cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Amhara development Assocation-Head Office

Amhara Developmet Assocation/ADA/

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
490
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 روز
-230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

በ24 ሚሊየን ብር ወጭ የተገነባው ጀረምስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ። ---------///////---------
نمایش همه...
በ24 ሚሊየን ብር ወጭ የተገነባው ጀረምስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ። ---------///////--------- በምስራቅ ጎጃም ዞን ደባይ ጥላት ግን ወረዳ በመንግስት፣ በአልማና በህብረተሰቡ ትብብር የተገነባው የጀረምስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የክልል፣የዞን፣ የወረዳ እና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት ዛሬ በድምቀት ተመርቋል። በአካባቢው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለመኖሩ ልጆቻቸውን ለማስተማር ይቸገሩ እንደነበር የተናገሩት የአካባቢው ማህበረሰብ ይህ ትምህርት ቤት መከፈቱ ችግራችን ይፈታዋል ብለዋል። የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ እንደተናገሩት በዞናችን በአልማ፣በመንግስትና በማህበረሰቡ ተሳትፎ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ስራ በስፋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዛሬው እለት የተመረቀው የጀረምስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ እንዲጠናቀቅ አስተዋጾ ላበረከቱ አካላት ምስጋና ያቀረቡት ኃላፊው ትምህርት ቤቱ በቀጣይ የትምህርት ዘመን ስራ ለማስጀመር የትምህርት ግብዓቶችን ለማሟላት በሚደረገው ርብርብ ባለድርሻ አካላት የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በትምህርት ዘመኑ በዞኑ በህብረተሰብ ተሳትፎ ከ5መቶ አርባ አምስት ሚሊየን ብር በላይ በገንዘብ፣ በቁሳቁስና በጉልበት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል መሰብሰቡን መምሪያ ኃላፊው አክለው ገልፀዋል። የአካባቢው ማህበረሰብ በትምህርት ስራው ንቁ ተሳታፊ እንዲሆንም አሳስበዋል። የአማራ ልማት ማህበር ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ መዝገቡ አንዷለም በበኩላቸው አልማ ከመንግስትና ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር የሚሰራቸው የትምህርት ተቋማት የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናትን ተስፋ የሚያለመልም ነው ብለዋል። ማህበረሰቡ ለትምህርት እጁ መዛል የለበትም ያሉት ም/ስራ አስፈጻሚው ከተባበርንና ለአንድ አላማ በጋራ መቆም ከቻልን ትውልድ መቅረጽ የሚችሉ ተቋማትን መገንባት እንችላለን ብለዋል። አልማ በዞኑ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጨማሪ የብሉክ ግንባታዎችንና አዲስ ትምህርት ቤቶችን በስፋት በመገንባት ላይ ይገኛል። መረጃው የአብክመ ትምህርት ቢሮ ነው። አልማ:23/11/2015 ዓ.ም
نمایش همه...
"የተጀመረውን ቅንጅታዊ ኀብረት አጠናክሮ ለማስቀጠልና ኀብረተሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንሠራለን" የአማራ ልማት ማኀበር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ -------------///////------------- የአማራ ልማት ማኀበር (አልማ) ኀብረተሰቡን በማሳተፍ የተለያዩ ማኀበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች እየገነባ ነው፡፡ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደባይ ጥላት ግን ወረዳ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እየተከናወነ ባለው ተግባር በአልማ፣ በክልሉ ትምህርት ቢሮና በኀብረተሰቡ ተሳትፎ ከ57 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጪ የ1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ለ2016 የትምህርት ዘመን ለመማር ማስተማር ክፍት ኾነዋል፡፡ በወረዳው 49 መማሪያ ክፍሎች ተገንብተውም ተጠናቅቀዋል፡፡ በአልማ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዘላለም አንዳርጌ ለአሚኮ እንደገለጹት 279 ሚሊዮን ብር በኾነ ወጪ በበጀት ዓመቱ 196 የመጀመሪያ ደረጃና 91 የ2ኛ ደረጃ መማሪያ ክፍሎች ተገንብተዋል፡፡ 21 የመጀመሪያ ደረጃና 2 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መማሪያ ክፍሎች በ2016 መጀመርያ ግንባታቸው ተጠናቅቆ ለአገልግሎ ክፍት ይኾናሉ ብለዋል ኀላፊው። ጤና ኬላዎች ቴክኒክና ሙያ ተቋማትና የሥራ እድል ፈጠራ ሼዶችን በመገንባት ኀብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መኾኑንም ነው የተናገሩት፡፡ በደባይ ጥላት ግን ወረዳ የሀሙሲት ታዳጊ ከተዋ ነዋሪ የኾኑት አቶ ይበልጣል መዘምር እንደተናገሩት በአካባቢው በአልማ በወረዳው በጀትና በኀብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነባው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከዚህ በፊት ልጆቻቸውን ለማስተማር ይከፍሉት የነበረውን መስዋዕትነት የሚያቃልልና ከወጪ የሚታደጋቸው እንደኾነ ለአሚኮ አስተያየታቸውን ሰጠዋል፡፡ ሌላኛው የወረዳው እግዚሀራብ ቀበሌ ነዋሪ የኾኑት አቶ መስፍን በዜ የትምህርት ቤት ግንባታው ከዚህ በፊት ልጆቻቸው ባልተመቸ ኹኔታ ውስጥ ኾነው ይማሩበት የነበረውን አስቸጋሪ ኹኔታ የሚቀይር ነው ብለዋል፡፡ የወረዳው ነዋሪዎች ለአልማ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው ያረጋገጡት፡፡ የደባይ ጥላት ግን ወረዳ አሥተዳዳሪ አቶ ጎጃም ሰዋለ በበጀት ዓመቱ ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሰረተ ልማቶች ሲገነቡ የኀብረተሰቡ ድርሻ የጎላ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ኀብረተሰቡ ከአልማ ጎን በመቆም ትምህርት ቤቶች እንዲገነቡ ላደረጉት አስተዋጽኦም ምሥጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በትምህርት ቤቶች የምረቃ መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የአማራ ልማት ማኀበር አልማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ መዝገበ አንዷለም በ2015 በጀት ዓመት ከ1ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ከ540 በላይ መማሪያ ክፍሎችን ገንብቶ ማጠናቀቅ መቻሉን አብራርተዋል፡፡ ከ700 በላይ መማሪያ ክፍሎች ደግሞ በክረምቱ ግንባታቸው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ይኾናሉ ብለዋል፡፡ይህን ማሳካት የተቻለው ደግሞ በክልሉ ካሉት 4 ነጥብ 3 ሚሊዮን የአልማ አባላት በሚሰበሰብ ገንዘብና አስተዋጽኦ መኾኑን አመላክተዋል፡፡ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው የተጀመረውን ቅንጅታዊ ኀብረትና የልማት አንድነት ወደፊት በሚሠሩ የልማት ተግባራት አጠናክሮ ለማስቀጠልና ኀብረተሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት እንሠራለን ብለዋል። ዘገባው የአሚኮ ነው። አልማ:23/11/2015 ዓ.ም
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
"የተጀመረውን ቅንጅታዊ ኀብረት አጠናክሮ ለማስቀጠልና ኀብረተሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንሠራለን" የአማራ ልማት ማኀበር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ -------------///////------------
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
በማአከላዊ ጎንደር ዞን የማሠሮ የመ/ደረጃ ት/ቤት ማሥፋፊያ አንድ ብሎክ 4 መማራያ ክፍሎች ያሉት ግንባታ በ23/11/5015 ዓ.ም ተመርቋል።መረጃው የማዕከላዊ ጎንደርና አካባቢው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለኸኝ ጓዴ ነው። አልማ:23/11/2015 ዓ.ም
نمایش همه...
03:38
Video unavailableShow in Telegram
በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ዙሪያ ወረዳ አለፋ ባሲ ቀበሌ በአልማና በማህበረሰቡ ተሳትፎ በአዲስ የተገነባው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት!
نمایش همه...
በአዲስ_የተገነባው_ትምህርት_ቤት_በቡሬ.mp413.88 MB
በአማራ ልማት ማህበር እና በህብረተሰቡ ትብብር 40 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው 15 ፕሮጀክቶች መሰራታቸው ተገለጸ፡፡ -----------///////-------------- በደብረብርሃን ከተማ በምንሊክ ክፍለ ከተማ በአማራ ልማት ማህበርና በህብረተሰቡ ትብብር በ1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የተሰራው የዲሊላ ትምህርት ቤት ቤተ መፃህፍት ተመረቀ፡፡ የደብረብርሃን የአልማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አባተ አውግቸ እንደገለጹት በዚህ በጀት ዓመት በአልማና በህብረተሰቡ ተሳትፎ 40 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው 15 የትምህርት ፕሮጀክቶች መሰራታቸውን አስታውቀዋል፡፡ ከፕሮጀክቶቹ ውስጥ በ13 ትምህርት ቤቶች 52 የመማሪያ ክፍሎች፣1 ቤተመፃህፍ እና 1 መጸዳጃ ቤት መሰራቱን አንስተዋል፡፡በ1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የተሰራው የዲሊላ ትምህርት ቤት ቤተመፃህፍት አንዱ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ የሰሜን ሸዋ አልማ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ፍቅሬ በበኩላቸው እንደገለጹት አልማ የክልሉን ህዝብ ችግር በራስ አቅም የመፍቻ የህዝብና የመንግስት የልማት ተቋም መሆኑን አመልክተዋል፡፡በዚህ በጀት ዓመት በዞኑ ከ119 ፕሮጀክቶች በላይ ተጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውንም ጠቁመዋል፡፡ የደብረብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታጠቅ ገድለአማኑኤል አክለው እንደገለጹት ብልህ መንግስትና ህዝብ ለትምህርት ልማት ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡ በአልማ፣በመግስትና በህብተሰቡ ተሳትፎ የሚሰሩ የትምህርት ተቋማት ለትህርት ልማት የተሰጠውን ልዩ ትኩረት አመላካች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በደብረብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ፕሮግራሙን ሲያጠቃልሉ እንደገለጹት የተሰራው ቤተመፃህፍት ለትምህርት ጥራት መጠበቅ ፋይዳው የጎላ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ አልማ ለትምህርት ልማት ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ፣ ህብረተሰቡም ተባባሪ በመሆኑ በከተማው ብዙ ለውጥ መመዝገቡንና ህብረተሰቡ ተጠቃሚ መሆኑን አንስተዋል፡፡በስራው ለተባበሩ አካላትን ሁሉ ከንቲባው ምስጋና አቅርበዋል፡፡ዘገባው የደብረብርሃን ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው፡፡ አልማ ፡23/11/2015 ዓ.ም
نمایش همه...
በአማራ ልማት ማህበር እና በህብረተሰቡ ትብብር 40 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው 15 ፕሮጀክቶች መሰራታቸው ተገለጸ፡፡ -----------///////--------------
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
በሰሜን ጎጀም ዞን በደቡብ አቸፈር ወረዳ ከ10ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት G+1 እና አንድ ብሎክ ህንጻ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን የደቡብ አቸፈር ወረዳ አልማ ቅ/ጽ/ቤት አሰታወቀ፡፡ የደቡብ አቸፈር ወረዳ የአልማ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እማዋይሸ ከፋለ እንደተናገሩት አልማ በዋናነት ከሚስራቸው ሰራዎች ትልቁን ድርሻ የሚይዘው የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል ተግባሩ ነው ። በወረዳው ከተገነቡ የመማሪያ ህንጻዎች በዱርቤቴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤትG+1 አስር የመማሪያ ክፍሎች ያሉት እና በአብችክሊ 2ኛ ደርጀ ት/ቤት አንድ ብሎክ አራት የመማሪያ ክፍሎች ያሉት በ10ሚሊዮን 658 ሺ 7መቶ 44 ብር ወጭ በማድረግ ማስገንባት ለመማር ማስተማሩ ሂደት ዝግጁ ማድረግ ተችሏል ብለዋል ፡፡ ከተማሪ ወላጆች መካከል አቶ አዳነ ዳኛው እንደተናገሩት አልማ አባላቱ ገቢ በመሠባስብ ለልጆቻችን የመማሪያ ክፍል በመገንባት ለትምህርት ጥራት ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ያለ ማህበራችን ነው ብለዋል፡፡ አልማ:21/11/2015 ዓ.ም
نمایش همه...
በደቡብ ጎንደር ዞን አልማ ማስተባበሪያ ጽ /ቤት የሰዴ ሙጃ ወረዳ  አልማ ቅ/ጽ/ቤት የዞን፣የወረዳ ፣ የቀበሌ አመራሮች እና  የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በሰሳማች፣በጎራዲት፣በመንዲል አምባ፣በታላቅሜዳ ቀበሌዎች እና በሮቢት ከተማ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች 5 ብሎክ 20 የመማሪያ ክፍሎችን ያሏቸው በ7 ነጥብ 3  ሚሊየን ብር  በመገንባት  ሐምሌ 18/2015 ተመርቀው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን  የደቡብ ጎንደር ዞን አልማ ማስተባበሪያ ጽ /ቤት ሃላፊ አቶ መሳፍንት ልብሴ ገልጸዋል ። አልማ :19/11/2015 ዓ.ም
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.