cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ግጥም በኢትዮጵያ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
3 265
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+67 روز
+1230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
እናትኮ አለም ናት ሁሉንም የቻለች ስንቱን ተሸክማ የምትኖር ሳትሰለች እናት ለምን ትሙት ትኑር ለዘላለም እርሷ የሌለችበት መራራ ናት አለም ስለያት ከጎኗ ካጠገቧ ስርቅ ሳቋ ብቻ ሳይሆን ቁጣዋ 'ሚናፍቅ ብበላ ብጠጣ አይደርስም ካንጀቴ ከጎኔ ከሌለች ገራገሯ እናቴ ፍቅሯ ወደር አልባ ቢነሳ ቢወደስ ፈገግታዋ ብቻ ከህመም የሚፈውስ                       ✍  𝕟𝕒𝕙𝕠𝕞 @topazionnn @ethiopia_poem
نمایش همه...
3👍 1
ብሔርና ክልል - ዘር ቀለም አልመርጥም፣ ሁሉም የሰው ልጅ ነው - አላበላልጥም፣ በፍቅር ጎዳና  - ካገኘኋት ጓዴን እድሌን ልሞክር - ልጀምር መንገዴን። ✍️𝕟𝕒𝕙𝕠𝕞 @topazionnn @ethiopia_poem
نمایش همه...
👍 9
እሽሙርም የለብኝ ቅኔም እልተካንኩ ብዕሬም አልተባ ፣ በይ ቸሩን ያጋጥምሽ ደጋግ እና የዋህ ቅን ቅን ቤትሽ ይግባ :: ✍✍ሥፍራዬ ጥላዬ @topazionnn @ethiopia_poem
نمایش همه...
😁 13👍 1 1🥰 1
ገንፎ ሀገሬስ ገንፎ ናት በስልጣን ማንኪያቸው የሚቆራርሷት ቂቤ ወሬያቸውን በርበሬ ስራቸው ጨመር አርገውባት እሷ ያዝኩት ስትል የስጧትን ሁሉ አጣቅሰው አላውሰው በዛ ስልጣን ማንኪያ በህብረት አብረው ያውም ክብ ሰርተው እንደ ጉድ ሚበሏት የሚጎራረሷት ሀገሬ ለእነርሱ ገንፎ ብቻ እኮ ናት @topazionnn @ethiopia_poem
نمایش همه...
👏 11👍 1
👮‍♂የአንድ ወቶአደር ሲቃ እናት ሀገር እናትዬ ፣ ላንቺ መድማት ፡ ላንቺ ብቆስል ይሁን ብዬ ፣ ካሳደገኝ ከእናቴ እቅፍ ፡ ከአባት ኩራት ተነጥዬ ፣ ከአያቶቼ የጀብድ ታሪክ ፡ ........ከዚያች ሸጋ ፡ የአፍላ ፍቅሬን አንጠልጥዬ፣ ወጣሁልሽ ፡ ስለ ሀገሬ አሜን ብዬ ...................ስለ እምዬ ። በዱር ባድር ፡ ከእቶን ስር በበርሃ ፣ ድካም በዝቶ ስንገላታ ፡ እጎነጨው አጥቼ ውሃ ። አፈር ምድሩን ፡ ባሩድ ሽታ እያወደ ፣ በውሽንፍር በጥይቱ ፡ አካላቴ እየራደ ። ደግሞም ጥሎ ዶፍ መአቱ ፡ የበረዶው ቅዝቃዜ ፣ ከጭቃው ጋር ሲመሳሰል ፡ የልጅነት መልኬ ወዜ ፣ ተጫጭኖኝ ፡ ዐቢይ ድካም ወትካዜ ። ከምሽግ ስር እንደወደኩ ፡ ቢያልፉ ቀናት፣ ሰላም ለኪ ብዬ ፡ አዛኝቱን ስማፀናት ፣ ልቤ ሲርድ ፡ ደም መርጨቱን እንዳቆመ እያስመሰለ ፣ ያ ጎልያድ ከበፊቴ ፡ እየፎከረ እየሸለለ ። ፍርሃት ወርሶኝ ፡ አካላቴ እያለቀ ፣ አዳኝ ጌታ እስኪመስለኝ፡ ከኔ የራቀ ። አበቃለት ሞተ ዛሬ ፡ ሲሉኝ ንቀው ፣ እውነቴን ነው ፡ ይህን ሁሉ ታግሻለው ፣ በምወደው ፡ በሰንደቅሽ እምላላው ። አምኖን ዛሬም ፡ ወንድምነቱን ዘንግቶ ፣ ክብርሽን ሊያጎድፍ ። ወስልቶ ፣ ድንግል አፈር መሬትሽን ፡ ቋምጦ ሽቶ ። ክፋት ወርሶት ፡ ጎኔን ሲወጋኝ ፣ ሳምነው ክዶ ፡ ቃየል ጨካኝ ሲሆንብኝ። እስራትሽን ልፈታልሽ ፡ ያንን አውሬ ስፋለመው ፣ ለካስ ያለው ጠላት ፡ ከጎኔ ነው ፣ በአላማ እንደወንድም ፡ አምኘው ፣ ሙሉ ልቤን ክፍት አድርጌ ፡ ባስጎበኘው ። ይሁዳ ነበረ ፡ ባንዳነት ያለበት ፣ በደካማው ጎኔ ፡ ጥይት ሰደደበት ። ላንቺ መድማት ፡ ላንቺ ብቆስል ይሁን ብዬ ፣ እናት አለም ፡ እናት ሀገር ፡ እናትዬ ። ከአያቶቼ የጀብድ ታሪክ ፡ .....ከዚያች ሸጋ ፡ የአፍላ ፍቅሬን ሳላጣጥም ፣ .....ስለክብርሽ ፡ ትግል ስገጥም ። አለፍኩልሽ ፡ በእስትንፋሴ ፣ እስትንፋስሽን ፡ አስቀጥዬ ። ✍ Yibeltal Belay Zeleke @topazionnn @ethiopia_poem
نمایش همه...
🥰 4👍 2👏 1
00:43
Video unavailableShow in Telegram
ገጣሚ ✍️ዘዉድ አክሊል @topazionnn @ethiopia_poem
نمایش همه...
👍 4 3
ትኩረት የገጣሚያንን ሞራልና ድካማቸውን እየገደለ የሚገኝ አንድ ልጅ አለ። የሰው ግጥምን እራሴ ነኝ የፃፍኩት ማለት እና የሌሎች ገጣሚያንን ስራ በመውሰድ ስሙን ብቻ እየቀየረ የሚያጭበረብር ልጅ ተገኝቷል። ቻናሉን እየገባችሁ REPORT በማድረግ እናዘጋዋለን👍 https://t.me/eyobzemariyam https://t.me/eyobzemariyam በሰው ስራ ለመክበር መጣር ነውር ነው።
نمایش همه...
👍 2 2
..... እሱ እኮ.. እያሉ ባሞገሱህ ቁጥር፤ አንተን እያነሱ ባወደሱህ ቁጥር፤ ልብህን አይሙቀዉ ፍፁም ደስ አይበልህ፤ ቀን የከፋ ለታ......... ቁልቁል ይጥሉሃል....... እላይ የሰቀሉህ። ...................................... በዔደን ታደሰ @topazionnn @ethiopia_poem
نمایش همه...
6👍 1👏 1
እዉነት እንዳይመስልሽ . . ዛሬ ......ምን ብትደምቂ፤ ከቆነጃጅቱ እጅጉን ብትልቂ፤ ኑሮ ተመችቶሽ ያ.... ፊትሽ ቢወዛ፤ ወደድኩሽ የሚለዉ አፍቃሪሽ ቢበዛ ፤ ሴትነትሽ ማለት... መልክ ከመሰለሽ፤ ፍፁም አትመኪ እዉነት እንዳይመስልሽ፤ አንቺን ሳያማክር........ የጠቆረዉ ፀጉርሽ.. በሽበት ይተካል፤ ጸአዳዉም መልክሽ በፍጥነት ይረግፋል፤ ሴትነትሽ ማለት መልክ ከመሰለሽ፤ ፍፁም አትመኪ እዉነት እንዳይመስልሽ። .......................................... በዔደን ታደሰ @topazionnn @ethiopia_poem
نمایش همه...
4👏 4👍 2
ይድረስልኝ ላንቺ ቀንሽ ለጨለመ፤ ልብሽ ለሚያነባ ዉስጥሽ ለታመመ፤ የመኖርሽ ዉሉ የህይወትሽ 'ጣሙ፤ መሪር ለሆነብሽ ሳይገባሽ ትርጉሙ፤ ይድረስልኝ ላንቺ ተስፋን ለቆረጥሽዉ፤ ከራስሽ ተጣልተሸ ሞት ለተመኘሽዉ፤ ይድረስልኝ ላንቺ......... ምን ድቅድቅ ቢዉጥሽ ፤ ምን ፅልመት ቢከብሽ፤ ሌቱም ይገፍና ደግሞ ይነጋጋል፤ አሮጌዉ ያልፍና 'ባዲስ ቀን ይተካል። ............................................. በዔደን ታደሰ @topazionnn @ethiopia_poem
نمایش همه...
🔥 5👍 2