cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ንቁ ትውልድ-Niku Twld

እኛ ንቁ ትውልዶች ነን!

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
4 046
مشترکین
-524 ساعت
-147 روز
-7930 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

📍«በሰው ዘንድ አለቀ ተቆረጠ የተባለን ነገር ሁሉ በእምነት ከጠበቅን #ፈጣሪ  የተቆረጠን ነገርን ይቀጥላል!» : 📍እምነት ማለት ማመን መታመን ማለት ነው። ፈጣሪ መኖሩን ዓለምን ያስገኘ አንድ አምላክ መኖሩን ሳናይ ሳንዳስስ ሳንጨብጥ ያለጥርጥር ይደረግልኛል ይሆንልኛል ማለት #ማመን ነው። ፡ 👉ይህን ማመናችንን የምናረጋግጠው ደግሞ በመታመን ብቻ ነው። መታመን ማለት እምነትን በሥራ መግለጥ ማለት ነው። መጾም፣ መጸለይ፣ መስገድ፣ መመጽወት መታመንን ይገልጣሉ። ፡ ↪አንድ ሰው ፈጣሪ ያዘዘውን ካልሠራ ታመነ አይባልም። ፈጣሪ ያስተማረህን እንድትሆን ያዘዘህን ሆነህ መገኘት ካልቻልህ ታማኝ አይደለህም ማለት ነው። ፡ ↪እምነት መታመን ከሌለበት ከንቱ ነው። ዝም ብሎ ጠዋት ማታ ጌታዬ ጌታዬ ማለት ብቻውን አያድንም። ፡ ↪አንድ ዘበኛ ቤት እንዲጠብቅ ተቀጥሮ ሳለ የቀጣሪውን ንብረት ከሰረቀ ታማኝ እንደማይባልና ከሥራ እንደሚባረር ሁሉ እምነታችንም መታመን ከሌለበት ከእምነት ለመውጣት እንገደዳለን። ፡ ↪እምነት የምትታመንበት ነው እንጅ በአፍህ ብቻ አምናለሁ እያልህ የምትቀልድበትና የምታሾፍበት አይደለም። ፡ ↪ለማመንህ መገለጫው መታመንህ ነው። አምንሃለሁ ለምትለው ፈጣሪ ልትገዛ ትእዛዙን ልትጠብቅ ያስፈልጋል። ፡ ➊.አትብላ ሲልህ አለመብላት፣ ፡ ➋.ትስረቅ ሲልህ አለመስረቅ፣ ፡ ➌.አትዋሽ ሲልህ አለመዋሸት፤ ፡ ➍.አመስግነኝ ሲልህ ማመስገን፤ ፡ ➎.ጹም ሲልህ መጾም፣ ፡ ➏.ጸልይ ሲልህ መጸለይ ወዘተ አለብህ የመገዛትህ ወይም የመታመንህ መገለጫ ነውና። : ↪ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ ምጽዋት የሌለበት እምነት ከንቱ ነው። ለምታምነው አምላክ የመገዛትህን መገለጫ ማቅረብ አለብህ። ፡ ↪ይህ የመታመንህ መገለጫ ደግሞ በዘፈቀደ የሚደረግ ሳይሆን ሥርዓት ሊኖረው ግድ ይላል። ፡ ሰናይ ቀን🙏🙏
نمایش همه...
👍 3👌 3
📕ያለፍክበት የህይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራስህ ምርጫ ነው፡፡ 📕በህይወትህ የደስታ ምንጭ መሆን ባትችል እንኳን ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትሁን፡፡ 📕ዝምታ ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡ 📕በምድር ላይ ምንም ፍፁም ነገር የለምና አንተም ፍፁም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍፁም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ሁሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡ 📕ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡ 📕በህይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡ መልካም ቀን!🙏
نمایش همه...
👍 8
ትዕግስት ይኑረን🙏🙏
نمایش همه...
🥰 7 3
📙አንብቤ ከወደድኩት ላካፍላቹ👇 ኔልሰን ማንዴላ ፕሬዝደንት ከሆኑ በኋላ አንድ ቀን ጠባቂዎቻቸውን ለምን በእግራችን ወጣ ብለን አንንሸራሸርም በዛው ምሳ እንበላለን ብለዋቸው ተያይዘው ወጡ። አንድ ሞቅ ያለ ሰፈር ሲደርሱ ምግብ ቤት አግኝተው ከጠባቂዎቻቸው ጋር ገብተው እንዳዘዙ ከፊት ለፊታቸው ያዘዘው ምግብ የዘገየበት አንድ ሰው ስላዩ "ጥሩትና ከእኛ ጋር ይብላ"ብለው አንዱን ወታደር ላኩ። ሰውየው መጥቶ አብሯቸው ተመገበ። ሰውዬው እየተመገበ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር። ጨርሶ ሲሄድ ከጠባቂ ወታደሮቹ መሃል አንዱ "ማንዴላ የቅድሙ ሰውዬ ህመምተኛ ነው መሰለኝ ። እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር"ይላቸዋል ማንዴላ "አይደለም!ድሮ የታሰርኩበት እስር ቤት ጠባቂ ዘበኛ ነበር ። ብዙ ግዜ ተደብድቤ ከቶርች ስመለስ ውሃ ስለሚጠማኝ ውሃ እንዲሰጡኝ በጩኽት ስጠይቅ ይሄ ሰው በምላሹ ይመጣና ፊቴ ላይ ሽንቱን ይሸናብኝ ነበር" አሁን ፕሬዝደንት ሆኜ ሲያየኝ የምበቀለው መስሎት ፈርቶ ነው" ሀገር በመቻቻል እና በፍቅር እንጂ በቂም በቀል አትገነባም ። ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም !!! ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ባህርይ ናት! ውብ ቀን ተመኘንላችሁ🙏
نمایش همه...
👍 6 4👏 2
እንደ አሸናፊ አስብ! ሰው ምንድነው ቢሉ ደጋግሞ ያሰበውን ነው ይባላል፤ ስለዚህ ለማን ብለህ ነው አብዝተህ የጎደለህን ከሰው ያሳነሰህን የምታስበው?! በቃ ተዓምር መስራት እንደምትችል ባንተ ምክንያት መጀመሪያ የራስህ ከዛ የቤተሰቦችህ ህይወት እንደሚቀየር አስብ እሱን እውነት ለማድረግ የምትችለው ጥግ ድረስ ጣር የቀረውን ለፈጣሪ ተወው! ሰናይ ቀን😍😍 ✍️ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች
نمایش همه...
👌 8🥰 1
እድሎችን አጠብቅ ፍጠራቸው!😍 መልካም 🙏
نمایش همه...
👍 8
ደፋር ሁን…!! ደፋር መሆን እንኳን ባትችል ደፋር መሆንን አስመስል ፣ልዩነቱን ማንም ሊያውቀው አይችልም‼️😝 መልካም ቀን🙏
نمایش همه...
👍 10
#ከድንጋይ_ፈላጩ_ተማር በስተመጨረሻ የእምቅ ችሎታ ጉብታህን ስታልፍ ሰዎች ስኬትህን የአንድ ቀን ስኬት ብለው ይጠሩታል፡፡ የውጪው ዓለም ሁሉንም የለውጥ ደረጃዎችህን አያይም፡፡ ሰዎች ማየት የሚችሉት ድራማዊ የሆነውን የለውጡን ፍሬ መገለጫ ብቻ ነው። አንተ ግን ለዚህ ያበቁህ ምንም ለውጥ እያሳየህ በማይመስል ሰዓት ሁሉ የሰራሀቸው ጠንካራ ስራዎች መሆናቸውን ታውቃለህ፡፡ በአንድ ነገር ላይ ለመንገስ ትዕግስት የግድ አስፈላጊ ነገር ነው። ከውጤታማዎቹ የኤን ቢ ኤ ቡድኖች መካከል ተጠቃሽ የሆነው ሳን አንቶኒዮ ስፐርስ ከማህበራዊ ቀራፂው ከጃኮብ ሪስ ወስዶ በተጨዋቾቹ ሎከር ላይ የሰቀለው አንድ ጥቅስ አለ፡፡ ጥቅሱ እንዲህ ይላል፤ ሁሉ ነገር ምንም ለውጥ የማያመጣ በሚመስለኝ ጊዜ ሄጄ የማየው አንድ ድንጋይ ፈላጭ አለ፡፡ ይህ ፈላጭ ድንጋዩን በድንጋይ መፍለጫው መቶ ጊዜ ይመታዋል፡፡ በዚህ ሁሉ ድካም ውስጥ ግን ምንም የመሰንጠቅ ምልክት ድንጋዩ ላይ አይታይም፡፡ በመቶ አንደኛው ምት ግን ድንጋዩ ለሁለት ይሰነጠቃል፡፡ እኔ ግን ድንጋዩን የሰነጠቀችው 101ኛዋ ምት ብቻዋን ሳትሆን መቶ አንዱም ምቶች በአጠቃላይ ተደማምረው እንደሆነ አውቃለሁ፡፡” ከልማድ ኃይል መጽሐፍ የተወሰደ
نمایش همه...
👌 6👍 1
እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል🙏🙏 @nikutwld
نمایش همه...
6