cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ኖኅ Book Delivery

The first and the only book delivery service in Ethiopia. Order books all over the world with fair price & fast delivery Free delivery ለአስተያየትና መፅሐፎችን ለማዘዝ ከታች ባሉት አድራሻ መልዕክት ያስቀምጡልን @Noahbook7 "ማንበብ ፋሽን ነው" Join us @noahbookdelivery

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
14 991
مشترکین
-524 ساعت
-37 روز
+3430 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

1. Eat, Pray, Love - Elizabeth Gilbert Price 950 2. Water for Elephants - Sara Gruen Price 850 birr 3. The Secret Life of Bees - Sue Monk Kidd Price 650 Birr 4. A very Nice Girl - Imogen Crimp Price 850 birr 5. Origin - Dan Brown Hardcover Price 1450 birr 6. The Story of a Beautiful Girl - Rachel Simon Price 750 Birr 7. The Art of Racing in the Rain -  Garth Stein Price 850 birr 8. Summerland - Elin Hilderbrand Price 850 birr 9. The Paris Seamstress - Natasha Lester Price 850 Birr 10. Milky and Honey - rupi kaur Price 850 Birr ማሳሰቢያ ፦ በorder መደራረብ  ምክንያት እና በክረምቱ ዝናብ order ሲዘገይ እና ለቀጣይ ሲደረግ ቅር እንዳትሰኙ ስንል ይቅርታ እንጠይቃለን። 🙏 ✅✅✅ መጽሐፎቹን በምታዙበት ወቅት እነዚህን በማድረግ ይተባበሩን 📚ማዘዝ የፈለጉትን መጽሐፎች 📞ስልክ ቁጥር እና 📍አድራሻ ይላኩልን። ⛵️ Free Delivery ለማዘዝ 👇🏾   @Noahbook7  0939115238   "ማንበብ ፋሽን ነው።" Join us @noahbookdelivery
نمایش همه...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
አክስቴ: "መልኬ በቃኝ ብሎ ነው"እያለች ታሽሟጥጠኛለች። የወጣልኝ አጎዶ። አባባ: "ጨዋ ጨዋነት ነው" ይላሉ ጋሸ: "ትዕቢት ፤ ትዕቢት ነው" ይላል ጓደኛዬ: "መደበር ይወዳል ፣ ደባሪ ነው"ይላል የጓደኛዬ ሴት ጓደኛ : ኩራት። ኩራት ነው። ሲበጣጠስ" ትላለች የጋሸ ሚስት: ፍርሐት ፣ ፍርሐቱ ነው" ትላለች ብቻ ሺህ ትርጉም ይሰጠዋል።    (ህማማትና በገና) በሚዛን አለመውደዴ አሰደበኝ። ምን ላድርግ ድክመቴ ነው። ድክመቴ ነው ገመናዬ ነው። ብታፍርብኝም አይገርመኝም። ሁላችንም ገመና አለን አየህ። ንፁህ ሰው የለም። የተለያየ ስህተት የሚያሰራ በለስ በልተናል። ሰው ነንና። አባትህ በለሴ ነበር መሰል!  ስትኖር ያጋጥምሀል።    (እቴሜቴ የሎሚ ሽታ) ‹‹...የሚከብድ ዘመን ነው...ባሏ ቤቷን ትቶላት ቢሄድም ሌላም ሰጥቷት ነው...የተቀዳደደ ውበቷን…ማድያቷን…….በሲጋራ የዛገ ጥርሷን…ማደግ በቅቶት እንደ ጥፍር የኾነው ጸጉሯን…የቀጠነ ጡንቻ መኾን የጀመረ ባቷን……በጀርባዋ ስትንጋለል ወደ ብብቶቿ የሚንሸራተቱ ጡቶቿን...እነኚህን ሁሉ 'ራስሽ ያዥያቸው' ብሏት ነው የሄደው……›› . . . ‹‹ከማግባቷ ሁለት ዓመት በፊት ሰለሞን የሰጣት ማስታዎሻ ነበር…….ከካች አምና እስከ ዘንድሮ ግን የስክሪብቶ ክዳን የሰጣት የለም…..››     (አለንጋና ምስር) --- መልካም ልደት ለአዳም ረታ! One of the prolific writers. - ⛴⛴⛴ "ማንበብ ፋሽን ነው።" Join us @noahbookdelivery
نمایش همه...
9
መልካም ልደት🙏🥰🙏 አዳም ረታ በ1950 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ። በትምህርት አለም - በጂኦግራፊ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀብሏል። ሁለተኛ (የማስተርስ) ዲግሪውን ደግሞ በውጭ ሀገር አግኝቷል። የሚፅፈው በአብዛኛው ልቦለዶችን ቢሆንም ግጥሞችንም ይፅፋል። በተለያዩ ጊዜያት ግጥሞቹ በተለያዩ መፅሔቶች ላይ ታትመዋል። ያልታተሙ ግጥሞችም አሉት። ከተደራሲው ጋር የተዋወቀበት እና በኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ ተከታታዮችና አንባቢዎች ልብ ውስጥ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጠበት “አባ ደፋር እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች” በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት የታተመው በ1977 ዓ.ም ነው። (በዚህ መድብል ውስጥ አራት ስራዎችን አዋጥቷል፡ “ድብድብ”፣ “ዕብዱ ሺበሺ”፣ “ሲሮኮ” እና “ሲፊንክስ”) ]ሜጋ አሳታሚ ድርጅት በ1990 ዓ.ም ባሳተመው “ጭጋግና ጠል” የአጭር ታሪኮች ስብስብ “ዘላን” የተባለው ልቦለዱ ታትሟል። እነዚህ ሁለቱ ከሌሎች ደራሲዎች ስራዎች ጋር የታተሙለት ስለሆነ እንደ ወጥ ሳይቆጠሩ ነው ከላይ የሰፈረው የተባለው። በ1981 ዓ.ም በኩራዝ አሳታሚ የታተመው “ማህሌት” የደራሲው የመጀመሪያ ወጥ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መፅሀፍ ነው። በሻማ ቡክስ በ1997 ዓ.ም የታተመው “ግራጫ ቃጭሎች” እንደ ብሉይ (classic) ሥራ ሊታይ የሚችልና የደራሲው ልዩ ብቃት የታየበት ወጥ ረጅም ልብወለድ ነው። በ2001 ዓ.ም ሁለት ልዩ ስራዎች ይዞ የቀረበው አዳም፡ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ የሆነው “አለንጋና ምስር” እና እርስ በርሳቸው በቀጭን የታሪክ ክር የሚገናኙ ልብወለዶች (ኖቬላዎች) ያካተተው “እቴሜቴ ሎሚ ሽታ” ለአንባቢያን አበርክቷል። ይህ የአጻጻፍ ስልቱ ሕጽናዊነት የሚባል ሲሆን ደራሲው በሌሎቹ መጻሕፍቱም ውስጥ በስፋት ተጠቅሞበታል፡፡ በቀጠሉት ሦስት ዓመታት በየዓመቱ አንዳንድ መፅሐፍ ለአንባቢያ ያደረሰ ሲሆን በ2002 ዓ.ም “ከሰማይ የወረደ ፍርፍር”፣ በ2003 ዓ.ም “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” እና በ2004 ዓ.ም “ሕማማት እና በገና” ታትመው ለንባብ በቅተዋል። “ከሰማይ የወረደ ፍርፍር” በተሰኘው መፅሀፉ ድንቅ የፋንታሲ (“ፈንጠዚያ”) ሥራዎች የተካተቱ ሲሆን በ”ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” ለመጀመሪያ ጊዜ መቼቱን ከሀገር ውጭ በማድረግ የውጭውን ሕይወት በስሱ የዳሰሰ ሲሆን ከሌሎቹ ስራዎቹ በተለየ መልኩ ስለሀገራችን ፖለቲካ ወጣ-ገባ መንገድ በታዛቢ አይን ምልከታው፣ ትውስታውን … አስፍሯል፡፡ ሕማማትና በገና የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ ሲሆን ለየት ያለ ቅርፅ ያላቸው አንዳንድ ልቦለዶች ተካተውበታል። ፍልስፍናውና ስልቱ ሕፅናዊነት በሚል ስያሜው ይፋ ሆኗል። አዳም ረታ በተለየ የአፃፃፍ ስልቱ እና በስራዎቹ ጥልቀት በሃያስያን ዘንድ አዎንታዊ ሂስ እና ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል። ጥቂቱን ለመጥቀስ ያህል… 👉🏾“…አዳም ረታ ታዋቂ ደራሲያን ከሆኑት ከሀዲስ አለማየሁ፣ በዓሉ ግርማ፣ ዳኛቸው ወርቁ፣ ፀጋይ ገብረመድህን… ጋራ መመደብ የሚችል ነው ሊባል ይችላል…” Aklilu Dessalegn Adam Reta as a Literary Existentialist: Textual and Descriptive Criticism (2010) 👉🏾…ዳኛቸው ወርቁ በ“አደፍርስ” የኢፒሶዲክ ሕግጋትን አጋምሶ ለማስተዋወቅ ከሞከረ ወዲህ በአማርኛ ሥነ-ጽሑፍ በኢፒሶዲክ ተሟልቶ የተገኘ ድርሰት “ግራጫ ቃጭሎች” ነው። … “ግራጫ ቃጭሎች” ከገፀ-ባህሪው አካልና ሥነ-ልቡና አሳሳል አልፈን ድንቅ ዓላማውን፣ ቋንቋውንና የሕይወት አተረጓጎሙን ስንመለከት የአዳም ረታ እውቀትና ልምድ ጠንከር - ጠጠር ብሎ በመዝገቡ በኩል ሲያስተጋባ ነው የምንመለከተው።… ዓለማየሁ ገላጋይ - ደራሲና ጋዜጠኛ ኢሜጅ መጽሔት፣ ቅጽ 1፣ ቁጥር 02፣ ግንቦት 1998 ምንጭ፦ 👉🏾ጭጋግና ጠል ገፅ 108 አአ ሜጋ አሳታሚ ድርጅት 1990 ዓ.ም 👉🏾አዲስ አድማስ ጋዜጣ 🚢🚢🚢 "ማንበብ ፋሽን ነው።" join us @noahbookdelivery
نمایش همه...
7👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ ምስል የአለም የምንም ጊዜ ድንቅ ቡጢኛ መሃመድ አሊ የህጻንነት እና የእርጅናው ፎቶ ነው በእነዚህ መካከል ደግሞ ፈርጣማው: ቡጢው ከመሬት የሚቀላቅል: በዝረራ ካልጣለ በቀር የማይዋጥለት: ነውጠኛው መሃመድ አሊ አለ 👇🏾 Humble Yourself እንዲህ እንዳማረብህ: እንዲህ እንደጎፈላህ: እንዲህ እንደዘነጥክ አትኖረም ተፈጥሮ ሳታሰክንህ ራስህ ስከን !!❤️🙌🏼 ⛵️⛵️⛵️ "ማንበብ ፋሽን ነው።" Join us @noahbookdelivery
نمایش همه...
12👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኬቨን በርቲሃ ኑሮ ታከተው: አለም አስከፋቺው :የገዛ ህይወቱን ማጥፋት ብቸኛ አማራጭ አድርጎ ወሰነ ይህንን ውሳኔውን ለማሳካት ደግሞ በአሜሪካ ሳንፍራንሲስኮ ግዛት ወደ ሚገኘው እና በከፍታው እውቁ ድልድይ ወደሆነው ጎልደን ጌት ድልድይ አመራ ሆኖም ግን ከድልድዩ ጫፍ ቆሞ ራሱን ለማጥፋት ሲዘጋጅ የፖሊስ መኮንኑ ኬቨን ብሪግስ በቦታው ደረሰ:: ህይወቱን እንዳያጥፋ እየተማፀነው ለአንድ ሰአት ከሰላሳ ሁለት ደቂቃዎች አብሮት ቆየ ኬቨን በርቲሃ ሀሳቡን ቀየረ : ህይወቱም ተረፈች 👇🏾 ከ10 አመታት በኃላ ኬቨን በርቲሃ እና ኬቨን ብሪግስ እዚያው ድልድይ ላይ ተገናኝተው አወጉ: እዚያው ድልድይ ላይ እየተሳሳቁ ተጨዋወቱ ** ዋናው ነገር ዛሬን ማለፍ ነው : ማን ያውቃል ነገ ውስጥ ምን አይነት ሳቅ እንዳለ🤷🏾 ❤️🙌🏼 ሰው መሆኛ መንገድ ብዙ ነው !! zemelak endrias✍ ⛵️⛵️⛵️ "ማንበብ ፋሽን ነው።" Join us @noahbookdelivery
نمایش همه...
21👍 8
ከቅዳሜ ጀምሮ እንለቃለን ብንልም በአንድ አንድ ነገሮች ሳንችል በመቅርታችን ትልቅ ይቅርታ እየጠየቅን ዛሬ የተወሰኑትን ይዘን መተናል። 1. Never Split the Difference - Chris Voss with Tahl Raz Price 1250 birr 2. Trading in the Zone - Mark Douglas 3. Letter to milena - Kafka Price 1350 birr 4. Secret of Divine Love - A. Helwa Price 1450 birr 5. How to talk to anyone - Eli Lowndes price 1250 birr 6. 8 Rules For Love - Jay Shetty Price 1250 birr 7. IkIGAI - Hector Garcia and Francesc Miralles Pocket-size Hardcover Price 1150 Birr 8. Friends, Lovers, and the Big Terrible Things - Matthew Perry Price 1450 birr 9. How to Read a Book - Mortimer J. Adler and Charles Van Doren price 1450 Birr 10. Law of Human Nature - Robert Green Price 1450 birr ማሳሰቢያ ፦ ለክረምቱ መውጫ የሚሆኑ ትኩስ ትኩስ መጽሐፎች እየመጡ ነው 😊🥰 እስከዛሬ በመጽሐፍ በስጦታ ስናብነሸንሻቹ የነበራቹ ደንበኞቻችን በቅርቡ ደሞ ይፋዊ የሆነ ሁላችሁንም ያሳተፈ  Giveaway  እንደሚኖረንም በታላቅ ደስታ እናሳውቃለን። 🙏🥰🙏 ✅ ለማዘዝ 📚የሚያዙትን መጽሐፎች 📞ስልክ ቁጥር እና 📍አድራሻ ይላኩልን። ⛵️ Free Delivery ለማዘዝ 👇🏾   @Noahbook7  0939115238   "ማንበብ ፋሽን ነው።" Join us @noahbookdelivery
نمایش همه...
👍 8 3🥰 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ ስዕል "ፈተናን በድጋሚ መውደቅ" ይባላል ስዕሉ የተሳለው በእውቁ ራሺያዊ ሰአሊ ፌዶር ራሽቲንኮቭ ሲሆን የስእሉ ጭብጥ ከትምህርት ቤት ፈተና ወድቆ ወላጆቹ ፊት በሃፍረት የቆመ አንድ ታዳጊን ያሳያል ታዳጊው ፈተናውን በድጋሚ በመውደቁ በቤተሰቡ ፊት ራሱን አቀርቅሮ ወንድሙን ጨምሮ የቤተሰቡ አባላት ሁሉ "እንዴት ድጋሚ ትወድቃለህ?" ብለው በሃፍረት አንገቱን አስደፍተውት ያሳያል የአርቲስቱ መልእክት "እንደ ውሻው ተቀበሉት" የሚል ነው በስእሉ ላይ እንደሚታየው ታዳጊው ፈተናውን ቢወድቅም የውሻው ፍቅር አልጎደለበትም - በውድቀቱም ሆነ በስኬቱ ከፍቅር አልጎደለበትምና 👇🏾 ይህ በ1952 እ.ኤ.አ የተሳለው ስእል ሰዎችን በፍቅር እና በትህትና  ከውድቀታቸው ስለማንሳት ተምሳሌት ሆኗል በሰዎች ውድቀት : ከፍቅር አትጉደሉ !! ❤️🙌🏼 zemelak endrias ✍ ⛵️⛵️⛵️ "ማንበብ ፋሽን ነው።" Join us @noahbookdelivery
نمایش همه...
20👍 8👏 2😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኦሾ በአንድ ወቅት ለምንድን ነው የሴት ተከታዮችህ ቁጥር በጣም ከወንዶች የበለጠው ተብሎ ሲጠየቅ ፤ ለምንድን ነው ሰይጣን መጀመሪያ ሔዋንን ያታለላት? የሚል መልስ ሰጥቶ ነበር። ወንድ ቶሎ አይሰማም ተከራካሪ ነው ፤ ቢሰማም ውስጡን ነው የሚያዳምጠው ። ሰይጣን ምናልባት የኋላ ኋላ ሊያሳምነው ቢችልም እግዚአብሄር ሊደርስበት ይችል ነበር። ሴቷ ግን የምታዳምጠው ከልቧ ነው ልብ ደግሞ ፈጣን ነው። አዕምሮ ቀርፋፋ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ማሳመኛዎችን ይፈልጋል።እጅግ ሲበዛ ተጠራጣሪም ነው። በዛ ላይ የሚያቀርባቸው ጥያቄዎች ወንዱ በአእምሮው ስለሚሰም ጥያቄዎቹ ማብቂያ የላቸውም። ሰይጣን መጀመሪያ የተገናኘው ከተጠራጣሪው ተጠያቂ(ወንድ) ጋር ቢሆን ኖሮ ጠያቂው ሁሉንም ነገር ግልፅልፅ እስኪልለት ድረስ ማወቅ ስለሚፈልግ እስካሁን ድረስ እንኳን ጥያቄውን አይጨርስም ነበር።      #osho ⛵️⛵️⛵️ "ማንበብ ፋሽን ነው።" Join us @noahbookdelivery
نمایش همه...
😁 18👍 10 2
ሜሪ አን ቤቫን  ውብ የሚባል መልክ የነበራት እንግሊዛዊት ነበረች  ፡ እና ከ32 አመት እድሜዋ በኋላ በያዛት የፊት ገፅታ ያለመጠን ማደግና መዛባት ምክንያት መልኳ መቀየር  ጀመረ ። ብዙም ሳይቆይ  የአራት ልጆቿ አባት በሞት ተለያት ፡ በዚህም ምክንያት   ልጆቿን ማብላት እስከማትችልበት ድረስ ተቸገረች ። .... በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች የአለም የቁንጅና ውድድር ከሚባለው በተቃራኒ የሚዘጋጅ The Ugliest Woman in the World የሚባል  ውድድር   እንዳለ ሰማች ። በዚህ ውድድር ተሳትፋ  ካሸነፈች ልጆቿን የምታበላቸው ነገር ታገኛለች ። እና ይህን ስታውቅ ከጊዜ በኋላ በበሽታ ምክንያት አዲስ ገፅታ የያዘውን ረጅሙን ፊቷን ይዛ በውድድሩ ላይ ተሳተፈች ። ልጆቿን ማኖር እስከቻለች ድረስ  አስቀያሚ በሚልም ሆነ  በምንም አይነት ውድድር ውስጥ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ነበረች ። የውድድሩ ቀን ደረሰ ። ሜሪ አና ከተለያየ ቦታዎች ከመጡ ሴቶች ጋር ተወዳድራ በአንደኝነት አሸነፈች ። የአመቱ አስቀያሚ ሴት የሚለው ሽልማት ከገንዘብ ጋር ተሰጣት ። ለልጆቿ ስትል አለም የሰጣትን " አስቀያሚ"  የሚል ስም እሽ ብላ  ተቀበለች ። ዝነኛ ሆነች ፡ ከውድድሩ በኋላም አንድ የሰርከስ ቡድን በቋሚነት አባል አድርጎ ቀጠራት ፡ ችግር  ከሜሪ ቤተሰብና ከልጆቿ ራቀ ። በ .እናት ልጆቿን ለማሳደግ የማትሞክረው ነገር የለም የሚለው ትዝ አለንና ከማንም በላይ የተዋበ  የእናት ልብ ያላትን  ሜሪ አን ቤቫንን አነሳናት ። ⛵️⛵️⛵️ "ማንበብ ፋሽን ነው።" Join us @noahbookdelivery
نمایش همه...
30👍 8
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.