cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ያዬ christ 🙏🙏🇪🇹🇪🇹

# ከትልቆቹ........... 🔶ትልቁ ስጦታ -----------------ፍቅር 🔶ትልቁ ስልጣን-------ራስን መግዛት 🔷ትልቁ ስብእና------------መልካምነት 🔷ትልቁ ማንነት-------------ታማኝነት 🔶ትልቁ ድህነት--------እውቀት ማጣት 🔶ትልቁ ድክመት------ለገንዘብ መገዛት 🔷ትልቁ ስልጣኔ ---------------መረዳዳት 🔷ትልቁ በሽታ --------ሁሉን ኣውቃለሁኝ 🔶ትልቁ

نمایش بیشتر
Advertising posts
190مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

. ባንተ ነው ዘማሪያን ሳልሞስ ኳየር |Track 01 💽Amen Na Album 💿 sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯 ✅ @adadisemezemur ✅ ✅ @adadisemezemur ✅ 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን
نمایش همه...
. ድል አለ ዘማሪያን ሳልሞስ ኳየር |Track 10 💽Amen Na Album 💿 sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯 ✅ @adadisemezemur ✅ ✅ @adadisemezemur ✅ 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን
نمایش همه...
. ኢየሱስ ዘማሪ ሳሙኤል ተ/ሚካኤል|Studio Live ⌚️10:43 ደቂቃ | 💾 8.4 MB sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯 ✅ @adadisemezemur ✅ ✅ @adadisemezemur ✅ 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉ
نمایش همه...
አዝ፦ የእግዚአብሔር እጅ የያዘው ነገር እንዳይወድቅ አይፈራ እንዳይጠፋ አይፈራ ከጥላው ሥር ያረፈው ሰው ዘለዓለሙ አያሰጋው (2x) አባትዬ የእኔ ወዳጅ (2x) ኑሮዬ በአንተ እጅ (2x) አባትዬ የእኔ ከለላ ከለላዬ በጥላህ ሥር ነው ማደሪያዬ (2x) በእናቴ ማህፀን ደምሳለ ሆኜ አጥንቶቼም ሳይዋደዱ አንተው ታውቀው ነበር እንዲህ እንዲሆን የሕይወቴ አካሄዱ ደግሞ እስከ አሳለፍከኝ በቸርነትህ የትላንቱኑ ጨለማ ለነገውስ ቢሆን ለምን አላምንም ሕይወቴ በእጅህ ነውና ተውኩት ሁሉንም ለአንተ ተውኩት ተይ ነፍሴ እኔ አላውቅም ብዬ እንዳልኩት ይሁን ያልከው የፀና ለመሆኑ ምስክር ነው ሰማይ የለም አገር መሆኑ አዝ፦ የእግዚአብሔር እጅ የያዘው ነገር እንዳይወድቅ አይፈራ እንዳይጠፋ አይፈራ ከጥላው ሥር ያረፈው ሰው ዘለዓለሙ አያሰጋው (2x) አባትዬ የእኔ ወዳጅ (2x) ኑሮዬ በአንተ እጅ (2x) አባትዬ የእኔ ከለላ ከለላዬ በጥላህ ሥር ነው ማደሪያዬ (2x) ክብርን የምትገልፅበት ደካማ ሰው ስትፈልግ አገኘኸኝ እንጂማ በእራሴ እንኳን በአንተ በሰውም ዓይን የማልሞላ ነኝ ገና በወደድከኝ በንጋት አየሁ ብልስ ምን እልሃለሁ አንተ ነህ ደጀኔ ተባረክልኝ ከትከሻህ የሚያወርደኝ ማነው አልጥልሽ አልተውሽ እያልክ ልፌ ስትደግፈኝ እንደዋልክ አይቼህ መንፈሴ ረካ አትተወኝም አትረሳኝም ለካ አዬ አትረሳኝም ለካ አትተወኝም በቃ አትረሳኝም በቃ አሄ አትረሳኝም በቃ አትተወኝም በቃ አትለቀኝም በቃ አሄ አትለቀኝም በቃ (2x) ዘማሪት ቤተልሄም ተዘራ
نمایش همه...
🧿ኧረ ስንቱ ስንቱ ስንቱ ስንቱ ታለፈ🎧 🧿ኢየሱስ እየቀደመ ወዳጄ እየቀደመ 🧿ውድዬ እየቀደመ (፪x) ስንቱን ተራራ ባንተ አለፍኩኝ ስንቱን ሸለቆ ውሃ ሞላኸው ጌታዬ ባንተ ሁሉ ሆነልኝ ክብር ምስጋና ላንተ ይድረስህ (፪x) በሕይወቴ በኑሮዬ ጣልቃ እየገባህ ጣልቃ እየገባህ ጣልቃ እየገባህ መንገዴን አቀና ጣልቃ እየገባህ መንገዴን አቀና (፪x) በአምላኬ ክንዱ ላይ ተደግፌ በርሱ ደግነት አምናን አልፌ ዘንድሮን አየሁ ጌታን ታምኜ ላከብረው መጣሁ ሁሉንም ትቼ (፪x) በሕይወቴ በኑሮዬ ጣልቃ እየገባህ ጣልቃ እየገባህ ጣልቃ እየገባህ መንገዴን አቀናህ ጣልቃ እየገባህ መንገዴን አቀናህ (፪x) ማዕረጌ ነህ ማዕረጌ ነህ ሁሉን ያለፍኩብህ ሁሉን ያለፍኩብህ ሁሉን ያለፍኩብህ ሁሉን ያለፍኩብህ (፪x) አምላኬ አምላኬ አምላኬ አምላኬ አምላኬ መታመኛዬ አንተ ነህ ለኔ ክብሬ ጌትዬ መታመኛዬ አንተ ነህ ለኔ ክብሬ ውድዬ መታመኛዬ አንተ ነህ ለኔ ክብሬ ኢየሱስ መታመኛዬ አንተ ነህ ለኔ ክብሬ (፪x¬)
نمایش همه...
በሰማዩ ስፍራ በክብር ያለው እግዚአብሔር ለኔ ልዩ ነው (2x) እግዚአብሔር ለኔ ልዩ ነው (2x) ሰማያትን በሃይሉ ያጸና በምክሩም ግሩም ነው እሱ ገናና እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም ለዘላለም (2x) አዝ፦በሰማዩ ስፍራ በክብር ያለው እግዚአብሔር ለኔ ልዩ ነው (3x) እስረኛውን የፈታ ያከበረ ምስኪኑን ሰው በከፍታ ላይ ያኖረ የባርነትን በትር የሰበረው እግዚአብሔር ነው (2x) አዝ፦በሰማዩ ስፍራ በክብር ያለው እግዚአብሔር ለኔ ልዩ ነው (3x) እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ አለ ጨለማውን የለየ ቀኑን ብርሃን ይሁን ያለ ዙፋኑ በሰማይ ነው በሰማይ ነው ኦሃሃሃ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው (ያለ ማነው) (4x) ዘማሪ መስፍን ጉቱ
نمایش همه...
አንድ ሀለት ብዬ ውለታውን አስቤ ፡ ልቆጥር ጥፍት ፡ ይለኛል ፡ ከየት ፡ ተነስቼ ፡ እንደምጀምር ይህ ፡ እንኳን ፡ ብረዳኝ ፡ ቢነግርልኝ ፡ ውስጤን ፡ ቢገልጸው እንደእግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የለም ፡ ብዬ ፡ ልደምድመው (፪x) እንደእግዚአብሔር ፡ የለም ፡ አቤት (፫x) ቢፈለግ ፡ ዘላለም ፡ አቤት (፫x) እንደእሱ ፡ የለም ፡ አቤት (፫x) ቢፈለግ ፡ ዘላለም ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት (፪x) አዝ፦ ምሕረቱን ፡ አስቤ ፡ አቤት ፡ ስል ፡ ፍቅሩ ፡ አለ ፡ ለካ ፍቅሩን ፡ አስቤ ፡ አቤት ፡ ስል ፡ ባርኮቱ ፡ አለ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ለካ ታዲያ ፡ እንዴት ፡ አመስግኜው ፡ ልርካ (፬x)
نمایش همه...
አንተ ላወቁብህ ክብር ነህ የማዕረግ መጐናፀፊያ የሃዘኑ ዘመን ማስረሻ ከማይነጥፍ ሰላም መድረሻ በዕረፍት ወንዝ ዳር ይተከላል ያገኘህ ከምንጭ ዳር ይኖራል ዕርዳታው ከሰማይ ደጅ ይወርዳል የእግዚአብሔር/የአምላኩ እጅ (2x) አዝ፦ እርስቴ ነህ የልቤ ምርጫ ነፍሴ አፀደቀህ የፈቃዴ ብልጫ ሁሉንም ንቄያለሁ ክብር በፊቴ አጣ ሁሉን ጥሎ ነፍሴ ወደ ሃሳብህ መጣ ጌታ ፍቅርህ እጅግ እያየለ መጣ (2x) በሰማይ በምድር ማይገኝ ቢተካስ በሌላ ማያሰኝ መኖሪያህ በብርሃናት ውስጥ ውበት ነህ ለርስትህ ጌጥ ለዘለዓለም ትኖራለህ ማያረጁ ዓመታት ይዘህ ለሁሌ ነህ የነፍሴ/የእኔ ምርጫ ከአዕላፋት አግኝተህ ብልጫ (2x) አዝ፦ እርስቴ ነህ የልቤ ምርጫ ነፍሴ አፀደቀህ የፈቃዴ ብልጫ ሁሉንም ንቄያለሁ ክብር በፊቴ አጣ ሁሉን ጥሎ ነፍሴ ወደ ሃሳብህ መጣ ጌታ ፍቅርህ እጅግ እያየለ መጣ (2x) ለሰማይ ዉበትን የሰጠህ ለምድር ዳርቻን ያበጀህ እኔን በአምሳልህ መፍጠርህ የከበርሁ አርገህ ማየትህ ልቤ በመደነቅ ተሞላ ክብሬ ሊያዜምልህ ተነሳ ከልብ የሚፈልቅ ምሥጋና መስዋዕቴ ወደ ላይ ይግባ (2x) አዝ፦ እርስቴ ነህ የልቤ ምርጫ ነፍሴ አፀደቀህ የፈቃዴ ብልጫ ሁሉንም ንቄያለሁ ክብር በፊቴ አጣ ሁሉን ጥሎ ነፍሴ ወደ ሃሳብህ መጣ ጌታ ፍቅርህ እጅግ እያየለ መጣ (2x)
نمایش همه...
ሰው አይሆንም ብለው ሰው አረገኝ ጌታ (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ) ደጀን የለው ብለው ሆነልኝ መከታ (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ) እንዳሰቡት ሳይሆን እንዳሰበልኝ ነው (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ) ገና መቼ አዩ ይሄ ጅማሬ ነው (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ) አምላኬ የእኔማ ተስፋ እንዳልወድቅ ከቶ እንዳልጠፋ የእኔ አባት የእኔ መድኃኒት በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት አንተ ነህ እኔማ ተስፋ እንዳልወድቅ ከቶ እንዳልጠፋ የእኔ አባት የእኔ መድኃኒ በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት በአንተ ነው ሁሉን ያለፍኩት በአንተ ነው ቀን የወጣልኝ ጌታዬ ተመስገንልኝ (2x) አስታዋሽ ለሌለኝ ለተረሳሁ በሰው (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ) ከተፍ ብሎልኛል ፍቅሩ በተግባር ነው (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ) እንባ አወጡ አይኖቼ በደስታ ተሞሉ (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ) ህመሜኮ ያመዋል ስለሆንኩ አካሉ (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ) አምላኬ የእኔማ ተስፋ እንዳልወድቅ ከቶ እንዳልጠፋ የእኔ አባት የእኔ መድኃኒት በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት አንተ ነህ እኔማ ተስፋ እንዳልወድቅ ከቶ እንዳልጠፋ የእኔ አባት የእኔ መድኃኒ በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት በአንተ ነው ሁሉን ያለፍኩት በአንተ ነው ቀን የወጣልኝ ጌታዬ ተመስገንልኝ (2x) የምስኪኑ ወዳጅ ለተከፋው ፈራጅ ለድሃደጉ አባት ለደከመው ብርታት (2x) ማረፊያ ጥላዬ መጠጊያ ከለላዬ ኢየሱስ ጌታዬ (2x) ኢየሱስ ጌታዬ (4x) Dagi Tilahun
نمایش همه...
ዓላማ ይዞ የተሰለፈ የሚያስፈራም የአንተ ሠራዊት ጠላትን ሁሉ እያሸነፈ በአንተ መሪነት ቀንና ሌሊት ባሕር ተሻግሮ በምድረበዳ ጊንጡን ረጋግጦ ጥቂቱ ሕዝብህ ከአንተ ጋር በዝቶ ርስቱን ጨበጠ ከብዙ በልጦ አዝ፦ ሕዝብን አበዛህ (2x) የአገሪቱንም ወሰን አሰፋህ የማዳን እጅን ለእኛ ዘረጋህ (2x) የሰናፍጯን ቅንጣት ቢዘራ ጌታ በምድር እንድትበዛ ያ ጉልበተኛው መጥቶ ረገጣት እንዳትበቅል መስላው ፈዛዛ ግን አልተሳካም አምልጣው ወጣች ሄደች አደገች ጌታ ይመስገን ድንበሯ ሰፋ ለደካከሙት መጠለያ ሆነች አዝ፦ ሕዝብን አበዛህ (2x) የአገሪቱንም ወሰን አሰፋህ የማዳን እጅን ለእኛ ዘረጋህ (2x) ኦ ሃሌሉያ ሃሌ ሃሌሉያ እያሸነፈ ዘለዓለም ነዋሪ እንደ አምላካችን ያለ ታዳጊ ከቶ የት አለ ተወዳዳሪ ጩኸትን ሰምቶ ምስኪን ድሆችን ዘይት የሚቀባ በአደባባዩ በቤቱ ተክሎ የሚያለመልም እንደ ዘንባባ አዝ፦ ሕዝብን አበዛህ (2x) የአገሪቱንም ወሰን አሰፋህ የማዳን እጅን ለእኛ ዘረጋህ (2x) ኦ ሃሌሉያ ሃሌ ሃሌሉያ እያሸነፈ ዘለዓለም ነዋሪ እንደ አምላካችን ያለ ታዳጊ ከቶ የት አለ ተወዳዳሪ ጩኸትን ሰምቶ ምስኪን ድሆችን ዘይት የሚቀባ በአደባባዩ በቤቱ ተክሎ የሚያለመልም እንደ ዘንባባ አዝ፦ ሕዝብን አበዛህ (2x) የአገሪቱንም ወሰን አሰፋህ የማዳን እጅን ለእኛ ዘረጋህ (2x) Pastor Tesfaye Gabisso
نمایش همه...