cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ጦብያ

አዕምሮ የአትክልት ስፍራ ነው፤ ሃሳብ ደግሞ ዘር ነው፤ ከፈለግን አበባ ካልፈለግን አረም ልናበቅልበት እንችላለን። ስለዚህም አእምሯችን ጥሩ ዘር እንዲኖረው ️በንባብ እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡ @tobiya2 join ካረጉ ሁሉም አለ

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
595
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

✅🚻 #በህይወት_እስካለህ 🚻✅ ✅ ልትሳሳት ፣ልትወድቅ ትቸላለህ ፣ ✅ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ ፣ ✅ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ፣ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ ፣ ✅ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ ✅ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ። 👉 በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። ❇ መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። ❇ አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ❇ ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ❇ ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል። ❇ ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። 👉 ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! 👉 ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!" #አንድነገር ልንገራችሁ! 💠 በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡዃችሀል 💠 መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑዃችሀል 💠 ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኑዃችሀል 💠 ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑዃችሀል። ጋሽ ስብሃት ገ/እግዘአብሔር @tobiya2 @tobiya2
نمایش همه...
ነገ እንደምንሞት ብናውቅ ዛሬ ምን እናደርግ ነበር? . የዘወትር ጥያቄዬ ነው፡፡‹‹ነገ እንደምሞት ባውቅ ዛሬ ምን ሳደርግ እውል ነበር?›› መልሼው አላውቅም፤ነገ ሞቼ አላውቅምና የመጨረሻው ዛሬዬን በምን ባሳልፈው እንደምረካ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ አስቡት እስቲ! ዛሬ የመጨረሻ ቀናችሁ ነው! ነገ ትሞታላችሁ፤ምን ስታደርጉ ሞታችሁን ትቆዩታላችሁ? . 1. ተክዛችሁ ምንም ሳትሠሩ? 2. ባንክ ሄዳችሁ ያላችሁን ገንዘብ አውጥታችሁ ለሰው ትሠጣላችሁ? 3. ያስቀየማችሁትን ሰው ሁሉ እየዞራችሁ ይቅርታ ትጠይቃላችሁ? . 4. ወደ ሥራ(ትምህርት) ትሄዳላችሁ? ከሌሎች ቀን የተለየ አይደለም በማለት? 5. የሬሳ ሣጥን ዋጋ ታጣራላችሁ? የቀብር ሥነ-ሥርዓታችሁን ታዘጋጃላችሁ? 6. ወይስ ሌላ. . . ምርጫው የትኛውም ይሁን. . .‹‹ነገ እሞታለሁ›› ብሎ መኖር ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል፡፡ተስፋችን የተሰነቀው ከሞት ተጋርዶ ነው፡፡ነገ የሚሞት ሰው ተስፋው ከሞት የሚመነጭ ብቻ ነው፡፡ከሞት በኋላ ጥሩ ነገር ይገጥመኛል እንጂ ያበደረው ገንዘብ ከሥሙ ባንክ የሚጠይቅ አለ ለማለት አይቻልም፡፡ ሁሉም ቀን የመጨረሻ ነው ብዬ አስቤ ስውል የማገኘው ደስታ ልዩ ነው፡፡ይሄን እውነት ከተረዳሁ በኋላ ዛሬን ለማጣጣም ቀለለኝ፡፡ነገ ሰው አልቀጥርም፤ነገን ተማምኜ ቂም አልይዝም፡፡የሕይወት ፍሬ ዛሬ ውስጥ ይገኛል፡፡ @tobiya2
نمایش همه...
ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ ሲጽፉ ምን ያህል ይፈጥናሉ? ============================== ካልፈጠኑ የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ ይመልከቱ። • ሀ ፡ H ሁ ፡Hu ሂ ፡Hዓi ሃ ፡ Ha ሄ ፡Hy ህ ፡He ሆ ፡Ho • ለ ፡L ሉ ፡Lu ሊ፡Li ላ ፡La ሌ፡Ly ል፡Le ሎ፡Lo • ሐ፡Shift +h ሑ፡Shift +hu ሒ፡Shift +hi ሓ፡Shift +ha ሔ፡ Shift + hy ሕ፡Shift +he ሖ፡Shift +ho • መ፡M ሙ፡Mu ሚ፡Mi ማ፡Ma ሜ፡My ም፡Me ሞ፡Mo • ሠ፡Shift + s ሡ፡Shift + su ሢ፡Shift + si ሣ፡Shift+sa ሤ፡Shift + sy ሥ፡Shift + se ሦ፡Shift + so • ረ፡R ሩ፡Ru ሪ፡Ri ራ፡Ra ሬ፡Ry ር፡Re ሮ፡Ro • ሰ፡S ሱ፡Su ሲ፡Si ሳ፡Sa ሴ፡Sy ስ፡Se ሶ፡So • ሸ፡Shift s ሹ፡Shift +su ሺ፡Shift+si ሻ፡Shift+sa ሼ፡Shift +sy ሽ፡Shift+se ሾ፡Shift+so • ቀ፡Q ቁ፡Qu ቂ፡Qi ቃ፡Qa ቄ፡Qy ቅ፡Qe ቆ፡Qo • በ፡B ቡ፡Bu ቢ፡Bi ባ፡Ba ቤ፡By ብ፡Be ቦ፡Bo • ተ፡T ቱ፡Tu ቲ፡Ti ታ፡Ta ቴ፡Ty ት፡Te ቶ፡To • ቸ፡C ቹ፡Cu ቺ፡Ci ቻ፡Ca ቼ፡Cy ች፡Ce ቾ፡Co • ነ፡N ኑ፡Nu ኒ፡Ni ና፡Na ኔ፡Ny ን፡Ne ኖ፡No • ኘ፡Shift +n ኙ፡Shift +nu ኚ፡Shift+ni ኛ፡Shift +na ኜ፡ Shift +ny ኝ፡Shift + ne ኞ፡Shift +no • ከ፡Ka ኩ፡Ku ኪ፡Ki ካ፡Ka ኬ፡Ky ክ፡Ke ኮ፡Ko • ኸ፡capslock+ Shift+ h ኹ፡capslock+Shift+hu ኺ፡ capslock+Shift +hi ኻ፡Capslock+ Shift +ha ኼ፡ Capslock+ Shift +hy ኽ፡Capslock+ Shift+ he ኾ፡Capslock+ Shift + ho • ኀ፡ Capslock + H ኁ፡ Capslock + HU ኂ፡ Capslock + HI ኃ፡ Capslock + HA ኄ፡ Capslock + HY ኅ፡ Capslock + HE ኆ፡ Capslock + HO • አ ፡Capslock X ኡ፡Xu ኢ፡Xi ኣ፡Xa ኤ፡Xy እ፡Xe ኦ፡XoDe • ዐ፡Shift +x ዑ፡Shift +xu ዒ፡Shift +xi ዓ፡Shift +xa ዔ፡ Shift +xy ዕ፡Shift +xe ዖ፡Shift +xo • ወ፡W ዉ፡Wu ዊ፡Wi ዋ፡Wa ዌ፡Wy ው፡ We ዎ፡wo • ዘ፡Z ዙ፡Zu ዚ፡Zi ዛ፡Za ዜ፡Zy ዝ፡Ze ዞ፡Zo • ዠ፡Shift + Z ዡ፡Shift + Zu ዢ፡Shift + Zi ዣ፡Shift +Zaዤ፡Shift + Zy ዥ፡Shift + Ze ዦ፡ Shift + Zo • ፈ፡F ፉ፡Fu ፊ፡Fi ፋ፡Fa ፌ፡Fy ፍ፡Fe ፎ፡Fo • ፐ፡P ፑ፡Pu ፒ፡Pi ፓ፡Pa ፔ፡Py ፕ፡Pe ፖ፡Po • ገ፡G ጉ፡Gu ጊ፡Gi ጋ፡Ga ጌ፡Gy ግ፡Ge ጎ፡Go • ደ፡D ዱ፡Du ዲ፡Di ዳ፡Da ዴ፡Dy ድ፡ ዶ፡Do • ጠ ፡ Shift + t ጡ፡ Shift + tu ጢ፡ Shift + ti ጣ፡ Shift+ta ጤ፡ Shift + ty ጥ፡ Shift + te ጦ፡ Shift + to • ጨ፡ Shift +c ጩ፡Shift +cu ጪ፡Shift +ci ጫ፡Shift+caጬ፡Shift +cy ጭ፡Shift +ce ጮ፡Shift +co • ጸ፡Capslock + t ጹ፡Capslock + tu ጺ፡Capslock + ti ጻ፡Capslock + ta ጼ፡ Capslock + ty ጽ፡Capslock + t ጾ፡Capslock + to • ፀ፡Capslock+ Shift + t ፁ፡Capslock + Shift + tu ፂ፡Capslock + Shift + ti ፃ፡ Capslock + Shift + t ፄ፡Capslock + Shift + ty ፅ፡ Capslock + Shift + te ፆ፡Capslock + Shift + to • ጀ፡J ጁ፡Gu ጂ፡Ji ጃ፡Ga ጄ፡Gy ጅ፡Ge ጆ፡Jo • ቨ፡V ቩ፡Vu ቪ፡Vi ቫ፡Va ቬ፡Vy ቭ፡Ve ቮ፡Vo • ቋ፡Capslock + qwa ቧ፡Capslock + bwa ቷ፡Capslock + twa ኟ፡Capslock + Shift + nwa ቿ፡Capslock + cwa ሟ፡ Capslock + mwa ቷ፡Capslock + twa ጓ፡Capslock + gwa ፏ፡Capslock + fwa ሯ፡Capslock + • rwa ዷ፡Capslock + dwa ቯ፡Capslock + vwa ኋ፡ Capslock + hwa ዟ፡Capslock + zwa ዧ፡Capslock + Shif +zwa ኗ፡Capslock + nwa ሏ፡ Capslock + lwa ኳ፡Capslock + kwa ሷ፡Capslock + swa ጇ፡Capslock + jwa ጧ፡ Capslock + twa የተቸገሩ ሰዎችን በጣም ይጠቅማል፡፡ ሼርርርር @tobiya2
نمایش همه...
🙏ሰላም ለናንተ ይሁን🙏 ✍ @wintay #ጠቃሚ-ምክር በህይወት ጉዞ ላይ አንዳንድ ያላሠብካቸዉ ነገሮች ሊገጥሙ ይችላሉ። ቢያጋጥሙህም ግን እሩጫህን እንዲያደናቅፍብህ አትፈቀድላቸዉ። እንደዉም ለሀይል ና ብርታት እንደሚጨምርልህ አርገህ ቁጠረው። *ምን ግዜም "ነገር ሁሉ ለበጎ ነዉ"የሚለዉን የመፀሀፈ ቅዱስ ቃል አስብ።ይሄን እዉነት መተግበር ስጀምር ምንም አይነት ነገር በህይወትህ ላይ ቢገጥሙህ፤የብረታት እንጂ ተስፋ የመቁረጥ ስሜትን ከህይወትህ ላይ ጠረገህ ታጠፈለህ። ስለዚህ ነገር ሁሉ ለበጎ ነዉ ብለህ አስብ። ፡ ራስህን አትጣል የሚያነሣህ የለምና፤ ጥንካሬህንና አቋምህን አስተካክል በዙሪያህ ዉድቀትህን የሚመኙ አይጠፉምና፤ ለራስህ ቦታ ስጠዉ ያንተዉ ነህና፤ ለራስህ ክብር ስሰጥ ነዉ የሌሎች ክብር የሚገባህ። : በህይወትህ ዘመን ታላቅ ሠዉ መሆን ከፈለክ ሞራልህን ጠብቅ ሞራልህን ሊያሣጣህ የሚችሉትን የአሉታዊ ሰዋች ንግግር አታዳምጥ አንተ የምቶድቀዉ ገንዘብ ሣይኖርህ ሲቀር ሣይሆን ሞራልህ ሲወድቅ ነዉና ሞራልህን ሣታስነካ ጠብቅ።ሞራልህ የወደቀ ቀን ጉልበት ይከዳሀል፣ማገናዘብ ይሣንሀል፣ መራመድ ያቅትሀል በመጨረሻም ትወድቃለህ። : አስተዉል👉አንዳንዴ ችግሮች ለመጣል ወይም ወድቀን እንድንቀር ብቻ ሣይሆን ያላየነዉን የስኬት ጉዞ ሊያሣየን፤ከድክመት ይልቅ ጥንካሬን ሊያስተምሩን ነዉና ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ እራሣችንን አጠንክረን ወደ ፊት እንጓዝ። ፡ ♦ፍፃሜህ እንዲያምር ራስህን አታመፃድቅ ሁሌም ከስህተትህ ለመማር ፍቃደኛ ሁን ጥፋትህን አሜን ብለህ መቀበልህ ክብርህን የሚጎዳብህ አይምሠልህ። ፡ ሰንደል ሢያቃጥሉት ነዉ ሚሸተዉ ስለዚህ አንተም እኔም አንቺም በችግር ብንፈተንም ያ ማለፊያችን ነዉና ታግሰን እናሳልፈዉ ከዛ ጥንካሪያችንን አጠንክረን ወደ ፊት እንጓዝ ያኔ እራያችን እዉን ይሆንና መአዛችን አለምን ያዉዳል። ፡ አስተዉል👉 ህይወት እንዲ ነዉ ፤በቃ! ሁሉንም የኛ ልናደርግ አንችልም! ንፈስን አባሮ እንደ መያዝ ነዉና ሁሉም ነገር የራስህ እንዲሆን ከመድከም ይልቅ ባለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን ሞክር ። ከአንዱ ምእራፍ ወደ ሌላዉ ምእራፍ እንደሚያሸጋግረህም ፈጣሪህም ታመን ።ከዛም በአምላክህ ደስ ይበልህ በእምነት ኑር!!! መልካም ጊዜ ወዳጆቼ♥ @tobiya2 @tobiya2 @tobiya2
نمایش همه...
📌 👉 አደገኛው ስብእና/ Narcissism👈📌 🔥አብዝተን ልንጠነቀቃቸው የሚገባ አስቸጋሪ ማንነት ያላቸው ሰዎች።🔥 📌👉 ሁል ጊዜ ጥፋተኛ እንደሆናችሁ እንድታስቡ የሚያደርጉትን። ለሚሰጧችሁ መጥፎ ምላሽ ተጠያቂው/ዋ አንተ/አንቺ ነሽ የሚሉትን። 📌👉 የእነሱን ችግር እንጂ ፈፅሞ የእናንተን ማዳመጥና መረዳት የማይፈልጉትን። 📌👉 ለጥፋታቸው ሀላፊነት መውሰድ የማይፈልጉ፣ ሁል ጊዜ ትክክል ነኝ ብለው የሚያስቡና ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ምክንያቱ እናንተ እንደሆናችሁ እንዲሰማችሁ የሚያደርጉትን። 📌👉 ጉራቸው ከልክ ያለፈ። ታላቅነታቸውን፣ ችሎታቸውን፣ ተፈላጊነታቸውን እና የበላይነታቸውን ሁሌ የሚናገሩትን። ከእናንተ የወሰዱትን ሀሳብ ጭምር የራሳቸው አድርገው የሚነግሯችሁን። 📌👉 የሰውን ትኩረት ለመሳብ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በእያንዳንዱ ንግግራቸው እኔ....እኔ....እኔ የሚሉትን። 📌👉 ለሌላ ሰው ችሎታ እውቅና የማይሰጡና የሚቀብሩትን። 📌👉 ሌሎችን በጣም የሚያሳንሱ። የእነሱ ትልቅነት የሚጎላው የሌላውን ውድቀት፣ ድክመትና አለመሳካት ሲያወሩ የሚመስላቸውን። 📌👉 ፈፅሞ አክብሮት የላቸውም። ተሳስቻለሁ....ይቅርታ የሚባል ነገር አይታሰብም። ለጥፋታቸው ሌላውን ተጠያቂ በማድረግ የሚያሸማቅቁትን። 📌👉 እነሱ የሚፈልጉትን ሀሳብ እንድትቀበሉና በነሱ ቁጥጥር ስር እንድትሆኑ የሚያደርጉትን። 📌👉ምንም አይነት ፍቅርና ርህራሄ የሌላቸውን። 📌👉 ክፋታቸውን ነቅታችሁ ስትርቋቸው ስማችሁን የሚያጠፉ። ሚስጥርና ድክመታችሁን ለሰው የሚያወሩተን። በሚችሉት ሁሉ ሊጎዷችሁ የሚሞክሩትን። 🔥ይህንን ካነበቡ በኋላ ግንኙነቶችዎን ደግመው ይመርምሩ። ለሌሎችም እንዲጠቅም ሼር ያድርጉ🔥 👉 @tobiya2
نمایش همه...
🚺🚹 በሕይወት ውስጥ አንዴ ከሄዱ የማይመለሱ ሦስት ነገሮች 💁🏿‍♂💁🏿‍♂👉🏾ጊዜ ፣ ቃል እና አጋጣሚ 🚺🚹 በሕይወት ውስጥ ልታጣቸው የማይገቡ ሦስት ነገሮች 💁🏿‍♂💁🏿‍♂👉🏾 ሰላም ፣ ተስፋ እና ታማኝነት 🚺🚹 በሕይወት ውስጥ እጅግ ዋጋ ያላቸው ሦስት ነገሮች 💁🏿‍♂💁🏿‍♂👉🏾ፍቅር ፣ እምነት እና ባልንጀሮች 🚺🚹 በሕይወት ውስጥ እርግጥ ያልሆኑ ሦስት ነገሮች 💁🏿‍♂💁🏿‍♂👉🏾 ሕልም ፣ ስኬት እና እድል 🚺🚹 አንድን ሰው ሰው የሚያደርጉ ሦስት ነገሮች 💁🏿‍♂💁🏿‍♂👉🏾 ጠንክሮ መስራት ፣ ቅንነት እና ጽናት 🚺🚹 በሕይወት ውስጥ አንድን ሰው ሊያጠፉ የሚችሉ ሦስት ነገሮች 💁🏿‍♂💁🏿‍♂👉🏾 ሱስ ፣ ትዕቢት እና ጭንቀት
نمایش همه...
🌀🌀"የተወለድንበት" ወር ስለኛ #ፀባይ ምን ይላል🌀🌀 ✅ #ጥር በጥር ወር የተወለዱ ሰዎች #መንፈሰ__ጠንካራ፣ የማይበገር አመለካከት ያላቸው እና ሰዎች እንዲህ አድርጉ ብለው እንዲመክሯቸው የማይፈልጉ ናቸው። በዚህ ወር የተወለዱ ሰዎች ጎበዝ ነገር ግን ሌሎችን የማይሰሙ አለቃ ይወጣቸዋልም ተብሏል። እነዚህ ሰዎች በተፈጥሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የማስተማር ብቃት ያላቸው ሲሆን፥ ጠንካራ የስራ ስነ ምግባርን የተላበሱ ናቸው። የመሰላቸውን ለመናገር ወደኋላ የማይሉ መሆናቸውም ነው የሚነገረው። ✅ #የካቲት የልደት በአላቸውን በየካቲት ወር የሚያከብሩ ሰዎች ደግሞ #በውይይት___የሚያምኑ፣ አመለካከቱ የወረደ ነው ብለው ከሚገምቱት ሰው ጋር ደግሞ መነጋገር የማይሹ ናቸው ተብሏል። የፈጣሪ አዕምሮ ባለቤቶች፣ በአዳዲስ እና ልዩ የስራ ዘርፎች መሰማራት የሚወዱ፣ ጉብኝት የሚያዘወትሩ፣ ታማኝ እና ሀቀኛ መሆናቸውም ይነገራል። ✅ #መጋቢት በመጋቢት ወር የተወለዱ ሰዎች #አዲስሀሳብለማፍለቅ የተፈጠሩ፣ አይን አፋር እና ጭምት እንደሆኑ ነው መረጃው የሚያመለክተው። የኪነ ጥበብ ስራዎች ራሳቸውን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው ሲሆን፥ ለመመሰጥ ጸጥታን እንደሚመርጡም ይነገራል። እነዚህ ሰዎች ለሰዎች ሩህሩህ፣ ቅን እና መልካም አሳቢ ቢሆኑም የራሳቸውን ሚስጢር እና ግላዊ ነገር ለመደበቅ የሚሞክሩም ናቸው። በራሳቸው አለም የሚኖሩ፣ ሰላማዊ አውድ የሚፈልጉ እና ብዙ ጊዜ ጫጫታ እና ጭንቅንቅ በሚበዛበት ስፍራ የማይገኙ ናቸውም ተብሏል። ✅ #ሚያዚያ ትዕዛዝን በአግባቡ #የማይቀበሉ፣ ነገሮችን በራሳቸው መንገድ የሚመለከቱ እና ሌሎችንም በዚሁ አስተሳሰባቸው ወደራሳቸው ለማምጣት የሚጥሩ ፤ በሚያዚያ ወር ይህቺን አለም የተቀላቀሉ ሰዎች መገለጫ ነው ይላል የናቹራል ሂሊንግ ሜጋዚን ድረ ገፅ ዘገባ። በአቅራቢያቸው ከሚገኝ ማንኛውም አካል ትኩረት እና ፍቅር ይሻሉ፤ በጀብዱ የተሞላ ህይዎት ይፈልጋሉ፤ አንዳንድ ጊዜም ጠንከር ባለ ንግግራቸው ይታወቃሉ። በህዝብ ፊት የሚያደርጉት ነገር ግድ የማይሰጣቸውና ቢጸጸቱ እንኳን ከድርጊታቸው በኋላ መሆኑም ይነገራል። ✅ #ግንቦት ለሁኔታዎች የሚቀያየሩ (የገበታ ውሃ)፣ የዛሬ እና ነገ ፍላጎታቸው የተለያየ፣ ብቸኝነት የሚከብዳቸው እና ጠንካራ #የማህበራዊ ህይወት ያላቸው ናቸው። በዚህ ወር የተወለዱ ሰዎች ስሜታቸውን በደንብ የመግለጽ ብቃት ያላቸው ሲሆን፥ በተለያዩ የእድሜ ክልል ከሚገኙ ሰዎች ጋርም ማውራት ይወዳሉ። በቀላሉ ለድብርት የሚጋለጡ በመሆኑም የተለያዩ የመዝናኛ አማራጮችን ይመለከታሉ ተብሏል። ✅ #ሰኔ በሰኔ ወር ከምቹው የእናታቸው ማህጸን ወደዚህች አለም የተቀላቀሉት ደግሞ ሰዎች የሚወዱት አይን አፋርነት እና ጭምትነትን የተላበሱ ናቸው ይላል ዘገባው። በቀላሉ ስሜታቸው የሚቀያየር እና ለሌሎች ሰዎች ደህንነት አብዝተው የሚጨነቁ መሆናቸውንም መረጃው ያመለክታል። አርቆ የመመልከት እና ሀሳባቸውን ወደ እውን የመቀየር ልዩ ችሎታ እንዳላቸውም ይነገራል። ✅ #ሀምሌ በሀምሌ ወር የተወለዱ ሰዎች በሰኔ ከተወለዱት ጋር ተመሳሳይ ባህሪ እንዳላቸው ነው የሚነገረው። ይሁን እንጂ ወሬ የሚያበዙ፣ ከላይ ከላይ በራስ መተማመን ያላቸው እና ለጋስ መስለው ለመታየት የሚሞክሩ ነገር ግን በውስጣቸው ተንኮል እና ሚስጢር የሚይዙ፤ ህመማቸውን ለሌሎች ሰዎች ከመናገር የሚታቀቡ ናቸው። በመዝናኛ ስፍራ የማይጠፉ፣ በሀይል የተሞሉ እና ጨዋታ አዋቂዎች በመሆናቸውም ሰዎች በአቅራቢያቸው አይጠፉም። ✅ #በነሃሴ ወር የተወለዱ ሰዎችም፦ - ጥልቅ ሀሳብ እና ትንተና በሚፈልጉ ስራዎች #ስኬታማ ናቸው። - ህይወት በደረጃ እና በምክንያት የምትራመድ ነች ብለው ያስባሉ። - ስሜታቸውን ለመግለፅ አይደፍሩም። - ተፈጥሮ ለመሪነት ያጨቻቸው ናቸው። - ልበ ሙሉ እና ሃሳባቸውን በድፍረት ለመናገር ወደኋላ የማይሉ ናቸው። ✅ #በመስከረም የተወለዱ ሰዎች፦ - ሰዎች መልካም ነገር እንዲያደርጉላቸው አብዝተው ይመኛሉ። - ለኩርፊያም ቅርብ ናቸው። - ስራቸው ፍፁም ትክክለኛ እንዲሆን ያስባሉ። - አዳዲስ ሀሳብ አፍላቂ፣ የተረጋጋ ስብእና የተላበሱ እና ሰዎችን ለመርዳት የሚታትሩ ናቸው። ✅ #ጥቅምት - ክርክር አይመቻቸውም፤ በሀሳብ የሚጋፈጣቸው ሲመጣም ከዚህ መውጫ አማራጭ መንገድ ይፈልጋሉ። - ስኬታማ የማህበራዊ ህይወት መመስረት የሚችሉ ሲሆን፥ ጓደኞቻቸውን እጅግ በጣም ይወዳሉ። - ለህይወት ያላቸው አመለካከት አዎንታዊ ነው። - ማራኪ እና ወሬ የሚያበዙ ናቸው። ✅ #ህዳር - በጣም ሚስጢራዊ ናቸው፤ ስሜታቸውን በመደበቅ ተክነዋል። - አይፈሩም፤ ለውጤቱ ሳይጨነቁ ወዳገኙት ሁኔታ ዘው ብለው የመግባት ልማድ አላቸው። - በህይወታቸው የሚፈልጉትን ከማግኘት የሚያግዳቸውን ነገር ያስወግዳሉ። - ከሰዎች ምክር መቀበል አይፈልጉም። ✅ #ታህሳስ - በስራ መወጠር ይፈልጋሉ፤ አንድ ቦታ ላይ ለረጅም ስአት መቀመጥ አይወዱም። - በአጭር ጊዜ የመግባባት ብቃት አላቸው። - ታታሪ እና የተረጋጋ ስብእና ባለቤቶች ናቸው። - በሀይል የተሞሉ እና ሰዎችን በማዝናናት ብቃታቸውም የተመሰከረላቸው ናቸው። ለጓደኛዎ ሼር፣ያድርጉት @tobiya2 @tobiya2 @tobiya2
نمایش همه...
ሰዎችን መሸወድ ቀላል ነው ፡፡ መሸወድ የማትችለው መስተዋት ፊት ቆመህ የምትመለከተውን ሰው ብቻ ነው ፡፡ ከዚህ ሰው ጋር ያለህ ግንኙነት መልካም ካልሆነ ሁሉም የህይወትህ አካል መጥፎ ይሆናል ፡፡ ስኬታማ ህይወት ለመኖር ከራስህ ጋር ያለህን ግንኙነት መልካም ማድረግ ከምንም ነገር ይቀድማል ፡፡ ዕለት ዕለት መስተዋት ተመልከት ፡፡ ከራስህ ጋር በታማኝነት ተወያይ ፡፡ "ስኬታማ እንዳልሆን ያደረጉኝ የግል ጠባዮቼ ምንድን ናቸው ?" ብለህ ራስህን ጠይቅ ፡፡ ባንተ ህሊና ፊት ትክክል ያልሆኑ ነገር ግን ሁልጊዜ የምታደርጋቸውን ነገሮች ለማቆም ወስን ፡፡ የማትኮራበትን ነገር ማድረግ አቁም ፡፡ አሮጌ አንተነትህን አፍርስ ፡፡ ሞያህን ኮትኩተው ፡፡ ንግግር ፣ አረማመድ ፣ አለባበስ ፣ አስተሳሰብ ፣ አሻሻጥ ፣ አጨዋወትህን አሳድገው ፡፡ በተለይ ራስህን በተሰማራህበት የስራ ዘርፍ ቁጥር አንድ አድርገው ፡፡ ከሰው ሁሉ ተማር እንጂ ከሰው ሁሉ አትፎካከር ፡፡ ፍክክሩ ከራስ ጋር ብቻ ይሁን ፡፡ ከሁሉም ሰው እየተማርክ ከራስህ ጋር ስትፎካከር የት ልትደርስ እንደ ምትችል አስበኸዋል ? በየለቱ የሚያድግ ማንነት ትገነባለህ ፡፡ በተሠማራህበት የስራ መስክ ትክ የሌለው ጀግና ትሆናለህ ፡፡ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርግና ራስህ ላይ ብቻ አተኩር :: 👇👇👇JOIN & SHARE👇👇👇 @tobiya2
نمایش همه...
ታሪኩ የሆነው ህንድ ውስጥ ነው። ሰውዬው ነፍሰገዳይ ነው። አንድ ሰው ለመግደል እያሳደደ ነው። ነፍሰገዳዩ ጠላቱን ክፉኛ መቶት አቁስሎታል። ቢሆንም ተሳዳጁ ነፍሱን ለማዳን አምልጦ ይሮጣል። ተሳዳጅ ፍጥነት ጨምሮ ከፊት ይሮጣል። አሳዳጅ ከኋላ ይከተላል። እንደዚህ እየተሳደዱ መስቀለኛ መንገድ ላይ ደረሱ። በዚህን ግዜ ተሳደጅ አንዱን አቅጣጫ ተከትሎ አመለጠ። አሳዳጁ ተሳዳጅ በየትኛው ቅያስ እንደታጠፈ ሳያየው ቀረ። መስቀለኛው መንገድ ላይ ሲደርስ አንድ መነኩሴ በአርምሞ ተውጦ ያገኘዋል። መነኩሴውን ከተመስጦው አናጥቦ "በዚህ በኩል የመጣው ሰው በየት በኩል እንደታጠፈ አይተሃል?" እንግዲህ መነኩሴው ከፍተኛ የንቃት ደረጃ ላይ የደረሰ ነው። ወደ ግራ ነው የታጠፈው ብሎ እውነቱን ከነገረው የግድያ ተባባሪ መሆኑ ነው። የተሳዳጁን ነፍስ ለማትረፍ ወደ ቀኝ ነው የታጠፈው ብሎ ከነገረው ደግሞ ዋሾ መሆኑ ነው። ሁለቱም አማራጮች ለመነኩሴው ተቀባይነት ያላቸው አማራጮች አይደሉም። መነኩሴው ምን ያድርግ? እውነቱን ተናግሮ የግድያ ተባባሪ ይሁን ወይስ ዋሽቶ ነፍስ ያትርፍ?! ከፍተኛ የሞራል ኮምፓስ ላለው ሰው ይህ አጋጣሚ እጅግ ፈታኝ ነው። መነኩሴው ምን እንደወሰነ አይታወቅም። ይሁን እንጂ ከዚያን ግዜ ጀምሮ ብዙ ሰዎች ጥያቄውን ለመመለስ ሞክረዋል። በመነኩሴው ቦታ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ? በተጠያቂዎቹ ቁጥር ያህል እልፍ መልሶች ተሰጥተዋል። አንዳንዶች ከውሸት ይልቅ ነፍስግድያ የከፋ በመሆኑ ዋሽተው ነፍስ እንደሚያድኑ ይናገራሉ። እጅግ አስደናቂ መልስ የሰጠው ግን ጋንዲ ነው። ጋንዲ የመለሰው እንዲህ ብሎ ነበር፦ ለኔ ሁለቱም ታላላቅ እሴቶች ናቸው። እውነትም ሆነ ነፍስ ማዳን ትልቅ ዋጋ አላቸው። አንዱን ለይቼ መምረጥ አልችልም። ስለዚህ መጀመሪያ እኔን ግደለኝና ሰውዬውን በስተግራ እንዲከተለው እነግረዋለሁ" ታዲያ አስደናቂው ነገር ጋንዲ ይህንን ያለው እንዲያው ለአፉ ያህል አይደለም። እውነትን እና የሰላም ትግልን(nonviolence) ኖሮበታል። ሃገሩን ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ለማላቀቅ የተከተለው የሰላም ትግል መንገድን ነው። ጋንዲ ነፍጥ አላነሳም፤ ጥይት አልተኮሰም፤ ሰው አልገደለም። ግን በሰላም እምቢኝ አለ። ታዲያ ይሄ መንገድ ቀላል አይደለም። ጋንዲ የሰላም ትግሉን ተከትሎ ታስሯል፣ የረሃብ አድማ አድርጓል ፤ ተሰቃይቷል። በመጨረሻም በሂንዱ አክራሪ ተገድሏል። ጋንዲ 'በመጀመሪያ እኔን ግደለኝና ሰውዬውን ተከተለው' ሲል ከልቡ ነበር። ጋንዲ ህንዳውያንን ለእንግሊዞች አሳልፎ ከመስጠቱ በፊት ሞትን ተቀብሏል። ጋንዲን የምታደንቀው ይኼኔ ነው። የሚናገሩት እና የሚያደርጉት ተቃራኒ የሆነ ግብዞች በሞሉበት አለም የሚናገሩትን በተግባር የሚኖሩ መንፈሰ ጠንካሮች እጅግ ጥቂቶች ናቸው። @tobiya2 @tobiya2
نمایش همه...
✅🌀 ትማሩበታላችሁ ይነበብ 🌀✅ ✴ በአንድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሚከተለውን ድንቅ ጥናት ተገኘ። ጥናቱም የእንግሊዘኛ ፊደሎችን ከመጀመሪያው አስከ መጨረሻው በቅደም ተከተል አስቀመጠ። "A B C D E F G H I J K L M N O P Q R S T U V W X Y Z" የእነዚህን ፊደላት አሃዛዊ ቅደም ተከተልም አስቀመጠ። "1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26" በመቀጠልም ለእያንዳንዱ ፊደላት፤ በቅድመ ተከተል ቁጥር ሰጣቸው። ለምሳሌ "A = 1"፣ "B = 2" እያለ አስከ "Z = 26" ድረስ አስቀመጠ። በመጨረሻም የቃላት ደረጃን መመዘን ተያያዘው! HARDWORK (H+A+R+D+W+O+R+K) (8+1+18+4+23+15+18+11) = 98% KNOWLEDGE (K+N+O+W+L+E+D+G+E) (11+14+15+23+12+5+4+7+5) = 96% LOVE (L+O+V+E) (12+15+22+5) = 54% (L+U+C+K) = 47% በዚህ መሰረት ከላይ የጠቀስናቸው ቃላት አንዳቸውም 100% ሊሰጡ አንደማይችሉ አስቀመጠ። ታዲያ 100% ሊሰጠን የሚችለው ቃል ምን ይሆን? ብር ይሆን? (M+O+N+E+Y) (13+15+14+5+25) = 72% አይደለም ምን አልባት አመራርነት ይሁን? (L+E+A+D+E+R+S+H+I+P) (12+5+1+4+5+18+19+8+9+16) = 97% አሁንም አይደለም! ለሁሉም ነገሮች መፍትሄ አለው። አስተሳሰባችንን፣ አካሄዳችንን እና አኳኋናችንን ስንቀይር ይቀየራል። ስለዚህ #አመለካከት የሚለውን ቃል ሞከረ። (A+T+T+I+T+U+D+E) (1+20+20+9+20+21+4+5) = 100% ስለዚህ 100% ለውጥ ሊያመጣልን የሚችለው የአስተሳሰብ ለውጥ (አመለካከት) መሆኑን አረጋገጠ። ሼርርርር @tobiya2
نمایش همه...