cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ህይወት ጥበብ ፍልስፍና

Qዳማዊw ነው ሰላምታዬ ✌ ማንኛውንም የስዕል ስራ ለመግዛት ወይም ለማሳል ከፈለጉ ይደውሉ 👇👇👇👇 0935647014 አላማችንሰአሊዋችንማበረታት Lift ባለማለት ተባበሩን🙏 @zolaarts

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
Advertising posts
182مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

☢Take time!! by DEMIS SEIFU  🔸“Give me six hours to chop down a tree and I will spend the first four sharpening the axe.” ― Abraham Lincoln 🔷እየሄዱ መቆም የመሄድን አቅም መጨመር ነው… መዘግየት አይደለም… እያረፉ መጓዝ የብልህነት ከፍታ ነው … ስንፍና አይደለም… ‘በየመሃሉ’ ማለት መታደስ ነው… ኋላ መቅረት አይደለም… ለረጅም ሰዓት ያሽከረከረ ሹፌር ጥጉን ይዞ ‘እረፍት’ የሚወስደው የበለጠ መጓዝ እንዲችል ነው… የጋለው ሞተር ቀዝቅዞ አቅም መግዛት አለበት… የዛለ ክንዱም በርትቶ መሪ ማዞር አለበት… በየሰከንዱ በምንስበው አየር የመታደስ ያህል ነው – ‘በየመሃሉ’ ማለት… አንዴ በሳቡት አየር ዕድሜ ልክ ልኑር አይባልምና… 🔷ሰውየው በአንድ ድርጅት ውስጥ በእንጨት ቆራጭነት ስራ አምስት ዓመት ያህል ቢያገለግልም ሁሌም የደመወዝ እድገት እንደናፈቀው ነው… ከእርሱ በኋላ የተቀጠሩ ሰራተኞች ዓመት ሳይደፍናቸው የክፍያ መሻሻል አይተዋል… እናም ሰውየው ዘወትር ‘ለምን?’ ይላል… የድርጅቱ ኃላፊ ‘እንደምታውቀው ድርጅታችን ውጤት ተኮር ነው… ብዙ የሰራ ብዙ ያገኛል… አንተን እንደማይህ የዛሬ አምስት ዓመት ትቆርጥ የነበረውን እንጨት ነው ዛሬም የምትቆርጠው… ይሄ ደግሞ ላንተ ለውጥም ሆነ ለድርጅቱ እድገት አንዳች አይፈይድም’ ብሎታል… እናም ይለፋል… ይጥራል… ይግራል… ጠብ የሚል ነገር የለም… 🔶በድጋሚ አለቃውን አግኝቶ ጠየቀ… ‘እስኪ ካንተ በኋላ የተቀጠሩትን ቆራጮች ተመልከታቸው… በየጊዜው መሻሻል እያሳዩ ነው… ለምን እነርሱን አታማክራቸውም… ለምሳሌ እከሌን ማናገር ትችላለህ… ምናልባት እኔና አንተ የማናውቀውን ምስጢር ይጠቁምህ ይሆናል’… ሲል መለሰለት… 🔹ሰውየው የተጠቆመው ሰው ዘንድ ሄዶ ችግሩን አስረዳው… ባለሙያውም ሁኔታውን በደንብ ካጤነ በኋላ ‘ለመሆኑ መጥረቢያህን ከሳልከው ስንት ጊዜ ሆነህ?’ ሲል ጠየቀው… እንጨት ቆራጩ እንደ ማሰላሰል አለ… በጣም ቆይቶ ነበር… በጣም… ባለሙያው አከለለት… ‘ይኸውልህ.. እኔ በየጊዜው የተወሰኑ የእንጨት ክምሮችን ከቆረጥኩ በኋላ መጥረቢያዬን እሞርዳለሁ… በዚህም ምክንያት ብዙ እንጨት መቁረጥ ችያለሁ’ አለው… ሰውየው ለረጅም ጊዜ የተደበቀበት የስኬት ምስጢር ለካ ‘በየመሃሉ’ ማለት ነው… 🔸ብዙዎቹ መጥረቢያዎቻችን ደንዘዋል… ችግሩ ዛሬም በትናንት አቅማቸው እንዲያገለግሉን እየጠበቅን ነው… ነጋ ጠባ በሚቆርጡት እንጨት ጥርሶቻቸው ተሸራርፎ አልቋል… ችርችፍ ብሏል… ዶልዱሟል… 🔺ላሞችህ ወተት እንዲሰጡህ የምትጠብቀው መመገብ እንዳለብህ ዘንግተህ ከሆነ ችግር አለ… የገባው ነው የሚወጣው .. መልኩን ከመቀየሩ ውጪ… የአገልግሎት ማሻሻያ ሳያደርግ ከፍተኛ ገቢ የሚጠብቅ ድርጅት… ሳያነብ ልጨኛ ጽሑፍ መፃፍ የሚፈልግ ‘ደራሲ’… በአግባቡ ሳያስተምር ጎበዝ ተማሪዎችን ማየት የሚናፍቅ መምህር… የድርሻውን ሳይወጣ ያደገች ሃገር ማየት የሚሻ ሕዝብ… የሚጠበቅበትን ሳያደርግ የሚጠበቅብህን የሚጠይቅ መንግስት… ለአርዓያነት ሳይበቃ ‘የተመረቀ ልጅ’ የሚጠብቅ ቤተሰብ… ሁሉም የደነዘ መጥረቢያቸውን አስተውለውት አያውቁም… የአንዳንዶቹ እንዲያውም ዝገት ጀምሮታል… 🔺ከድግሪህ በኋላ ማንበብ ካቆምክ ድግሪህ እርባን የለውም… ዶክትሬትም ቢሆን… ከሽልማት በኋላ መስራት ካቆምክ መሸለምህ ከንቱ ነው… ቅዱስም ብትሆን… ዜኖች እንዲህ ይላሉ… “Before enlightenment, chop wood, carry water. After enlightenment, chop wood, carry water.” 🔸መጥረቢያህን ሳል… በመቁረጥ ላይ ብቻ እንደተመሰጥክ ያስታውቃል… ስትሞርድ ስለት ብቻ አይደለም የምትጨምረው… የሆነ የምታራግፈው ቆሻሻም አለ… ውጋጅ ነገር… አሮጌ አስተሳሰብ… ጠማማ ገጽታ… የተንሸዋረረ እይታ… ግድግዳ ኩራት… 🔹ለመሞረድ የምታጠፋው ጊዜ የባከነ አይደለም… ነዳጅ እንደመጨመር ነው… የሆነ ጊዜ ድንገት ቀጥ ትላለህ… ምናልባት ያኔ ለመሞረድ ሁነኛ ጊዜህ አይሆን ይሆናል… እናም መቆሚያህ እንዳያጥር መቋቋሚያህን አጽና… 🔹A woodsman once asked “what would you do if you had just five minutes to chop down a tree?’… He answered, ‘I would spend the first two & a half minutes sharpening my axe.”… 👇MORAL OF THE STORY👇 📍 Let us take a few minutes to sharpen our perspective. ባላችሁበት ሰላም!!🙏 🔹🔸🔹🔸🔹🔹🔸🔹🔸🔹 ♦️ምርጫችሁ ስለሆንን ስናመሰግኖት ከልብ ነው !!! @zolaarts
نمایش همه...
#ለመጥፎ_ነገሮች_ራስህን_አዘጋጅ “ከእንቅልፍህ ስትነቃ እና አይንህን ስትገልጥ ለራስህ እንዲህ በለው፡- መጨናነቅን፣ ምስጋና ቢስነትን፣ ውሸቶችን፣ ቅናት እና ቁጣን እፋለማቸዋለሁ። ሁሉም ሰዎች በእነዚህ ህመሞች ይሰቃያሉ፤ ምክንያቱም በመልካም እና በክፉ መሃል አለዩምና። የመልካምን ውበት ተመልክቻለሁ እና የመጥፎነትም ማስጠላት አውቃለሁ፤ መጥፎ አድራጊዎች ከእኔ አይርቁም፤ ሆኖም ምንም ጉዳት አያደርጉብኝም ወይም በእነሱ አስቀያሚነት ውስጥ ራሴን አልዘፍቅም - እነሱንም አልጠላቸው ወይም በእነሱ ላይ አልቆጣም።” ማርከስ_አውሬሊየስ ልክ እንደ ግድግዳ ሰዓት ሁሉ አንተም ፍጹም እና እርግጠኛ ልትሆን ትችላለህ፤ ሆኖም ዛሬ ላይ ከአስቸጋሪ ሰዎች ጋር መስማማት ትችላለህ? ጥያቄውም ተዘጋጅተህበታል? ነው፡፡ይህም ልምምድ በአስራ አምስተኛው ክፍለዘመን የነበረው ጸሐፊ ኒኮላስ ቻምፎርት ሃሳብ ጋር ይወስደናል፤ “ሁል ጊዜ በጥዋት እንቁራሪት ዋጥ” እናም ቀኑን ሙሉ ከዚህ የባሰ አስቀያሚ ነገር ሳይገጥምህ ያልፋል። ምናልባትም ይህን ቃል እንዳለ ባትረዳው መልካም ይሆናል - ሰዎች ራስ ወዳድ እና ስለሌሎች ስሜት ግድ የሌላቸው ይሆናሉ፤ ያንተ እንቁራሪቶችም እነዚህ ሰዎች ናቸው - ቀኑን ሙሉ ስለነሱ ስትጨነቅ መዋልም የለብህም። ማርከስም “እነሱንም አልጠላቸው ወይም በእነሱ ላይ አልቆጣም።” ይለናል - የዚህም ትርጓሜው ያጋጠሙህን ሰዎች ሁሉ ክፋታቸውን መጻፍ የለብህም ይሆናል። እናም ምናልባት ከቤትህ ስትወጣ የምትሸከምበትን ጫንቃ ካሰፋህ፣ ቀንህን በትዕግስት፣ በይቅርታ እና በመረዳት ውስጥ ታሳልፋለህ። ምንጭ፦አፒክቲተስ @zolaarts
نمایش همه...
"ትርጉም አልባነት Absurdism" Absurdism የሰው ልጅ ህይወት በተቃርኖ የተሞላች ናት ይላል። absurd የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች ለህይወት ፍቺ ለመስጠት ባላቸው ጥልቅ ፍላጎትና ህይወት ደግሞ በተፈጥሮ ትርጉም አልባ በመሆኗ የሚፈጠር ተቃርኖን ነው። ህይወት ትርጉም የለሽ ነች ይላል absurdism! በህይወት ውስጥ ትርጉም ለማግኘት የምትሯሯጠው ነገር መጨረሻው አያምርም ይልሃል! ምክንያቱም irrational በሆነ ዓለም ውስጥ rational ለመሆን መጣር ከንቱ ልፋት ነው።ስለዚህ absurdity ምክንያታዊ ባልሆነ ዓለም ውስጥ የሚደረግ የሰዎችን ከንቱ ልፋትን ያሳያል።መፍትሔው ምንድን ነው? 1.escaping the existence or suicide አልበርት ካማስ የተባለው የእዚህ ፍልስፍና አባት ምን ይላል!የዓለምን እውነታ መቀበል ወይም ተቀብሎ መኖር painful ነው ስለዚህ ራስን ማጥፋት መፍትሔ ሊሆን ይችላል! 2.ReligiousSpiritual world. መንፈሳዊ ዓለም ለራስ መፍጠር ሌላው መፍትሔ ነው።እንደ ሶረን ኬርኬጋርድ ፍልስፍና በውስጣችን ውስጥ የሚፈጠረውን የትርጉም ውዝግብ ምክንያቱንና ምንጩን externalize ማድረግ መፍትሔ ነው ይላል። ስለዚህ ይላል ፈጣሪህን አዕምሮህ ውስጥ ፍጠረው: እውነትን ከዓለም አንፃር reconstruct አድርገው።ስለዚህ የዓለምን ኢ-ምክንያታዊነት እንደመለኮታዊ እውነት ውሰዳቸው! ስለዚህ ምድራዊ ተቃርኖዎች ሰማያዊ ፍትህና እውነት አላቸው ብለህ ታምናለህ! 3.Acceptance of the Absurd. ሌላው መፍትሔ የህይወትን ትርጉም እንደመጣችበት ውዝግብ ትቀበላለህ! ትርጉም የሌለህ ሰው ትሆናለህ! ከነባራዊ እውነት ጋር አትጋጭም! እዚህ መፍትሔው ዛሬን ብቻ ማየት የሕይወትን ፍቺ አለመፈለግ ነው፡፡ በእናንተ ምልከታ ህይወት ይህን ያክል ትርጉም አልባ ናት? አለምስ ከሰዋዊ ማንነት ጋር ያላት paradox ምንድን ነው? ስለ አልበርት ካምስ ብዙ የምላቹ ነገር አለ ! @Philosphyloves
نمایش همه...
_ሁሉም ሰው የሚወድህ ስትሞት ብቻ ነው፡፡ በህይወት እያለህ የሚወድህም የሚጠላህም ብዙ ሰው ነው፡፡ ስትሞት ግን ያለልዩነት ሁሉም ሰው ይወድሃል፡፡ ለምንድን ነው? ለዚህ ብዙ የስነ -ልቦና ትንታኔዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ለእኔ ለጊዜው የገባኝ ግን ሁለት ነገር ነው። 1) ስትሞት ጠላት መሆን አትችልም። ማለት ከሞትክ የእነሱን ህይወት አትጋፋም ማለት ነው፡፡ ስትኖር ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ትፈጥራለህ፡፡ በዚህ የተነሳ የሚወድህም የሚጠላህም ይኖራል። ስትሞት ግን ምንም ተፅዕኖ መፍጠር አትችልም። ሰዎች ስትሞት ሁሉም ሰው የሚወዱህ ተፅዕኖ መፍጠር ስለማትችል ለማንም ሰው ጠላ። መሆን እንደማትችል ስለሚረዱ ነው።በዚህ የተነሳ ከሞትክ ያለ ልዩነት ሁሉም ሰብ ይወድሃል።ስለዚህ ስትሞት ሁሉም ሰው የሚወድህ እነሱን እንደማትጉዳቸው ስለሚያውቁ ይሆናል፡፡ የማትጎዳቸው ከሆነ ለምን ይጠሉሃል? 2) ስትሞት ሁሉም ሰው የሚወድህ አንተ ሬሳ ውስጥ ራሱን ሞቶ ስለሚያየው ነው ሁሉም ሰው ራሱን ይወዳል፡፡ ራሱን ስለሚወድ አንተ ስትሞት ስለራሱ ሞት ያስባል። የዚህ ጊዜ የሚወደው ራሱን አንተ ሬሳ ውስጥ ያየዋል። ስትሞት ሁሉም የሚወድነ የሚወደውን ራሱን አንተ ሞት ውስጥ ሞቶ ስለሚያየው ነው፡፡ ስለዚህ ስትሞት ሁሉ የሚወድህ ራሱን ስለሚወድ ነው፡፡ ሌላ ትንታኔ ይኖረው አይኖረው አላውቅም። ለኔም በጣም የገረመኝ ግን ይህ ነው፡፡ሁሉም ሰው ያለልዩነት የሚወድህ ስትሞት ብቻ ነው፡፡ ለምንድነው? @Philosphyloves @Philosphyloves
نمایش همه...
ከተሰቃየህ የስቃይህ ምክንያት አንተ ነህ::ሀሴት ከተሰማህ የሀሴትህ ምክንያት እራስህ ነህ:: ማንም ተጠያቂ አይደለም:: አንተ እና አንተ ብቻ ነህ :: ተጠያቂ !! አንተ የራስህ ገነት እንዲሁም ገሀነም ነህ:: ~ኦሾ 💚ውብ ምሽት!!
نمایش همه...
ለውጥ - በ‹ጊዜ» እና «ዘላለማዊነት መካከል የተሰነቀረ ተቃርኖ ? እነሆ ለለውጥ ያህል ራሱን «ለውጥ» /የማይለወጥስ ምን አለ? ከፈጣሪ በስተቀር ! እሱ እንደማይለወጥ እርግጠኛ ብንሆንም «ይለወጣል» የሚሉንን ተከራካሪዎች ሐሣብ ከማቅረብ ደግሞ ወደኋላ አንልም:: እንኳን በዘላለም ውስጥ ለሚኖረው ለ«እሱ» ይቅርና እኛ እንኳን በዚህች አጭር የዕድሜ ዘመናችን ስንቱን እንለውጣለን፤ እንለወጣለንም! «ለውጥ» አቻ ትርጉም ሲፈልጉለት «እንቅስቃሴ፧ ከነበረው ውስጥ አዲስ ነገር መፍጠር፤ ወደመሆን መምጣት (ማምጣት) እንዲሁም ማለፍ ወይም መለየት» በማለት ያስቀምጡልናል:: «ለውጥ»ን እንግዲህ በዚህ መነጽር ስንመለከተው በቋሚና በሚንቀሳቀስ ነገር መካከል የሚገኝ ክስተት ይሆብናል:: በ«ጊዜ» እና «ዘላለማዊነት» መሀከል የተሰነቀረ ተቃርኖም ነው:: የሚለወጥ ነገር ሁሉ በ«ጊዜ» /time/ ሲገለፅ፤ የማይለወጠው ነገር ደግሞ (የማይለወጥ ነገር ካላ) እሱን ዘላለማዊ eternal/ እንለዋለን ። ወደ አሳብያኑ የ«ለውጥ» ምንነት ለመዝለቅ ደግሞ ቀጣይዋን ዕድሜ ጠገብ ትርጉም እናስቀድም፡- «ለውጥ» “ይሉናል ጥንታዊ አሳብያን፡- «የቀደመውና የኋለኛው መለኪያ ነች አንደአሳብያኑ እምነት በጊዜ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ነገር “ይለወጥ ዘንድ የግድ ይሆናል:: ይኸ ማለት ግን የሚኖር ነገር ሁሉ ይለወጣል ማለት እንዳልሆነ ደግሞ ይነግሩንና በአንድ የዘመን ሂደት ሳይለወጥ «ፀንቶ» የቆየን ነገር እንደማይለወጥ ማሰብ ይቻላል ባይ ናቸው:: ዞሮ ዞሮ የለውጥ ወይም አለመለወጥ መለኪያው ጊዜ ከሆነ «ለውጥ» በራሱ ከጥንት እስከዛሬ የፍልስፍናው ዓለም በቂ ምላሽ ያጠረው አስቸጋሪ ጥያቄ ሆኖ እንዲዘልቅ አድርጐታል፡፡ የጥንት የግሪክ ፈላስፎች በ«ለውጥ» ጉዳይ እጅግ አጥብቀው የሚያስቡና የሚከራከሩ ነበሩ፡፡ እንዲያውም ለውጥን እንደአንድ የፍልስፍና ዘርፍ የሚያጠኑ ተማሪዎች በዚያ ዘመን የነበሩ ሲሆን መጠሪያቸውም «ፊዚስት» ይባል ነበር፡፡ የፊዚክስ የቀድሞ ትርጓሜም የእንቅስቃሴ በዓለም የምናያቸው ነገሮች እንቅስቃሴና ለውጥ) ጥናት እንደነበር እናውቅ ዘንድ እግረ መንገድ ይነግሩናል:: የ«ለውጥ» /Change/ ክርክር ከጥንቱ ዘመን ፍልስፍና በመነሳት ስንመለከት ሁለት ተፃራሪ ጐራዎችን የፈጠሩ ታላላቅ አሳብያንን ከግሪክ እናገኛለን፡- ሄራክሊተስ እና ፓርሜኒደስ፡፡ ሄራክሊተስ «ማንኛውም ነገር ይለወጣል» የሚል የአንድ ፅንፍ አስተሳሰብ ይዞ ሲያራምድ ፤ ፓርሜኒደስ ደግሞ «ማንኛውም ነገር አይለወጥም፤ ባለበት የፀና ነው» የሚል ሌላ ፅንፍ ይዞ ሲያራምድ ኖሯል:: ይኸ ክርክርና ልዩነት እስከዘመናችን ፈላስፎች ድረስ የቀጠለ ቢሆንም እንደእነዚህ ሁለት የጥንት የግሪክ ፈላስፎች አስተሳሰብ ግን አንድን ፅንፍ በወጉ ይዞ ሲያራምድ አልተገኘም:: ሄራክሊተስ የማይለወጥ ነገር የለም» የሚለውን አስተሳሰቡን ማረጋገጫ ሊያቀርብልን:- ማንም ሰው አንድ ወንዝ ላይ ሁለት ጊዜ ዘሎ መግባት አይችልም» በማለት ነበር፡፡ እንዴት? የሚል ጠያቂ ሲነሳበት:- «መጀመሪያ የገባበት ወንዝ ውሃ አልፎ ሄዷልና በድጋሚ ዘሎ ሲገባ የሚገባው አዲስ ውሃ ውስጥ ነው» ይለዋል፡፡ ይቀጥላል ጥበብ ከ ጲላጦስ @zolaarts
نمایش همه...
በዶ/ር ኤልያስ ገብሩ ''አርምሞ"  ©ከመጽሐፉ የውስጥ ገጾች የተወሰዱ፦ - የእያንዳንዳችን የውስጥ ዓለም ሲያምር እንደ ህዝብ ውጫዊ  ህይወታችንም ይዋባል። ውስጣቸው የተረበሹ ሰዎች ግን ህዝብና ሀገርን ይረብሻሉ። - ሰው በጥሞና ተቀምጦ አእምሮውን ሲያዋቅር፣ ነፍሱን ከሀልዮቱ ሲያስታርቅ ከራሱ አልፎ በዙሪያው ባሉ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ያደርጋል። - ውስጣቸው የሰለጠነ፣ እግረ-ህሊናቸው የበረታ፣ በአርምሞ የመጠቁ ዜጎች ሲበዙ፣ ያኔ ሀገር ሰላምና አንድነቷ የእውነት ይፀናል።
نمایش همه...