያደርግ ሎሌያቸው ነበር። ገነት ኢትዮጵያ ውስጥ ዘው ብለው እንዲገቡ የሚያደርግ እባብ ዘንዶአቸው ነበር። አዎ ይሄ የክፋት የርኩሳቸው ዘንዶ መነቀሉ ነው ነው ያበሳጫቸው። ይሄ የዘንዶ አንገት ራሱም መቀጥቀጡ ነው ኢትዮጵያን እንደ አንደኛዋ ክፍለ ሃገራቸው ቆጥረው ነጠላ ዘቅዝቀው እዬዬ እንዲሉ ያደረጋቸው። የሚገርመው ግን ኢትዮጵያን አይችሏትም። አያሸንፏትም። … ኢትዮጵያ ዓሣ ናት፣ ለሰይጣናት ፈቃድ የማትጨበጥ ዓሣ። ኢትዮጵያ ተልባ ናት። ለአፋቃሬ አጋንንቶች ሁሉ የማትጨበጥ ተልባ። ሙልጭልጭ የምትል ተልባ። ኢትዮጵያ የጋለ የብረት የኳስ አሎሎ ናት። ሲያዩዋት የምታምር፣ ሲጨብጧት የምትፋጅ እሳት ናት። ኢትዮጵያን የሚያውቋት የሉሲፈር መንፈስ ርዝራዦች አይደሉም። ኢትዮጵያን የሚያውቋት በስሱም ቢሆን ማንነቷ እንዲገለጥላቸው የተፈቀደላቸው አካላት ብቻ ናቸው። ኢትዮጵያ የሙሴ ጽላት መቀመጫ መንበሩ ናት። ኢትዮጵያ የክርስቶስ ኢየሱስ መስቀሉ ማረፊያ ዙፋኑ ናት። ኢትዮጵያ 24/7 ስመ እግዚአብሔር የሚጠራባት የቅዱሳን ምድር ናት። (ይሄ የአውሮጳና የአማሪካ የሃይማኖት ፍልስፍና የወለደውን ዲቃላ አይመለከትም) አዎ ኢትዮጵያ በምድር ካሉ ሃገራት የተለየች ናት። በ20 ዓመት የአፍጋኒስታን ቆይታዋ የተባበሩት መንግሥታት ሁለት ጊዜ ብቻ የተሰበሰባት አፍጋኒስታንን አይተህ በአንድ ዓመት 12 ጊዜ ስብሰባ ሲቀመጡባት ስታይ የኢትዮጵያ ክብር እና ውድ ዕንቁ የመሆኗ ምስጢር ይገለጥልሃል። …ይሄን ስንል የሚበሳጩ፣ የሚጎፈሉ፣ የሚናደዱ፣ የሚንበጫበጩ፣ ለሃጫቸው እስኪዝረበረብ የሚንተፋተፉ፣ እሷ ከሶሪያ፣ ከየመን፣ ከኢራቅ ከሊቢያ በምን ትለያለች የሚሉ የራሳችን ባንዳ የአጋንንት ፈረሶች የትየለሌ ናቸው። የእናት ጡት ነካሾች፣ የተረገሙ። አዕምሮአቸው የተደፈነ፣ የጠላት ቅጥረኞች፣ ነፍሰበላ አረመኔዎች ብዙ ናቸው። በኢትዮጵያ ታላቅነት የሚያፍሩ፣ ነጭ ስላልገዛን የሚቆጩ፣ ባርያ የባርያ ልጆች ሞልተዋል። ኢትዮጵያን ሲኦልም ድረስ ገብተን እንበትናታለን እስከማለት የደረሱ የአጋንንት ፈረሶች የትየለሌ ናቸው። የፈረሱ ጋላቢዎችም፣ ፈረሶቹም ግን ሁላቸውም በአንድነት ይወቃሉ። ይደቅቃሉ። እግዚአብሔር ታላቅ ነው። …አሜሪካ የጥንታውያን ሃገራት ቀበኛ ናት። ገና ለጋ ጩጬ ስለሆነች በጥንታውያን ሃገራት ትቀናለች። አይኗ ደም ነው የሚለብሰው። ጥንታዊቷን ሶሪያን አፍርሳለች፣ ጥንታዊቷን ኢራቅን አፍርሳለች፣ ጥንታዊቷን ሊቢያን አውድማለች፣ ጥንታዊቷን የመንን ፍርስርሷን አውጥታለች። አሁን የቀረቻት ጥንታዊቷ ሃገር ኢትዮጵያ ናት። ሶማሌን ገንጥለው፣ ጁቡቲን፣ ኤርትራን ቆርጠው ገንጥለው። ያለ ወደብ፣ ያለውኃም አስቀርተው፣ ከባህሩ አርቀውን ሊያጠፉን በብርቱ ደክመዋል። አሁን ደግሞ ትግራይን ገንጥለው፣ ኦሮሚያ የምትባል አዲስ ሃገር ፈጥረው፣ ሶማሌን ለብቻው፣ ጋምቤላን ወደ ደቡብ ሱዳን፣ ቤኒሻንጉልን ለሱዳን ሰጥተው ኢትዮጵያን ብትንትኗን ለማውጣት ነበር ድካማቸው። አይሳካም። … አሜሪካ አሁን መዋረድ ትጀምራለች። #Nomore አለምአቀፋዊ የአማሪካና የተባባሪዎቿ የመውጊያ ብረት ሆኖ ያገለግላል። ዳግማዊ ዓድዋ ዳግም በዚህ ዘመን ይገለጣል። አሜሪካ ሁሉ ነገሯ " ጓ " ይልባታል። ብኩርናዋ ለሌላ ይሰጣል። መቅኖ ቢስ ትሆናለች። ኢትዮጵያ ዳግም ታሸንፋለች። የኢትዮጵያ ተዋጊዋ እግዚአብሔር ነው። የኢትዮጵያ ተዋጊ ልዑል እግዚአብሔር ነው። እሱ ባይሆንማ ኖሮ እንደ ውስጥ ከሃዲው ብዛት፣ እንደውስጥ ሻጩ፣ ባንዳው ብዛት ይሄኔ እኮ የለችም ነበር። አንድም ፓስተር አማሪካን ሲቃወም የማታየው ለምን ይመስልሃል? አሜን ነው? አሜን ሃሌሉያ ብቻ ሙያ መስሎሃል። … ማርያምን ኢትዮጵያ ግን ትነሣለች  !!
نمایش همه...
ህብረተሰቡ ፊቱን ወደ ጦርነት ሙሉ ለሙሉ እንዲያደርግ በሴራ ተደርጎ የ Corena ክትባት በዘመቻ መልክ በት/ቤት ውስጥ እና በተለያዩ ቦታዎች እየተሰጠ ነው ሰው ግን አሁንም Dramaw ላይ ነው ሁሌም እንደ አዲስ ነው ሚያየው የሴራውን Drama
نمایش همه...
⚜⚜-------------⚜⚜-------------⚜⚜ የቀጠለ ይላል........እንግዲህ አክሱማውያን አክሱምን ከመከተማቸው በፊትና በኋላ ጥብቅ ቁርኝነት የፈጠሩት ከግሪክ ጋር መሆኑን በአማልክቶቻቸው መረዳት ይቻላል። እንዲሁም በፅሁፋቸው። ስለዚህ የቀድሞዎቹ ነገሥታት በግብፆች በነአሞን ሲያመልኩ የነበረ ሲሆን፣ አክሱማውያን ደግሞ በግሪኮች አማልክት እያመለኩ ነው የቀጠሉት። ከላይ ባየነው ፅሁፍ መሠረትም ቀደም ሲል መርዌ መናገሻ በነበረች ጊዜ ንጉሥ ሐንዲው አብራ ፋርሶችን ባሸነፈ ጊዜ አክሱሞች መታያ ይዘው ሄደው እንኳን ደስ ያለህ እንዳሉት አይተናል። አሁን ደግሞ ክርስትና ከገባ በኋላ፣ ይህ ንጉሥ ከአክሱም ተነስቶ ብዙ አገሮችን ማስገበሩን ስናይ የኢትዮጵያ መናገሻ ከተማ ከመርዌ ወደ #አክሱም የተዛወረው በዚሁ ንጉሥ ጊዜ ማለትም ክርስትና ከገባ ከጥቂት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን እንረዳለን። ይህ የአክሱም ንጉሥ እነዚያን የጠራቸው አገሮች አዋ ያለው አድዋ ወይም የዬሃ አውራጃ፣ ዜንጋቤንና አንጋቤ ያለው ደግሞ ኮስማስ እንደገለፀው በአዶሊስ ዙሪያ ያለው የትግሬ አገር፣ ቲያሬ /ጪያሞ/ ያለው የጋምቤላን ህዝብ፣ አታልሞ ያለው የኩናማን አገር፣ ቤጋ፣ ታንጋይቲ፣ አታቢቲ፣ የሚላቸውም ከአክሱም ምዕራብ ሠሜን እስከ ግብፅ ግዛት /ወሠን/ የሚገኙትን ሲሆን፣ የበጅያ /ብሌማይ/ ህዝቦችን ነው። ራውዚ የሚለው ሱሌማን፣ ሳሱ የሚለው ወርቅ የሚገኝበትን የወለጋን አገር እንደሆነ ታውቋል። ሎውኮሚ፣ አራቢት፣ ኪናይዶኮልፒት የተባሉት ደግሞ በዓረብ ማዕከላዊና ሠሜን፣ በኤርትራ ባህር ዳር በደቡብ በኩል ያሉትን ህዝቦች እንደሆነ ተረጋግጧል። ኮስማስ............... ይቀጥላል። እስከዛ ሼር እያረጋቹ ሼር ሼር ሼር🙏🙏
نمایش همه...
እጅግ በጣም ካስደመሙኝና ካስደነቁኝ መጽሐፎች መሐል አንደኛው ነው። 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹እመጓ🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🇪🇹 "እመጓ ቆላ ሆይ!" 🇪🇹"አንቺ የተባረክሽ ምስጢራዊ ምድር! 🇪🇹 ሶርያዊው አባ አድሪል ቅዱሱን ቅርስና ቃል-ኪዳን በሆዷ ይዛለች ብሎ የተቀኘልሽ፤ 🇪🇹 አንቺ የቅርብ ሩቅ ማዕከላዊ ምድር ስትሆኚ ጠረፍ የሆንሽ፤ 🇪🇹 አንቺ የአደራ ማማ ስትሆኚ በተራሮችሽ የተከለልሽ አዘቅት፤ 🇪🇹 አንቺ መላእክት የሚረብቡብሽ ስትሆኚ ሰዎች ግን የናቁሽ፤ 🇪🇹 አንቺ ዓለምን የሚያስቀና ግሩም ቃል-ኪዳን ያለሽ ስትሆኚ ራስሽን ደብቀሽ ተራ ሆነሽ የኖርሽ መናኝ፤ 🇪🇹 አንቺ ሁሉም ስለራሱ ሲያወራ፣ ለዘመናት ዝም ያልሽ ልጉም ሙዳይ፤ 🇪🇹 ቫቲካን ስታቅራራ፣ ቆጵሮስ ስትጮህ፣ እስክንድርያ ስታመሰጥር፣ ኢየሩሳሌም በጸጸት ስትቃትት፣ ለንደን ያለስጦታዋ ስትቦተልክ፣ ፈረንሳይዋ ማርሴይ በምኞት ስትቃዥ ምንም የማይመስልሽ፣ አርምሞን የመረጥሽ አሳቻ ታዛቢ፤ 🇪🇹 የእኅቶችሽን የአክሱምን፣ የግሸንን የላሊበላን፣የጣና ቂርቆስን ያክል እንኳን ፊትሽ የማይፈታ የተቋጠርሽ ሸማ! ዓለም ሁሉ ወደ እነርሱ ሲጎርፍ ቅናት የሌለብሽ ልዝብ ደርባባ......። 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹እመጓ🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 👉መጽሐፉን እንድታነቡትና አንብባቹህ እንድትገረሙበት እንድትደነቁበት እጋብዛቹሀለው። 👇👇👇👇ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር @yegitmmedbil @yegitmmedbil @yegitmmedbil
نمایش همه...
የቀጠለ ፩. ንጉሡ በምስራቅና በደቡብ በኩል ወደ ግዕዝ /አጋዚያን/ ወደ አጋሜ፣ ወደ ሴጌኔ፣ ወደ አዋ፣ ወደ አንጋቤ፣ ወደ ቲያኣማ፣ ወደ አታጋው፣ ወደ ካላኦ አገር ሔዶ ከዚያም የተከዜን ወንዝ ተሻግሮ ሠሜንን ማስገበሩን፣ ፪. በምዕራብ ሠሜን በኩል ላዚኔ፣ ዛኦ፣ ጋባላ፣ አታልሞ፣ ቤጋስ /ቦጎስ በጅያ/ የሚባሉትን፣ ፫. አኒኔ፣ ሜቲኔ፣ ሴሲያ፣ /ሳሆ/ ራውዘን፣ ሳውለት የሚባሉትን፣ ፬. በዛሬው የአረብ አገር በየመን ያሉትን የሳባን አገሮች ሄዶ በጦር ማስገበሩን ይገልፃል። በንጉሱ አገላለፅም እንዲህ እያለ ይተርከዋል። "በግዛቴ አጠገብ ያሉትን አገሮች በብርታት ተዋግቼ በሠላም እንዲገዙ ካደረግሁ በኋላ ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን አገሮች በጦርነት አስገበርኩ። ጋዜ /አግአዚ/ አጋሜን፣ ሴጅዬን ወጋሁዋቸውና የሀብታቸው አጋማሽ ወሰድኩ። አውአ፣ ዚንጋቤን፣ አንጋቤ፣ ቲአማኣ፣ አታጋውስ፣ ከለአ፣ ከዚያ ከዓባይ ወዲያ ያሉትን የሳሚኔን ህዝብ ወጋሁ። ይህ አገር ተራራማና ብርድ ያለበት አገር ነው። የበረዶው ክምር እስከ ጉልበት ይደርሳል። እነዚህን አገሮች ሁሉ ወንዙን ተሻግሬ አስገበርኳቸው። ከዚያ ላዚኔ፣ ዘአኣ፣ ጋባላ፣ የሚባሉትን ፍልውሃ በሚመነጭበት ተራራ የሚቀመጡትን ህዝቦችና ከእነርሡም ጋር አታልሞንና ቤጋን /በጅያን/ ከታንጋይቲ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወሠን የሚኖሩትን ህዝቦች በጦር ካሳመንኩ በኋላ ከግዛቴ ጀምሮ እስከ ግብጽ ግዛት ድረስ መንገድ አሰራሁ። በተራራ ላይ የሚኖሩትን የሴሴያ ህዝቦች በትልቅና በማይወጣ ተራራ ላይ ሆነው ስላስቸገሩኝ ዙሪያውን አስከብቤ እጃቸውን እንዱሰጡ አስገደድኳቸው። በሜዳና በበርሐ ውሃ በሌለበት አገር እጣን እየነገዱ በበርበራ አገር የሚኖሩትን የራውዚን ሠዎች፣ የሰላጤንም ሰዎች እስከ ባሕር ድረስ ያሉትን ሁሉ በተራራ እየተሸሸጉ ያስቸገሩኝን ሁሉ እኔው ራሴ በጦርነቱ ቦታ እየተገኘው ካሸነፍኳቸው በኋላ ሁሉንም ግብር እንዲገብሩልኝ አድርጌ በነፃነት ለቀቅኋቸው። 👉በዚያን ጊዜ ሌሎችም ታላላቅ ህዝቦች ያለጦርነት ገበሩልኝ። ከኤርትራ ባህርማዶ የሚኖሩትንም /ዓረቦችን/ የኣራቢትንና የኪናይዶኮልፒቲን አገሮች እንዲወጉ የእግረኛና የመርከበኛ ጦር ልኬ ነገሥታቶቻቸውን በመሬታቸው እንዲገብሩልኝና በባህሩም ላይ በሠላም ንግዱ እንዳካሔድ አዘዝኳቸው። ከሌውኮ እስከ ሳቤይ ድረስ ያሉትን ህዝቦች ከኔ በፊት የነበሩት ነገሥታት ያላስገበሯቸውን አስገበርኩ። 👉ስለዚህም ለትልቁ አምላኬ ለወለደኝ፣ ከምስራቅ እጣን እስከሚገኝበት፣ ከምዕራብ እስከ ኑብያ፣ እስከ ሳሱ ያሉትን ህዞቦች ሁሉ በእርዳታው ስላገዘኝ ለአሬስ ምስጋና አቀርባለው። እኔም ራሴ ሔጄ፣ የጦር መኮንን ልኬ በውስጤ የሚገዛውን ህዝብ ሠላማዊ ካደረግኩ በኋላ ለመርከበኞች ደህንነት ይሆን ዘንድ ለዜውስ፣ ለአሬስ፣ ለፖሲዶን፣ መስዋዕት ለማቅረብ እወዳለሁ። በዚሁ ስፍራ የጦር ሠራዊቴን ሠብስቤ በሠልፍ በነገስኩ በ27ኛው ዓመት ይሄን ዙፋን አምጥቼ ለአሬስ ሰጠሁ።
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.