cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ቅድስት ናግራን

ይህ የአያት ጠበል መካነ ሕይወት መድኃኔዓለም እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ወልድ ዋሕድ ሰንበት ት/ቤት የኪነ ጥበብ ክፍል መልክቶች እና አስተማሪ የኪነ ጥበብ ሥራ የሚተላለፍበት ሲሆን ለሁሉም ህዝበ ክርስቲያ ነው:: አስትያየቶን እና ሃሳቦን ወይም ያልትመቸዋት ነገር ካለ ከታች ባለው ሊንክ ላይ ያጋሩን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @nagrank @nagrank @nagrank

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
351
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-47 روز
+2030 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

አንድን በክፉ ምግባር የተያዘን ሰው ወደ መልካም ነገር ልትመልሰው ብትወድድ መጀመርያ ሰላሙን እንዲያገኝ አድርገው፡፡ በፍቅር ቃል ከፍ ከፍ አድርገው። እንዲህ ያለን ሰው ከክፉ ስራው እንዲመለስ ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ዘዴ የለምና። ሰው በተግባር የሚያደርገው ፍቅር ሰዎችን የመለወጥ ፍጹም ሀይል አለውና። ቀጥለህ በፍቅር አንድ ሁለት ቃልን ንገረው፣ በቁጣ አትንገረው። በእርሱ ላይ አንዳች የጠላትነት ስሜት አታሳይ። ፍቅር ሰዎችን ለመለወጥ መንገዱን እርሱ ያውቅበታል። ብቻ እንተ እድሉን ስጠው። የፍቅር ሰውም ሁን። (መክስምያኖስ ባህታዊ ዘሶርያ - የበረሃ ፈርጦች)
نمایش همه...
2👍 1
የትምህርት ዕድል ያመለጠህ መስሎህ ነው? ገና ሺህ የትምህርት ዕድሎች አሉህ:: ዕድሜህ ያመለጠህ መስሎህ ነው? ነገ የሚጠብቁህ ብሩሕ ዘመናት እኮ ቁጭ ብለው አሉ?  የሚረዳኝ ሰው የሚያስብልኝ ሰው አጥቼያለሁ? ብለህ ከሆነም ካልሰሙህ ጥቂቶች በላይ ልንሰማህ የምንሻ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" መከራ ጸናብኝ ኑሮ ጨለመብኝ የሀገሪቱ ሁኔታ ተስፋ አሳጣኝ ብለህ ይሆን? እኛስ አብረንህ አይደልንም? አብረን ከገባንበት ችግር አብረን ብንወጣ አይሻልም?  ከአንተ በባሰ ሁኔታ የታሰርንና የተገረፍን ጳውሎሶችና ሲላሶች "ሁላችን በዚህ አለንና በራስህ ክፉ አታድርግ" ስንልህ ስማን:: ይልቅ አንተም እንደ ወኅኒው ጠባቂ "እድን ዘንድ ምን ላድርግ ብለህ?"ነፍስህን የምታድንበትን መንገድ ወደ መቅደሱ ቀርበህ ጠይቅ:: ወዳጄ ይህንን ጽሑፍ ያነበብኸውም በሕይወት ስላለህ ነው:: የአንተን ዓይን የሚጠብቁ ብዙ ጽሑፎች ፣ የአንተን ጆሮ የሚፈልጉ ብዙ ድምፆች ፣ የአንተን መሐረብ የሚፈልጉ ብዙ ዕንባዎች ፣ የአንተን ሳቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀልዶች ... ገና ብዙ ብዙ አሉ:: ስለዚህ ሰይጣንን አሳፍረው:: እንዲህ በለው :- "ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ" ሚክ. 7:8 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጥቅምት 2016 ዓ.ም. ሜልበርን አውስትራሊያ ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
نمایش همه...
4
ሁሉም_ርኩሳን_ሁሉም_ቅዱሳን_ናቸው_መንፈሳዊ_ትረካ_TEWAHEDO_DOCUMENTARY_EOTC_DOCUMENTARY128k.m4a5.58 MB
ደንገጡሯ_እመቤት_መንፈሳዊ_ትረካ128k.m4a15.60 MB
ከወንድሞች መነኮሳት አንዱ አባ ጳጉሚስን "አባታችን በራእይ ምን እንደ ተመለከትህ ንገረን?" በማለት ጠየቃቸው። አባ ጳጉሚስም "ንጹሕ እና ትሑት የሆነን ሰው ባየህ ጊዜ እርሱ ታላቅ ራእይ ነው። የማይታየውን (ረቂቅ) አምላክ በሚታየውና የእግዚአብሔር መቅደስ በሆነው ሰው ውስጥ ከማየት የሚበልጥ ምን ራእይ አለ?" ሲሉ መለሱለት። ልቡናው ንጹሕ እና ትሑት የሆነን ሰው ማየት ራእይ ከማየት ይበልጣል። ረቂቁ አምላክ በእርሱ በኩል ግልጥ ሆኖ ይታያልና።
نمایش همه...
3👍 1
01:00
Video unavailableShow in Telegram
2.10 MB
የማለዳው ቃለ እግዚአብሔር 1ኛ ሳሙኤል 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹  ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፥ ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛል። ² እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ አምላካችንም ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም። ³ አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ። ⁴ የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችንም በኃይል ታጥቀዋል። ⁵ ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፤ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች። ⁶ እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል። ⁷ እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።  
نمایش همه...
👍 3
ጭንቀት።__አባ_ገብረ_ኪዳን።✝️(48k).mp34.07 MB
"እውነተኛው ክርስትና "#እኔ" ሳይሆን "#እኛ" እያሉ የሚኖሩት ህይወት ነው። ክርስትናም ፍቅር ነው። እንደ አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ እንደነ ቅዱስ ባስልዮስ የድሆች ቁስል ከተሰማህ ረሃባቸው ከራበህ አንተ ክርስትያን ነህ። እስከ መስዋዕትነት ለመድረስ ከችግረኞች ጎን ከቆምክ የሚያስፈልግህ ሁሉ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ካመንክ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ ነህ፡፡" #አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
نمایش همه...
(ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕ. ፭) ---------- ፲፯፤ አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፤ ተመልከት ስድባችንንም እይ። ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ። ፲፰፤ ድሀ አደጎችና አባት የሌለን ሆነናል፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆነዋል። ፲፱፤ አቤቱ፥ አንተ ለዘላለም ትኖራለህ፤ ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው። ፳፤ ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ? ፳፩፤ አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ። ፳፪፤ ነገር ግን ፈጽመህ ጥለኸናል፤ እጅግ ተቈጥተኸናል። ሰላም ለኢትዮጵያ፤ ሰላም ለምድራችን🕊🕊
نمایش همه...