cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

🙏🙏🙏ታሪክን እወቅ እዳትሆን መናፍቅ🙏🙏🙏

✅እስቲ አንዳንዴም ጊዜዎን በመንፈሳዊ ተምህርቶች ላይ ያሣልፉ። ✅እንሆ ለክርስትና እምነት ተከታዮች ሊያስተምር የተከፈተ አዲሡ የመንፈሣዊ ትምህርቶች መማሪያ ቻናል።እንሆ JOIN ብለው መንፈሳዊ እውቀቶን ያስፋፉ‼️ ዛሬም ነገም ቢሆን ኦርቶዶክስ ጠላቶቿን አሸንፋ ታብባለች 🌼ኢትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ 🌼 https://t.me/Maheberekedesat_bot

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
Advertising posts
512مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

🌖🌗🌘እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም እና በጤና አሸጋገራችሁ! 🌒🌓🌔 "የሰማዩን ንፋስ #ባርክ ዝናሙንም #በዚህች_ዓመት የማያፈራውንም የምድሩን ፍሬ በቸርነትህ #ባርክ ዘወትር ተድላንና ደስታን #አድርግ።" ሥርዐተ ቅዳሴ "የዚህችን #ዓመት አክሊል/ፍሬዋን በቸርነትህ #ባርክ÷...#እንደቸርነትህ ለእኛ በጎ ነገርን #አድርግልን።" ቅዳሴ ባስልዮስ "#በቸርነትህ ዓመትን #ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን #ይጠግባል።” መዝሙር 65፥11 🌟🌼መልካም በዓል!🌼🌟
نمایش همه...
‹‹ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላም እና የጤና እንዲሆንላችሁ ትሻላችሁን? እንግዲያስ ገና ከጅምሩ በስካር፤ በዘፈን፤ በገቢረ ኀጢአት ለማሳለፍ አትፍቀዱ፡፡ የዓዲሱ ዓመት የመጀመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኀጢአት አትጀምሩ፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፤ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚሆኑት በተፈጥሮአቸው እንደዛ ሆነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲሆን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማክሰኞ ከዘንድሮ ማክሰኞ የተለየ አይደለም፤ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው፡፡ የጽድቅን ስራ የምንሰራበት ከሆነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይሆን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኀጢአት የምንሰራበት ከሆነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይሆን አዲሱ ዓመትም ክፉ እና መከራ የበዛበት ይሆንብናል፡፡ አዲሱን ዓመት በበጎ ስራ የምንጀምረው ከሆነ በዓመቱ የምናደርገው ማንኛውም ክንውን ላይ በጎ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
نمایش همه...
‹‹ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላም እና የጤና እንዲሆንላችሁ ትሻላችሁን? እንግዲያስ ገና ከጅምሩ በስካር፤ በዘፈን፤ በገቢረ ኀጢአት ለማሳለፍ አትፍቀዱ፡፡ የዓዲሱ ዓመት የመጀመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኀጢአት አትጀምሩ፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፤ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚሆኑት በተፈጥሮአቸው እንደዛ ሆነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲሆን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማክሰኞ ከዘንድሮ ማክሰኞ የተለየ አይደለም፤ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው፡፡ የጽድቅን ስራ የምንሰራበት ከሆነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይሆን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኀጢአት የምንሰራበት ከሆነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይሆን አዲሱ ዓመትም ክፉ እና መከራ የበዛበት ይሆንብናል፡፡ አዲሱን ዓመት በበጎ ስራ የምንጀምረው ከሆነ በዓመቱ የምናደርገው ማንኛውም ክንውን ላይ በጎ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
نمایش همه...
🕊 † እንኳን ለርኅወተ ሰማይ: ለቅዱስ ሩፋኤል: መልከ ጼዴቅ: ዘርዓ ያዕቆብና ሰራጵዮን ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊   †    ርኅወተ ሰማይ    †     🕊 † ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት: አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት: ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ዕለት ስለሆነች "ርኅወተ ሰማይ-ሰማይ የሚከፈትባት ቀን::" ትባላለች:: አሁን በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም:: የሰው ልጆችን ልመና ቅዱሳን መላእክት ያለ ከልካይ የሚያሳርጉበት: አንድም ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንዲህ ተባለ እንጂ:: እመቤታችን ድንግል ማርያም ለአጼ ናዖድ እንደ ነገረቻቸው በዚህች ዕለት ሁሉም ቅዱሳን ስለሚታሰቡ: የእግዚአብሔር የምሕረት መዝገቡ ስለሚከፈት: ዕለቷን ክብርት ያሰኛታል:: በቅዱስ ሩፋኤል አበጋዝነት [መሪነት] በዚህች ዕለት ለዓመት የሚበቃ ምሕረት ይገኛል:: ስለዚህም አባቶቻችን በዚህች ሌሊት ሦስት መቶ ስልሳ አምስት አቡነ ዘበሰማያትን ሲጸልዩ ያድራሉ:: በሌላ ወገን ደግሞ የጌታ ዳግም ምጽዓቱ መታሰቢያ እንደ መሆኗ ትልቅ ትኩረትም ይሰጣታል:: ቸሩ ጌታችን ከተከፈተች ገነት ከተነጠፈች ዕረፍት ሁላችንንም ያድርሰን:: 🕊    †    ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት     †     🕊 † ቅዱስ ሩፋኤል በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በደረጃው ሦስተኛ ነው:: በመጀመሪያዋ ዕለተ ፍጥረት እግዚአብሔር መቶ ነገደ መላእክትን ፈጥሮ በአሥር ከተማ ሲያኖራቸው የቅዱስ ሩፋኤል ዕድል ፈንታው ራማ ሆነች:: በዚያም "መናብርት" ተብለው ለሚጠሩ አሥሩ ነገድ አለቃ [መሪ] ሆኖ በፈጣሪው ተሹሟል:: በኋላም "መጋብያን" በሚባሉ በሃያ ሦስቱ ነገድ ላይ ሹሞታል:: ይህች ዕለትም በዓለ ሲመቱ ናት:: አንድ ቀን ጌታችን ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ሐዋርያቱ ቅዱስ ሩፋኤልን እንዲያስተዋውቃቸው ለመኑት:: ጌታም ሦስቱን ሊቃናት [ሚካኤል: ገብርኤል እና ሩፋኤል] ይመጡ ዘንድ አዘዛቸው:: ቀጥሎም ቅዱስ ሩፋኤልን "ክብርህን ንገራቸው::" አለው:: እርሱም ለጌታ ሰግዶ ለሐዋርያት ብዙ ምሥጢር ነገራቸው:: በተለይ ስሙን ለሚጠሩ: መታሰቢያውን ለሚያከብሩ የሚደረገውን ጸጋ አብራርቶላቸው ዐረገ:: በመጽሐፈ ጦቢት ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ቅዱሱ መልአክ ሰው [አዛርያን] መስሎ: ጦብያን ለትዳር አብቅቶ: ሣራን አስማንድዮስ ከሚባል ሰይጣን አድኖ: የጦቢትን ዓይን አብርቷል:: በገድላተ ቅዱሳን እንደምናየውም ለብዙ ቅዱሳን ረዳታቸው ሆኖ ገድላቸውን አስፈጽሟል:: ታሪክ እንደሚለው ይህች ቀን ለቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱም ናት:: በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘእስክንድርያ አማካኝነት ቤቱ ታንጿል:: የሚገርመው ደግሞ የታነጸው በዓሣ አንበሪ ጀርባ: ደሴት ላይ ነው:: በመልአኩ አጋዥነትም ለሦስት መቶ ዓመታት አገልግሏል:: † ቅዱስ ሩፋኤል ¤ መስተፍስሒ [ልቡናን ደስ የሚያሰኝ] ¤ አቃቤ ሥራይ [ባለ መድኃኒት ፈዋሽ] ¤ መዝገበ ጸሎት [የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው] ¤ ሊቀ መናብርት [በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት መሪ] ¤ ፈታሔ ማኅጸን [የሰውንም ሆነ የእንስሳትን ማኅጸን የሚፈታ] ¤ መወልድ [አዋላጅ: ምጥን የሚያቀል) ይባላል:: "ለሰብእ ወለእንስሳ ፈታሔ ማኅጸኖሙ አንተ" እንዲል:: 🕊    †    ቅዱስ መልከ ጼዴቅ    †      🕊 † ካህኑ መልከ ጼዴቅን ቅዱስ ጳውሎስ "የትውልድ ቁጥር የለውም: ለዘመኑም ጥንትና ፍጻሜ የለውም::" ይለዋል:: [ዕብ.፯፥፫] ሐዋርያው ይህንን ያለው ለወልደ እግዚአብሔር ምሳሌ ሲያደርገው እንጂ ትውልዱ ከነገደ ካም ነው:: ወላጆቹም "ሚልኪ እና ሰሊማ" ይባላሉ:: ገና ከእናቱ ማኅጸን የተመረጠው ቅዱሱ "ካህነ ዓለም: ንጉሠ ሳሌም" ይባላል:: የዛሬ አምስት ሺ አምስት መቶ ዓመት አካባቢ ሴም ባኖረበት ቦታ [በደብረ ቀራንዮ] ለዘላለም ይኖራል:: ካህኑ መልከ ጼዴቅ ከሰው ወገን እጅግ ክቡርም ነው:: 🕊   †    አፄ ዘርዓ ያዕቆብ     †      🕊 † ሃይማኖቱ የቀና ኢትዮጵያዊው ንጉሥ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ በኢትዮጵያ በነገሠባቸው ሠላሳ አራት ዓመታት [ከ1426 እስከ 1460 ዓ/ም] ብዙ በጐ ነገሮችን ሠርቷል:: ላለፉት ሰባ ዓመታት ግን አንዳንድ ጥቃቅን ሰብአዊ ስህተቶችን እየነቀሱ ተሐድሶዎቹ ስሙን ሲያጠፉት ኑረዋል:: ዛሬ ዛሬ ደግሞ የእኛ ቤት ሰዎችም ተቀላቅለዋቸዋል:: እነርሱ ያሉትን ይበሉ እንጂ ለእኛ ግን ዘርዓ ያዕቆብ ማለት :- ፩. ጣዖት አምልኮን ከሃገራችን ለማጥፋት ብዙ ሺህ ካህናትን አሰልጥኖ አሰማርቷል:: ፪. የኑፋቄ ችግሮችን ለመቅረፍ ጉባኤያትን አዘጋጅቷል:: ፫. ከአሥራ አንድ ያላነሱ መጻሕፍትን በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ደርሶ ለአገልግሎት አብቅቷል:: ፬. ብዙ መጻሕፍትን ከውጪ አስመጥቶ አስተርጉሟል [በተለይ ተአምረ ማርያምን] ፭. ሰው ሁሉ ለእመ ብርሃንና ለመስቀሉ ፍቅር እንዲገዛ ጥረት አድርጓል ፮. እመቤታችንን በፍጹም ልቡ ከመውደዱ የተነሳ ዛሬ ድረስ በሃገራችን ድንግል ማርያም "የዘርዓ ያዕቆብ እመቤት" እየተባለች ትጠራለች:: ፯. ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጾ: ብዙ ሥርዓቶችም በሊቃውንት እንዲሠሩ አድርጐ: ሌሎች ብዙ በጐ ተግባራትንም ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል:: ቤተ ክርስቲያን ስለውለታቸው ዘርዓ ያዕቆብን: እናታቸው ጽዮን ሞገሳን እና አባታቸው ዳዊትን በክብር ታስባለች:: 🕊    †    ቅዱስ ሰራጵዮን ዘሰንዱን     †       🕊 † ይህ ቅዱስ እጅግ የበዛ ሃብቱን ለነዳያን አካፍሎ: ወደ ሌላ ሃገር ሔዶ ለባርነት ተሽጧል:: በተሸጠበት ሃገርም በጸሎት ተግቶ ከክህደት ወደ ሃይማኖት መልሷቸዋል:: ክብሩን ሲያውቁበትም በተመሳሳይ ወደ ሌላ ሃገር ሒዶ አሕዛብን አድኗል:: በፍጻሜው ወደ በርሃ ገብቶ በተጋድሎ ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል:: † አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ሁሉ በረከትና ጸጋ ያብዛልን:: ለዓለምም ሰላሙን ይዘዝልን:: 🕊 † ጳጉሜን ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩ . ርኅወተ ሰማይ [የሰማይ መከፈት] ፪ . ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት ፫ . ቅዱስ መልከ ጼዴቅ ካህን ፬ . አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ንጉሥ [የእመቤታችን ወዳጅ] ፭ . ቅዱስ ሰራጵዮን ዘሰንዱን ፮ . ቅዱስ አኖሬዎስ ፯ . ቅዱስ ቴዎፍሎስ ፰ . አባ ዮሐንስ ፱ . ቅዱስ ጦቢት ፲ . ቅዱሳን ጦብያና ሣራ ††† ወርኀዊ በዓላት [የለም] † "እውነት እውነት እላችኋለሁ:: ሰማይ ሲከፈት: የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ::" † [ዮሐ. ፩፥፶፪] †  ወስብሐት ለእግዚአብሔር  † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🕊                    💖                        🕊
نمایش همه...
🕊 † እንኳን ለተባረከ ወር ጳጉሜን እና ለቅዱሳኑ ዮሐንስ መጥምቅ : ዑቲኮስ ሐዋርያና ቀሲስ አባ ብሶይ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † ††† ወርኀ ጳጉሜን ††† 🌼 † እግዚአብሔር አዝማናትን የፈጠራቸው ለሰው ልጆች ጥቅም መሆኑ ይታወቃል:: እርሱ ባወቀ: በረቂቅ ሥልጣኑ ዓለምን ፈጥሮ: ጊዜያትን እንዲከፍሉ ብርሃናትን [ፀሐይ: ጨረቃ: ከዋክብትን] ፈጥሮልናል:: ጊዜያትንም በደቂቃ: በሰዓት: በቀን: በሳምንት: በወር: በዓመታት: በኢዮቤልዩ: በክፍላተ ዘመናት እንድንቆጥር ያስማረንም እርሱ ነው:: የሰከንድ 540,000 ክፋይ ከሆነችው 'ሳድሲት' እስከ ትልቁ ቀመር [532 ዓመት] ድረስ እርሱ ለወደዳቸው እንዲያስተውሉት ገልጧል:: በየዘመኑም በቅዱስ ድሜጥሮስ: በቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ : በቅዱስ አቡሻኽር እና በሌሎቹም አድሮ መልካሙን አቆጣጠር አስተምሯል:: ሃገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ የአሥራ ሦስት ወራት የፀሐይ ጸጋ [thirteen months sun shine] ያላት: አራቱ ወቅቶች የተስማሙላት ናት:: † ሌላው ዓለም ወሮችን 31,30,29 (28) እያደረገ ሲጠቀም እኛ ግን እንደ ኖኅ (ዘፍ. 8:1-15) አቆጣጠር ወሮችን በሠላሳ ቀናት ወስነን: ጳጉሜንን ለብቻዋ እናስቀምጣለን:: ጳጉሜን 'ኤጳጉሚኖስ' ከሚል የግሪክ [ጽርዕ] ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም 'ትርፍ: ጭማሪ' እንደ ማለት ነው:: የወርኀ ዻጉሜን አምስቱ [ስድስቱ] ቀናትም ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገሪያ እንደ መሆናቸው ብዙ ምሳሌያት [ምሥጢራት] አሏቸው:: ዋናው ግን በዚህ ጊዜ ዳግም ምጽዓት ይታሠባል:: ጊዜውንም በጾምና በጸሎት ሊያሳልፉት ይገባል:: ግን በፈቃድ ነው እንጂ የግዴታ አይደለም:: 🕊   †   ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ    †    🕊 ¤ የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ¤ በማኅጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት ¤ በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ ¤ እሥራኤልን ለንስሐ ያጠመቀ ¤ የጌታችንን መንገድ የጠረገ ¤ ጌታውን ያጠመቀና ¤ ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው:: † ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን :- - ነቢይ : - ሐዋርያ : - ሰማዕት : - ጻድቅ : - ገዳማዊ : - መጥምቀ መለኮት : - ጸያሔ ፍኖት : - ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች:: † ቅዱሱ በዚህች ዕለት ወደ እሥር ቤት ገብቷል:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- ንጉሡ ሔሮድስ የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሔሮድያዳን በማግባቱና በመሰል ክፋቶቹ ቅዱስ ዮሐንስ ይገስጸው ነበር:: ቅዱስ ዮሐንስ "መምሕር ወመገስጽ: ዘኢያደሉ ለገጽ - ፊት አይቶ የማያዳላ" ነውና ገሰጸው:: ሔሮድስ ቅዱሱን ይፈራው: ያከብረውም ነበር:: በኋላ ግን ፈቃደ ሥጋው ስላየለበት: በተለይ ደግሞ ከሰባት ቀናት በኋላ ልደቱን ሲያከብር እንዳይረብሸው በመስጋት በዚህች ቀን በወታደሮቹ አስይዞ እሥር ቤት ውስጥ ጥሎታል:: ለሰባት ቀናት በጨለማ ውስጥ አሥሮ መስከረም 2 ቀን አንገቱን እንዴት እንዳስቆረጠው ዕለቱን ጠብቀን እንመለከታለንና የዚያ ሰው ይበለን:: 🕊  †   ቅዱስ ዑቲኮስ ሐዋርያ    †     🕊 † ቅዱሱ ሐዋርያ ጭራሽ ከነስማቸው እንኳ እየተዘነጉ ከሔዱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን ቁጥሩም ከሰባ ሁለቱ አርድእት ነው:: በወጣትነት ዘመኑ የጌታችን ደቀ መዝሙር መሆንን መርጦ ለሦስት ዓመት ከሦስት ወር ምሥጢረ ወንጌልን ጠንቅቆ ተምሯል:: መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜም እንደ መጠኑ ተቀብሎ ለአገልግሎት ወጥቷል:: በመጀመሪያ የወንጌላዊው ዮሐንስ ተከታይ ሁኖ ብዙ ምሥጢራትን ተካፍሏል:: ቀጥሎም ቅዱስ ጳውሎስን ተከትሎ ብዙ አሕጉራትን በስብከተ ወንጌል አዳርሷል:: በመጨረሻም በእስያ አካባቢ ለብቻው ተጉዞ: ብዙ ነፍሳትን ማርኮ: ጣዖታትን አጥፍቷል:: ስለዚህ ፈንታም በእሳት: በስለትና በግርፋት ብዙ መከራዎችን አሳልፏል:: በዚህች ቀንም በበጐው እርግና [ሽምግልና] ዐርፏል:: 🕊    †    ቅዱስ ብሶይ ቀሲስ    †      🕊 † ከ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ካህናት አንዱ የነበረው አባ ብሶይ ለአገልግሎት ወጥቶ ሲመለስ የቤተሰቦቹ ቤት ሰው አልነበረበትም:: "የት ሔዱ?" ብሎ ቢጠይቅ "ወንድምህ አባ ሖር እና እናትህ ቅድስት ይድራ ወደ እስክንድርያ ሔደዋል:: በዚያም ስለ ክርስቶስ ፍቅር ተሰውተዋል::" አሉት:: በማግስቱ የኔ ብጤዎችን ጠርቶ ሃብቱን: ንብረቱን: ቤቱን አካፈላቸው:: ለራሱ ግን አንዲት በትር እና ሦስት የዳቦ ቁራሾች ይዞ ጉዞ ተነሳ:: ወደ እስክንድርያ እንደ ደረሰ አፈላልጐ የቤተሰቦቹን መቃብር አገኘ:: ከፊታቸው ወድቆም የናፍቆት ለቅሶን አለቀሰ:: ወዲያውም እንዲህ አላቸው:- "ፈጥኜ ወደ እናንተ ስለምመጣ ጠብቁኝ:: ደግሞም ጸልዩልኝ::" ከዚያ ተነስቶ በመኮንኑ ፊት ስለ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት መሰከረ:: በዚህ ምክንያት ብዙ ተሰቃይቶ በዚህች ቀን ሰማዕት ሆኗል:: ከወገኖቹም ጋር ተቀብሯል:: † አምላከ ቅዱሳን ተረፈ ዘመኑን ባርኮ ለአዲሱ ዘመን በቸር ያድርሰን:: ከወዳጆቹም ጸጋ በረከትን ይክፈለን:: 🕊 † ጳጉሜን ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ [የታሠረበት] ፪. ቅዱስ ዑቲኮስ ሐዋርያ [ከሰባ ሁለቱ አርድእት] ፫. ቅዱስ ብሶይ ቀሲስ [ሰማዕት] ፬. አባ ጳኩሚስ /ባኹም [የሦስት ሺ ቅዱሳን አባት] ፭. አባ ሰራብዮን /ሰራፕዮን [የአሥር ሺ ቅዱሳን አባት] †  ወርኀዊ በዓላት [የለም] † "ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ::" † [ማቴ. ፲፩፥፯-፲፭] †  ወስብሐት ለእግዚአብሔር  † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🕊                    💖                        🕊
نمایش همه...
ጳጉሜ/ጳጉሜን በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከነሐሴ በኋላ ጳጉሜን የምትባል አምስት ቀን አለች፡፡ ወር እንዳትባል አቅም ያንሳታል፡፡ ሳምንት እንዳትባል አምስት ቀን ብቻ ኾናለች፡፡ ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ ግን “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ መኾኑ በአበው ቃል ተነግሯል፡፡ “ኤፓጉሜኔ” ማለት ጭማሪ ማለት ነው ፡፡ በግእዝ ቋንቋችን ተውሳክ ማለት ነው፡፡ ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ኤውሮፓዎች ጳጉሜን የወር ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ እኛ የወርን ቁጠር ሠላሳ ስናደርግ እነርሱ ሠላሳ አንድ ብለው የሚቆጥሩት ወር አላቸው፡፡ ይኹን እንጂ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ የዓመት ተጨማሪ  አድርገዋታል፡፡ የዓመቱንም ቀን ቁጥር ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀን ቀነስኩ ብለው ደምረውታል፡፡ ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ዮሐንስ(በአቡሻክር/ህር ትምህርት ጳጉሜን ከመስከረም ቀድማ የተፈጠረች እንደሆነች ሊቃውንት ይናገራሉ ያንን በመያዝ በሉቃስ መጨረሻ የሆነችውን ለዮሐንስ መጀመሪያ አድርገው ጳጉሜን 6 በዮሐንስ ይላሉ) ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ / Thirteen months of sunshine / በመባል ትታወቃለች ፡፡ ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፡-2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡ ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፡-2 ፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡ የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡ ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው ከሌሊት ጀምረው በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸበል ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን የምናደገውም እግዚአብሔር የተባረከ ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው ዓመት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር እንዲለን ነው፡፡ የምንጠመቀውም ንስሐ ገብተን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጸበል ደግሞ ከበሽታችን ያድነናል፣ የተቀደስንም ያደርገናል፣ መጪውንም ህይወታችን የተባረከ ያደርግልናል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር መልካም የአዲስ ዓመት ዋዜማ (ጷጉሜ) ይሁንላችሁ፡፡
نمایش همه...