የግጥም ምሽት በቴሌግራም
رفتن به کانال در Telegram
ይህ ቻናል ከተለያዩ መጽሐፍት የተቀነጨቡ ግጥሞች የሚቀርቡበት እንዲሁም ወርሃዊ የግጥም ውድድሮች የሚካሄዱበት ነው ግጥም ለምትወዱ ሁሉ...የራሳችሁን ሙከራም የምታቀርቡበት ነው ለማንኛውም አስታየት @Nirvana134 እንዲሁም @simba23 ላይ አለን ፧ @yegetem32
نمایش بیشتر5 931
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-87 روز
-4030 روز
آرشیو پست ها
5 931
ማራኪዬ
ማራኪዬ
ምን ብዬ ልንገረው
ለጎደለው ቤቴ አትመጪም ብዬ
======= =========
በምዕራብ ፀሀይ ጠልቆ ሲጨላልም ሰማይ
ለማናፈስ ብዬ
ያስወጣሽ እግሬ ተቆላልፏል ብታይ
"አድኚኝ"....ያልሸኝ
ትተሽ እንደ ተለየሽኝ...ባንኜ ነቃለው
ካንቺ የቀረኝን
አሻንጉሊት ይዤ ሌቱን አነባለው
====================
ማራኪዬ
ማራኪዬ
ምን ብዬ ልንገረው
ለጎደለው ቤቴ አትመጪም ብዬ
አንቺ የህይወቴ ሲሳይ
ሁለ-መናሽ ናፍቆኝ ዘወትር ስሰቃይ
እንደ ሳልሽው ስዕል
ክንፉን ያማታሽ እየበረርሽ ነይ
===================
ማራኪዬ
ማራኪዬ
ምን ብዬ ልንገረው
ለጎደለው ቤቴ አትመጪም ብዬ
መጋለብ አይደለም የጀግና ሞገሱ
ተረጋግቶ ሲኬድ
የሩቁን አስቦ ያደርሳል ፈረሱ
ለተበጠሰ ልጓም ስንት ይሆን ክፍያዬ
ካለሽበት ወስዶ አይመልስም ቀዬ
=======================
ልብረር ልብረር ይላል
............ጋቢና እንደ ተቀመጠ
ልብረር ልብረር ይላል
...........መሪ እንደ ጨበጠ
ልብረር ልብረር ይላል
.............አንድ ሁለት የተጎነጨ
ልብረር ልብረር ይላል
...............ሰውን የገጨ
====================
መች ጠገብኩሽ እና እኔ
ሌት ይድላኝ አልጋዬ
ፍቅርሽ ስቶብኛል እኔ አልተኛም ጨርሶ
ማታ ማታ ማልቀስ ነው ስራዬ
ማራኪዬ
ማራኪዬ
ምን ብዬ ልንገረው
ለጎደለው ቤቴ አትመጪም ብዬ
=====================
በቃ...
እረፍት ላጣው ልቤ ነገርኩት እንደ ማትመጪ
እግዜሩ ወስዶ እግዜሩ ነው ሰጪ
======================
.
.
.
✍ሳሙኤል አለሙ
@Samialemu5
@yegetem32
@yegetem32
@yegetem32
5 931
ደመ -ነፍስ
....... ©ሲራክ
የነገ ህልሙ ዛሬ ቀድማ በቅፅበታት ስትዘከር
ሰውነቱ አይጥ ሁና በድመቶች ስትባረር
የአዝማናት አይነ ውሃ በአዘኔታ እምባ ሲያቀር
ክፉ ህልም ናት ይህቺ ነገር
ብሂም ሆነው ለታወሩ
በተዘጋች ሀገር ሲያንኳኩ ለኖሩ
.......................////......................
ሲራክ @siraaq
@yegetem32
@yegetem32
5 931
ጎጠኝነት ከቦኝ
ደፋሪዎች ከበውኝ...ጥለሽኝ ስቴጂ፣
ያንቺ ፍቅር ነበር ተስፋ ያደረኩት
አንቺ ካድሽኝ እንጂ፣
ምናለ ስቴጂ፣
ያየሽ ሲከበኝ ግሳንግሱ ሁሉ፣
በዓይነ-ስጋ ባይታዩ መላዕክቶች አሉ፣
...........ብለሽ ጠባቂ ሳትቀጥሪ፣
ፍርሃቴ በዝቷል
አንድ ሁለት ጠባቂ ያንሰኛል ጨምሪ፣
.
.
✍ሳሙኤል አለሙ
@Sazi5
@yegetem32
@yegetem32
@yegetem32
5 931
ምጣድ ልብ
""""""""'''''''''''''
ይሄ ምጣድ ልቤ ምንኛ ጠቆረ፤
በስንቱ ተማግዶ
ሁሌ እየጨሰ በረመጥ ቆሰለ፤
እንደዋዛ ሆኖ
ስንቱ ሰው አባክኖት ያላግባብ ቀለለ!
ይሄ ምጣድ ልቤ
ለሳቀው ለካበው እየቀላለጠ፤
አያ ሞኛ ሞኜ
ዘላለም ጉዳትን ሰርክ እየመረጠ፤
ስንቱ ቂል አረገው
እሳት ሲለቁበት
አብስሎና ጋግሮ እንጀራ እየሰጠ!
#መገን
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@Run_Viva_Run
@yegetem32
@yegetem32
@yegetem32
5 931
🌞🌞 ጥቂት ቀናት ቀሩት 🌞🌞
#ሠኔ 14 ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽን ልናይ በጣም ጥቂት ቀናት ቀርተውናል። ግርዶሹ በመላው የኢትዮጵያ ክፍል እንደየቦታው ከ60% እስከ 80 % ፀሐይ በጨረቃ ተሸፍና ከፊል ግርዶሹን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በአማካይ ከጠዋቱ 12:50 -- 3:15 ድረስ በኢትዮጵያ የሚታይ ይሆናል።
#በተለይ የግርዶሹ ዋናው መስመር የሚያቋርጥባቸው 97 % ፀሐይ ተሸፍና የእሳት ቀለበት ሠርታ በብቸኝነት የሚያይዋት እድለኞች የሀገሪቱ ቦታዎች ውስጥ፦ ቶንጎ፣ ቦምባሲ፣ መንዲ፣ እንጅባራ፣ ግሽ ዐባይ፣ ጢስ ዐባይ፣ ሞጣ፣ ጋይንት፣ ዳሞት፣ ቡሬ፣ አገው፣ ግምጃ ቤት፣ ንፋስ መውጫ፣ ቆቦ፣ ኮረም፣ አላማጣ፣ ላሊበላ ይጠቀሳሉ።
#በተለይ 97% በሙሉ ፀሐይ በጨረቃ ተሸፍና አብረቅራቂ እሳታማ ቀለበት “ring of fire” ሠርታ በነዚያ አስደናቂ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በላይ በሰማይ ከጠዋቱ 1:59 ላይ ከመታየቷ በተጨማሪ ፕላኔት ሜርኩሪና ቬነስም አብርተው በቀን ጠዋት ላይ ይታያሉ። ይልቁኑ የግርዶሹ መስመር ንጉሥ ላሊበላ የሠራውን የፈለገ ዮርዳኖስን መስመር በቀጥታ አቋርጦ ማለፉ የላሊበላውን በተለይ አጓጊና አስደማሚ ያደርገዋል።
ማሳሰቢያ፦ ፀሐይ በጊዜው የምትረጨው ጨረር ዐይናችሁን ሊያሳውርና eclipse blindness ስለሚያስከትልባችሁ eclipse viewer ከሌላችሁ ወደ ሰማይ አንጋጣችሁ ፀሐይን ለማየት እንዳትሞክሩ። ክስተቱን በጊዜው በቪዲዮ የምትቀርጹ ጋዜጠኞችም የካሜራችሁ ሌንስ እንዳይቃጠል ካሜራችሁ ላይ solar filter ተጠቀሙ።
ሮዳስ ታደሰ እና ዶ/ር ጌትነት ፈለቀ
#share
@yegetem32
@yegetem32
@yegetem32
5 931
አንቺ የሌለሽ ግዜ
"""""""""""""""""""""
አንቺ የሌለሽ ግዜ
ደ.ስ.ታ.ዬ ደምቆ ከት ብዬ ባልስቅም፤
ደካማ ፈገግታ
ከንፈር አስከድኖ ከጥርሶቼ አይጠልቅም!
አንቺ የሌለሽ ግዜ
ሆዴን ሆድ ቢብሰው እንባ ቢያቁር አይኔ፤
ከአይኔ አፈንግጠው
ከጉንጮቼ አይወዱም አላለቅስም እኔ !
አንቺ የሌለሽ ግዜ፤
አይዘኝ አባዜ፤
አይወስደኝ ትካዜ፤
ነቃ ብዬ አለሁ ሰው ባወራኝ ግዜ!
አንቺ የሌለሽ ግዜ
አንቺ የምትወጃቸው
አበቦች ቢያስጠሉም በጥቂቱ ያምራሉ፤
አንቺ የሌለሽ ግዜ
ያወራንባቸው
መስኮቹ ቢቀፉም ትንሽ ይስባሉ፤
አንቺ የሌለሽ ግዜ
ጥዑም ዜማ ያላቸው
ወፎቹ እንደነገር ይዘማምራሉ፤
እህህ...እህህ...እህህ ይላሉ!
አንቺ የሌለሽ ግዜ
መኖር ማለት ቀፎኝ
ነፍሴ አስጠልታኝ መሞት ብናፍቅም፤
እንዲያው በጥቂቱ
ኑሮ ታጓጓለች
በራስ ክፉ አስቤ ህይወቴን አልነጥቅም፤
መሞቴን አልመርጥም!
እንዲህ ነው አለሜ፤
አንቺ የሌለሽ ግዜ የምኖረው እኔ!
ዓይኔ ላይ ያቆረ
እንባዬ መውጫ አጥቶ ወደውስጥ ያነባል፤
ሰው ባወራኝ ቁጥር
ምስልሽ ተደቅኖ ከኔው ጋር ያወጋል፤
ጥርሶችሽን አይቶ
ለዓይኖችሽ ጓግቶ
ደብዛዛ ፈገግታ ከጥርሶቼ ይፈልቃል!
አንቺ የሌለሽ ግዜ
ዘግይተሽም ቀርተሽ ጠፍተሽ ከሰፈሩ፤
አበቦቹ መሀል
ከመስኩ ተቀምጠሽ
ወፎቹ እንደ ነገር እየዘማመሩ፤
ምስሎችሽ ተቀርፀው
በህሊና መንደር
በትዝታ ቀዬ ይታየኛል ሁሉ፤
አንቺ የሌለሽ ግዜ
በትዝታ ፈረስ
ጎድለሽ ሞልተሽልኝ አለሽ እንዳመሉ!
ኖረሽ እንዳመሉ
በሌለሽበትም ኖረሻል ከልቤ፤
ኖረሽ እንዳመሉ
በጠፋሽም ግዜ በርተሻል ከቀልቤ፤
ኖረሽ እንዳመሉ
እንደ ፀጉር በዝተሽ
አለሽ ሁሉም ቦታ ከ'ተሽ ከሀሳቤ፤
አይቼሽ አድራለሁ
አይቼሽ ውላለሁ ስናፍቅሽ እኔ!
(የኔ ውብ አለሜ)
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@Run_Viva_Run
@yegetem32
@yegetem32
@yegetem32
5 931
በአንድ ወቅት ‘ጉግል’(Google) አለም ላይ አብዝተው ወሲብ (Sex) የሚለውን ቃል ፈልግልን ከሚሉኝ 5 ሐገራት መካከል እናንተ ኢትዮጵያውያን ዋነኞቹ ናችሁ ብሎን ነበር።
ይህ የሚያሳየን በሐገራችን እጅግ በጣም ብዙ ሰው የፖርኖግራፊ ተጠቃሚ ወይም በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቃ መሆኑን ነው።
ይህ ሱስ እንደሌሎች ሱሶች በግልጽ በሱሰኛው ላይ የማይታይ በመሆኑ እንዲሁም በማህበረሰባችን ውስጥ ስለ ጉዳዩ አሳሳቢነት በቂ መረጃ ስለሌለ የተጠቂዎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ይገመታል።
👉 በቅድሚያ ግን ፖርኖግራፊ ምንድን ነው?
ሙሉ ትምህርቱን በዚህ ገብተው ይማሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAEqIr4y5A-KFH2Iexw
5 931
በአንድ ወቅት ‘ጉግል’(Google) አለም ላይ አብዝተው ወሲብ (Sex) የሚለውን ቃል ፈልግልን ከሚሉኝ 5 ሐገራት መካከል እናንተ ኢትዮጵያውያን ዋነኞቹ ናችሁ ብሎን ነበር።
ይህ የሚያሳየን በሐገራችን እጅግ በጣም ብዙ ሰው የፖርኖግራፊ ተጠቃሚ ወይም በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቃ መሆኑን ነው።
ይህ ሱስ እንደሌሎች ሱሶች በግልጽ በሱሰኛው ላይ የማይታይ በመሆኑ እንዲሁም በማህበረሰባችን ውስጥ ስለ ጉዳዩ አሳሳቢነት በቂ መረጃ ስለሌለ የተጠቂዎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ይገመታል።
👉 በቅድሚያ ግን ፖርኖግራፊ ምንድን ነው?
ሙሉ ትምህርቱን በዚህ ገብተው ይማሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAEqIr4y5A-KFH2Iexw
